آخرین پست‌های Anchore media አንከር ሚድያ ( በጋዜጠኛ መሳይ መኮነን) (@mesaymekonnen1) در تلگرام

پست‌های تلگرام Anchore media አንከር ሚድያ ( በጋዜጠኛ መሳይ መኮነን)

Anchore media አንከር ሚድያ ( በጋዜጠኛ መሳይ መኮነን)
ይህ ©መሳይ መኮነን የተሰኘ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።⬇️ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች ጆይን👇
https://t.me/mesaymekonnen1
1,635 مشترک
226 عکس
8 ویدیو
آخرین به‌روزرسانی 06.03.2025 22:44

کانال‌های مشابه

Hair styles for girls
6,720 مشترک
Alam Mobile Tech
2,010 مشترک

آخرین محتوای به اشتراک گذاشته شده توسط Anchore media አንከር ሚድያ ( በጋዜጠኛ መሳይ መኮነን) در تلگرام

Anchore media አንከር ሚድያ ( በጋዜጠኛ መሳይ መኮነን)

11 Jan, 01:45

801

#GoodNews ዛሬ በይፋ ስራ የጀመረው የኢትዮጵያ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (Ethiopian Securities Exchange) ትልቅ እምርታ ነው

ሩቅ ሳንሄድ እዚሁ ጎረቤት ሀገሮች እንኳን ዜጎቻቸው ለስቶክ ገበያ ክፍት የሆኑ ድርጅቶችን በግልፅ ገበያ ሼር በመግዛት እና በመሸጥ ይነግዳሉ፣ ያተርፋሉ፣ ኑሯቸውን ይገፋሉ።

የውጭም ሆነ የሀገር ውስጥ ኢንቨስተሮችን ለመሳብም ሁነኛ መንገድ እንደሆነ የሚታመንበት ይህ Securities Exchange በቅርብ ወራት 50 የሀገር ውስጥ ኩባንዎች ይካተቱበታል ተብሏል።

በአሜሪካ ሀገር እንዳለው Securities and Exchange Commission (SEC) ያለ ጥብቅ ቁጥጥር የሚያደርግ አካል ግን እንደሚያስፈልገው ግልፅ ነው።

አለበለዛ ገበያው በቀላሉ ሊጭበረበር እንደሚችል በቅርብ በሌላ ሀገራት የተከሰቱ እንደ Insider Trading,  Pump and Dump እና Ponzi Scheme ያሉ ወንጀሎችን ማየት ይቻላል።

በጅማሮው ተስፋ አድርገን መልካሙን ሁሉ ለተገበያዮች ተመኘን።
Anchore media አንከር ሚድያ ( በጋዜጠኛ መሳይ መኮነን)

08 Jan, 05:56

862

YouTube ሰዎችን ከ0 ብር በመነሳት ሚሊኒየር አድርጓል።
🍭 እናንተም ፊልም፣ ድራማ፣ቲክቶክ፣አክሽን እያላችሁ ግዜአችሁን ከማጣፋት ዩትዩብ ላይ ገንዘብ እንዴት እደሚሰራ ብታዉቁ ትርፋማ ትሆናላችሁ ።

🍭 ማንም ሰው ገንዘብ ካላገኘበት እናንተን ለማዝናናት ብሎ ፊልም ሆነ ድራማ ገንዘቡን ኢንቨስት እያደረገ እናንተን አያዝናናም።

🍭 ስታስቡት በቀላሉ ዪትዩብ ላይ ወይም ሌሎች ሶሻል ሚድያ ለመጠቀም ወይም ቪድዮ ለመጫን ቢያንስ የካርድ ወጭ አለዉ።
🍭 ያሰዉ ገንዘብ ካላገኝ ለምን ብሎ ካርድ እያወጣ ግዜዉን እያጠፋ ቪድዮ ይለቃል ።
🍭 🔴ዩቱብ ማስተር ክላስ ኮርስ ምንድነው?🔴
ዩቱብ ማስተር ክላስ በEthio Computer Acadamic በአማረኛ የተዘጋጀ በውስጡ ከ55 በላይ ቪዲዩ የያዘ ሲሆን ከዩቱብ አከፋፈት ጀምሮ ብር እስከመቀበል ድረስ በቅደም ተከተል ያሳያል። በውስጡም ተጨማሪ ኮርሶችን ይዛል
🔴ፎቶ ኤዲቲግ
🔴ቪዲዮ ኤዲቲንግ
🔴አውድዮ ኤዲቲንግ
🔴አፍሊየት ማርኬቲንግ
🔴 ድጅታል ማርኬቲንግ
🔴 ፎሬክስ ትሬዲንግ
🔴 ዪትዩብ ማስተር ክላስ
🔴 በ1ሺህ እይታ  ብዙ ገንዘብ ማግኘት እንደሚቻል
🔴ቪዲዮ ሪኮማንዴሽን እና ተጨማሪ 50 ቪዲዮዎችን ይዛል
ዩቱብ ማስተር ክላስ ኮርስ ወስዳቹ መማር ለምትፈልጉ ቻናላችንን ጆይን በማለት ይቀላቀሉ።
ትምህርቱን በነፃ ይከታተሉ🙏

https://youtube.com/@ethiocomputeracademic?si=x6ENMQIa-McPolWQ
Anchore media አንከር ሚድያ ( በጋዜጠኛ መሳይ መኮነን)

07 Jan, 21:40

785

🔴ዩቱብ ማስተር ክላስ ኮርስ ምንድነው?🔴
ዩቱብ ማስተር ክላስ በEthio Computer Acadamic በአማረኛ የተዘጋጀ በውስጡ ከ55 በላይ ቪዲዩ የያዘ ሲሆን ከዩቱብ አከፋፈት ጀምሮ ብር እስከመቀበል ድረስ በቅደም ተከተል ያሳያል። በውስጡም ተጨማሪ ኮርሶችን ይዛል
🔴ፎቶ ኤዲቲግ
🔴ቪዲዮ ኤዲቲንግ
🔴አውድዮ ኤዲቲንግ
🔴አፍሊየት ማርኬቲንግ
🔴 ድጅታል ማርኬቲንግ
🔴 ፎሬክስ ትሬዲንግ
🔴 ዪትዩብ ማስተር ክላስ
🔴 በ1ሺህ እይታ  ብዙ ገንዘብ ማግኘት እንደሚቻል
🔴ቪዲዮ ሪኮማንዴሽን እና ተጨማሪ 50 ቪዲዮዎችን ይዛል
ዩቱብ ማስተር ክላስ ኮርስ ወስዳቹ መማር ለምትፈልጉ ቻናላችንን ጆይን በማለት ይቀላቀሉ።
ትምህርቱን በነፃ ይከታተሉ🙏

https://youtube.com/@ethiocomputeracademic?si=x6ENMQIa-McPolWQ
Anchore media አንከር ሚድያ ( በጋዜጠኛ መሳይ መኮነን)

04 Jan, 16:52

1,189

በአዋሽ ፈንታሌ እና ሌሎች አካባቢዎች የሚገኙትን ወገኖች በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት ሊከሰት ከሚችለው አደጋ ለማዳን በሚካሄደው እንቅስቃሴ ላይ የመከላከያ  ተሽከርካሪዎች በስፋት እየተሳተፉ እንደሆነ ታውቋል 🙏🏽
ይህ ©መሳይ መኮነን የተሰኘ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።⬇️ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች ጆይን👇
https://t.me/mesaymekonnen1
Anchore media አንከር ሚድያ ( በጋዜጠኛ መሳይ መኮነን)

14 Nov, 21:18

2,106

ዳይመንድ ላይ ተኝታ ፡   ሰላማዊ እንቅልፍ የራቃት ኮንጎ

#Ethiopia  | በአለም በድህነት  ከሚታወቁ ሃገራት ሶስተኛዋ ዲሞክራቲክ  ኮንጎ ስትሆን ፡ በጣም የሚገርመው በአለም በከፍተኛ ደረጃ  አልማዝ ከሚያመርቱ ሃገራትም ሶስተኛዋ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ናት 🤔

ዛሬ ፡ በዱባይ የጌጣጌጥ መደብሮች. .  በኒውዮርክ ፡ ፓሪስ ፡ ለንደን እና ቶኪዮ በሚገኙ   ትላልቅ የዳይመንድ መሸጫ ሱቆች ላይ ሚሊየን ዶላሮች የሚጠራባቸው የአልማዝ ጌጣጌጦችና ወርቆች  .. ተዝቀው የሚወሰዱት. . ከዚች ካልታደለች ደሃ ሃገር ነው  ። እንደውም  በአለም ላይ በአልማዝ ክምችታቸው ዲሞክራቲክ ኮንጎን የሚበልጡት ሩሲያና ቦትስዋና ብቻ ናቸው ።

ይሄ ብቻ አይደለም ፡ ከነዳጅ ሀብቷ በተጨማሪ ፡  በአለም ደረጃ ለሚመረቱ ለአውሮፕላን ፡  ለመኪና ለሴራሚክስና ለኤሌትሪክ እቃዎች መስሪያ  የሚያገለግለው 60% የኮባልት ምርት የሚሄደው ከዚችው ሃገር ነው ።
ከላይ ያወራነው በመመረት ላይ ያለ ማእድኗን ነው ፡ ግን ይህ ብቻ አይደለም. .

ዲሞክራቲክ ኮንጎ. . ገና   ያልተነካ ከ 23 ትሪሊዮን ዶላር በላይ የሚሆን ማእድን ያላትም ሃገር ነች ። በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ አመት ብቻ 26 ሚሊዮን ህዝቦቿ ለምግብ ዋስትና ችግር ተጋልጠዋል ።  3.4 ሚሊዮን ህጻናት ደግሞ  ለከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በመዳረጋቸው የምእራባውያንን እርዳታ ይሻሉ  ።

ፈጣሪ በአልማዝና በወርቅ ቀላቅሎ በሰራው በዚች ሃገር ፡  ከሚኖሩ ዜጎቿ መሃል ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚያገኙት ግማሽ ያህሉ ብቻ ናቸው ።

ጆይን👉 @mesaymekonnen1
Anchore media አንከር ሚድያ ( በጋዜጠኛ መሳይ መኮነን)

18 Sep, 14:40

2,937

ብዙ ጊዜ እባክህ ስለ ሰላም ስበክ ትሉኛላችሁ። ሰላም በስብከት ቢመጣ ኖሮ፣ ከአብይ አህመድ በላይ ማን ስለ ሰላም የሰበከ ነበር። አብይ ግን በግራ ጎኑ ሰላም እየሰበከ፣ በቀኝ ጎኑ ጦርነት ሲቀፈቅፍ ይውላል።
ሰላም በስራ እንጅ በስብከት አይመጣም።ታሪክ እንደሚነግረን የአለማችን ደም አፋሳሽ ጦርነቶች የተፈጠሩትና የተመሩት በሰላም ሰባኪዎች ነው።

ከሃይማኖተኞች በላይ ስለ ሰላም የሚሰብክ አለ? በአለማችን ከተካሄዱ ጦርነቶች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆነው፣ ሃይማኖት ተኮር ጦርነት አየደለምን?

በክርስትና እና በእስልምና ከሰው ጋር ስትገናኝ የመጀመሪያው መልዕክት እኮ " ሰላም ላንተ ይሁን" የሚል ነው። ሰላም ለከ፤ ሰላም ለኪ፤ ሰላም ለከሙ ይላል ግዕዙ ። አረብኛው ደግሞ " አሰላሙ አለይኩም" ይላል። የአላህ ሰላም በአንተ ላይ ይሁን ማለት ነው።

የሃገሬ ሰው ጠዋት ሲነሳም፣ ሰላም አውለኝ ይላል።
ግን ሰላም አውለኝ ብለህ፣ ጦርነት ቢያግጥምህ፣ እግዚአብሔርን ወይም አላህን ተጠያቂ ማድረግ የለብህም። ስለሰላም እየጸለይኩ ለምን ሰላም አልሰጠኝም ብለህ እሱን ልትወቀሰው አትችልም። እሱ አዕምሮ ሰጥቶሃል። ሰላም በስብክት ሳይሆን በስራ እንደሚመጣ፣ ማሰብ ያንተ እንጅ የእሱ ግዴታ አይደለም።

ሌሎች ሃገሮች ሰላማቸውን እንዴት አገኙ ብለህ ጠይቅ። ሌሎች ሃገሮች ሰላማቸውን ያመጡት፣ የዜጎቻቸውን ነጻነት የሚያስከብር ስርዓት በመመስረታቸው ነው። ይህን ነጻ ስርዓት ታግለህ እውን ስታደርግ እንጅ፣ ቁጭ ብለህ ስለ ሰላም ስለሰበክ ቋሚ ሰላምን አታመጣም።

በአምባገንና ዘረኛ መንግስት ስር ደግሞ ቋሚ ሰላም ፍጹም የማይታሰብ ነው።
ሙሐሙድ አህመድ ሰላም ይሁን ብሎ የዘመረው እኔ ሳልወለድ ይመሰለኛል። እኔ ተወልጄ እስካረጅ ግን በኢትዮጵያ ሙሉ ሰላምን አላየሁም። የጎደለን ምንድነው? ደፈር ብለን let's find the missing link.
ጆይን👉 @mesaymekonnen1
Anchore media አንከር ሚድያ ( በጋዜጠኛ መሳይ መኮነን)

18 Sep, 04:49

2,218

ታሪካዊቷንና ስትራቴጂካዊቷን የጎንደር ከተማን ለመቆጣጠር በፋኖና በመከላከያ መካከል የሚካሄደው ውጊያ ቀጥሏል። ወደ ጎንደር የሚወስዱ መንገዶች በፋኖ ሃይሎች ተዘግተዋል። የአየር በረራም ተቋርጧል። ኢ ኤም ኤስ የፋኖ መሪዎችን አነጋግሯል። ጎንደር በፋኖ እጅ ከገባች፣ ባህርዳር ባለሳምንት ልትሆን ትችላለች።

በዚህ አጋጣሚ በሲቪሎችና በቅርሶች ላይ ጉዳት እንዳይደርስ ከባድ ጥንቃቄ ያስፈልጋል።

ይህ ©መሳይ መኮነን የተሰኘ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።⬇️ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች ጆይን👇
https://t.me/mesaymekonnen1
Anchore media አንከር ሚድያ ( በጋዜጠኛ መሳይ መኮነን)

05 Aug, 23:27

3,278

እንግዲህ በአያልቅበት አህመድ ''የኢትዮጵያ ቀውስ መፍትሄ የሚገኘው እዚህ መጽሀፍ ውስጥ ነው'' የተባለለት የዳንዔል ክብረት መጽሀፍ ይህ ነው። አሉባልታ የታጨቀበትን፥ ትርክት እናስተካክላለን ተብሎ ንትርክ የሞላበትን፥ የቡና ላይ ወሬ ተሰብስቦ የተጠቀጠቀበትን መጽሀፍ ነው አያልቅበት አህመድ የኢትዮጵያ የመዳን መንገድ ሲል ያሞካሸው። የአይጥ ምስክር ድንቢጥ ብለን ለጊዜው እንለፈው እንጂ ነገሩ እጅግ አሳፋሪ ነው።

እነዶ/ር ዳኛቸው ታላላቅ ፈላስፋዎችን እየጠቀሱ ያወደሱት መጽሀፍ ይህ ነው ማለት ነው? ፕ/ር አለማየሁ ቀጄላ(ይቅርታ ገ/ማርያም) ሲሞልጨንና ሲሸልልብን የነበረው ለዚህ ዝባዝንኬ መጽሀፍ ነው? ያ ሁሉ ግርግር፥ ድግስና ፌሽታ ይህቺን አሉባልታ ለማስመረቅ ነበር? ከመጽሀፉ አንዳንድ ገጾች ላይ ሳነብ ፊቴ ላይ ድቅን ያለችው የኦቴሎ ቲያትር ላይ ያለችው የእሪ በከንቱ ሰፈሯ አለሌ ሴት ናት። ወገቧን ይዛ አላፊ አግዳሚውን በስድብ ጥርግርግ የምታደርገዋ ኮማሪት። ዳንዔል አሉባልታና ስድብ አጭቆ በመጽሀፍ በማሳተም የመጀመሪያው አይደለም። የመጨረሻውም አይሆንም። ግን ሁሌም 'አሉባልተኛው ደራሲ' በሚል ሲጠራ ይኖራል።

መጽሀፉን እንድታነቡ አልጋብዝም። ተቃጥሎ አመዱ ኮሪደር አስፋልት ላይ እንዲበተን ታዟል 😜😜🤣😋

ይህ ©የመሳይ መኮነን የተሰኘ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።⬇️ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች ጆይን👇
https://t.me/mesaymekonnen1
Anchore media አንከር ሚድያ ( በጋዜጠኛ መሳይ መኮነን)

26 Jul, 10:13

3,155

እስካሁን ባለኝ መረጃ ሰሎሞን ገሪማ ፋኖን የተቀላቀለ የመጀመሪያው የትግራይ ተወላጅ ነው::


ይህ ©የመሳይ መኮነን የተሰኘ ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው።⬇️ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች ጆይን👇
https://t.me/mesaymekonnen1
Anchore media አንከር ሚድያ ( በጋዜጠኛ መሳይ መኮነን)

26 Jul, 10:10

2,622

የምንመኘው ውድ ዋጋ የተከፈለለት ትንታግ ትውልድ ተፈጥሯል። የምንሰራው የአማራ ህዝብ በሺ ዓመታት ተከብሮ የሚኖርበትን ዘላቂ ስርዓት ነው።መሰረታዊ ነገር የነገው ትውልድ ላይ መስራት ነው።

ጆይን 👉 https://t.me/mesaymekonnen1