Latest Posts from MS League - የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ (@ms_league) on Telegram

MS League - የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ Telegram Posts

MS League - የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ
ይህ የMS League (የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ) ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።
ሌሎች የማህበራዊ ድህረ ገፆቻችንን ይወዳጁ
YouTube https://www.youtube.com/@Muslim_Students_league
Facebook
https://www.facebook.com/emsleague
Instagram
https://www.instagram.com/msleague23
5,550 Subscribers
1,287 Photos
18 Videos
Last Updated 01.03.2025 06:27

Similar Channels

AASTU Software Engineering
12,156 Subscribers
GDG Addis
10,799 Subscribers

The latest content shared by MS League - የሙስሊም ተማሪዎች ሊግ on Telegram


የረመዳን ጨረቃ ታይታለች ፣ ጀነትም በሮቿን ከፍታለች ፤ ቀናት ቀናትን ተክተው ለተከበረው የእዝነት ወር አላህ አድርሶናልና :
እንኳን አደረሳችሁ !!
የጀሃነም ደጃፎች ተዘግተው ፣ ለረያን ጾመኞች የሚታጩበት ቀናት እነሆ ጀምረዋል ። አላህ በዚህ ረመዳን ወደ ቅኑ መንገድ ይምራን ፣ እስከ ወዲያኛውም ከሱ ደጋግ ባሮች ውስጥ ይመድበን ፣ ትናንት ከነበርንበት የተሻልን ሆነን ረመዳንን የምንጨርስ ያድርገን ( አሚን )
ረመዳን ሙባረክ !

✍️ ኢናያ አብራር

ሪሳላ ፖድካስት የተለያዩ የመልካም ስብእና ተምሳሌቶችን እየጋበዘ በማራኪ የአቀራረብ መንገድ ይዞ በሙስሊም ተማሪዎች ሊግ አዘጋጅነት ወደናንተ የሚደርስ ፖድካስት ነው።

በዛሬው ክፍል ከእንግዳችን ሙሐመድ ሙራድ ጋር ከልጅነት ግዜው እስከ ጉልምስና ከተወለደበት ሀገር ተነስተን ለትምህርት የወጣባቸውን ሀገራት ስለልምዶቹ ስለ ትምህርት ህይወቱ ዳሰናል::
ምሽት 2:00 በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን::

ሙስሊም ተማሪዎች ሊግ ከሚንበር ቲቪ ጋር በመተባበር

ወ/ሮ መካነሰላም መሐመድ በትምህርት ሥራ ላይ ታላቅ አሻራን ያሰረፈች፣ በሕይወት ክህሎት ሥልጠና አስተዋጽኦዋ የላቀ፣ የንግግር አቅምዋ ከፍ ያለ ምሑር ነች። በያስሚን ሙጃሂድ ተጽፎ በሙሐመድ ሰዒድ (ABX) እና በሙሐመድ ረሺድ የተተረጎመውን መጽሐፍ ባሳለፍነው እሁድ የካቲት 02/2017 በዋልያ መጽሐፍ መደብር ቅኝት አድርጋ ነበር። የቅኝቱን ሁለተኛ ክፍል ዛሬ ምሽት ከ03:00 ጀምሮ የምናቀርብላችሁ ይሆናል!

#ልብህን_አስመልስ
#ቅኝተ_መጻሕፍት
#ክፍል_2 #Part2
#BookReview
#Yasmin_Mogahed

ዕለተ ዓርብ የካቲት 7 -2017 | ሻዕባን 15 -1446

★ ★ ★
Minber TV | Ethio Sat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

ሪሳላ ፖድካስት የተለያዩ የመልካም ስብእና ተምሳሌቶችን እየጋበዘ በማራኪ የአቀራረብ መንገድ ይዞ በሙስሊም ተማሪዎች ሊግ አዘጋጅነት ወደናንተ የሚደርስ ፖድካስት ነው።

በዛሬው ክፍል ኢትዮጵያን በመወከል በዓለም አቀፍ የኮዲንግ ውድድር ተካፋይ ከነበረው ሙከረም ጋር ቆይታ አድርገናል። የተማረው software engineering ሲሆን በዛው ሙያ ዓለም አቀፍ ተቋማት ላይ እየሰራ ይገኛል። ዘመን አፈራሹ AI ጣጣ ነው ወይስ ዕድል የሚለውን ሰፋ ባለ እና ባልታየ መልኩ አስዳሶናል። ክፍል-2 ምሽት 02:00 በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን።

ሙስሊም ተማሪዎች ሊግ ከሚንበር ቲቪ ጋር በመተባበር

#ስለሚያበላ_አይደለም_ግን_ያበላል
#ሪሳላ_ፖድካስት
#ክፍል_2 #Part_2
#Risala #Podcast

ዕለተ ሰኞ የካቲት 3 - 2017 | ሻዕባን 11 - 1446
★ ★ ★
Minber TV | EthioSat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #Minber_TV

በሙስሊም ተማሪዎች ሊግ የሚሰናዳው መፅሐፍ ዳሰሳ 20ኛውን ዙር መፅሐፍ ዳሰሰ በያስሚን ሙጃሂድ የተደረሰውን ልብህን አስመልስ (reclaim your heart) ከተረኛ ዳሳሻችን ኡስታዛ መካነሰላም ሙሐመድ ጋር ዳሰናል::



#በንባብ_ወደከፍታ
#በዋልያ_መፅሐፍት_መደብር
#reclaim_your_heart
#ልብህን_አስመልስ

20ኛው ዙር መፅሐፍ ዳሰሳ በመከናወን ላይ


#በንባብ_ወደከፍታ
#በዋልያ_መፅሐፍት_መደብር
#reclaim_your_heart
#ልብህን_አስመልስ

● Reclaim your heart : Seeing Your Home In Jennah - On Seeking Divine Help

#ነገ_እንገናኝ

ታሪክ ነው ብቻ ተብሎ ማይታለፍ አንድ ታዋቂ ታሪክ አለ ! ታሪኩ የዚህን አለም ሳቢና አብረቅራቂ ነገር ሁሉ ንቃ እና ችላ ብላ በቀጣዩ ዓለም ስላለው ቤቷ ስለምትጨነቅ አንዲት ሴት የተወሳበት ነው ። ራሷን በዚህ ዓለም ጊዜያዊ ጥቅም መገመት አልፈለገችም ። ከወዲያኛው አለም ስለሚጠብቃት ከፍተኛ ሽልማት ስላሰበች በዚህ አለም ለሚደርስባት አሳማሚ ነገርም አልተበገረችም ። ለዚያ በልቧ ለያዘችው ጥልቅ እምነቷ ለመሞት ዝግጁ ነበረች ።


የሚገርመው ባለታሪካችን ንግስት መሆኗ ሲሆን በዚህ አለም ላይ አለ በሚባል ቤተመንግሥት እና ቅንጡ ቪላዎች ወስጥ ትኖር የነበረችም እመቤት ናት  ። ግና እሷ ከነዚያ ግንቦች እና ካለችበት ቤተመንግሥት ባሻገር ተመለከተች ። የታያት የመጨረሻው ዓለም ዋናው እና እውነተኛው ቤቷ ነበር ።




#ነገ_እንገናኝ
#ልብህን_አስመልስ
#reclaim_your_heart
#እነሆ_20ኛው
#በንባብ_ወደከፍታ
#የካቲት_2
#በዋልያ_መፅሐፍት_መደብር

● Reclaim your heart : Take Back Your Heart


የተውባ ሃያልነት ልቦናን ንጹሕና ከቀድሞው በተሻለ ውብ አያደርጋትምን??
ያሰጠማችሁን ወንጀል አስወግዱ ፤ በናንተና በህይወታቸሁ መካከል ያለውን ግርዶ አንሱ ፤ በናንተ እና በነጻነታችሁ ፤ በናንተ እና በአላህ ብርሃን መካከል የተደረገውን ግርዶ ግፈፉ ! ግርዶአችሁን ግለጡና ዳግም አንሰራሩ ! ወደ እራሳችሁ ፣ ወደ መነሻችሁ ፣ ወደ እውነተኛው ቤታችሁ ተመለሱ ! ሁሉም በሮች ቢዘጉ እንኳ ሁሌም ክፍት የሆነ በር አለ ። ሁሌም ያንን በር ፈልጉ ። እሱን ፈልጉ !! በአስፈሪው የባህር ማዕበል መካከል ፀሓይ ወደሆነው እዝነቱ ይመራችኋልና።
ይህች አለም እናንተው ፈቃድ እስካልሰጣችኋት ድረስ አትሰብራችሁም ። የልቦናችሁን ቁልፍ እስካላቀበላችኋት ድረስ ልትገዛችሁም ሆነ የራሷ ልታደርጋችሁ አትችልም ። ቁልፉን የሰጣችኋት እንደሆነ መልሳችሁ ተቀበሏት ! ልባችሁን አስመልሱ እና ለትክክለኛው ባለቤቱ አስረክቡ !!

እርሱም አላህ ነው !



#ሁለት_ቀናት_ብቻ_ቀሩት
#ልብህን_አስመልስ
#reclaim_your_heart
#እነሆ_20ኛው
#በንባብ_ወደከፍታ
#የካቲት_2
#በዋልያ_መፅሐፍት_መደብር

● Reclaim your heart : Emptying the vessel


አንድን ዕቃ ከመሙላትህ በፊት መጀመሪያ ዕቃውን ባዶ ማድረጉ ግድ ነው። ልብም እንደ ዕቃ ናት ፤ ልክ እንደሌላው ዕቃ ሁሉ በሌላ ነገር ከመሞላቷ በፊት ልብም ወስጧ ባዶ መደረግ አለበት ። አንድ ሰው ልቡ በሌላ ነገር የተሞላ ሆኖ ሳለ በአላህ ልሙላው ቢል አይቻለውም  ፤ ለአላህ ጥራት የተገባው ይሁን ።
ልብንም ባዶ  እና ንፁህ የማድረግ ሂደት የመጀመሪያው እርከን የምስክርነት /ሸሃዳ ቃል ሲሆን ፤ እርሱም -ላ ኢላሀ ኢለላህ - ከአላህ በስተቀር በሃቅ የሚገዙት ሌላ አምላክ የለም ብሎ መመስከር ነው ።
የመጀመሪያው የእምነት ምስክርነት የሚጀምረው ውስጧ የነበረውን ነገር በመሰረዝና ልብን ባዶ በማድረግ መሆኑን ማስተዋል ይኖርብናል ። ይህም ከመጀመሪያው የሸሃዳ ክፍል ጋር ይመሳሰላል - ላ ኢላሀ " አምላክ የለም" - ከሚለው ጋር ፤ ሁለተኛው ደግሞ ባዶ ያደረጉትን ዕቃ መሙላት ሲሆን ከሸሃዳ ቀጣዩ ክፍል - ኢለላህ  "ከአላህ በስተቀር" - የሚለውን ይመስላል ። ባዶ አድርጎ መሙላት ማለት ይህ ነው እንግዲህ !!



#ሶስት_ቀናት_ብቻ_ቀሩት
#ልብህን_አስመልስ
#reclaim_your_heart
#እነሆ_20ኛው
#በንባብ_ወደከፍታ
#የካቲት_2
#በዋልያ_መፅሐፍት_መደብር

ሪሳላ ፖድካስት የተለያዩ የመልካም ስብእና ተምሳሌቶችን እየጋበዘ በማራኪ የአቀራረብ መንገድ ይዞ በሙስሊም ተማሪዎች ሊግ አዘጋጅነት ወደናንተ የሚደርስ ፖድካስት ነው።

በዛሬው ክፍል ኢትዮጵያን በመወከል በዓለም አቀፍ የኮዲንግ ውድድር ተካፋይ ከነበረው ሙከረም ጋር ቆይታ አድርገናል። የተማረው software engineering ሲሆን በዛው ሙያ ዓለም አቀፍ ተቋማት ላይ እየሰራ ይገኛል። ዘመን አፈራሹ AI ጣጣ ነው ወይስ ዕድል የሚለውን ሰፋ ባለ እና ባልታየ መልኩ አስዳሶናል። ምሽት 02:00 በሚንበር ቲቪ ይጠብቁን።

ሙስሊም ተማሪዎች ሊግ ከሚንበር ቲቪ ጋር በመተባበር

#ስለሚያበላ_አይደለም_ግን_ያበላል
#ሪሳላ_ፖድካስት
#Risala #Podcast