በዚኽች ዕለት የካቲት 27 ቀን ያረፉት አቡነ ዓምደ ሥላሴ 28 መነኮሳትን በግፍ ገድለው ገዳሙን አጥፍተው ወደመጡበት ሲመለሱ በነበሩት የጣሊያን አውፕላኖች ላይ ይኽን ተአምር አደረጉ፦ አቡነ ዓምደ ሥላሴ ያቀኑትንና የጥንቱን ደገኛውን የገዳም ሥርዓት እንደጠበቀ የሚገኘውን ታላቁን ማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳምን የደበደቡት ሁለት የጣሊያን አውፕላኖች ወደመጡበት ሲመለሱ እዛው የገዳሙ ክልል ውስጥ እንዳሉ በጻድቁ በአቡነ ዓምደ ሥላሴ ገቢረ ተአምር አውፕላኖቹ ማንም ሳይነካቸው ወድቀው ተከስክሰዋል፡፡ የአውፕላኖቹ ስብርባሪ ዛሬም ድረስ በገዳሙ ክልል ውስጥ ለምስክርነት በወደቁበት ሥፍራ ይገኛል፡፡
የጥንቱን ደገኛውን የገዳም ሥርዓት እንደጠበቀ የሚገኝ አንጋፋው ማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም ሥርዓቱና ሕጉ ጥንት እንደነበረው ነው፡፡ ገዳሙ ለመላው ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን መመኪያና ለነፍስ ደኅነት በር ከፋች ሲሆን በቦታው በታላቅ ተጋድሎ የሚኖሩት አባቶችም በጸሎት አገርን ከመዓት ከመቅሰፍትና ከወራሪ ጠላት ምእመናንን በረድኤት የሚጠብቅ ታላቅ መመኪያችን ገዳም ነው፡፡
ከጌታችን ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በፊት በርዕሰ ገዳማት ማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ቀደምት አባቶች የጌታችንን መወለዱን በተስፋ ትንቢቱን ይጠብቁ ነበር፡፡ በብህትውና ለነበሩ አባቶችን የጌታችንን መወለድ ያበሰረቻቸው ሰሳ ናት፡፡ በገዳሙ ውስጥ የነበረች አንዲት ሰሳ (ቶራ) ጌታችን በቤተልሔም በተወለደ ጊዜ በተአምራት በሰው አንደበት ‹‹ዮም ተወልደ ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ ከሣቴ ብርሃን ዮም ተወልድ መድኃኔዓለም-ዛሬ የብርሃን አምላክ የዓለም ቤዛ መድኃኔዓለም ተወለደ›› ብላ በመዝለል ልደቱን በሀገራችን አሰምታለች እርሷም በቤተልሔም ካሉ መላእክትና እረኞች ጋር በልደቱ ተደስታለች። (የገነት ምድርን ከሚያጠጡት ወንዞች አንዱ የሆነው የግዮን ወንዝንም በጌታችን ልደት ጊዜ ወደ ወተትነት እንደተለወጠ ልብ ይሏል።)
ታላቁን ማኅበረ ሥላሴ ገዳምን መሳፍንት፣ ታላላቅ ነገሥታት፣ ታላላቅ ጳጳሳት፤ የከበሩ ቅዱሳን አባቶችና ቅድሳት እናቶች መናኻሪያቸው በማድረግ የተጋድሏቸው በዓት፣ የቅድስናቸው መገኛ መጀመሪያ የዘላለም ማረፊያቸውም አድርገውታል። ለምሳሌ ከነገሥታቱ እነ ዐፄ ፋሲል፣ እነ ዐፄ ቴዎድሮስ፣ እነ ዐፄ ዮሐንስ፣ እነ ዐፄ ምኒሊክን ጨምሮ ብዙ ታላላቅ ነገሥታትም በዚህ ገዳም ሥርዓተ መንግሥትና ቅዱሳት መጻሕፍትን በመመርመር ያደጉበት ታላቅ ገዳም ነው። የመይሳው ካሳ (ዐፄ ቴዎድሮስ) ገና ከልጅነታቸው ጀምረው ፊደል ቆጥረው፣ ዳዊት ደግመው የተማሩትና ያገለገሉት በመጨረሻም በሞት ባረፉ ጊዜ የተቀበሩት በዚህ ታላቅ ገዳም ነው። ዐፄ ቴዎድሮስ "...ባደኩበትና በተማርኩበት በማኅበረ ሥላሴ ገዳም ቅበሩኝ" ብለው አስቀድመው ስለተናዘዙ በልጃቸው በመሸሻ ቴዎድሮስ አማካይነት ነው ማኅበረ ሥላሴ ገዳም የተቀበሩት።
ገዳሙን በ4ኛው መ/ክ/ዘ የነበሩት ደገኞቹ ወንድማማቾቹ ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሓ ያስፋፉት ቢሆንም ገዳሙ ሱዳን ድንበር ላይ የሚገኝ በመሆኑ አሕዛብ እስላሞችና የውጭ ጠላቶቸ በተለያየ ጊዜ ከ7 ጊዜ በላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰውበታል፡፡ለምሳሌ ቅዱሳን ነገሥታት አብርሃ ወአጽብሓ ያነጹትን ዮዲት ጉዲት አቃጠለችው፣ መነኮሳቱን ገድላ ቅርሱን ዘረፈች፡፡ ንጉሥ አግብዓ ጽዮን ያሠሩትን ደግሞ ግራኝ መሐመድ አጥፍቶታል፣ እርሱም መነኮሳቱን ድጋሚ ገድለ ቅርስ ዘረፈ፡፡ በኋላ በዐፄ ሠርጸ ድንግል የተሠራውን ደርቡሾች አቃጠሉት፤ በዐፄ ዮሐንስ ዘመንም (1600-1625) ሃይማኖት ተፋልሶ ገዳሙ ጠፍቷል፤ በ1877 ዓ.ም ደርቡሾች ድጋሚ ገዳሙን አቃጥለው መነኮሳቱን ገድለዋል፡፡ በዐፄ ቴዎድሮስ ዘመንም እንግሊዞች የገዳሙን ቅርሶች ዘርፈው ወስደዋል፡፡ በኋላም በተፈሪ መኮንን አልጋ ወራሽነት እቴጌ ዘውዲቱ (1909-1922) የተቃጠለውን ቤ/ክ አሠርተው ለመነኮሳቱ የሚሆን የውኃ ማጠራቀሚያ ትልቅ ታንከር አስቆፍረው ያሠሩላቸው ቢሆንም ጣልያን በ1928 በከባድ መሳሪያ በአውሮፕላን መትቶ ገዳሙንና ታንከሩን አቃጥሎታል፡፡ 28 መነኮሳትንም በግፍ ገድሏል፡፡ የፈረሰው የውኃ ታንከር ዛሬም ድረስ በምስክርነት አለ፡፡ ገዳሙን የደበደቡት ሁለት አውፕላኖችም ወደመጡበት ሲመለሱ እዛው የገዳሙ ክልል ውስጥ እንዳሉ በጻድቁ በአቡነ ዓምደ ሥላሴ ገቢረ ተአምር አውፕላኖቹ ማንም ሳይነካቸው ወድቀው ተከስክሰዋል፡፡ የአውፕላኖቹ ስብርባሪ ዛሬም ድረስ በገዳሙ ክልል ውስጥ ለምስክርነት በወደቁበት ሥፍራ ይገኛል፡፡
የማኅበረ ሥላሴን ገዳም ጻድቁ እንደመሶብ አንሥተው ለአጋዝእተ ዓለም ሥላሴ አስባርከውታል፡፡ ጻድቁ በቦታው ላይ ለ60 ዓመታት ሙሉ በፀሐይ ብቻ የበሰለ ምግብ እየተመገቡ በታላቅ ተጋድሎ ኖረው ታላቅ ቃልኪዳን ተቀብለውበታል፡፡ ዛሬ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ በምትገኝበት በየትኛውም ዓለም ላይ ቅዳሴ በሚቀደስበት ወቅት የማኅበረ ሥላሴ ገዳም ስሙ ሳይጠራ አይውልም፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን የቅዳሴ ሥርዓት ላይ በጸሎተ ቅዳሴ ወቅት ከቅዱስ ቁርባን በፊት ‹‹ሰላም ለክሙ ማኅበረ ሥላሴ…›› በማለት በዜማ የሚደረስ የጸሎት ክፍል አለ፡፡ ዜማውን የደረሱትና ሥርዓቱን የሠሩት ገዳሙ ካፈራቸው ታላላቅ ቅዱሳን አባቶች መካከል አንዱ የሆኑት ቅዱስ አርከ ሥሉስ ናቸው፡፡ ማኅበረ ሥላሴ አንድነት ገዳም ታላቅና ጥንታዊ ገዳም መሆኑ በዚህ ይታወቃል፡፡ በየትኛው ዓለም ላይ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ውስጥ ቅዳሴ በሚቀደስበት ሰዓት ስሙ ሳይጠራ አይውልም፡፡
አቡነ ዓምደ ሥላሴ ዐፄ ሱስንዮስ ካቶሊካውያን ደግፈው 8ሺህ የሀገራችንን ሊቃውንት በአንድ ቀን ባሳረዱ ጊዜ ንጉሡ ወዲያው ‹‹ኦርቶዶክስ ይርከስ ካቶሊክ ይንገስ›› ብሎ ያወጀበት ምላሱ ተጎልጉሎ ወጣ፡፡ እንደ አርዮስም ሆዱ አብጦ አንጀቱ ተልቶ ሊሞት ባለ ሰዓት አቡነ ዓምደ ሥላሴ አዘዞ ድረስ ሄደው ‹‹ፋሲል ይንገሥ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ትመለስ የሱስንዮስም ምላስ ይመለስ›› በማለት ተጎልጉሎ የወጣውን ምላሱን በመስቀላቸው ቢባርኩት ምላሱ ተመልሶለታል፡፡ ከዚህ በኋላ አቡነ ዓምደ ሥላሴ የዐፄ ፋሲልን ሹመትና ሃይማኖትን በአዋጅ አጽንተው ተመልሰው ወደ ገዳማቸው ማኅበረ ሥላሴ ገዳም ገብተዋል፡፡ ዐፄ ፋሲልንም የማኅበረ ሥላሴን ገዳም ግዛቱን ከሱዳን እስከ ጣቁሳ ድረስ እንዲሆን በአዋጅ ወስነው ሰጥተውት ነበር ነገር ግን ላይጠቀምበትና ላይጸና ነገር የደርግ መንግሥት የገዳሙን ሥርዓት ከማፍረሱም በላይ ርስት ጉልቱን ነጥቆ ወሰደበት፡፡ በደርቡሾች ወረራ ጊዜ እንግሊዞች አጋጣሚውን ተጠቅመው የአቡነ ዓምደ ሥላሴን ቅዱስ ገድል ዘርፈው ወስደውታል፡፡ ዛሬ በእንግሊዝ ሀገር ገድለ አቡነ ዓምደ ሥላሴ ይገኛል፡፡ ጻድቁ በዛሬዋ ዕለት የካቲት 27 ቀን ነው ያረፉት ዐፅማቸው በዚያው በመሠረቱት በማኅበረ ሥላሴ ገዳም በክብር ተቀምጧል፡፡
የአቡነ ዓምደ ሥላሴ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን (ከገድላት አንደበት)

کانالهای مشابه



የቅዱሳን ኅሩያን፣ ከገድላት አንደበት ወቅታዊ መረጃ
ቅዱሳን ኅሩያን የአማርኛ ድምፅ ቻናል አዲስ ይዘው እንደሚገኙ የሚያዘዙ ሀይማኖታዊነትና የእምነት ጸጋ ይበልጣል። ይህ ቻናል ለዚህ ወቅት የወሰነ አዲስ ዝርዝር በሚኖርበት ጊዜ ገድለ ቅዱሳንን በጽሑፍና በድምፅ ይተላለፉበታል። በየቀኑ የሚኖሩ ትዕዛዞች እና መረጃዎች ይታወቃሉ። ቅዱሳን ኅሩያን እንዲሁም የፍትሕ እና የአስተዋል ብሄርን ይዮው የሚሰጣል ነው።
ቅዱሳን ኅሩያን ቻናል ምን ይዟል?
ቅዱሳን ኅሩያን ቻናል ከእምነት እና በመንፈሳዊ ዓይነት ጋር የተያያዘ ድምፅ እና ገለጻ ላይ ይገኛል። የቻናሉ ዋነኛ ጊዜ ለውህድ በሚገኘው ዕንቅስቃሴ የአማርኛ እና ሐዘን መሰረታዊ እንደዚህ ያለው አይነት ድምፅ ይሰጣል።
ይኽ ለ3ኛ ጊዜ የተከፈተ የውይይት እና የፍትሕ መሀይል መረጃዎች ተጨማሪ ተመልካት ይሰጣል። እነዚህ ገንቢዎች የከንቱ እና የዝማኔ ገድለ ሃይማኖታትን ይወዳድሩ ይችላሉ።
ቅዱሳን ኅሩያን አንድ የሚሰጣቸው አገልግሎት ምንድን ነው?
ቅዱሳን ኅሩያን ለመጠቀም የዝርዝር አገልግሎት አብሮትን ይሰጣል። አንዱ ዝርዝር በገድለ ቅዱሳን መሠረት የሚኖሩ እና በእምነታቸው የተነሱ የምርት ማዕከላዊ ጋር ይታወቃሉ።
እንዲሁም ዘርዝር አገልግሎታት በጽሑፍ ገበሬ ይቀርባሉ። የሚኖሩ ቅዱሳን ገድለ አይነት ዕውነታቸው ይወዳድሩ ይችላሉ።
የቅዱሳን ኅሩያን ምን የሚተላለፊ ይዘት አለው?
የቅዱሳን ኅሩያን ይዘት እንደዚህ ይሰጣል። ይህ በውይይት እና በክፍል ያሉበት ሀይማኖታቸውን ግንቦት ይወዳድሩ ይችላሉ።
ይህ ዘመናዊ ይዘት ይወዳድሩን ይብዛል እና እርግብ የብዙ ተጽእኖን ያለው ይሆን። ይገኝተህ እንደ ሀይማኖት ሞልክን የቀደም ጨዋታ ይወዳድሩ ይሆን።
ቅዱሳን ኅሩያን ምንድን ዓይነት ዝርዝር አገልግሎት አለ?
ቅዱሳን ኅሩያን ይዚህ ዓይነት ዝርዝር ይሰጣል። ይኸው ተረጃን ወደ ቅዱሳን ዙሪያ እና ዘርዝር እንደ ዘይውን በሚገኝ የወጣበትን ይወዳድሩ ይችላሉ።
ይህ ቅዱሳን ላይ ያቀርባቸው ያለው ዝርዝር አገልግሎት ኀኪም ይልቅ ይሆን። የእምነት አይነት የሚገኘው ዝርዝር ይሰጣል።
کانال تلگرام በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን (ከገድላት አንደበት)
በእንተ ቅዱሳን ኅሩያን (ከገድላት አንደበት) የታሪኩን ስነስርዓት የተማሪዎችን ማስታወቂያዎችን እና ጽሑፍን ከአፈቃላይ መልእክት ማወቅ ይችላሉ ። እስካሁንም ገድላት የኅሩያን ወንድሞችን እና ሴትሞችን ለመመልከት መረጃዎች ይሰጡበታል። ብቁ ከገዳብ ልብ ውስጥ የሚደረጉትን ውይይት ሰልቦና በኮንትራቨኝ መናገር ይችላሉ።