የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL @learn_orthodox03 Channel on Telegram

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL

@learn_orthodox03


✞ በየጊዜው አዳዲስ መንፈሳዊ
➢ ፅሁፎች
➢ መዝሙሮች
➢ ኦርቶዶክሳዊ መልእክቶች
➢ መንፈሳዊ ነገሮችን
✞ ሁሉንም በአንድ ላይ ለማግኘት ከፈለጉ ይቀላቀሉ✞
➢ ለአስተያየት➢ @YEmeAmlak_DnglMaryam_Ljoch_Bot
➢ @Azaheill ይጎበኙ
Telegram: https://t.me/Learn_Orthodox03
➢ለሁሉም እንዲደርስ SHARE ያርጉ እናመሰግናለን!

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL (Amharic)

ማንቂያ ደወል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያችንን በመጠቀም የተሻለ የአገር እና የቀያን ሕዝብ ድንገተኛ ነው። በዚህ ምህረት ኦርቶዶክስ መልዕክትን እና መዝሙሮችን በጽኑ በእውነተኛ እና በትንሳኤ ደምቆና ሰብል ከማየት የተነሳውን እና በራሱ ላይ ራሱ የሚታዩትን መንፈሳዊ ነገሮችን ከገለጹ በኋላ መለየትና እንዲጎበኙ በማስተዋወቅ ከፈለን። ይህ ምህረት ለሁሉም እንዴት ተከፋና ስለአስተያየት እና ለሌላ ግዜ የሚንቀሳቀሱ መረጃዎችን እንዲጠቀሙ አስፈላጊዎችን እንወድቃለን። እርስዎ ከአባይ የአገር ቡናላዊና ከቀያን ህዝብ ጋር በተከፈተው ጽሁፍዎን ገልጹ።

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL

11 Feb, 09:49


በስመ አብ፤ ወወልድ፤ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ
በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ ጉዳይ ከመንግሥት ጋር
እየተደረገ ስለሆነው ውይይት እና የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
በሀገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊደረግ ስለታሰበው ሰላማዊ
ሰልፍ አስመክቶ የተሰጠ መግለጫ

ሮሜ ፭፤፫-፬ “ መከራ ትእግስትን እንዳያደርግ፤ ትእግስትም
ፈተናን፤ ፈተናም ተስፋን እንዳያደርግ እያወቅን በመከራችን
ደግሞ እንመካለን”

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!
በመንፈስ ቅዱስ የሚመራው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በቅርቡ ከቤተ ክርስቲያናችን
ሃይማኖታዊ፤ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ሥርዓት ፍጹም ሕገ
ወጥ በሆነ መንገድ በመደራጀት የቤተ ክርስቲያንን መብትና
ጥቅም የጎዳ ተግባር መፈጸሙ ይታወሳል፡፡ የተከበረውን
የአበው ሐዋርያዊ ሢመተ ኤጲስ ቆጶስነት ሥርዓት
በመፈጸማቸው ምክንያት በተፈጠረው የቤተ ክርስቲያንን
ሉዓላዊ ክብርና ልዕልና የማቃለል፣ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ
ውለታ የዘነጋ፣ ሕልውናዋን እና አንድነቷን ለመናድ የተደረገ
ከፍተኛ ጥቃት በመፈጸሙና መንግሥትም የቤተ
ክርስቲያናችንን ሕግና ሥርዓት፣ እንዲሁም ተቋማዊ ሕልውና
እንዳያስከብር እና እንዳያከብር በተደጋጋሚ ሲጠይቅ ቆይቷል፡፡
ከዚህም ውስጥ ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት ፪ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
ባወጣው መግለጫ መንግሥት በዚሁ አካሄድ ሕግ እየጣሰ እና
የቤተ ክርስቲያኒቱን ክብር እና ልእልና እያዋረደ የሚቀጥል
ከሆነ ቤተ ክርስቲያን መንግሥት የጣሰውን ሕግ መሠረት

በማድረግ መብቷን ለማስከበር እስከ አሁን ድረስ ፍጹም
ሰላማዊ የሆነውን እንቅስቃሴዋን አድማሱን በማስፋት በየካቲት
፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለማድረግ ያቀደችውንና ያሳወቀችውን ሀገር
አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ያለማንም ከልካይነት
በራሷ አደባባይ የምታከናውን መሆኑን ስታሳውቅ ቆይታለች፡፡
በዚሁ መሠረት መንግሥት ቅዱስ ሲኖዶስ በመግለጫው
የሰጠውን ቀነ ገደብ ከግምት ውስጥ በማስገባትና ጥሪውን
በመቀበል በየካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም ለአስቸኳይ ውይይት
ዝግጁ መሆኑን በተመረጡ የሀገር ሽማግልዎች አማካኝነት
መልእክቱ ሲደርሰን ካለው ወቅታዊ የሰላም እና ጸጥታ ሁኔታ
አንጻር ጥሪውን በመቀበላችን በብፁዕ ወቅዱስፓትርያርክ
የተመራ አሥራ ሁለት ብፁዓን ሉቃነ ጳጳሳት ፣ የኢፌዴሪ
ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣
ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የሀገር
ሽማግልዎች በተገኙበት ሰፊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱም የተነሱት ነጥቦች በዋንኛነት ቤተ ክርስቲያን
ሃይማኖታዊ፤ ቀኖናዊ እና አስተዳደራዊ ሕግን መሠረት ባደረገ
መልኩ ጠብቃ የምትሠራ እና ከዚህ ውጭ ምንም አይነት
ድርድር የልለው መሆኑን ገልጻለች፡፡ በዚህም መነሻ መንግሥት
የቤተ ክርስቲያንን አቋም በመቀበል ወደፊትም የቤተ
ክርስቲያንን አንድነት እና ሉዓላዊነትን በጠበቀ መንገድ
እንደሚሠራ አረጋግጧል፡፡
በዚህ የፈተና ጊዜ ውስጥ የቅዱስ ሲኖዶስን መመሪያ በመቀበል
ራስን የቤተ ክርስቲያን ሕልውና መስዋእት አድርጎ በማቅረብ፤
በክርስቶስ ደም የከበረችውን ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ እና
የማስጠበቅ ከጸጉር መላጨት እስከ ገመድ መታጠቅ በእንባና
በዋይታ መላው ሕዝበ ክርስቲያን ሀዘናችሁን የገለጻችሁበት

መንገድ የቤተ ክርስቲያን ሕልውና ማስጠበቅ መሠረት ሆኗል፡፡
በዚህም ሂደት ሕይወታቸውን በሰማእትነት፤ አካላችሁን ለአካል
ጉዳት፤ ኑሯችሁን ለፈተና ፤ ለስደት፤ ለእንግልት እንዲሁም
ለእስራት አሳልፋችሁ የሰጣችሁ ልጆቻችን ቅዱስ ሲኖዶስ
ሁልጊዜም ውለታችሁን ሲያስታውስ የሚኖር ሲሆን የጉዳት
ሰለባ ለሆኑቱም መንግሥት የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለይቶ በሕግ
አግባብ ተጠያቂ እንደሚያደርግ እና አሁን ላይ እስር፤ ወከባ፤
እንግልት እየተፈጸመባቸው ያለት ብፁዓን ሉቃነ ጳጳሳት፤
የሀገረ ስብከት ሠራተኞች፤ አገልጋይ ካህናት እና በተለያዩ
አደረጃጀቶች የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች ችግሩ
በአስቸኳይ እንዲቆምና የታሠሩትም እንዲፈቱ፤
አገልግልታቸውን በሰላምና በነጻነት መስጠት እንዲችሉ
ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
በትናትናው እለት ከመንግሥት ጋር ባደረግነው ውይይት
መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም ሙሉ በሙሉ የተቀበለ
ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት
ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ እሁድ የካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም
እንዲካሔድ የተወሰነው ሀገር ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ የአደባባይ
ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ቅዱስ ሲኖዶስ
ወስኗል፡፡
በዚሁ እለትም ሕዝበ ክርስቲያኑ ሁለም በየአጥቢያችሁ
በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ዓውደ ምሕረት ላይ ባለመቅረት
የተለመደውን የእለተ ሰንበት የሥርዓተ ቅዳሴ፤ የጸሎት፣
የምሕላ እና የትምህርተ ወንጌል ከወትሮው በተለየ የመንፈሳዊ
ሥርዓት በማከናወን እንድታሳልፉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
የተከበራችሁ ውድ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን፤

ቅዱስ ሲኖዶስ በየካቲት ፭ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም የጠራውን ሀገር
አቀፍና ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰኑ ቀናት
እንዲተላለፍ ያደረገው የአቋም ለውጥ አድርጎ ሳይሆን
አስቀድማ ቤተ ክርስቲያናችን በሮቿን ለሰላም ክፍት በማድረግ
ባስተላለፈችው ጥሪ እና በአስቀመጠችው ቀነ ገደብ መሠረት
በመንግሥት በኩል ወዲያውኑ ችግሩን ለመፍታት ፍላጎት
በማሳየቱ ምክንያት ብቻ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡
ነገር ግን መንግሥት የገባውን ቃል እና የወሰነውን ውሳኔ
የማይፈጽም ከሆነ መንፈሳዊ ተጋድሏችን የሚቀጥል ይሆናል፡፡
ይህ ሂደት በባህሪው ረዥም ተጋድል እና ጽናት የሚጠይቅ
በመሆኑ እስከ አሁንም በፍጹም አንድነት እና መደማመጥ
የቅዱስ ሲኖዶሱን ድምጽ እየሰማችሁ በአንድነት እና በሕብረት
እንደቆማችሁት ሁሉ ወደፊትም የቅዱስ ሲኖዶስን ድምጽ
በትጋት እንድትጠብቁ እያሳሰብን በሕግ የተያዙት ጉዳዮችም
የሕግ ሂደታቸውን ተከትለው የሚቀጥሉ መሆኑን እና እኛም
በልዩ ሁኔታ የምናውቃቸው መሆኑን እንገልጻለን፡፡
መንግሥትም የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ ተቀብሎ የውይይት
መድረክ በማዘጋጀት የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በማክበር
በውሳኔው መሠረት የሚፈጸም መሆኑን ስላረጋገጠልን ቤተ
ክርስቲያን ታመሰግናለች፡፡
በተጨማሪም በዚህ የፈተና ወቅት በየደረጃው የምትገኙ በሀገር
ውስጥ እና በመላው ዓለም የምትገኙ የቤተ ክርስቲያናችን
የሥራ ኃላፊዎች፤ ሉቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፤ መነኮሳት፤
አገልጋይ ካህናት፤ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች፤ ልዩ ልዩ
የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ማህበራት እና መላው
ምእመናንና ምዕመናት እንዲሁም ከቤተ ክርስቲያኗ ጎን
የቆማችሁ እና አጋርነታችሁን የገለጻችሁ የሃይማኖት

ተቋማት፤ የሕግ ባለሙያዎች፤ ግለሰቦች፤ የማህበረሰብ
አንቂዎች፤ የጥበብ ሰዎች፤ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እና
በዚህ ሂደት ውስጥ ድጋፍ ስትሰጡ የነበራችሁ የተለያዩ አካላት
ቤተ ክርስቲያን እያመሠገነች ወደፊትም ልዩ ዕውቅና የምትሰጥ
መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
❤‍🩹ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች❤‍🩹
                •➢ ሼር // SHARE

 •✥•@Learn_Orthodox03  •✥•
  •✥•@Learn_Orthodox03  •✥•
•✥•@Learn_Orthodox03  •✥•        
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌

         †            †            †

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL

11 Feb, 09:44


የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ ተጠናቋል
ጠቅለል ያለ መልእክቱ እሁድ ቀን ሊካሄድ ታስቦ የነበረውን ሰለማዊ ሰልፍ ላልተውሰነ ግዜ ተራዝሞል የሚል ነው ።።

❤‍🩹ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች❤‍🩹
                •➢ ሼር // SHARE

 •✥•@Learn_Orthodox03  •✥•
  •✥•@Learn_Orthodox03  •✥•
•✥•@Learn_Orthodox03  •✥•        
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌

         †            †            †

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL

11 Feb, 09:41


ልጄ ሆይ ማናቸውንም ነገር በምትፈፅምበት ጊዜ ሥራህን በፀሎት ጀምር። የምትሰራቸውን ሥራዎች ሁሉ በትምህርተ መስቀል ባርካቸው።

በምትበላም፣ በምትጠጣም ጊዜ፣ በምትተኛም፣ በምትነቃም ጊዜ፣ በቤት ውስጥም ሳለህ ይሁን በጎዳና፣ ማማተብን አትዘንጋ። የጌታህን ስቅለት አስታውሶ ከክፋት የሚጠብቅህ ይህን የመሰለ ጠባቂ ከቶ አታገኝም።

እርሱ ለምታደርጋቸው ድርጊቶችህ ሁሉ እንደ ግንብ ነው (ማስተዋልን ይሰጥኻል)። ማማተብን በስርዓት ይፈፅሙት ዘንድ የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት ሁሌም በፊታቸው ይስሉ ዘንድ ለልጆችህ በጥንቃቄ አስተምራቸው።

#ሊቁ_ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ

❤‍🩹ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች❤‍🩹
                •➢ ሼር // SHARE

 •✥•@Learn_Orthodox03  •✥•
  •✥•@Learn_Orthodox03  •✥•
•✥•@Learn_Orthodox03  •✥•        
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌

         †            †            †

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL

11 Feb, 09:38


የቤተክርስቲያንን አቋም እና ውሳኔ ለመዘገብ የተፈቀደላቸው እና የተገኙ ሚድያዎች
ተዋሕዶ ሚዲያ
ማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን
ንቁ ሚዲያ
ኢቲ አርት ሚዲያ
አሻም ሚዲያ
ሮሃ ሚዲያ
ኢሳት
ባላገሩ
ናሁ ቴሌቪዥን
አሐዱ ቴሌቪዥን
ዓባይ ሚዲያ
ማንቂያ ደውል ሚዲያ.......ወዘተ

ሌሎችሁ Fana ,EBC, ebs, walta ታግደዋል

ቸር ያሰማን
🕊️🕊️🕊️
❤‍🩹ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች❤‍🩹
                •➢ ሼር // SHARE

 •✥•@Learn_Orthodox03  •✥•
  •✥•@Learn_Orthodox03  •✥•
•✥•@Learn_Orthodox03  •✥•        
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌

         †            †            †

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL

11 Feb, 06:46


አባቶቻችን የሚሉንን በትዕግሥት እንጠብቅ
(ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ)

መሥዋዕተ አበውን ዕጣነ ዘካርያስን የተቀበለ አምላክ በእነዚህ ሦስት ቀናት በፍጹም ኦርቶዶክሳዊ ጨዋነት እና ትሕትና ሲከናወን የነበረውን ጸሎታችንና ምሕላችንን ይቀበልልን:: መልስን ይሠጠን ዘንድ ያነባነው ወደ ሰማይ አምላክ ነውና እርሱ የቸርነቱን ሥራ ይሥራልን::

ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመታዘዝ ማቅ እንደለበስንና እንደጸለይን ከዚህም በኋላ ለከሳሾች አንዳች ዕድል በማይሠጥ በፍጹም ጨዋነትና ትዕግሥት ቅዱስ ሲኖዶስ የሚያዝዘንን ብቻ መፈጸም ክርስቲያናዊ ግዴታችን ነው::

አባቶቻችን የሚሉንን በትዕግሥት እንጠብቅ::

"ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ትእዛዝ ጠብቅ" ምሳ. 6:20
❤‍🩹ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች❤‍🩹
                •➢ ሼር // SHARE

 •✥•@Learn_Orthodox03  •✥•
  •✥•@Learn_Orthodox03  •✥•
•✥•@Learn_Orthodox03  •✥•        
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌

         †            †            †

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL

11 Feb, 06:45


የዶ/ር ወዳጄነህ መልዕክት

#Ethiopia | እኔማ የኢትዬጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንን የማውቃት ይመስለኝ ነበር። ባለፉት ሦስት ቀናት እንደተረዳሁት ግን ስላንቺ የነገሩኝ ሰዎችና መጻህፍት ሁሉ ካለሽ ክብር፣ ሞገስና ዝና ከፊሉን እንኳን እንዳልነገሩኝ ነው።

ተዋህዶ ሆይ!

ንፁህ እምባ፣ ጥልቅ ትህትና፣ ብርቱ ትዕግስት፣ ታላቅ ጥበብ፣ ብዙ እውቀት፣ ሰፊ ማስተዋል፣ የሚያስፈራ ግርማ አየሁብሽና ተገረምኩኝ፣ ልቤ ተደነቀ፣ እጄን በአፌ ላይ ጫንኩኝ! የጸሎትና የምልጃሽ እጣን የልዑል እግዚአብሔርን ቤተመቅደስ ሲያጥነው፣ ዙፋኑን ሲያውደው ማየት እንኳን እኔን ደካማውን ሰው ይቅርና ቅዱሳን መላዕክቱን ያስደንቃል።

በነቢዩ በዳንኤል መፅሃፍ እንደሚነበብ እጅ ያልነካው ድንጋይ ከሰማይ ወርዶ ሳይፈርስ ፣ ሳይከፈል፣ ሳይቆረስ ታላቅ ተራራ ሆኖ ጸንቶ እንደኖረ አንቺም በኢትዮጵያ ምድር ላይ ታላቅ ተራራ ሆነሽ ለአፍሪካ ትምክህት፣ ለመላው አለምም ክብር ሆነሽ ትኖሪያለሽ።

ከእግዚአብሔር የተማሩት፣ ትሁታንና ብሩካን የሆኑት፣ ማቅ የለበሱልሽ የተወደዱ ልጆችሽ እንዴት የታደሉ ናቸው!

ከሩቅ እያየሽ የሚወድሽና የሚያከብርሽ

ዶ/ር ወዳጄነህ መሐረነ
❤‍🩹ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች❤‍🩹
                •➢ ሼር // SHARE

 •✥•@Learn_Orthodox03  •✥•
  •✥•@Learn_Orthodox03  •✥•
•✥•@Learn_Orthodox03  •✥•        
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌

         †            †            †

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL

11 Feb, 05:46


Channel photo updated

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL

11 Feb, 05:42


Channel name was changed to «የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL»

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL

11 Feb, 05:40


ለኛም ይነጋል......

ጨለማው ቢረዝም፣
ንጋት ቢርቀንም፣
ሁሉም ነገር ከፍቶ
ተስፋ ቢያሳጣንም፣
ብርሀን መፈለግ
መቼም አናቆምም።

ዝናቡ ዶፍ ቢለቅ፣
ንፋሱም ቢተልቅ፣
መንገድ አሾህ ሞልቶት
መራመድ ቢያሳቅቅ፣

በጭራሽ አንቆምም፣
ተሰፋም አንቆርጥም፣
ወደፊት መሄድን፣
መቼም አንተውም፣
ፈጣሪ ስላለን
ማንም አይጥለንም።
            †           


    ስንክሳር የካቲት - ፬ -    
❤‍🩹ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች❤‍🩹
                •➢ ሼር // SHARE

 •✥•@Learn_Orthodox03  •✥•
  •✥•@Learn_Orthodox03  •✥•
•✥•@Learn_Orthodox03  •✥•        
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌

         †            †            †

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL

10 Feb, 19:41


ማረኝና ማራት


ማረኝና ማራት
ይቅር ብለኸኝ ይቅር በላት
በኔ በደል በኔ ክፋት
ተዋሕዶን አታጥፋት
❤‍🩹ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች❤‍🩹
                •➢ ሼር // SHARE

 •✥•@Learn_Orthodox03 •✥•
  •✥•@Learn_Orthodox03 •✥•
•✥•@Learn_Orthodox03 •✥•        
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL

10 Feb, 18:36


"በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት በፍፁም መንፈሳዊ መሪነትና ክብር ሄደናል፤ እግዚአብሔር ሰምቶናል፤ ከጠቅላይ ሚኒስትሩም ለጥያቄዎቻችን መልስ ተሰጥቶናል::" ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ

ዛሬ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የነበረውን ውይይት አስመልክቶ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም ብፁዕነታቸው እንደገለጹት ትናንት በሰጠነው መግለጫ “በአስቀመጥነው ቅድመ ሁኔታ መሠረት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ተጠርተን ጥያቄያችንን አቅርበናል፡፡ ጥያቄያችንም አንድ ነው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ይከበር፤ በሀገሪቱ ያለው ኦርቶዶክሳውያን መብት ይጠበቅ፤ የቤተ ክርስቲያኒቱ ሀብትና ንብረት በሀገሪቱ ሕግ መሠረት ንብረቷ ይጠበቅ፤ እነዚህ ካልሆኑ ወደ ሰላማዊ ሰልፍ እንሄዳለን ማለታችን ይታወሳል፡፡ በዚህም  በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት በፍፁም መንፈሳዊ መሪነትና ክብር ሄደናል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በነበረን ቆይታ በደንብ ተወያይተንበት ለጥያቄዎቻችንም መልስ ተሰጥቶናል ብለዋል ብፁዕነታቸው፡፡  እንዲሁም ዝርዝር መግለጫውን ነገ የምንሰጥ ይሆናል ብለዋል፡፡
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

 •✥•@Learn_Orthodox03 •✥•
  •✥•@Learn_Orthodox03 •✥•
•✥•@Learn_Orthodox03 •✥•        
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL

09 Feb, 13:29


#ሰበር_ዜና

#አለም_ገና በመዝሙር ምርቃት ሰበብ አቶ አካለ ወልድ ነገ ወደ ሚካኤል ቤተክርስትያን ሊገቡ ነው።ከላይ የተያያዘው የስልክ
ልውውጥ ስሙት።

#በግልፅ ኦሮሞ ነን ማንም አያስቆመኝ እያሉ ነው።ልጅቷን በግልፅ እያስፈሯሯት ነው። ይሄን መረጃ ዛሬ ሁሉም ኦርቶዶክስ ሊሰማው ይገባል።ሼር አርጉት
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

 •✥•@Learn_Orthodox03 •✥•
  •✥•@Learn_Orthodox03 •✥•
•✥•@Learn_Orthodox03 •✥•        
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL

09 Feb, 10:57


"በየቤተ ክርስቲያኑ በር ላይ የፈሰሰውን ደም እረግጠው ገብተው እንዴት ብለው የክርስቶስን ደም ቀድተው ያጠጡን ይሆን?"

ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ
ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

 •✥•@Learn_Orthodox03 •✥•
  •✥•@Learn_Orthodox03 •✥•
•✥•@Learn_Orthodox03 •✥•        
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL

09 Feb, 10:56


ወንድሜ አንተ በመከራ ውስጥ ካለህ የዩናስን ዓሣ ነባሪ አስታውስ። ከፍራቻ ትገላገላለህ። መከራው እግዚአብሔር ጸጋውን ሊያበዛልህ ስለፈለገ ያዘጋጀው ዓሣ ነባሪ እንደሆነ የምታውቅበት ጊዜ ይመጣል። የዚህ ዓለም የባሕር ዓሣዎች ብዙ ስለሆኑ ስትዋጥ እንዳይከፋህ መጠንቀቅ ይኖርብሃል። የመጀመሪያው ባህታዊ ጻድቁ አባ ጳውሊ የተናገረውን መዘንጋት የለብህም "ከመከራ መራቅ የሚወድ ከእግዚአብሔር ይርቃል" ብሏል። በእውነት መከራ የጸሎት ትምህርት ቤት ነው። "በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ጮኽሁ እርሱም ሰማኝ። በሲኦልም ሆድ ውስጥ ሆኜ ጮኽሁ። ቃሌንም አደመጠ" ዮናስ 2፥3

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
✥•@Learn_Orthodox03 •✥•
  •✥•@Learn_Orthodox03 •✥•
•✥•@Learn_Orthodox03 •✥•        
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌ ሼር ይደረግ !!

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL

09 Feb, 07:41


📲📲 ለብፁዕነታቸው ደወልኩ…!

"…ከብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ እና ከብፁዕ አቡነ ያሬድ ቀጥሎ በዛሬው ዕለት ወደ ሃገረ ስብከታቸው ልጆቻቸውን ለማጽናናት ይሄዱ የነበሩት አረጋዊው ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል በጅማ ከተማ ሹፌራቸው ተደብድቦ፣ እሳቸውም ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው፣ የይለፍ ወረቀት ተጠይቀው፣ ሌላ ሃገር ነው እንዴ በስህተት የገባሁት ብለው እስኪደነቁ ድረስ አንገላትተው፣ አሳዝነው፣ አስለቅሰው በሄዱበት አውሮፕላን ወደ አዲስ አበባ ተመልሰዋል።

"…የካፋ፣ የቤንች ሸኮ፣ የሸካ እና የምዕራብ ኦሞ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የኢትዮጵያ ሰዋሰው ብርሃን ቅዱሰ ጳወሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ የሆኑ ብጹዕ አቡነ ሕዝቅኤል ከአዲስ አበባ ወደ አህጉረ ስብከት መንበራቸው ወደሆነው ቦንጋ ከተማ ሲመጡ ነው በጅማ አካባቢ በጸጥታ አስከባሪዎች እንዲመለሱ የተደረገው።

"…ኧረ ጉድ እኮነው ልጄ… ወደ ሃገረ ስብከቴ ለመሄድ ትኬት ቆርጬ በአየር ተሳፍሬ ጅማ ደረስኹ። ከጅማም በቀረበልኝ መኪና ተሳፍሬ ወደ ሃገረ ስብከቴ ጉዞ ጀመርኹ። ከጅማ እንደወጣሁ ፖሊሶች ቁሙ አሉንና ቆምን። ወዲያው ሹፌሩን ውረድ አሉት። ወረደ። ይዘው ይቀጠቅጡት ገቡ። እኔንም ውረድ አሉኝ ወረድኹ። የይለፍ መታወቂያ ይዘሃል ወይ አሉኝ። ለምኑ ነው ይለፍ አልዃቸው። አይሆንም መሄድ አትችልም አሉኝ። ለምንድነው ታዲያ ሹፌሩንስ የደበደባችሁት አልዃቸው። እሱን አያገባህም ብለው ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወሰዱን። ኧረ ይቅር ልጄ።

ከዚያስብፁዕ አባታችን…?

"…ፖሊስ ጣቢያ ሲመረምሩን ቆዩና በሉ ሂዱ እለፉ አሉን። እሺ ብለን ጉዞ ጀምረን አሁንም ኬለው ጋር ስንደርስ እነዚያው ፖሊሶች ጠበቁን፣ ተመለሱ አሉን። እሺ ብለን ተመለስን። አውሮፕሏና አልተመለሰችም ነበርና አውሮፕላኑ ሊንቀሳቀስ ሲል መጥተው ይውረዱ ይቅርታ አሉን። ግድየለም ይቅር አልወርድም ብዬ ተመለስኹ እልሃለሁ። አሉኝ ብፁዕነታቸው።

"…አዲሱ የምሥራቅ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥትም ድርጊቱን አውግዞ የተቃወመ ሲሆን፣ የጅማ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ ፖሊስ ጣቢያ ሲንገላቱ የዋሉትን አረጋዊ አባት በማይታወቁ የጽጥታ አካላት የተፈጸመ ነው ብሎ በግልጽ ዋሽቷል።

"…አንድ የሚታየኝ ነገር አሁን ያለው የኦነግኦህዴድ መንግሥት ኦሮሞን ከኢትዮጵያውያን ሁሉ ጋር አናክሶ ምን አይነት ሃገር ሊመሰርት እንዳሰበ ብቻ ነው ግራ የሚገባኝ። ድሬድዋ እምቢ ብሏል። ዲላ እምቢ ብሏል። ከሚሴ እምቢ ብሏል። አሰበተፈሪ እምቢ ብሏል። ሻሸመኔ ደም አፍስሰዋል። ሰው አርደው በልተዋል። ተጠያቂ ኦሮሞ የለም። ይገድላል፣ ይዘርፋል፣ ደም ያፈሳል ዘና ብሎም ይኖራል። በኦሮሚያ ሕግም፣ ሥርዓትም ፈርሷል። የወጠጤ መንጋ መጫወቻ ሆኗል ኦሮሞ።

"…ከዚያ ለዚህ ግፍ OMN KMN OBN ትንተና ሲሰጡ በቋንቋችን መማር ፈልገን ነው የደበደብናቸው፣ የገደልናቸው። ያረድናቸው ይልልኛል። ከብት ሁላ…! የኦሮሞ ሕዝብ ግን እንዲህ የማንም ድፍን ቅል ራስ ወጠጤ መፈንጫ ሆኖ አይቀርም። ሁሉም ነገደ ኢትዮጵያዊ እየታዘበ ነው። ኦሮሞ ገዳይ ተብሎ ስሙም እየቆሸሸ ነው።

"…ያሳዝናል…!

ሼር ይደረግ
👇👇👇👇👇👇
•✥•@Learn_Orthodox03 •✥•
  •✥•@Learn_Orthodox03 •✥•
•✥•@Learn_Orthodox03 •✥•        
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌ ሼር ይደረግ !!

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL

08 Feb, 16:31


#የክርስቲያን_መከራ

ለአንድ ክርስቲያን መከራ ለጥቅሙ የሚሰጠው ነው፡፡ ለአንድ ክርስቲያን መከራን መቀበል ማለት ከሰማያዊ ክብር መሳተፍ ነው፡፡ ይህስ እንደ ምን ነው ያልከኝ እንደ ኾነም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ ፡- ስንፍናንና ክፉ ፈቃድን የሚያርቅ፣ ዓለማዊ ግብር መውደድን፣ ውዳሴ ከንቱ መውደድን የሚያርቅ ነውና የክርስቲያን መከራ ክብርን ያስገኛል፡፡ ነፍስን የሚረዳ፣ በክብር ላይ ክብርን የሚያስገኝ ነውና የክርስቲያን መከራ የሚያሳዝን መከራ አይደለም ብዬ እነግርሃለሁ፡፡

የቅዱሳኑ ክብራቸው እንዲህ ደምቆ ልናየው የቻልነው ከምን የተነሣ እንደ ኾነ እንመልከተው፡፡ ስላገኛቸው መከራ አይደለምን? ፈቃድህ ከኾነ ገና ከመነሻው አንሥተን እንቍጠራቸው፡፡ አዎ! ከአቤልና ከኖኅ ጀምረን እስኪ እንቍጠራቸው፡፡ እነዚህ ቅዱሳን በዚያ ለመቍጠር እንኳን በሚታክቱ ክፉዎች ሰዎች መካከል እየኖሩ ያለ መከራ ክብርን ማግኘት አልተቻላቸውም፤ እንዲህ እንደ ተባለ፡- “ኖኅም በትውልዱ ጻድቅ ፍጹምም ሰው ነበረ፤ እግዚአብሔርንም ደስ አሰኘው” (ዘፍ.6፥9)፡፡ ተመልከት! ለእኛ አብነት የሚኾኑን እጅግ በጣም ብዙ ሰዎች አሉን፡፡ ብዙ አበውን፣ ብዙ ሕፃናትን፣ ብዙ መምህራንን አብነት አድርገን መከራ እንቀበላለን፡፡ በሰብአ ትካት መካከል ኾኖ መከራ ስለ ተቀበለው ስለ ኖኅ ምን እንላለን? በዙሪያው ስለ ነበረው እንግዳና አስደናቂ ዝናብስ ምን እንናገራለን? ወይስ አብርሃም ከአገር አገር ሲሰደድ መኖሩን፣ ሚስቱን እንደ ቀሙት፣ ጦርነትና ረሃብ እንዳገኘው እናገር ዘንድ ይገባኛልን? ወይስ እጅግ አስጨናቂ ነገሮች ስላገኙት፣ ከቦታ ቦታ ስላሳደዱት፣ ድካሙ ከንቱ ይኾንበት ስለ ነበረው፣ በድካሙ ላይ ሌሎች ሰዎች ይጠቀሙበት ስለ ነበረው ስለ ይስሐቅ ልናገርን? ወይስ ስለ ያዕቆብ ልናገርን? ያዕቆብ ያገኘውን መከራ እዘረዝር ዘንድ አይገባኝም፤ እርሱ ራሱ ለፈርዖን የተናገረውን ምስክር አድርጌ ላቅርብ እንጂ፤ እንዲህ ያለውን፡- “የሕይወቴ ዘመኖች ጥቂትም ክፉም ኾኑብኝ፡፡ አባቶች በእንግድነት የተቀመጡበትንም ዘመን አያህሉም” (ዘፍ.47፥9)፡፡ ወይስ ስለ ዮሴፍ ልናገር ይገባኛልን? ወይስ ስለ ሙሴ፣ ወይስ ስለ ኢያሱ፣ ወይስ ስለ ዳዊት፣ ወይስ ስለ ኤልያስ፣ ወይስ ስለ ሳሙኤል፣ ወይስ ስለ ነቢያት ኹሉ ልናገር ይገባኛልን? እነዚህ ኹሉ በመከራ እንደ ከበሩ አታውቅምን? ሰው ሆይ! ከዕረፍትና ከቅምጥል ሕይወት ክብርን ልታገኘ ትሻለህን? እኔ እነግርሃለሁ፤ በፍጹም አታገኘውም፡፡

ወይስ ስለ ሐዋሪያት ልናገርን? እነዚህስ ከኹሉም በላይ መከራ ተቀበሉ፡፡ ጌታችን ክርስቶስም እንዲህ ብሏልና፡- “በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ” (ዮሐ.16፥33)፤ “እናንተ ታለቅሳላችሁ፤ ታዝኑማላችሁ፡፡ ዓለም ግን ደስ ይሏል” (ዮሐ.16፥20)፤ “ወደ ሕይወት የምትወስደው በር እጅግ ጠባብ መንገዷም ቀጭን ናትና የሚገቡባትም ጥቂቶች ናቸው” (ማቴ.7፥14)፡፡ ታዲያ እስኪ ንገረኝ! ጌታችን መንገዷ ጠባብ ናት እያለ አንተ ሰፊውን መንገድ ትፈልጋለህን? ይህስ እንደ ምን ሊኾን ይችላል? በሌላ መንገድ የምትኼድ ከኾነም ወደ ሕይወት አትደርስም፤ እንደ ምርጫህ ምረረ ገሃነም ያገኝሃል እንጂ፡፡

የክርስቲያን መከራ እና ሌሎች #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ እንዳስተማረው በገብረ እግዚአብሔር ኪደ

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL

08 Feb, 08:37


“#ማግባት_ለሚሹ”
የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር

ከምንም በፊት የጋብቻ ዓላማን ማወቅ አለባችሁ፡፡ በሕይወታችን ለምን ጋብቻ እንደሚያስፈልገን መረዳት አለባችሁ፡፡ ከዚህ ውጪ ሌላ ነገርን አትጠይቁ፡፡ እናስ የጋብቻ ዓላማው ምንድነው? ለምንድነው እግዚአብሔር ጋብቻን የሰጠን? ብጹዕ ጳውሎስን እናድምጠው፤ እንዲህ ያለውን፦ "ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑሮው፤ ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራሷ ባል ይኑራት" (1ኛ ቆሮ.7፥2)። "ከድህነት ይወጣ (ትወጣ) ዘንድ" ነው የሚለውን? ወይስ "ሀብት ለማግኘት ሲባል" ነው የሚለውን? አይደለም፡፡ ታዲያ ምንድነው የሚለው? ከዝሙት እንጠበቅ ዘንድ፤ ራሳችንን መቆጣጠር እንችል ዘንድ፤ ንጽህናን ገንዘብ እናደርግ ዘንድ፤ በትዳር አጋራችን ደስ ተሰኝተን እግዚአብሔርን እናመሰግን ዘንድ፡፡ አያችሁ ይኼ ነው የጋብቻ ስጦታው ይኼ ነው የጋብቻ ፍሬው፤ ይኼ ነው የጋብቻ ጥቅሙ፡፡

ስለዚህ #ልጆቼ! እማልዳችኋለሁ ትልቁን ጥቅም ዘንግታችሁት ዓይናችሁን በትንሹ ላይ አታሳርፉ፡፡ የትዳር አጋርን ስትመርጡ የሀብት ጉዳይ የእናንተ ትልቅ አጀንዳ ሊኾን አይገባም፡፡ ስለ ሀብት ብሎ የትዳር አጋርን መምረጥ ድንቁርና ነው፤ ሀብት ነገ ሊጠፋ ይችላልና፡፡ ስለዚህ ለትዳር የምትመርጡት ሰው ከምንም በላይ መንፈሳዊ ሀብቱን ተመልከቱ፡፡ በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም ይበልጥ የሚጠቅማችሁ ይኼ ነውና፡፡

#አባቶች_ሆይ! አብርሃምን ምሰሉት፡፡ አብርሃም ለልጁ ለይስሐቅ ሚስትን ሲፈልግለት፦ ሀብትን አላየም፤ የንጉሣውያን ቤተሰብን አልተመለከተም፤ አፍአዊ ውበትን መመዘኛ አላደረገም፤ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ መስፈርትን አልደረደረም፡፡ የነፍስ ንጽህናን እንጂ፡፡

#እናቶች_ሆይ! ሴት ልጆቻችሁን እንደ ርብቃ አሳድግዋቸው፡፡

እናንተ ማግባትን የምትሹ #ወጣቶች_ሆይ! ይስሐቅን ምሰሉት፦ ዘፈንን፣ ዳንኪራን፣ ሳቅና ስላቅን፣ የከበሮንና የዋሽንት ጫጫታን፣ ሌላውንም የዲያብሎስ ትርኢት በሰርጋችሁ ቀን አታስቡ፡፡ ከዚህ ይልቅ በምታደርጉት ኹሉም ላይ እግዚአብሔር እንዲቀድማችሁ ለምኑት፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ትዳራችሁ ፍቺ፣ ዝሙት፣ ቅናት፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ የሌለበት ኾኖ ይፀናላችኋል፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ፥ ሌላው በረከትም ተትረፍርፎ ይመጣላችኋል፡፡ የአውሎ ነፋስ ዓይነት በዙሪያችሁ ቢነፍስም፥ አትነዋወፁም፡፡

#እናንተ_ልጃገረዶች_ሆይ! ርብቃን ምሰሏት፡፡ የትዳር አጋራችሁን ፍጹም ለማፍቀር የተዘጋጃችሁ ኹኑ፡፡ ይህን ያደረጋችሁ እንደኾነ ቤታችሁ ፍጹም ሰላማዊ ባሎቻችሁ የምትልዋቸውን የሚያደርጉና በፍቅራችሁ የሚንበረከኩ ይኾናሉ፡፡ ትዳር እንዲህ ኾኖ ሲጀመር፥ እግዚአብሔርንና ወላጆቹን ደስ የሚያሰኝ ልጅ ይገኝበታል፡፡

የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ፥ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡
•✥•@Learn_Orthodox03 •✥•
  •✥•@Learn_Orthodox03 •✥•
•✥•@Learn_Orthodox03 •✥•        
  ✧━━━━━━━━━━━━━━━━✧‌‌

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL

08 Feb, 03:53


"ፈተና ሲገጥመን ውስጣችን ሊረበሽ ወይም በቀቢጸ ተስፋ ሊያዝ አይገባውም፡፡ ወርቅን የሚያነጥር ሰው በእሳት ውስጥ የጨመራትን የወርቅ ቅንጣት እዚያ ውስጥ ምን ያህል ጊዜ መቆየት እንዳለባት ያውቃል፤ መቼ ከእሳቱ ሊያወጣት እንደሚገባውም ያውቃል፡፡ እንዲሁ እስከ መጨረሻው በእሳቱ ውስጥ ተጥላ እንድትቀርና በዚያ እንድትቃጠል አይፈቅድም፡፡

እግዚአብሔር ደግሞ ይህን ከወርቅ አንጣሪው በላይ ያውቃል፡፡ መቼ ከርኩሰታችን እንደምንነጻ ያውቃል፡፡ በመኾኑም ራሳችንን በመጣልና ተስፋ በመቁረጥ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመርን እንዳንኼድ ሽቶ መቼ ከዚያ ፈተና እንደሚያወጣን ያውቃል፡፡

ስለዚህ ድንገት ያላሰብነው ነገር ቢገጥመን በፍጹም የምናማርር፣ ወይም ተስፋ የምንቆርጥ ልንኾን አይገባንም፡፡ ከዚህ ይልቅ የእነዚህ ነገሮች ምንነትን የሚያውቅ እግዚአብሔርን መጠበቅ፣ እርሱ እስከ ፈቀደው ጊዜ ድረስም ልቡናችንን በእሳት እንዲፈተን ማድረግ ይገባናል። ምክንያቱም ይህ ነገር በእኛ ላይ እንዲኾን (እንዲመጣ) የፈቀደው ለእኛ ጥቅምና በዚያ ውስጥ ኾነን በምናሳየው ጥረት ይበልጥ ሊያከብረን ስለሚወድ ነው፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ወደ ኦሎምፒያስ መጽሐፍ በ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

የማንቂያ ደወል - YEMANKYA DEWELL

07 Feb, 20:53


ዛሬ ምሽት 10ሺ መሙላት ይኖርብናል ውድ የተዋህዶ ልጆች

~~~~ኢትዮጵያውያን አርቲስቶች ጥቁር ለበሱ ~~

ይህ የዛሬ ምሽት ስራችን ነው ትስማማላችሁ ?

እባካችሁ ኦርቶዶክሳውያን  60 million ብዛት  ያለን  ሰዎች  እንዴት አንድ  ኦርቶዶክሳዊ ግሩፕ ከፍተን እንደነሱ ማሳደግ ያቅተናል ?  አንድ  ሚሊየን subscriber  ማስገባት  እንዴት  ይሳነናል  ::  ebs ,ebc,fana   subscribe አድርገን  እንዴት  ድምፀ ተዋህዶ  1 million  መግባት  ያቅተናል ::  ስለዚህ የተወደዳችሁ የእግዚአብሐር ልጆች  በድንግል ማርያም  ስም  ይዣችኋለሁ ኦርቶዶክሳውያን  challengun  እንቀላቀል   ድምጸ ተዋህዶን subscribe በማድረግ    እና  ለ100  ሰው  share  በማድረግ እና    ebs ebc fana   subscribe  ያደረጋችሁ  unsubscribe   በማድረግ  ኦርቶዶክሳዊ  ሀላፊነታችንና ግዴታችን እንድንወጣ ጥሪ ቀርቧል ።።

@Bete_Christian
@Bete_Christian  አሁን ግቡና #Added አድርጉ

❤‍🩹የተዋህዶ ልጆች እንበዛለን ሺዎች እንሆናለን #Added ካደረጋችሁ❤‍🩹