Dernières publications de ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል (@mkpublicrelation) sur Telegram

Publications du canal ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
46,849 abonnés
6,907 photos
80 vidéos
Dernière mise à jour 06.03.2025 03:40

Le dernier contenu partagé par ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል sur Telegram

ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

13 Feb, 08:13

10,350

“ሃሎ መምህር” የተሰኘ ለሃይማኖታዊ ጥያቄዎች በስልክ ምላሽ የሚሰጥ አገልግሎት መጀመሩ ተገለጸ።

የካቲት ፮/፳፻፲፯ ዓ.ም

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት “ሃሎ መምህር” የተሰኘ ለሃይማኖታዊ ጥያቄዎች በስልክ ምላሽ የሚሰጥ አገልግሎት መጀመሩን አስታውቋል።

የስብከተ ወንጌልና ዕቅበተ እምነት ዋና ክፍል ምክትል ኃላፊ ዲያቆን ዐቢይ ጌታሁን እንደገለጹት አገልግሎቱ በዋናነት የስብከተ ወንጌልን ተልዕኮ ለማዳረስ በተለይ በቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ምዕመናንን በእምነታቸው እንዲጸኑ ለማድረግና ከአዳዲሰ አማንያን የሚመጡ ጥያቄዎችን ለመመለስ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል።

ከተጀመረ 5 ቀን የሆነው ይህ አገልግሎት ከ 30 እስከ 40 ለሚሆኑ ምዕመናን ለጠየቋቸው ጥያቄዎች ምላሽ መሰጠቱን በመግለጽ ሰዓቱን ያልጠበቁ የስልክ ጥሪዎችን ለማስተናገድ ፈተና እንደሆነባቸው አክለው ገልጸዋል።

በዚህም ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ ከጠዋቱ 4፡00 - 10፡00 ሰዓት አገልግሎቱ የሚሰጥ ሲሆን ሰኞ፣ ረቡዕና ዓርብ በኦሮምኛና በአማርኛ እንዲሁም ማክሰኞና ዓርብ በአማርኛ ቋንቋ ብቻ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም ም/ኃላፊው የምዕመናን ተሳትፎ ጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው “በተለያየ ምክንያት መማር ያልቻሉ፣ ጥያቄ የፈጠረባቸውና በአካል መገኘት ለማይችሉ ምዕመናን በያሉበት ስልክ በመደወል ጥያቄዎችን በመጠየቅ ምላሽ ማግኘት ቢችሉ ከሃይማኖት እንዳይወጡና ከቤተ ክርስቲያን እንዳይለዩ ይረዳቸዋል” በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

12 Feb, 07:50

8,190

ዕቅበተ እምነትና ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ላይ ያተኮረ ሕዝባዊ  ጉባኤ መካሄዱን በማኅበረ ቅዱሳን የደብረ ታቦር ማእከል አስታወቀ ።

የካቲት ፭/፳፻፲፯ ዓ.ም

በማኅበረ ቅዱሳን የደብረ ታቦር ማእከል ዕቅበተ እምነትና ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ላይ ያተኮረ ሕዝባዊ ጉባኤ ከየካቲት 01- 02/02/2017 ዓ.ም ለሁለት ተከታታይ ቀናት በደብረ ታቦር ደብረ ልዑላን መድኃኔዓለም ቤ/ክ አከናውኗል።

በመርሐ ግብሩ መምህረ መምህራን የኔታ በጽሐ ዓለሙ በደ/ታቦር ደ/ልዑላን መድኃኔዓለም ቤ/ክ የ፬ቱ ጉባኤያት ምስክር መምህር፣ መ/ር ልሳነወርቅ አእምሮ የጉባኤ ቤቱ የሐዲሳት መምህር እና መ/ር ተመስገን ዘለዓለም በፍኖተ ሰላም ምሥራቀ ፀሐይ አቡነ ቶማስ መታሰቢያ የመጻሕፍት ጉባኤ ቤት የሐዲሳት መምህር ተገኝተዋል።

መምህራኑም ዕቅበተ እምነትና ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ ላይ ትኩረት ያደረገ ማብራሪያ በትምህርት እና በምክረ አበው መልኩ ሰጥተዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

11 Feb, 18:09

8,453

https://youtu.be/Xt9UPCUhxzY
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

11 Feb, 13:22

12,202

በማኅበረ ቅዱሳን የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ አገልግሎት በ“ሃሎ መምህር” እንዲመለስልዎ የሚፈልጉትን ሃይማኖታዊ ጥያቄ በስልክ ቁጥር 0111 55 32 32  በመደወል ይጠይቁ፡፡

ለጥያቄዎ ማብራሪያ እና መልስ ከመምህራን ያገኛሉ፡፡

ዘወትር ከሰኞ - አርብ ከጠዋቱ 4:00 እስከ ቀኑ 10:00

# ሰኞ ፣ ረቡዕ እና ሐሙስ በአማርኛና በኦሮምኛ
# ማክሰኞ እና ዓርብ በአማርኛ ቋንቋ ብቻ
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

11 Feb, 08:02

9,190

በአውሮፓ ማእከል የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት የገጽ ለገጽ ስብስባ ማካሄዱ ተገለጸ።

የካቲት ፬/፳፻፲፯ ዓ.ም

ማኅበረ ቅዱሳን በአውሮፓ ማእከል የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት የዘንድሮውን ዓመት የገጽ ለገጽ ስብሰባ በዴንማርክ ኮፐንሀገን ከተማ ደብረ ምሕረት ቅዱስ አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ከጥር 30 እስከ የካቲት  2 ቀን 2017 ዓ.ም አካሂደዋል።

በስብሰባው የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ዘሚካኤል ዴሬሳ፣ አገልጋይ ካህን ቀሲስ ኃይለ ጊዮርጊስና የዴንማርክ ግንኙነት ጣቢያ አባላት ተገኝተዋል።

በዚህም የማእከሉ የ6 ወራት የአገልግሎት አፈጻጸም፣ የንዑሳን ማእከላትና የግንኙነት ጣቢያዎች አሁናዊ ሁኔታ ምን እንደሚመስል በመምከር ለቀጣይ የማእከሉ የአገልግሎት አቅጣጫዎች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

"መልካም ሥራን ለመሥራት አንታክት" በሚል ርእስም በአባ ዘሚካኤል  በማኀበራዊ ሕይወት ዙሪያ ትምህርት የተሰጠ ሲሆን ከመደበኛ የአገልግሎት ክንውን በተጨማሪም መንፈሳዊ ሕይወትን በሚመለከት የምክክር መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡

የገጽ ለገጽ ስብሰባ፥ የማእከሉ የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ አባላት በአካል በመገናኘት ይበልጥ የሚተዋወቁበትና የሚወያዩት በዓመት አንድ ጊዜ የሚካሄድ ልዩ መርሐግብር ነው፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

11 Feb, 07:11

7,307

ከተለያዩ ወረዳ ማእከላት እና ግንኙነት ጣቢያዎች ለተውጣጡ የደረጃ አንድ ተተኪ መምህራን ሥልጠና መሰጠቱን በማኅበረ ቅዱሳን የአሶሳ ማእከል ገለጸ።

  የካቲት ፬/፳፻፲፯ ዓ. ም

ማኅበረ ቅዱሳን በአሶሳ ማእከል በስብከተ ወንጌልና በዜማ አገልግሎት ዋና ክፍል አዘጋጅነት ከወረዳ ማእከላት እና ከግንኙነት ጣቢያዎች ለተውጣጡ ከ26 በላይ ለሚሆኑ ሰባኪያነ ወንጌል የደረጃ አንድ ተተኪ መምህራን ሥልጠና በመንበረ ሠላም ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ሰበካ ጉባኤ አዳራሽ ውስጥ ከጥር 30 እስከ የካቲት 02/2017 ዓ.ም ድረስ ተሰጥቷል።

የማእከሉ  የስብከተ ወንጌልና የዜማ አገልግሎት ዋና ክፍል  አስተባባሪ ዲያቆን ወርቁ ጋሹ እንዳሉት የተሰጠው ሥልጠና በነገረ ሃይማኖት፣ነገረ ቅዱሳን ፣በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ፣ሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን፣ በክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር፣ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዲሁም በሐዋርያዊ ተልዕኮ ትምህርቶች ላይ ያተኮረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አስተባባሪው አክለውም ሥልጠናው ተተኪ ሰባኪያነ ወንጌልን ማፍራት፣ ምእመናን በአካባቢያቸው ቋንቋ ትምህርተ ወንጌልን አንዲማሩ እና ሠልጣኞች ባገኙት ዕውቀት አዳዲስ አማንያንን የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች  እንዲያደርጉ ነው ብለዋል፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

08 Feb, 09:53

4,487

አቶ አበበ አክለውም ከዚህ ቀደም የሙከራ ትግበራ ሥልጠና በበይነ መረብ (በቨርቹዋል) ሲሰጥ እንደነበር በመግለጽ በመስፈርት የተመረጡ ደረጃ አንድ ግቢ ጉባኤያት ያሉባቸው ማእከላት ተወካዮቻቸውን በመላክ መምህራንና አስተባባሪዎች በአካል ለሁለት ቀናት እየሠለጠኑ እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል።

ሠልጣኞቹ ከዚህ እንደተመለሱ በተመረጡት ግቢ ጉባኤያት ላይ ሥርዓተ ትምህርቱን እንዲተገብሩ፣ በየማእከላቱ እንዲያሠለጥኑና እንዲያስተምሩ ለማድረግ እንደሆነም በመግለጽ የሙከራ ትግበራውን ውጤት በመገምገም በሚቀጥለው ዓመት ለሁሉም ማእከላት ተግባራዊ እንደሚሆን ተጠቁሟል።
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

08 Feb, 09:53

4,348

ማኅበረ ቅዱሳን የግቢ ጉባኤያት ሥርዓተ ትምህርት የአሠልጣኞች ሥልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ ተገለጸ

የካቲት ፩/፳፻፲፯ ዓ.ም 

ማኅበረ ቅዱሳን በአዲሱ ግቢ ጉባኤያት ሥርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራና ለማእከላት የአሠልጣኞች ሥልጠና በዛሬው ዕለት በማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል እየሠጠ እንደሚገኝ የግቢ ጉባኤያት አገልግሎት ማሥተባበሪያ ሥራ አስፈጻሚ አቶ አበበ በዳዳ ገልጸዋል።

ለሥልጠናው ከ12 ማእከላት ማለትም (ባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃን፣ አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ሐረር፣ ሚዛን፣ አርባ ምንጭ፣ አምቦ፣ ወልቂጤ፣ ሐዋሳና ባሌ ሮቤ) የተወጣጡ ሠልጣኞችን አያሠለጠነ ሲሆን ሥልጠናውን የሚሠጡት በሥርዓተ ትምህርት ዝግጅቱ ላይ በከፍተኛ ኃላፊነት ሲሰሩ የነበሩ ባለሙያዎች ናቸው ተብሏል።

የሥልጠናው ዋና ዓላማም አዲሱ ሥርዓተ ት/ት  ሙሉ ትግበራ ከመከናወኑ በፊት ከ 2013-2015 ዓ.ም ግምገማ በማድረግ ሥርዓተ ትምህርቱን ለመከለስ የተዘጋጀ ሲሆን ይህም ነባሩ ሥርዓተ ት/ት ላይ የነበሩ ጉድለቶችን ለማተካከል ፣ የማኅበረ ቅዱሳን ተቋማዊ ለውጥ በግቢ ጉባኤያት ላይ በተጨማሪነት እንዲሠሩ ያሰባቸውን ተግባራዊ ለማድረግ፣ የሰንበት ት/ቤት ሥርዓተ ት/ት ከግቢ ጉባኤያት ጋር በት/ትና በይዘት የሚመሳሰለውን ለማስተካከል እንዲሁም ትምህርት ሚንስቴር የቀየረው  የት/ርትና የሥልጠና ፍኖተ ካርታ በግቢ ጉባኤያት ት/ት  ላይ ያለውን ተጽዕኖ ከግምት ያስገባ እና መፍትሔ የሚሰጥ ሥርዓተ ት/ት ለማዘጋጀት እንደሆነ ሥራ አሥፈጻሚው ተናግረዋል ።
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

07 Feb, 16:56

5,724

  .#ዐውደ ስብከት  ሥር” # “በእንተ ጾም ”  በሚል ርእስ  ጾም ማለት ምን ማለት እንደሆነ ፣ጾም በብሉይ ኪዳን ፣ጾም በሐዲስ ኪዳን ፣የጾም አይነቶች ፣የጾም መሠረታዊ ጥቅሞች ፣ዐቢይ ጾምን የምንጾምበት ምክንያት  በስፋት  ታስነብባለች።
  #በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “# “መኑ ይእቲ ዛቲ   ክፍል አንድ " በሚል ዐቢይ ርእስ  እመቤታችን ማን  እንደሆነች፣ የእመቤታችን ከሴቶች መለየት እንዴት እንደሆነ ፤በነገረ ድኅነት የእመቤታችን ድርሻ  የሊቃውንት መጽሐፍ በማጣቀስ ትምህርት ይሰጣል ።

    #ዐቢይ ጉዳይ  ዐምድ  ሥር  ደግሞ “# መከራው እንጂ ፣ለሞት ጣር እንዳይሆን እንሥራ" በሚል ርእስ  የመከራው ዶፍ መገለጫዎችና ማድረግ ያለብን ጉዳዮች በዝርዝር ያሳያል
   •  #ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር  ደግሞ  "#የኦርቶዶክሳዊ ጋብቻ ትምህርት "በሚል ርእስ   ዐቢይ ርእስ  በመልአከ ሰላም  ቀሲስ ደጀኔ ሺፈራው  ስለ ምሥጢረ ተክሊል፣ጋብቻ እንዴት እንደተጀመረ፣የጋብቻ ዓላማው ፣ከመጀመሪያው ጋብቻ ምን እንማራለን? ጋብቻ ብዙኃኑ የሚመኘው ሲሆን እንደምኞቱ ጸሎቱ የደረሰለት ስእለቱ የሰመረለት ስንቱ ይሆን? በሚል ሰፊት ትምህርት  ታሰተምራለች።
   • #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “#ቅዱስ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ፣ወላዴ አእላፍ አበ ብዙኃን" በሚል ርእስ  ስለ ቅዱሱ መጠራት፣ አገልግሎት በስፋትታስቃኛለች ።
   •  #በነገዋ  ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ  ሥር “ መንፈሳውያን ማኅበራት ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን " በመ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል ክፍል ፫   በሚል ርእስ በ፭ መቶ ክፍለ ዘመን፤በዘመነ ላስታና ድኅረ ላስታ ፣ መንፈሳውያን ማኅበራት ለነገዋ ቤተ ክርስቲያን በ21ኛው ክ/ዘመን ፣መንፈሳውያን ማኅበራት በአሁኑ ዘመን የሚሉ ርእሶች ይዛለች ።
  #በኪነ ጥበብ ዐምድ "#ጥሪ_ክፍል _፪ "በሚል  ታስነብባለች ።
•  #የጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምድ “የማዕረግ ስም አሰጣጥ # ክፍል ፩ " በሚል ርእስ #በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲስ ኪዳን የአንድምታ ትርጓሜ መምህር የሆኑትን #መጋቤ ሐዲስ ስቡሕ አዳምጤን ጋር የተደረገ  ጥያቄና መልስ ይዛለች።  ።
   ሐመር መጽሔት #፴፩ ኛ ዓመት   ቁጥር ፲፪ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !

magazine @eotcmk.org  #ሐመር #መጽሔት  ዝግጅት  ክፍል
ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

07 Feb, 16:56

5,007

✍️✍️ሐመር መጽሔት በየካቲት ወር እትሟ!  
  ".. እጅግ ብዙ የመከራ ማዕበል ቢጎርፍም ሁልጊዜም አምላኳ ከእርሷ ጋር ስለሆነ ይገፏት ይሆናል እንጂ አትወድቅም "  የካቲት ዕትም በ፳፻፲፯ ዓ.ም መልእክት ዐምድ
 #የኅትመት ዘመን ፦#የካቲት ፳፻፲፯  ዓ.ም
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ  ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
•  ገጽ ብዛት፦፳፰
   ዋጋ ፦፵ ብር 
•  ሐመር  መጽሔት  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት  ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር  በመጽሔት ዝግጅት ክፍል  በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡
•  ሐመር መጽሔት ፴፪ኛ ዓመት  ቁጥር ፪  # የካቲት ፳፻፲፯  ዓ.ም መልእክት ዘማኅበረ ቅዱሳን " # ‹‹  #የአሕዛብን ስድብ አትሸከሚም ››  በሚል ጠንንካራ መልእክት  የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ምእመናን የክፋት ጠማቂዎችን ሤራ በመታገስና በታላቅ ንቃት በመመልከት ትኩረታቸውን በበዓላቸው ላይ፣ ልባቸውንም ከአምላካቸው ጋር በማድረግ በዓሉን በሰላም እንዳሰለፋና ትንኮሳዎቹ ትዕግሥትን የሚፈታተኑ ቢሆንም ‹‹ራሳቸው አምጥተው፣ ራሳቸው በሚያሮጡ›› ተንኮለኞች ሤራ ላለመጠለፍ ያደረጉት ጥንቃቄ የሚያስመሰግን እንደነበረ ።
       በአጠቃላይ ሲታይ ግን እንዲህ ዓይነቱ የክፉዎች መዳፈር ለሀገርም፣ ለመንግሥትም፣ ለቤተ እምነቶች ግንኙነትም አይጠቅምም፡፡ ድፍረቱ ደግሞ በሰዎች ላይ ብቻ ሳይሆን ሁሉን በሚችል አምላክ ላይ የተፈጸመ ደፍረት በመሆኑ ሀገርና ወገንን የሚያስከፍለው  ዋጋ አሁን እየተቀበልን ካለው በላይ እንዳይሆን መጠንቀቅ  እንደሚገባ ሐመር በመልእክት ዐምድ ታስነብባለች።