ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ @mahkelay Channel on Telegram

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

@mahkelay


ይህ ለማዕከላውያን ክፍል አባላት የተዘጋጀና የተለያዩ የክፍሉ ማስታወቂያዎች እና መረጃዎች የሚለቀቁበት ይፋዊ ገፅ ነው።

mahkelay (Amharic)

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ 'mahkelay' በአማርኛ እናመሰጥለን። እንደምርምር የማዕከላዊ ክፍል አባላት የተዘጋጀና የተለያዩ የክፍሉ ማስታወቂያዎች እና መረጃዎች የሚለቀቁበት ይፋዊ ገፅ ነው። 'mahkelay' በዚህ ገፅ አንድ ተስፋ የለበለባቸው። በከፍተኛ የማዕከላዊ ክፍል አባላት ሳንቲም እና ከፍተኛ ስለሆነ በአባትነት ለመጠቀም የሚያስፈልገውን እንጠቀማለን።

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

26 Jan, 19:37


ሰላም እንደምን አመሻችሁ.... ከዚ በታች ስማችሁ የተዘረዘረ ልብሰ ስብሐት ነገ 11:00 ሰዓት እንድትመልሱ ይሁን ።
1ማትያስ ስማለዉ
2 ስጦታ አሸናፊ
3 ጽናት ክብሩ
4 ቃልኪዳን ብርሃኑ
5 ይድዲያ ፈጠነ
#ማሳሰቢያ
ልብሰ ስብሐት ነገ ያልመለሰ ቀጣይ አገልግሎት ላይ ቅጣት ይኖረዋል !
መልካም ምሽት

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

21 Jan, 19:06


ሰላም እንዴት አመሻችሁ.... ነገ 14/05/2017 ወርሐዊ የአባታችን የአቡነ አረጋዊ ጸሎት እንደሚኖረን ይታወቃል የጥምቀት ተሰላፊዎች 10:30 ላይ ከጸሎት በፊት ልብሰ ስብሐት ( uniform) እንድትመልሱ ይሁን.... ማታ ለአውደምህረት ስለሚፈለግ ሁላችንም እንዳንዘነጋ ይዘን እንድንመጣ ይሁን

መልካም ምሽት

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

13 Jan, 19:26


ሰላም እንደምን አመሻችሁ

ነገ ፈተና 10:00 ሰዓት ላይ ይኖረናል መዝሙራቱን በደንብ ከልሰን እንድንመጣ ይሁን::
# ፈተና ስትጨርሱ ፈተናውን የምታልፉ አባላት መደበኛ ጥናታችን የሚቀጥል ይሆናል። የጥናት ጊዜያችንን ለመቆጠብ ሰዓት አክብረን እንገኝ ::
፨ ወራኃዊ መዋጮ ያልከፈላችሁ ነገ እንድትከፍሉ ይሁን
መልካም ምሽት
መልካም አገልግሎት

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

11 Jan, 10:10


ሰላም እንዴት አረፈዳቹ

የንዑሳን ድልድል

ደቂቅ  ክፍል     ሱራፌል ስንታየሁ
ቀዳማይ ክፍል      አብርሃም ቡሩክ
ካልዓይ ክፍል          ዲ/ን ናኦል በቀለ
ሣልሳይ ክፍል         ዲ/ን ናሆም ቸሩ
ትምህርት ክፍል       ዲ/ን ቃለአብ ፍቃዱ
ኪነጥበብ ክፍል        ሐና እንድሪስ
መዝሙር  ክፍል        ምስጢረ ሳሙኤል
አ/ክትትል ክፍል      ባስልዮስ መለሰ
ሥነምግባር ክፍል     መቅደስ ጎሳዬ
አብነት ክፍል ክፍል     ዲ/ን ታምራት ሁሴን
ጸሐፊ                      ጽናት ምንተስኖት
ምክትል ሰብሳቢ        ዲ/ን ማስረሻ ሰብስብ

የንዑሳን ድልድል ይሄንን ይመስላል ማንኛውም ዓይነት ጥያቄ በሚኖራቹ ሰዓት የሚመለከተውን ንዑስ እንድታናግሩ ይሁን

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

10 Jan, 19:36


ሰላም እንደምን አመሻችሁ

፨ ነገ ከመርሐግብር ቡሀላ የጥምቀት ጥናታችን ይቀጥላል። አገልግሎቱ እየተቃረበ ነው ያለን ጊዜ በጣም ውስን ነው ስለዚህ ረጃጅም መዝሙራትን በቃል እንድትይዙ ይሁን

፨ ቀጣይ ሳምንት ፈተና ስለሚኖረን በደንብ ተዘጋጁ

፨ ሰልፍ ላይም ሆነ ሌሎች አገልግሎት ላይ አስተባባሪዎችን በመታዘዝ አገልግሎቱ አከናውነን የረድኤቱ ተሰታፊ እንሁን ሁላችንም የበኩላችንን እንድንወጣ ይሁን
መልካም ምሽት
መልካም አገልግሎት

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

05 Jan, 18:47


🌸እንኳን የአምላኮች አምላክ ፣ የጌቶች ጌታ ፣ የንጉሦች ንጉሥ ለሆነው አምላካችን ለቅዱስ አማኑኤል የልደት በዓል በሰላም አደረሰን።🌸

     ፀሐይ ሠረቀ እግዚእ ተረክበ አማኑኤል ፀሐይ ሠረቀ /2/

      ወተወልደ/2/ እም ቅድስት ድንግል እስመ መለኮቱ ኢማሠነ/2/

📌 የዚህ ታላቅ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት የተዘጋጀው በደ/ገ/ ቅዱስ ዐማኑኤል የግቢ ባህል መሰረት ነው።

         መልካም በዓል

የዩቲዩብ ቻናል፡
http://youtube.com/@EMislene

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

03 Jan, 19:43


፨ የት/ት ክፍል
- የመርሐግብር የግል ሥራ( ASSIGNMENT ) ማስገቢያ ቀን ነገ እንደኾነ እንዳይረሳ ። ስትመጡ ከመርሐግብር በፊት ለአገልጋዮች እየሰጣችሁ እንድትገቡ ይኹን።

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

01 Jan, 11:28


ሰላም እንዴት ዋላችሁ

ለልደት በዓል "እኛም እንደ ሰብአ ሰገል" ብለን ሰብአ ሰገል ለጌታችን እጅ መንሻ እንዳመጡለት እኛም በነዳያን ውስጥ ክርስቶስን ስለምናገኝ ከዚ በፊትም እንደምናደርገው የማንገለገልባቸውን አልባሳት፣የንፅህና መጠበቂያዎች እና ሌሎችንም መስጠት የምንፈልጋቸውን ስጦታዎች በመስጠት የበረከቱ ተካፋይ እንድንሆን ከበዓል በፊት ባሉት ቀናቶች እያመጣን ቢሮ እንድናስቀምጥ ይሁን🙏

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

31 Dec, 18:26


ሰላም እንደምን አመሻቹ

የማዕከላይ ክፍል አባል የሆነችው ይድዲያ ፈጠነ ሀያት አርፈዋል። ስለሆነም የምትችሉ አባላት በመሄድ እንድታፅናኑ ይሁን

አድራሻ :- አማኑኤል ጀርባ

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

30 Dec, 19:23


ማስታወቂያ
ነገ የተጨማሪ ቀን ማጠቃለያ ፈተና ነው።
፨ ማሳሰቢያ : ሰዓት ይከበር።

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

29 Dec, 15:32


የሥነ ምግባር መልዕክት

" መልዐክ ከሚያይ ሰው ይልቅ ንስሐ ገብቶ አባቱን የሚያይ ሰው ይደንቀኛል "

   ቅዱስ ዩሐንስ አፈወርቅ

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

29 Dec, 15:32


ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ pinned «ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መዋእል የሐዲስ ኪዳን ዳንኤል፣ አፈ ወርቅ ፣ አፈ ዕንቁ ፣ ልሳነ ወርቅ ፣ ከጥሩ ክርስቲያን ቤተ ሰብ በ347 ዓ.ም. በአንጾኪያ ከተማ ተወለደ ። ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስ ሊባኖስ አንድራስ ፣ ጋስዮስ ከተባሉ መምህራን ዘንድ ፍልስፍናን እና የመናገርን ክህሎት በአቴና ተማረ። በዚህም በፍልስናውና በንግግር ችሎታው ከኹሉም በላይ ኾነ። በኋላ ግን ሰውነቱ በሃይማኖት ተሳበ። መንፈሳዊ…»

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

28 Dec, 17:03


ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ pinned «ሰላም እንደምን አመሻቹ ፨ ነገ የፍሬ ሰንበት ትምህርት ከመዝሙር ጥናት በኋላ ይኖረናል፤ እንዲሁም በተለመደው ሰዓታችን የመዝሙር ጥናት እና የጊዜያዊ አባላት ትምህርት ይኖረናል።»

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

28 Dec, 17:03


ሰላም እንደምን አመሻቹ

፨ ነገ የፍሬ ሰንበት ትምህርት ከመዝሙር ጥናት በኋላ ይኖረናል፤ እንዲሁም በተለመደው ሰዓታችን የመዝሙር ጥናት እና የጊዜያዊ አባላት ትምህርት ይኖረናል።

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

28 Dec, 14:51


ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መዋእል
የሐዲስ ኪዳን ዳንኤል፣ አፈ ወርቅ ፣ አፈ ዕንቁ ፣ ልሳነ ወርቅ ፣ ከጥሩ ክርስቲያን ቤተ ሰብ በ347 ዓ.ም. በአንጾኪያ ከተማ ተወለደ ። ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስ ሊባኖስ አንድራስ ፣ ጋስዮስ ከተባሉ መምህራን ዘንድ ፍልስፍናን እና የመናገርን ክህሎት በአቴና ተማረ። በዚህም በፍልስናውና በንግግር ችሎታው ከኹሉም በላይ ኾነ። በኋላ ግን ሰውነቱ በሃይማኖት ተሳበ። መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ውስጥ ገብቶም ብሉያትንና ሐዲሳትን እንዲሁም ሥርዓተ ቤተ-ክርስቲያንን ተማረ ። በዚያን ዘመን ከነበረው ሊቀ ጳጳስ ከቅዱስ ሚሊጢዮስ ዘንድም በወጣትነት ዕድሜው አርዑተ ምንኩስናን ተቀበለ ። በ381 ዓ.ም. ዲቁናን ፣ በ386 ዓ.ም ደግም ቅስናን ተሾመ ። በአንጾኪያው ሊቀ ጳጳስ በፍላብያኖስ በተሰጠው የቤተ-ክርስቲያን ጠባቂነትና እንደራሴነት መሠረት ከ386 እስከ 397 ዓ.ም ድረስ ወንጌልን አስተማረ። በ397ዓ.ም ላይ ኒከታሪዮስ የተባለው  የቁስጥንጥንያ ፓትሪያርክ ስላረፈ በንጉሥ አርቃድዮስ አሳሳቢነት  የካቲት 26 ቀን 398 ዓ.ም. ላይ በብዙ ልመና በግድ የቁስጥንጥንያ  ፓትሪያርክ ኾኖ ተሾመ። ማንንም የማይፈራ ፊት አይቶም የማያደላ '' መምህር ወመገሥፅ  ዘኢያደሉ ለገጽ '' ስለኾነ ከኤጲስ ቆጶሳትም ኾነ ከመንግሥት ወገን ሕገ እግዚአብሔር የሚተላለፉትን ኹሉ ክፉኛ ይገሥፃቸው ስለ ነበር ብዙ መከራዎችን ተቀብሏል፤ አግዘዉታልም። በዚህም ምክንያት በ403ዓ.ም እነዚህ ክፉ ሥራ ሠርተው ፈጣሪያቸውን በድለው ከሹመታቸው ተሽረው የነበሩት ኤጲስ ቆጶሳት መፍቀሪተ ንዋይ ገፋዒተ ነዳይ በምትባለው በንጉሥ አርቃዴዎስ ሚስት በንግሥት አውዶክስያ አሳሳቢነት ተሰብስበው '' ተግዞ ፣ ተሰዶ ሊሞት ይገባል '' ብለው ፈረዱበት። ከመንበሩ አውርደውም አጥራክያ ወደተባለች ደሴት ወሰዱት።ነገር ግን መኳንንቱ ሕዝቡ እንዲሁም ካህናቱ ሊቁን እንደ አባት ያከብሩት እንደ መምህርም ያፍሩት ስለ ነበር ከሠረገላቸው ወርደው ያለ ጫማ ሔዱ። ከል ለበሱ፤ ከል ጠመጠሙ፤አዝነው ተክዘው ተቀመጡ። ዳግመኛም በሀገሩ ኹሉ ፍጹም መነዋወጽ ኾነ። ንጉሥ አርቃድዮስም የሚስቱን የአውዶክስያን ፈቃድ ሳይጠይቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን ከተሰደደበት አስመጥቶ ከቀደመ ቦታው ከቀደመ ማዕረጉ መለሰው። ንግሥቲቱ ግን ሌላ ምክንያት ፈልጋ እንደገና ቀድሞ ወደ ተጋዘበት ስፍራ ሰደደችው። እርሱም መንገድና እስራት እንዲሁም ድካም ስለፀናበት ገና ከመድረሱ ግንቦት 12 ቀን 407 ዓ.ም.ዐረፈ። በአንደበቱ የነበረው የመጨረሻ ቃልም  ''ስለ ኹሉ ነገር ክብር ለእግዚአብሔር ይኹን '' የሚል ነበር አፅሙም ወደቁስጥንጥያ ተመልሶ ዐርፏል። ዝንጉዎችን የሚያስደነግጣቸው የተጨነቁትን ደግሞ የሚያጽናናቸው ይህ እጅግ የተወደደ የቤተክርስትያን መምህር የብሉያትና የሐዲሳት ትርጓሜያትን የያዙ ከ900 በላይ መጻሕፍትን ጽፏል። ከሌሎች አባቶች የትርጓሜ ሥራ ይልቅ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትርጓሜ ለየት የሚለው በእያንዳንዱ ትርጓሜው መጨረሻ ላይ ራሱን የቻለ ስብከትና ተግሣጽ አሉ። ለምሳሌ የማቴዎስ ወንጌል ብቻ 88 ስብከቶች አሉ። እርሱ በተረጐማቸው ሌሎች መጻሕፍትም እንደዚኹ ቁጥራቸው የበዙ ስብከቶች አሉ። ምንም እንኳን የሚበዙት ሥራዎቹ ስብከት ነክ ቢኾኑም ሙሉ ለሙሉ ነገረ ሃይማኖትንና ሥርዓተ ቤተ-ክርስቲያንን እንዲሁም ዕቅበተ እምነትን ማዕከል ያደረጉ መጻሕፍትም ጽፏል።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር  የቅዱስ ዩሐንስ አፈወረቅ ጸሎቱ ይርዳን አሜን!

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

27 Dec, 11:39


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

በነገው ዕለት የሚከበረውን የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓልን በማስመልከት በኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርስቲያን በዕለቱ የሚቀርበውን እጅግ ጥልቅ ምስጢር የያዘውን ቃለ ማኅሌትና ዋይ ዜማን በአንድ ልብ በአንድ ቃል ለማመስገን ይረዳን ዘንድ  ይህ ሥርዓተ ማኅሌት እንደሚከተለው ቀርቧል።

        🌸 መልካም በዓል🌸

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

25 Dec, 18:55


ሰላም እንዴት አመሻችሁ

፨ የጥምቀት እና የልደት attendance የሚነሳው 11:15 ነው በሰዓቱ ተገኝተን ጥናቱን እንድንካፈል ይሁን ::

፨ ከዚህ በታች ስማችሁ የተዘረዘረ የጥምቀት ሰልፍ ላይ የተጨመራችሁ አባላት ናችሁ አርብ 11:00 ሰዓት ጥናት እንድትገኙ ይሁን

1 ጽዮን ሲሳይ
2 ኤፍራታ ኢዮብ
3 ሜሮን ተመስገን

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

25 Dec, 14:01


ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ pinned «ሰላም እንዴት ዋላቹ ፨ የፍቅር ጉባዔ የምታቀርቡ አባላት ነገ ሐሙስ 17/04/2017 ዓ/ም ጥናት ስለሚኖረን 11:00 ሰዓት እንድትገኙ»

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

25 Dec, 14:01


ሰላም እንዴት ዋላቹ

፨ የፍቅር ጉባዔ የምታቀርቡ አባላት ነገ ሐሙስ 17/04/2017 ዓ/ም ጥናት ስለሚኖረን 11:00 ሰዓት እንድትገኙ

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

24 Dec, 18:57


ሰላም እንደምን አመሻችሁ

፨ ነገ መደበኛ የጥምቀት የልደት እና የቅዱስ ገብርኤል እንዲሁም የወረብ ጥናታችን ይቀጥላል በሰዓታችን 11:00 እንድንገኝ ይሁን
፨ ከላይ የተለቀቁ መዝሙራትን የቅዱስ ገብርኤል ተሰላፊ አባላት በደንብ ሰምታችሁት እንድትመጡ ይሁን።

መልካም ምሽት

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

24 Dec, 16:43


ነዓ/3/ ገብርኤል/2/
ነዓ ገብርኤል/4/ የአናንያ የአዛርያ ኃይል
ነዓ ገብርኤል /4/ ገብርኤል የአምላክ ባለሟል

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

24 Dec, 16:43


አርየኒ ገፀከ በአስምዓኒ ቃልከ/2/
ገብርኤል/3/ ሊቀ መላዕክት /2/

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

24 Dec, 16:43


ዓይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ/2/
አመልማለወርቅ/3/ ገብርኤል ሊቅ/2/

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

21 Dec, 18:07


ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ pinned «ሰላም እንደምን አመሻቹ ነገ የመዝሙር ጥናት እና የጊዜያዊ አባላት ትምህርት አለ በሰዓታችን ቀደም ብለን እንድንገኝ ይሁን። ቦታ ፨ የመዝሙር ጥናት አዳራሽ (6:30 ላይ ስለምንጀምር ሰዓት ይከበር!) ፨ የጊዜያዊ አባላት ላይብረሪ»

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

21 Dec, 18:07


ሰላም እንደምን አመሻቹ

ነገ የመዝሙር ጥናት እና የጊዜያዊ አባላት ትምህርት አለ በሰዓታችን ቀደም ብለን እንድንገኝ ይሁን።

ቦታ

፨ የመዝሙር ጥናት አዳራሽ (6:30 ላይ ስለምንጀምር ሰዓት ይከበር!)
፨ የጊዜያዊ አባላት ላይብረሪ

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

17 Dec, 19:10


ሰላም እንደምን አመሻቹ

፨ ማክሰኞ 22/04/2017 ዓ/ም የተጨማሪ ቀን ፋይናል ፈተና ስላለ እንድትዘጋጁ

፨ ምድብ ቅዱስ አትናቴዎስ ሐሙስ (10/04/2017 ዓ/ም) 11:00 ሰዓት ጠበል ቤት እንድንገናኝ

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

15 Dec, 19:42


በደብረ ገሊላ ቅዱስ አማኑኤል ካቴድራል እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት ሕፃናት እና ማዕከላዊያን ክፍል የማዕከላዊያን ክፍል መርሐግብር በቀን 05/04/2017 ዓ/ም በማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ለማርያም እና ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በተክለ ሳዊሮስ ሰንበት ት/ቤት በማዕከላዊያን ክፍል አባላት ሙሉ መርሐግብሩ የተሸፈነ ሲሆን በዕለቱም
ትምህርተ ወንጌል
                 የህብረት ዝማሬ
                 መዝሙራዊ ተውኔት
                 እንዲሁም ወረብ  ቀርቧል
ለወንድምና እህቶቻችን ከዚህ በላይ የሚያገለግሉበት ዕድሜ እና ጤና ያድልልን🙏

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

04 Dec, 04:36


የ2017 ዓ.ም የሥነ ሥዕል ክፍል መግቢያ ፈተና ያለፉቹ አባላት
1. ሶፎንያስ ሚሊዮን                
2. አቤኔዜር አድማሱ                       
3.  ራሔል ጨነቀ                                  
4.  እምነት የሺጥላ                                
5.በአምላክ ቸርነት                      
6.ቃለአብ በረከት           
7.የአብስራ ሽመልስ                  
8.የአብስራ ታምሩ                          
9. ትናኤል ጌቱ           
10.ኤርምያስ ፋሲል      
11.ማኅሌት ደግፌ        
12. ሳምሶን አለባቸው
13.የአብስራ ጸጋ
14.ናትናኤል ደጀኔ        
15. አናንያ ሚሊዮን       
16. ምሕረት ኤርምያስ
17. ሙሉቀን ሰይፈ
18. አልዓዛር ይልማ     
19. መስከረም ትግስቱ
20. ቃልኪዳን መኮንን
21. ሰላማዊነ ዓለማየሁ
22. ሩት ለገሠ
23.ረድኤት ታደሠ
24.ዳግም ኤፍሬም
25.ሜሮን አማረ
26.ሊያ ንጉሤ
27.ናታኒም አዲስዓለም
28.ሚኪያስ መስፍን
29.ቤዛዊት ደምሴ
30.ቃለኢየሱስ ያሬድ
31.በሱፈቃድ መሰለ
32.ዮሐንስ ቢልልኝ
33.ዘዳግም ባህሩ


ቅዳሜ 28/03/2017 ከጠዋቱ 3:00 ዋጮ እንድትገኙ

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

02 Dec, 18:07


ፈተናው የሚሸፍንባቸው ትምህርቶች
1. ትምህርተ ሃይማኖት
2. ሥነ ፍጥረት
3. 3ቱ ጉባኤያተ ቤ/ክን
4. ጠቅላላ ዕውቀት

የፈተና ቀን እሑድ በ29 ከመዝሙር ጥናት በኋላ ።

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

01 Dec, 14:46


ማስተካከያ

ነገ ሰኞ 11:00 የሚጀምረው የቅዱስ ገብርኤል ሰልፍ ጥናት ነው የልደት እና የጥምቀት ጥናት በቀጣይ ይነገራል ማስታወቂያ ተከታተሉ

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

30 Nov, 17:38


እንደምን አመሻችሁ

፨ ነገ ለምናደርገው ጉዞ የተወሰነ ቦታ ስላለ ጠዋት መክፈል የምትችሉ አባላት እንድትመጡ ይኹን ። ( እስከ 20 ሰው ድረስ ብቻ )

ማሳሰቢያ
፨ ተጓዦች ጠዋት 12 ሰዓት ደረሰኛችሁን ይዛችሁ ኑ።

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

29 Nov, 19:42


ቴሌግራም ለማይጠቀሙ ጓደኞቻቹም ማስመዝገብ ትችላላቹ

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

29 Nov, 18:36


ሰላም እንዴት አመሻቹ

ጉዞ ነገ የምትከፍሉ አባላት እንደምትከፍሉ እርግጠኛ የሆናቹ @weletehana11 ላይ ስማቹን እና ቁጥራቹን እስከ 5:30 እንድትልኩ::

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

28 Nov, 20:16


ሰላም እንዴት አመሻቹ
      
                ጉዞ
ቦታ:- መካነ ቅዱሳን ዋሻ ቅድስት ሥላሴ እና ቅዱስ ሩፋኤል ገዳም እንዲሁም ዘንዶ አስራ በዓታ ማርያም
             
ቀን:- ህዳር 22
ዋጋ :-250 ብር

ያለን ቦታ እየሞላ በመሆኑ ጉዞውን መሳተፍ የምትችሉ አባላት ነገ አርብ ከ11:00 - 12:30 ቢሮ እየመጣቹ መክፈል ትችላላቹ::

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

28 Nov, 07:00


ማየ ሕይወት

👉 በጨዋታ የማርያም መንገድ ከተባለ ማንም ሰው ያሳልፋልና እኛም ለቤተክርስቲያናችን፣ ለሀገራችን .... በማርያም መንገድ ማየ ሕይወትን ይዘን መጣን

እነሆ ለማዕከላይ ክፍል አባላት ትኬት 25 ብር በመሆኑ ይህ ታላቅ እድል እንዳያመልጣችሁ
ትኬቱን የህፃናትና ማዕከላውያን ኪነ ጥበብ ክፍል ማግኘት ትችላላችሁ

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

27 Nov, 11:53


ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ pinned «ሰላም እንዴት አመሻቹ                        ጉዞ ቦታ:- መካነ ቅዱሳን ዋሻ ቅድስት ሥላሴ እና ቅዱስ ሩፋኤል ገዳም ዋሻ፣አምሳለ ሲዖል፣የቅዱሳን አፅም ያለው እንዲሁም                 የቅድስት ሥላሴ                 የቅድስት ኪዳነምህረት                 የቅዱስ ገብርኤል                 የቅዱስ ሩፋኤል እና                 የቅድስት አርሴማ ፀበል…»

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

25 Nov, 18:59


ሰላም እንዴት አመሻችሁ
* ለጥምቀት ሰልፍ ትምህርት ክፍል ቅሬታ ያስገባቹ አባላት ነገ 17/03/2017 ዓ.ም አባላት ክትትልን እንድታናግሩ ይሁን።

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

25 Nov, 18:38


ሰላም እንዴት አመሻችሁ
* ለጥምቀት ሰልፍ ቅሬታ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን ነገ 17/03/2017 ዓ.ም ይሆናል። ከነገ ውጪ ቅሬታ ለማስገባት የሚመጣ አባል የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን።
ማስታወሻ
* የፊታችን ቅዳሜ ማለትም በ21/03/2017 ለጥምቀት ሰልፍ መዝሙር ማጥናት የሚችሉ አባላትን ስም ዝርዝር እናሳውቃለን።

                 የአባላት ክትትል ንዑስ ክፍል

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

24 Nov, 18:24


ሰላም እንዴት አመሻቹ
      
                ጉዞ
ቦታ:- መካነ ቅዱሳን ዋሻ ቅድስት ሥላሴ እና ቅዱስ ሩፋኤል ገዳም
ዋሻ፣አምሳለ ሲዖል፣የቅዱሳን አፅም ያለው እንዲሁም
                የቅድስት ሥላሴ
                የቅድስት ኪዳነምህረት
                የቅዱስ ገብርኤል
                የቅዱስ ሩፋኤል እና
                የቅድስት አርሴማ ፀበል ያለው ሲሆን ፀበሎቹም ቀጥታ ከቤተ መቅደስ የሚመጡ የቅዳሴ ፀበል ናቸው 
  :- ዘንዶአስራ በዓታ ማርያም ቤተክርስቲያን
  ብዙ ተአምራት ፈውስ የሚደረግበት እንዲሁም ዋሻ ያለው ሲሆን ከቦታው ረድኤት በረከት እናገኝ ዘንድ ጉዞውን እንሳተፍ
ቀን:- ህዳር 22
ዋጋ :-250 ብር

እስከ አርብ 12:30 ቢሮ እየመጣቹ መክፈል ትችላላቹ

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

24 Nov, 12:30


ከታች ስማቹ የተዘረዘረ አባላት ለስነ-ስዓል ትምህርት ተመዝግባቹ ፈተና ያልተፈተናቹ ስለሆነ ነገ ማለትም ሰኞ 10:30 ስነ-ስዕል ክፍል (ዳቦ ቤት) እንድትገኙ


1,ጽናት ፈቀደ
2,ጽናት ክብሩ
3,መቅደላዊት ትዕግስቱ
4,ሶልያና ስዩም
5,ራሔል ቸሩ
6,ሜናታ ተስፋዬ
7,ሳምራዊት ይርጋለም
8,ቢታንያ ሽብሩ
9,ናርዶስ ሳሙኤል
10,በጽናት መኮንን
11,አስቴር ደምስ
12,ህሊና ኃይሉ
13,መክሊት አድማስ
14,ማኅሌት ሲሳይ
15,ዳናዊት ያሬድ
16,ማህሌት ደግፌ
17,ምንተስኖት ዳዊት
18,በለጠች አሰግደው
19,ቤተልሔም መኮንን
20,ማኅሌት ወ/አማኑኤል
21,ዝናሽ የትዋለ
22,ኤልዳና ስመኘው
23, ደስታ ጣሰው
24, መክሊት ስመኘው
25, ሮዝማሪ ተክሉ
26, ሳምራዊት ተክሉ
27, ረድኤት አብዮት
28, ዳግማዊት ሰሎሞን
29, ብዙአየሁ ገዛኸኝ
30, ናታኒም አዲስአለም
31, በሱፍቃድ መሰለ
32, ዳግም ገረመው
33. ሮቤል አበበ
34, ሚካኤል ተስፋዬ
35, በረከት ሉሉ
36, የአብስራ ፀጋ
37, ስምዖን አብይ
38, ሀሮን ኃ/ማርያም
39, ኢዮስያስ አክሊሉ
40, ኃ/ማርያም ወለላ
41, ያሬድ ወንድሙ
42, የአብስራ ጀማል
43, አቤሜሌክ አሸናፊ
44, ነቢዩ ኤልያስ
45, ቡሩክ ጌታቸው
46, ዳግም ገረመው
47, ምንተስኖት ገረመው
48, ዳግም እሸቱ
49, ናትናኤል ጥላሁን
50, ሕዝቅኤል መስፍን
51, ዳግም ዮሴፍ
52, ዮናታን አስፋው
53, ኤርሚያስ ወ/ዩሐንስ
54, ሚክያስ መስፍን

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

23 Nov, 19:21


ሰላም እንዴት አመሻቹ

የት/ት ክፍል የመርሐግብር ውጤት ለጥምቀት አገልግሎት ማየት የምትፈልጉ ነገ ከመዝሙር ጥናት በኋላ ቢሮ ማየት ትችላላችሁ ።

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

19 Nov, 18:07


ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ pinned «ሰላም እንዴት አመሻቹ ምድብ ቅዱስ ዩሐንስ አፈወርቅ ሐሙስ 11:00 ሰዓት እንድትገኙ»

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

19 Nov, 18:07


ሰላም እንዴት አመሻቹ
ምድብ ቅዱስ ዩሐንስ አፈወርቅ ሐሙስ 11:00 ሰዓት እንድትገኙ

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

18 Nov, 06:46


ለተከታታይ 8 ወራት ሲሰጥ የነበረው የዜማ መሳሪያ የበገና እና የመሰንቆ ትምህርት
ህዳር 7/2017 ዓ/ም ተጠናቀቀ

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

15 Nov, 06:59


እንዴት?
በኃጢአት በሰከረው ባደፈው ማንነቴ
አንተን በበደለ በከልዋሳ ህይወቴ
ፍሬዬን ፈልገህ ብትመጣም ወደ'ኔ
ለሙን መሬትህን ባጎሳቁልብህ በኃጢአት አረሜ
እንዴት?
እልፍ ብበድልህ
ፊቴን ባዞርብህ
ባልተናነስ እንኳ ያኔ ከተፉብህ
ፈራጅ ሆነክ ሳለ ከፈረዱብህ
ለምን?
ለእኔ ሞትን ከጀልክ
ለበደሌ መከራን ዋጀክ
ለምን?

               ፀሀፊ ዮካብድ መኮንን

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

14 Nov, 19:15


ይመልሱ ያንብቡ መጽሐፍ ወስዳችሁ ያልመለሳችሁ እስከ ቅዳሜ ድረስ በሰንበት ት/ቤቱ ሱቅ እንድትመልሱ ይሁን

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

11 Nov, 05:51


ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ:
ሰላም እንደምን አመሻቹ

ሰኞ 11:00 ሰዓት ሦስቱንም ምድብ ያቀረባቹ አባላት ( ምድብ አባ ጽጌ ድንግል ፣ ዩሐንስ አፈወርቅ እና ቅዱስ አትናቴዎስ የሆናቹ) በሥነ ምግባር ክፍል የተዘጋጀ ውይይት ስላለ እንድትገኙ

ቦታ - አዳራሽ
መቅረት አይቻልም

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

09 Nov, 15:00


🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

እንኳን ለዘመነ ጽጌ የመጨረሻ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ በሰላም አደረሳችሁ።

📌በኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርስቲያን  የተፈጸመ ጽጌ ማኅሌትን በአንድ ልብ በአንድ ቃል ለማመስገን ይረዳን ዘንድ  ይህ ስርዓተ ማኅሌት እንደሚከተለው ቀርቧል።

💻ዛሬ ማታ ከ3፡00 ሰዓት ጀምሮ በዩቲዩብ ገጻችን ፤ የቀጥታ ስርጭት ይጠብቁን ።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
http://youtube.com/@EMislene

🌸🌺🌹🌷💐🌸🌺🌹🌷💐🌸🌺

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

06 Nov, 11:39


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

📌ሐሙስ ጥቅምት ፳፰ የሚከበረውን የአምላካችንን የአማኑኤል ዓመታዊ በዓልን በማስመልከት በኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርስቲያን በዋዜማው የሚቀርበውን እጅግ ጥልቅ ምስጢር የያዘውን ቃለ ማኅሌትና ዋይ ዜማን በአንድ ልብ በአንድ ቃል ለማመስገን ይረዳን ዘንድ  ይህ ስርዓተ ማኅሌት እንደሚከተለው ቀርቧል።

   🌸 መልካም በዓል🌸


የቲክቶክ ገጽ፡
https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

04 Nov, 18:27


ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ pinned an audio file

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

04 Nov, 18:14


የትምህርት ክፍል ማስታወቂያ
፨ የተጨማሪ ቀን ት/ት ነገም ይቀጥላል ።
፨ ክፍል 3: የሥርዓተ መጻሕፍት
፨ ሰዓት : 10: 45

ማሳሰቢያ : ማርፈድም መቅረትም አይቻልም።

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

04 Nov, 09:26


እምነ በሀ ቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርጉት አረፋቲሃ ወስዕልት በዕንቊ ጳዝዮን እምነ በሀ ቅድስት ቤተክርስቲያን

መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሠርገወ ሰማየ እምኲሉሰ ፀሐየ አርአየ መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሠርገወ ሰማየ

ኲሉ ዘገብራ ለጽድቅ ጻድቅ ውእቱ ወዘያከብር ሰንበተ ኢይበል ፈላሲ ዘገብአ ኀበ እግዚአብሔር ይፈልጠኒኑ እምሕዝቡ ኲሉ ዘገብራ ለጽድቅ ጻድቅ ውሕቱ ወዘያከብር ሰንበተ

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

25 Oct, 18:52


ሰላም እንደምን አመሻችሁ

እንደሚታወቀው የመጀመርያዉ ዙር ጉዞ ህዳር ወር ላይ ይኖረናል እናም አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኝ ብንሄድበት የምትሉትን ደብር ወይም ገዳም ካለ(የቦታው ሰላማዊ ሁኔታውንም ያማከለ) ለነገ መርሐግብር አስባቹ እንድትመጡ እንዲሁም ቦታ ጥቆማ በምታደርጉ ጊዜ ከተቻለ የቦታውን ሙሉ አድራሻ ይጠቀስ

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

25 Oct, 18:21


፨ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ።
- የነገው የመደበኛ መርሐግብር ፈተና እንዳይረሳ።

ትምህርት ክፍል

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

23 Oct, 15:14


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርስቲያን በዋዜማው የሚቀርበውን እጅግ ጥልቅ ምስጢር የያዘውን በአንድ ልብ በአንድ ቃል ለማመስገን ይረዳን ዘንድ  ይህ ስርዓተ ማኅሌት እንደሚከተለው ቀርቧል።


📌ሥርዓተ ማኅሌትና የንግሥ በዓሉን በቀጥታ ስርጭት ከምሽት 3 ሰዓት ጀምሮ ይጠብቁን።

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
http://youtube.com/@EMislene

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

21 Oct, 19:19


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ለጥቅምት አማኑኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል መዝሙር ማጥናት የሚችሉ አባላት ስም ዝርዝር
ቤዛዊት ትግሉ
ናርዶስ ዮሐንስ
ኑሃሚን ይርጋ
ረቂቅ ተሰማ
ፅናት ክብሩ
አስቴር ግዛቸው
ቤተልሄም ስዮም
ትዕግስት አንድአምላክ
ፍቅር ፍቃዱ
መቅደላዊት አላቅማቸው
ኩሜ ተገኝ
ቤዛዊት ገዛኸኝ
ሰላም ጌታሰው
ኤፍራታ ኢዮብ
ቃልኪዳን አድማሱ
ዮርዳኖስ ተገኝ
ቃልኪዳን ፈለቀ
የአብስራ በላቸው
ጽዮን ስንታየው
ረድኤት ሰለሞን
ሰላም ግርማ
ሰላም ከበደ
ያኔት ታሪኩ
ፍሬህይወት መውለድደግ   
መስፈርት አባላት ክትትል አቴዳንስ ብዛት የታየው ከ37 አቴንዳንስ 70% ትምህርት ክፍል ውጤት ከ100 30%  ነው

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

21 Oct, 16:16


ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ pinned «፨ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ። - ነገ የተጨማሪ ቀን ትምህርት ይጀምራል ። ሰዓት : 10:45 ቦታ : አዳራሽ ማሳሰቢያ : ማርፈድም መቅረትም አይቻልም።»

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

21 Oct, 16:06


፨ በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ።
- ነገ የተጨማሪ ቀን ትምህርት ይጀምራል ።
ሰዓት : 10:45
ቦታ : አዳራሽ
ማሳሰቢያ : ማርፈድም መቅረትም አይቻልም።

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

19 Oct, 12:36


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

እንኳን ለዘመነ ጽጌ 3ኛ ሳምንት ማኅሌተ ጽጌ በሰላም አደረሳችሁ።

በኦርቶዶክሳዊት ቅድስት ቤተክርስቲያን ሁለተኛ ሳምንት የጽጌ ማኅሌትን በአንድ ልብ በአንድ ቃል ለማመስገን ይረዳን ዘንድ  ይህ ስርዓተ ማኅሌት እንደሚከተለው ቀርቧል።

🌸 እንኳን አደረሳችሁ🌸

🏡ቤተሰብ ይሁኑ!
የዩቲዩብ ቻናል፡
http://youtube.com/@EMislene
የቴሌግራም ቻናል፡
https://t.me/EMislene
የፌስቡክ ገጽ፡
https://www.facebook.com/EMislene/
የኢንስታግራም ገጽ፡
https://www.instagram.com/egziabher_meslene28/
የቲክቶክ ገጽ፡
https://www.tiktok.com/@egziabhermeslene28
ድሕረ ገጽ፡
www.debregelila.org

🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷🌹🌷

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

19 Oct, 06:55


ለጥቅምት አማኑኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል መዝሙር ማጥናት የሚችሉ አባላት ስም ዝርዝር
1.ቤዛዊት ትግሉ
2.ናርዶስ ዮሐንስ
3.ዳናዊት ኤልያስ
4.ኑኃሚን ይርጋ
5.ረቂቅ ተሰማ
6.ጽናት ክብሩ
7.አስቴር ግዛቸው
8.ቤተልሔም ስዩም
9.የዓለምወርቅ ግርማ
10.ትዕግስት አንድአምላክ
11.ሩት ተመስገን
12.ፍቅር ፍቃዱ
13.መቅደላዊት አላቅማቸው
14.ርብቃ ክብሩ
15.ኩሜ ተገኝ
16.ቤዛዊት ገዛኸኝ
17.ሰላም ጌታሰው
18.ኤፍራታ እዮብ
19.ሔለን እንዳለ
20.ቃልኪዳን አድማሱ

መስፈርት
አባላት ክትትል አቴዳንስ ብዛት የታየው 37 አቴንዳንስ
70% አቴንዳስ

ትምህርት ክፍል ውጤት ከ100
30% ውጤት

ቅሬታ ከመርሐ ግብር በኋላ ቢሮ
በተለያየ ምክንያት መሰለፍ የማትችሉ አባላት እንድታሳውቁ ይሁን

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

17 Oct, 18:42


ከመደርደሪያችን

             የደብረ ገሊላ አማኑኤል ካቴድራል  
           እግዚአብሔር ምስሌነ ሰንበት ት/ቤት

       የሕይወት ምግብ የሆኑትን ቅዱሳት መጻሕፍት    
 ሊመግብዎ መደርደሪያውን ሞልቶ ይጠብቅዎታል።
    ከመደርደሪያዎ ሊጠፋ የማይገባውን ይህንን መጽሐፍ በቤቶ ከተሰነዱ ሌሎች መጻሕፍት ጋር ቤተሰብ እንዲያደርጉት እና በቃሉ ተጠቅመው ወጣትነቶን እንዲያሳምሩ  የሰንበት ት/ቤታችን ሱቅ የጀርባው ዋጋ 400 የሆነውን መጽሐፍ በ 20 % ቅናሽ በዚህ ዋጋ 320  ለአንባብያን አቅርበናል።

ይህ ቅናሽ የሚቆየው እስከ መጽሐፍ ዳሰሳው ቀን ብቻ ነው ያለን ኮፒዎች ጥቂት ስለሆኑ ቀድመው በማዘዝ መውሰድ ይችላሉ።

ለማዘዝ https://t.me/mes_suk

እና 0989196891 ይደውሉ

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

17 Oct, 13:27


እነሆ ክረምቱ አለፈ በረከትም ሆነ ምድርም በአበባ ተጌጠች ተሸለመች
# ፅጌ ማለት አበባ ማለት ሲሆን ዘመነ ፅጌ ማለት የአበባ ወራት (ወቅት )ማለት ነው። የተዘራው ዘር በቅሎ ለፍሬ ዝግጁ መሆኑን የምናይበት መሬት ደምቃ አሸብርቃ የምትታይበት ወቅት በመሆኑ ነው
* ከመስከረም26 ጀምሮ እስከ ህዳር 5 ቀን ያለውን ወቅት ቤተክርስትያናችን ዘመነ ፅጌ እያለች ትጠራዋለች
# ዘመነ ፅጌ የክረምቱን ማለፍ ተከትሎ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በእናቱ ጀርባ ላይ ሆኖ ንጉስ ሔሮድስን ሽሽት ወደ ግብፅ ሀገር መሰደዱን የሚታሰብበት ወቅት ነው።
* በዚህ ወቅት የእመቤታችንን ከልጇ ጋር በበረሀ መሰደድዋን በማሰብ ሊቃውንቱ በሰንበት ማህሌተ ፅጌ የተሰኘውን የአባ ፅጌ ድንግልን እና የአባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሀንታ ድርሰት በማህሌት ይቆሙታል።
# የእመቤታችንን ፍቅሯን እናትነቷን አማላጅነቷን በማሰብ ሊቃውንቱ ጋር ሆነን በዝማሬ እናወድስበታለን እመአምላክን ከነልጇ እናስብበታለን።

* ፈልቀሽ የተገኘሽ ከአፈ መላእክት፣
ያሬድ የተማረሽ ከላይ ከሰማያት፣
እንከን የሌለብሽ አዲሷ ምስጋና።

# ምስጢርሽ ሲገለጥ በአስደናቂ ዜማ፣
ከሰማይ መንጭተሽ በምድር ሲሰማ፣
በቃናሽ መሰጠሽ ልቡናን በመክፈት፣
ማርከሽ ትወስጃለሽ ነፍስን ወደ ገነት።

* የፍቅር መግለጫ የሕይወታችን አርማ፣
ጣእምሽ ልዩ ነው ሲገለጥ በዜማ።
የአድባራቱ ሁሉ ቋንቋና ድምጻቸው፣
የካህናት ቅኔ ሰምና ወርቃቸው፣
ለህዝብ ሁሉ የነፍስ ምግባቸው፣
ማኅሌት እኮነሽ ጸጋና ሃብታቸው

# ደረሰ ሰዓቱ_እንገስግስ መቅደሱ
ሊዘረጋልን ነው_ቅኔ መወድሱ
የአባ ጽጌ ድንግል_የምስጋናው ሻማ
ሊበራ ሊነድ ነው_ለነፍስ የሚስማማ

# ተጠርተው በፍቅሩ_ የሄዱት ምዕመናን
መስቀልያ አጣፍተው_ተውብው በብርሃን
ሐሴት ተጎናፅፈው_በቅድስቷ ድንኳን
ሲታይ በረከቱ_ መዓዛ ወ ዕጣን
ይወስዳል በሀሳብ_ ወደ ሰማይ ዙፋን።

* የስደቷን ነገር_ መከራዋን አይቶ
ከአለማመን መንፈስ_ ፈቅዶ ተለይቶ
የክርስቶስ ፍቅር_ እውነቱ ሲገባው
ጣቶቹን አንስቶ_ ማሕሌቷን ጻፈው
አባ ጽጌ ድንግል_ የእውነት አበባ ነው።

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

17 Oct, 09:58


እንባ
ከፈሳሾች መርጠህ ካደረከኝ እንባ
አልቃሹን አድርገው ለሀጥያቱ ሚያነባ
ልክ እንደ ይሁዳ ጩኸቱ ላይሰማ
ፀጥታ በዋጠው በቀለጠው ጩኸት
                       ልቡን ከሚያደማ
ልክ እንደ ከሀዲው ትንቢቱን ፈፃሚ
ደብዛዛውን ስህተት በጥፋት አቅላሚ
መፍሰስ እንኳ ባልችል ከባለሽቷይቱ
አሳልፈህ አትስጠኝ ለእንደዚ አይነቱ
ምሕረትን ያሰጠ ልብህን ያባባ
መሆን እንኳ ባልችል የራሄልን እንባ
ሳቁ አንሰቅስቆት ከሚያነባ ከንቱ
የሳቅ ቀመር ከእንባ ከተምታታ ስልቱ
ከአለም ወራዚ ቋሳን ከሸመቀ
እንደባልቴት ዲናር ራሱን ከደበቀ
ልክ እንደ ጨለማ ላይዛለቅ ነገር
ምሕረትን ባያሰጥ ሽባን ባይተረትር
ከሕግህ ጠባቂ ከቅዱስ ባልወርድም
ነካታን ፈውሼ ላዘልል አልልም
እንደእናትህ እንባ ፍጥረትን ባልቀድስ
ከንቱነት ካሰረው በከንቱ ከሚያለቅስ
ከእንደዚ አይነቱም እባክህ አልፍሰስ
መሆን እንኳ ባልችል አፅናኝ የዘመኑ
ከንቱ እንዳያፈሰኝ መልሰኝ ከአይኑ ።

                     ፀሀፊ:- ቅድስት ጌታሁን
                         ከሥነ-ፅሁፍ ክፍል

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

15 Oct, 03:19


ለድርሰት ቡድን አባልነት የተመዘገባችሁ
1,ዮናስ እልኩ
2,አማኑኤል ተስፋዬ
3,ፅዮን አንሙት
4,ቃልኪዳን ብርሀኑ
5,ራኬብ አሸብር
6,ገሊላ ስለሺ

     ከዚህ በላይ ስማቹ የተጠቀሰ አባላት ለድርሰት ቡድን መግቢያ ፅሁፍ አስገቡ ተብላችሁ አላስገባችሁም እና የውድድር ጊዜው ሳያበቃ ሀና እንድሪስን (    @Hana_Endris28 ) እንደታወሯት ይሁን

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

14 Oct, 09:46


ምድብ ዩሐንስ አፈወርቅ
 
1. ኤደን ጠንክር
2. ዮርዳኖስ አለማየሁ
3. ማህሌት አድነው
4. ተአምር አበበ
5. እድላዊት ዮሴፍ
6. እድላዊት ዳዊት
7. ቤተልሔም ሀብታሙ
8. መቅደላዊት ትእግስቱ
9. ሔለን እንዳለ
10. የዓለምወርቅግርማ
11. ምህረት ኤርምያስ
12. ቤተልሔም ስዩም
13. ፍቅርተ ሲሳይ
14. ሃና ባህሩ
15. ቃልኪዳን አስራት
16. ምህረት ደሳለኝ
17. ሜሎና በዳሳ
18. ሕይወት ኤልያስ
19. ይድድያ ፈጠነ
20. ቃልኪዳን ደጀኔ
21. ማህደር ወንደሰን
22. ጫልቱ ተስፋዬ
23. ትዕግሥት ዘውዴ
24. መስከረም ቢረዳ
25. ቅድስት ጌጡ
26. እናት በቀለ
27. ዮሃና ኤፍሬም
28. ኤፍራታ እዮብ
29. ሔርሜላ ኃ/ገብርኤል
30. ጽዮን ካሳሁን
31. ሳሮን አዲስ
32. አስቴርፈታ
33. ሃና ሽፈራው
34. ትዕግሥት ሳህሌ
35. ፅጌረዳ ድንቅነህ
36. ረድኤት ዳንኤል
37. ምህረት ደበበ
38. ኑኃሚን ብርሃኑ
39. በለጠች አሰግደው
40. ምህረት ታደሰ
41. እድላዊት አሰግደው
42. ቤዛዊት ገዛኸኝ
43. ጽዮን ጌታነህ
44. ሰላም ግርማ
45. ሔዋን ፍቃዱ
46. ቅድስት ገ/ሚካኤል
47. ኤልዳና ቀኝጌታ
48. መቅደላዊት እንዳለ
49. ጁልያና ቀኝጌታ
50. ባንተ ሲሳይ
51. ኢዮብ ጠንክር
52. ዘዳግም ባህሩ
53. በእምነት አለማየሁ
54. ዮናስ ኤፍሬም
55. ናትናኤል ወንደሰን
56. ዳናዊት ኤልያስ
57. ኤልዳና አቻምየለህ
58. ሩት ሲሳይ
59. ቤተልሔም ተመስገን
60. ሩሀማ ሚሊዮን
61. ናታን አክሊሉ
62. ፀጋዘአብ ወሰንየለህ
63. የአብስራ ፀጋ
64. ጌድዮን መሸሻ
65. ርብቃ ሰሎሞን
66. ረድኤት ታደሰ
67. ያኔት ነብዩ
68. ፀጋ ማሞ
69. ፀጋ ዥቦቴ
70. ቤዛዊት አስናቀ
71, ያኔት ታሪኩ


ነገ ማክሰኞ 11:00 ሰዓት እንድትገኙ

ሕፃናትና ማዕከላዊ ክፍል የማዕከላዊ ክፍል አባላት ገጽ

13 Oct, 15:12


🍂 #ኢትዮጽያዊው_ቄርሎስ በመባል የሚታወቁ “የምስራቃውያን ከዋክብት የትምሕርታቸው ልጅ የኾንኹ” ብለው ራሳቸውን የገለጹ #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ 

        ጥቅምት 3  በዓለ ጽንሰታቸው ነው

+  አባቱ ሕዝበ ጽዮን
 +  እናቱ አምኃ ጽዮን ይባላሉ

🍂ኢትዮጵያዊው ሊቅና ጻድቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ከቅዱስ ያሬድ ቀጥሎ ታላቅ ቦታ የያዘ ኢትዮጵያዊ ሊቅ ነው፡፡

🍂አባ ጊዮርጊስ የተወለደው በ1357 ዓ.ም በወሎ ክፍለ ሀገር በቦረና ወረዳ ሰግላ በተሰኘች ቦታ ነው። ወላጆቹ ልጅ ስለሌላቸው ዘወትር እያዘኑ ወደ እግዚአብሔር ይጸልዩ ነበር።

አባ ጊዮርጊስ የተወለደው በቅዱስ ዑራኤል አብሳሪነት መሆኑን ድርሳነ ዑራኤል ላይ ተዘግቦ እናገኛለን ፡፡ 

 አባቱ ጠቢብና የመጻሕፍት ዐዋቂ፤ የእግዚአብሔር ወዳጅና በቤተ መንግሥት በነበረችው ድንኳን “ሥዕል ቤት” ከሚያገለግሉ ካህናት ወገን ሲሆን የሰግላ ሀገረ ገዥም ነበር።
🍂የአባ ጊዮርጊስን እናት እምነ ጽዮን ከወለቃ /የዛሬው ደቡብ  ወሎ፣ ቦረና/  ከሹማምንት ወገን የሆነች ደግ ሰው ነበረች ።

🍂መንፈሳዊ ትምሕርትን ከአባታቸው በሚገባ ተምረዋል
  በ1341 ወደ ኢትዮጵያ ከመጡትና እስከ አጼ ዳዊት ዘመነ መንግስት ጳጳስ ከነበረሩት አቡነ ሳላማ ዘንድ ማዕረገ ዲቁናን ተቀብለዋል።

🍂ከዚያም ከ1376 - 1405 ዓ/ም ወደ ሐይቅ እስጢፋኖስ የአባ ኢየሱስ ሞዐ ገዳም ወስደው ከታላቁ ሊቅ ዓቃቤ ሰዓት አባ ሠረቀ ብሃን ቤተ ጉባኤም ተምረዋል።

🍂ይኹን እንጂ የቀለም ትምሕርት አልረዳ ቢላቸው በፍጹም ልባቸው ከእመቤታችን ወላዲተ አምላክ ሥዕል ፊት ቆመው ቀን ከሌት በተሰበረ ልብ እየጸለዩ በጾም በጸሎት ተወስነው አየማጸኑ ሳለ በነሐሴ 21 ቀን አመቤታችን ተገልጻላቸው በዕውቀትና በትምሕርት የሚያተጋቸውን ኃይል አሳድራላቸዋለች።

  🍂አባ ጊዮርጊስ የያሬድን ዜማ ከአቡነ ሳሙኤል ዘጋርማ እንደተማረው ገድሉ ይነግረናል፡፡ በዚያ ዘመን በዐፄ ዳዊት አማካይነት በሰሜን ኢትዮጵያ የያሬድ ድጓ ዋና ማዕከል በሆነው በደብረ ነጎድጓድ ተሾሞ ያስተምር ነበር፡፡

🍂በመንፈሳዊ ድርሰት በኩል ኢትዮጵያዊው ሊቅ ጻድቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እስከአሁን በሀገራችን አምሳያ የላቸውም ቅዱሳት እጆቻቸው ከብዕርና ከጽኑዕ ተግባረ እድ ሳይቦዝኑ ዋሻ እየፈለፈሉ የውኃ ጉድጓድ እየቀቆፈሩ ድልድይ እየሠሩ ጣዕመ ዓለም ንቀው ምልዐ ዘመናቸውን በተጋድሎ አሳልፈዋል።

🍂በጊዜውም በትምሕርታቸው የተመሠጡ የቤተክርስቲያን ሊቃውንትና ምእምናን በእኛ ዘመን በፈቃደ እግዚአብሔር የተነሡ “ #ዳግማይ_ዮሐንስ_አፈወርቅ” ሲሏው።

🍂ዓጼ ይስሐቅ ደግሞ” #ኢትዮጵያዊው_ቄርሎስ” ብለዋቸዋል።

🍂በምልዐ ዘመናቸው ከደረሷቸው መጻሕፍት መካከል።ከብዙ በጥቂቱ በቅደም ተከተል ገድላቸው እንዲህ ይገልጻቸዋል
   / መጽሐፈ ምስጢር፣ መዝሙረ ክርስቶስ፣ መጽሐፈ አርጋኖን፣ ውዳሴ መስቀል፣ ኆኅተ ብርሃን፣ ተፈሥሒ ማርያም፣ ሊጦን ፣ ዕንዚራ ስብሐት ፣ ተአምኆ ቅዱሳን ፣ ውዳሴ አምላክ ፣ መልክዐ ስዐል፣ . . ./ ሌሎች ብዙ ድርሰቶችንም ደርሰዋል።

🍂በኹለንተናቸው የፈጣሪያቸውን ምስጋና ሳያቋርጡ ለቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ሥርዓት ሲጋደሉ የኖሩና በቅድስና ሕይወት የአጌጡ የተዋሕዶ ኮከብ ታላቁ ጻድቅ አባ ጊዮርጊስ 🍂ዘጋስጫ በስድሳ ( 60 ) አመታቸው በ1417 ዓ/ም በወርኃ ሐምሌ 7 ቀን ዐርፈዋል ።

በጥቅምት 3 ቀን የጽንሰታቸው መታሰቢያ ነው
     

የጻድቁ አባታቸን የአባ ጊዮርጊስ ረድኤት በረከት አይለየን 🙏🏽

ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሣት ስዕላት ሠዓሊ

1,243

subscribers

1,488

photos

37

videos