የህሊና እስረኞች ችሎት ውሎ ዘገባ‼️
በእነ ቴዎድሮስ ጣምራይ መዝገብ የዐቃቤ ሕግ ምስክር የማሰማት ሂደት ቀጥሏል ፤ እስካሁን ከ13 ምስክሮች መካከል 7 የሚሆኑት በችሎት ተገኝተው የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል።
አውሎግሶን- Awulogson
የካቲት 25/2017
አዲስ አበባ- ኢትዮጵያ
በእነ ቴዎድሮስ ጣምራይ የሽብር ክስ መዝገብ የተከሰሱ (23) ሰዎች ማለትም ፦
1) ቴዎድሮስ ጣምራይ ፈንታው፣
2) ብርሃኑ ተውልኝ አምበሉ፣
3) ታሪኩ ታደሰ ታፈሰ፣
4) ደሳለ አለሙ በላቸው፣
5) ሀብታሙ ፍቃዴ ሞላ፣
6) እዮብ ታምሩ ካሳ፣
7) ፍታለው አድማሱ መላኩ፣
8) መኮንን ደሳለኝ መንግስቴ፣
9) ጌትነት አማረ አሰፋ፣
10) ደጀኔ ገ/ጻዲቅ ገ/ሕይወት፣
11) ግዛቸው ታምር ጥሩነህ፣
12) ፈንታሁን ፍቃዴ ጎቤ፣
13) ወንድም በርሄ ወልደ ጋብር፣
14) አብዱረኸማን አህመዲን ኑር፣
15) ም/ኢ/ር የሽዋስ አልታሰብ ደስታ፣
16) ሳጅን ጌትነት ድንቁ ዘገዬ፣
17) ኮን/ል ሳምሶን ማሞ እንዳይላሉ፣
18) ኮን/ል ደሳለኝ ውቡ ተሾመ፣
19) ኮን/ል ሀብታሙ ተሻገር ሙሉነህ፣
20) ኮን/ል መልኩ ተስፋዬ ፍቃዱ፣
21) ኮን/ል አስማማው አረጋ ካሳ፣
22) ኮን/ል ምስጋናው አባትነህ አያሌው እና
23) ሁሴን ሰይድ ሙሀባ የካቲት 25/2017 በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀርበው ነበር።
ከአሁን ቀደም በቅድመ ምርመራ ወቅት አንዷለም የሚለውን ስሙን አቤኔዘር ታደሰ በሚል ቀይሮ እንዲሁም ከሁለት ወር በላይ ከሚመሰክርባቸው ሰዎች ጋር አብሮ የታሰረ ቢሆንም ይህንን እውነታ ክዶ ከቤቱ እንደመጣ አድርጎ እንዲመሰክር በዐቃቤ ሕግ የተገደደው ሰው ብቻ በእለቱ ተገኝቶ የምስክርነት ቃሉን ሰጥቷል ።
የምስክርነት ቃሉ ክህደት የሞላበትና ዐቃቤ ሕግ እየቀለበ ውሸት ሲያስጠናው የከረመ ስለመሆኑ ከቃሉ ለመረዳት ይቻላል ይላሉ ተከሳሾች ።
ከሰዓት በኋላ ጀምሮ ምስክሩ የተሰማ ቢሆንም የዐቃቤ ሕግ እና የጠበቆች የማብራሪያ እና መስቀለኛ ጥያቄ ገና ባለመጠየቁ በይደር ቀሚል ለየካቲት 26/2017 ተቀጥሯል ።
ዐቃቤ ሕግ አሉኝ ካላቸው 13 ምስክሮች መካከል እስካሁን 7 የሚሆኑት በችሎት ተገኝተው የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል።
በተመሳሳይ በእነ ዘነበ ሽታ እንዳይላሉ መዝገብ በሽብር ወንጀል የተከሰሱ ማለትም ፦
1. ዘነበ ሽታ እንዳይላሉ፣
2. አማኑኤል ሳህልዬ እና
3. ብስራት ካሳዬ የተባሉ ተከሳሾች በእለቱ ፍ/ቤት ቀርበው ለመጋቢት 30/2017 በችሎት እንዲገኙ በሚል ተለዋጭ ቀጠሮ የተሰጣቸው መሆኑ ታውቋል ።
#የቴሌግራም እና ፌስቡክ ቻናላችን ይቀላቀሉ።
#ድል፣ ለመላው አምሓራ ፋኖ!
https://www.facebook.com/profile.php?id=61571637893418
25/06/2017 ዓ.ም
ሞዐ ሚዲያ
አዲስ አበባ
https://t.me/Moamediamoresh