Latest Posts from የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ (@lafto_qirat) on Telegram

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ Telegram Posts

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ
ይህ ቻናል በላፍቶ ቢላል መስጂድ የሚሰጡ ደርሶችን እና የተለያዩ ሙስሊሙን የሚጠቅም ሙሀደራዎችና አጫጭር መልዕክቶች የሚለቀቅበት ሲሆን ሊንኩን በመጠቀም ለራሳችንም ሌሎችም እንዲጠቀሙ እናድርግ

https://t.me/lafto_qirat
1,739 Subscribers
195 Photos
65 Videos
Last Updated 09.03.2025 05:06

The latest content shared by የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ on Telegram

የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

09 Mar, 02:04


የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ pinned «ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በላፍቶ ቢላል መስጂድ❗️ ⚡️ሊያመልጦ የማይገባ ወሳኝ ፕሮግራም 🎙 በኡስታዝ ተውፊቅ ራህመቶ 🗓 እሁድ የካቲት 30 ዙሁር እንደተሰገደ ⚠️ሴቶችንም ወንዶችንም ይመለከታል❗️❗️❗️ 🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ! ሼር በማድረግ ላልደረሰው ያድርሱ!»
የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

07 Mar, 07:05

558

ልዩ የዳዕዋ ፕሮግራም በላፍቶ ቢላል መስጂድ❗️

⚡️ሊያመልጦ የማይገባ ወሳኝ ፕሮግራም

🎙 በኡስታዝ ተውፊቅ ራህመቶ

🗓 እሁድ የካቲት 30 ዙሁር እንደተሰገደ

⚠️ሴቶችንም ወንዶችንም ይመለከታል❗️❗️❗️

🔖ኑ! ተባብረን የተሻለ ማንነት በመፍጠር የሁለት ሀገር ስኬትን እንጎናፀፍ!

ሼር በማድረግ ላልደረሰው ያድርሱ!
የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

05 Mar, 12:38

363

⚫️السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
በሸገር ሲቲ ገላን ክ/ከተማ አንዶዴ ወረዳ ላይ 2013 ዓ.ል ذا النورين (ዘኑረይን)  ለተሰኘ መስጂድ መስሪያ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ከሆነ ግለሰብ ላይ 300 ካሬ የተገዛ ሲሆን ከርሱም ላይ 100 ካሬ ማለትም 10*10 የሆነ አነስ ያለ መስጂድ በቆርቆሮ ተሰርቶ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። ከግለሰቡ ቅንነት የተነሳ ተጨማሪ መሬት ለመስጠት ፈቃደኛ በመሆን ተጨማሪ 1400 ካሬ ልስጣችሁ ክፍያውንም(2 ሚሊየን ገደማ) በረጅም ጊዜ ክፍያ ትከፍላላችሁ በማለት ከሌላ እምነት ተከታዮች የመጣውን መሬቱን የመውሰድ ጉጉት ውድቅ በማድረግ በተለይ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች በፈለገው ዋጋ እንደሚስማሙ እና መሬቱን እንዲሰጣቸው ቢጠይቁትም ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል።ነገር ግን የአካባቢው ሙስሊም ቁጥር አናሳ መሆንና በአቅም ማነስ ምክንያት አይደለም የተሻለ መስጂድ ለመገንባት የመሬቱን እዳ እንኳን ሳንሸፍን ለአመታት ቆይቷል፣ግለሰቡም ከዛሬ ነገ ይከፍሉኛል በሚል በትእግስት ሲጠባበቅ ቆይቷል።አሁን ግን የሚፈልገውን ጥቅም ባለማግኘቱ መሬቱን መልሶ መውሰድ እንደሚፈልግ አሊያም በአስቸኳይ ክፍያውን እንድንፈፅም ለመስጂዱ ጀመአና ኮሚቴ በተደጋጋሚ  እያስጠነቀቀ ይገኛል። ስለዚህ ይህንን የአላህ ቤት ለማስፋፋት (መድረሳ እና ሌሎች ለአካባቢው ሙስሊም ማህበረሰብ ሚጠቅሙ) ስራዎችን ላዩ ላይ ለመስራት መሬቱ የግድ ስለሚያስፈልገን የሌሎች ሙስሊም ወገኖቻችን እርዳታ ያሻናል!!!

🔗(የዘኑረይን መስጂድ ጀመዐ እና ኮሚቴው)
ንግድ ባንክ:  1000614390321 የአካውንት ስም: zenureyn mesjd (ዘኑረይን መስጂድ)
አዋሽ ባንክ:  014251315326100 ኤሊያስ፣ ኡስማን እና ጀማል
የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

03 Mar, 18:31

544

ጥፋት ላይ መውደቅ እና ጥፋትን መንገድ አድርጎ መያዝ የተለያዩ ጉዳዮች ናቸው። ጥፋት ላይ መውደቅ እንደ ሰው ማንንም ሰው የሚያጋጥም ነው። በሐዲሥ እንደተጠቀሰው "ሁሉም የሰው ልጅ በጣም ተሳሳች ነው።"
ጥፋትን የሚጓዙበት መንገድ አድርጎ መያዝ ግን የተለየ ከባድ ጥፋት ነው።
የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

03 Mar, 08:26

391

አደራህን❗️
የአላህ ዲን አንድ ነው እና በዲን ጉዳይ አትለዋወጥ


(ታላቁ ሰሀቢ ሁዘይፋ ቢን የማን رضي الله عنه)
የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

01 Mar, 19:20

452

ጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ እንዲህ ብሏል፦

ፆመኛ ከሆንክ ዓይንና ጆሮህም ይፁም ፤ ምላስህም ከውሸት እና ከክፉ ነገር ይፁም ፤ የፆምክ ቀን ፍፁም የሆነ መረጋጋትም ይታይብህ፤ የፆምክበት እና ያፈጠርክበት ቀን እኩል እንዲሆንም አትፍቀድ።”

(ሹዐቡ’ል ኢማን 3374)

#ረመዷን_1
የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

28 Feb, 15:03

762

ምን አልባት የመጨረሻው ረመዳንህ ሊሆን ይችላልና ነገ ትሞታለህ ቢባል የምትፆመውን ፆም ለመፆም ቆራጥ ሁን❗️
የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

28 Feb, 15:02

586

🔴ሰበር ዜና
የዘንድሮው1446/2025 የረመዳን ወር ጨረቃ በሳውዲ አረቢያ ታይቷል!

በዚህም መሰረት ነገ ቅዳሜ ረመዳን 1 ይሆናል።
የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

27 Feb, 15:32

549

ደጋጎች በኢባዳ ትጉ ከመሆናቸዉ ጋር አይናቸዉ ያነባል ልባቸዉ በፍራቻ ተሞልቷል እኛ የወንጀል ማእበል ዉስጥ ሁነን ሳቅ ጨዋታችን በዛ ከአኺራ ተዘናጋን ።
رحماك يا رب
የላፍቶ ቢላል መስጂድ የትምህርት መድረክ

27 Feb, 13:34

505

* የሰው ሐቅ ተሸክመህ ወደ ረመዳን አትግባ። መክፈል እየቻልክ የሰው ሐቅ ይዘህ አታጉላላ። አቅቶህ ከሆነ ጊዜ እንዲሰጡህ በትህትና አስረዳቸው።

* የበደልከውን ይቅርታ ጠይቅ። የበደሉህን ይቅር በል።

* መክፈል የማይችል ሰው ላይ ሐቅ ካለህ ብትችል እለፍ ወይም ቀንስላቸው። ካልሆነ ጊዜ ስጣቸው። "የትም ገብታችሁ አምጡ" አትበል። ወንጀል ላይ ገብተው ቢሰጡህ ሐላል አይሆንልህም።

* ስትሸጥም ስትገዛም ገር እና ቅን ሁን። ገዥም ሻጭም ሆነህ ሶደቃ የምታደርግበት ሁኔታ እንዳለ አስተውል።

* ግብይትህ ላይ ከውሸት፣ መሀላ ከማብዛት፣ ከማታለል፣ ... ተጠንቀቅ። ጊዜ ካለህ ቁርኣን ቅራ። ዚክር አድርግ።

* ቤትህ ውስጥ ሰላም ሁን። ከጭቅጭቅ ራቅ። ሶብር ይኑርህ። ለሚስትህ፣ ለልጆችህ አሳቢ፣ ተቆርቋሪ ሁን። ከአላህ በታች ያላንተ ማን አላቸው? ለባልሽ ምቹ ሁኚ። አንቺ ፈተና ከሆንሽበት ውሎውን ሁሉ ሰላም ያጣል።
=
ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር