Latest Posts from የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ (@lafto_qirat) on Telegram

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ Telegram Posts

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ
ይህ ቻናል በላፍቶ ቢላል መስጂድ የሚሰጡ ደርሶችን እና የተለያዩ ሙስሊሙን የሚጠቅም ሙሀደራዎችና አጫጭር መልዕክቶች የሚለቀቅበት ሲሆን ሊንኩን በመጠቀም ለራሳችንም ሌሎችም እንዲጠቀሙ እናድርግ

https://t.me/lafto_qirat
1,739 Subscribers
195 Photos
65 Videos
Last Updated 09.03.2025 05:06

The latest content shared by የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ on Telegram

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

27 Feb, 09:50

1,347

السلام عليكم ورحمة اللہ وبركاته

እንኳን ደስ አላችሁ

ዛዱል መዓድ ኢስላሚክ ሴንተር በ ሸይኽ አሕመድ ሸይኽ ኣደም የሚሰጡ ትምህርቶችና መረጃዎችን በሶሻል ሚዲያ እንዲሁም በቅርቡ ይፋ ባደረገው ዌብሳይት ሲያስተላልፍ መቆየቱ ይታወቃል ።
አሁን ደግሞ ሁሉንም በዛዱል መዓድ የሚሰጡ ትምህርቶችን፣ የፈትዋ መጠየቂያ፣ እንዲሁም ወቅታዊ መልዕክትና መረጃዎችን
ያካተተ ለአጠቃቀም ቀላል የሆነ ልዩ አፕሊኬሽን ለዛዱል መዓድ ቤተሰቦች ይፋ ማድረጉን ስንገልፅልዎ በታላቅ ደስታ ነው።

አፕሊኬሽኑን ለማውረድ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ።

https://play.google.com/store/apps/details?id=com.alif.zadulmead_islamic_center_app
የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

26 Feb, 18:39

596

ረመዷን ላይ ይበልጥ የሚወደድ ዒባዳህ፥

1/ትክክለኛና የተሟላ ጾም መጾም፣

2/ቁርኣን በብዛት ማንበብ (ካልተቻለ ማድመጥ)፣

3/አምስት ወቅት ሰላትን በወቅቱና በጀማዓህ መስገድ፣

4/ቀብሊያና በዕዲያህ ሱንናህ ሰላቶች ላይ መበርታት፣

5/ተራዊሕና የምሽት ሰላቶችን በነቢዩ እና በሰሓባዎች ሱንናህ መሰረት መስገድ፣

6/ዚክርና ዱዓእ (በተለይም ኢስቲግፋር፣ አላህን ጀነትን መጠየቅና ከጀሀንም እንዲጠብቀን መማጸን) ማብዛት።

7/እንደ አቅም ሁኔታ የተቸገረን ሰው መርዳትና ጾመኛን ማስፈጠር፣

8/ሙሉ ሰውነትን አላህ ከሚጠላው ነገር በሙሉ ማራቅና ነፍስን አደብ እንድትገዛ መታገል፣

9/ከአላህም ይሁን ከሰዎች ጋር ስነምግባርን ማሳመር


ዛዱል-መዓድ
የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

26 Feb, 04:44

411

"መጥፎ የምትለዉ ሰዉ ተዉበት አድርጎ የተሻለ ማንነት ኖሮት ... አንተ መልካም ነኝ ብለህ ምታስበዉ መንገድ ልትስት ትችላለህና  ምንም በኢባዳ ትጉ ብትሆንም የአላህ ባርያዎች ላይ አትንጠራራ ... አትኮፈስ ..በነፍስህ አትቸንገል ተናናሽ ሁነህ አላህ ጽናቱን እንዲሰጥህ የምንጊዜም ዱዐህ ይሁን ።"
اللهم يا مقلب القلوب ثبت قلبي على دينك
የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

25 Feb, 19:05

428

☑️ መጣላችሁ የተባረከዉ ወር!!
  
እንዴት ነው ዝግጅት  ለቂርዐት ለሰላት
ከወንጀል ርቆ   ኢባዳን ለማብዛት
ከሰፊው ራህመት  ሸምቶ ለመውጣት።
==
منقول
የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

25 Feb, 14:23

505

ልዩ የትምህርትና ስልጠና መድረክ

# የተከበራችሁ የአላህ ባሮች ዛዱል-መዓድ ኢስላማዊ ማዕከል በአላህ ፈቃድ የረመዳን ምሽት ሰላትን ምክንያት በማድረግ በፉሪ በድር መስጅድ ውስጥ ልዩ የግማሽ ቀን የሰላት አሰጋገድ ስልጠና (ኮርስ) በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም ለመስጠት ተዘጋጅቷል።

# የስልጠናው/ የትምህርቱ ዋና ዓላማ

ለሁሉም ሰጋጆች ትክክለኛውን (የነቢዩ ሙሐመድን*) አሰጋገድ በቃልና በምስል መግለጽና ማብራራት ሲሆን፤
መድረኩ ላይ ከሰፊው ህዝብ በተጨማሪ ጀማሪና በቂ የሸሪዓህ እውቀት የሌላቸው በአዲስ አበባና በዙሪያዋ እንዲሁም በቅርብ ርቀት ላይ የሚገኙ የመስጂድ ኢማሞች፣ ሙአዚኖች እና የተራዊሕና የተሃጁድ አሰጋጆች፣ እንዲሁም የተራዊሕ አሰጋጅን የመከታተልና የማረም ኀላፊነት ያለባቸው አካላት ቢሳተፉ ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይታሰባል።

# ባጠቃላይ፥ ማንኛውም ትክክለኛውን (የነቢዩን*) የሰላት አሰጋገድ ከተያያዥ ህግጋት ጋር ማወቅ የሚፈልግ ሰው በሙሉ ፕሮግራሙ ላይ እንዲሳተፉ በክብር እንጋብዛለን።

በእለቱ እንደ መነሻ የኢማም ኢብኑ ባዝን ሲፈቱ ሰላት አን-ነቢይ
صفة صلاة النبي صلى اللہ عليہ وسلم
የሚለውን መጽሐፍ እንጠቀማለን፤ ማንበብ ለሚችሉ የኪታቡ ፒዲኤፍ ከዚህ ማስታወቂያ ጋር ተያይዟ ተለቋልና ፕሪንት አድርጎ በመያዝ መከታተል ይቻላል።
የኪታቡ pdf-
https://tinyurl.com/bdfkp7mh

#የስልጠናው ቀንና ሰዓት: የረመዳን የመጀመሪያው እሁድ ወይም የፊታችን እሁድ የካቲት 23/ 2017ዓ.ል
ከጠዋቱ   3:00  -  ዙህር   ሰላት

አደራሻ: ሸገር ሲቲ ፉሪ በድር መስጅድ

ሎኬሽን: ሸገር ሲቲ ፉሪ በድር መስጅድ። Masjid Al-Badr በድር መስጅድ مسجد
https://maps.app.goo.gl/7aWjj1vYneqbUL3W8

ለበለጠ መረጃ፡ ስልክ:-
096 502 9940
0929244778

ትምህርቱን በአካል ተገኝተው መከታተል የማይችሉ በእለቱ የዛዱል መዓድ ዋና የቴሌግራም ቻናል ላይ በቀጥታ ይተላለፋል
https://t.me/ahmedadem
የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

24 Feb, 17:59

1,070

"መሀይም ማለት ማንበብና መፃፍ የማይችል ሳይሆን...የቂብላን አቅጣጫ እያወቀ ሶላት የማይሰግድ ሰው ነው።እወቅ ወደ ሶላት ያልወሰደችህ እግርህ ወደ ጀነት ልትወስድህ አትችልም።"

#ሰላት
የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

24 Feb, 13:10

903

ከነሱ እንዳትሆን❗️

"በምድር ላይ የሸይጧን ምትኮች የሚባሉት እነዚያ ሰዎችን እውቀትን ከመፈለግ የሚያሳንፉት ናቸው።እነዚህ አካላት በሰዎች የሚያደርሱት ጉዳት የጂን ሸይጣናት በሰዎች ላይ ከሚያደርሱት ጉዳት የከፋ ነው ምክንያቱም በዚህ ተግባራቸው በሰዎች ልብ እና በአላህ መካከል ግርዶ ስለሚሆኑ።"

(ኢብኑል ቀይም ሚፍታሁ ዳሪ አሰአዳህ 1:160)
የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

24 Feb, 07:13

1,117

«አንድ ሰው የምታውቀውን እውቀት ይዞ ወደ አንተ ቢመጣ፣ “አውቀዋለሁ” ማለት ጥሩ ባህሪ አይደለም። ይልቁንም ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሰማህ አድርገህ አዳምጠው።»

(ሸይኽ ዐብዱ አር– ረዛቅ አልበድር)
የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

23 Feb, 18:37

1,279

ረመዳንን እንዲያደርስህ አላህን ስትለምነው ወሩን እንዲባርክልህ ለምነው
ወቅቱን በአግባቡ የመጠቀም ጉዳይ እንጂ ረመዳን ላይ መድረስህ ቁም ነገር አይደለም ።”

📚 አሽ ሸይኽ አብዱል ራህማን አል-ስዕዲይ
የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

21 Feb, 18:11

921

ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በላፍቶ ቢላል መስጂድ❗️

⚡️ሊያመልጦ የማይገባ ወሳኝ ፕሮግራም

🎙 በሸይኽ ጁነይድ ሁሴን

🗓 ነገ ቅዳሜ  ከመግሪብ-ዒሻ

⚠️ሴቶችንም ወንዶችንም ይመለከታል❗️❗️❗️

🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

ሼር በማድረግ ላልደረሰው ያድርሱ!