ወንድም እህቶቼ እንኳን አደረሳችሁ
🙏🙏🙏🙏ይህንን ያውቃሉ🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
❖ ❖ ❖እነሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት ተወልዶላችኋል ሉቃ.2፥11 ❖ ❖ ❖
❖ ❖ ❖ እንኳን ለጌታችን ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡ ❖ ❖ ❖
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
❖ ❖ ❖ " ጌና" ❖ ❖ ❖
ጌና እና ልደት {ዋዜማና ክብረ በዓል }
/የተለያዩ ቀናት/ ቢኾኑም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን ጌና ልደትን እየተካ እንጠቀምበታለን ፤ ነገር ግን ይህ ሊስተካከል ይገባዋል፡፡ ልዩነት ስላለውም የኢትዮጵያ ብርሃን የተባለው አፈ ጳዝዮን አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ለጌናና ለልደት ለ2ቱም በዓላት ለየብቻቸው በመጽሐፈ ምሥጢር ድርሰት ደርሶላቸዋል፡፡
#ጌና ፤ የልደት በዓል ዋዜማ ቀን ሲኾን በዚህ ቀን ‹‹በገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ›› የተባለለትን ‹‹የገና ጨዋታ›› እንጫወታለን፤ የምንጫወትበት የኳሱ ስያሜ ‹‹ሩር›› ሲባል ስያሜውን ያገኘው፤ ሰብዓ ሰገል እልፍ እልፍ ሠራዊት አስከትለው የተወለደውን የአይሁድ ንጉሥ ፍለጋ ወደ ንጉሡ ሔሮድስ ደርሰው ነበርና ፤ ሔሮድስ ሕፃኑን ሊገድለው ፈልጎና በውስጡ ሸሽጎ ለሰብዓ ሰገል ሂዱ ሕፃኑን ፈልጉ ስታገኙትም ንገሩኝ ብሎ ሰድዷቸዋል ፤ ነገር ግን በዚያው ሳይነግሩኝ እንዳይሄዱ በማለት እነርሱ ሳያውቁ ‹‹ሩር›› የተባለ ሰላይ በመሃላቸው አስገብቶ ነበርና ሰብዓ ሰገልን ይመራቸው የነበረው ኰከብ ተሠውሮባቸዋል ፤ ሰብዓ ሰገል ሠራዊታቸውን ቢያጣሩ ከመሃከላቸው የተቀላቀለ ሩር የተባለ የሔሮድስን ሰላይ አገኙ ይህንንም ሰላይ የሰብዓ ሰገል ሠራዊት አንገቱን በሰይፍ ቀልተውታልና ያን ለማስታወስ ዛሬ በገና ጨዋታ ላይ ሩር የተባለው ኳስ የሔሮድስ ሰላይን ‹‹ሩር›› እንዲያስታውስ አባቶች ሥርዐትን ሠሩ፡፡
❖ ❖ ❖ የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ❖ ❖ ❖
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውኃ ፈሳሽ አይደለም፡፡ ከጥንት ከመሠረት ጀምሮ በመላእክት ፤ በነቢያት ሲነገር ፤ ሲሰበክ የመጣ ነው እንጂ፡፡ ማቴ.1፥18፡፡ ሰው የመሆኑን ምሥጢር ለመጀመሪያ ጊዜ በማዕከለ ገነት የተናገረ እርሱ እግዚአብሔር ነው፡፡
አባታችን አዳም ከእግዚአብሔር ትዕዛዝ ወጥቶ ዕፀ በለስን በልቶ ከጸጋ እግዚአብሔር በተራቆተ ጊዜ /አዳም ኮነ ከመ አሐዱ እምኔነ/ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ዘፍ.3፥22 ብሎ ከሦስቱ ቅዱስ አንዱ ቅዱስ እግዚአብሔር ወልድ በተለየ አካሉ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው እንደሚሆን ተናግሯል፡፡ በዚህ ቃል መሠረት /መሪነት/ ቅዱሳን መላእክት ምሥጢረ ትንቢት ተገልጾላቸዋል፡፡ እነሱም የተገለጸላቸውን ምሥጢረ ትንቢት ኀላፍያትንና መጻእያትን ለሚናገሩ ነቢያት ነግረዋቸዋል፡፡ ቅዱሳን ነቢያትም ከእግዚአብሔር ያገኙትን ከመላእክት የሰሙትን መነሻ አድርገው በተለያዩ ጊዜያት በተለያዩ ምሳሌያት በተለያዩ ዘመናት የወልደ እግዚአብሔርን ሥጋዌ ሰብከዋል /ገልጸዋል/ ዕብ.1፥1፡፡ ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጎዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናግሮ ፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ በዚህ ዘመን መጨረሻ ለእኛ ተናገረን፡፡
✔ የጌታችን ልደት በትንቢተ ነቢያት ፦
👉 ከዓበይት ነቢያት መካከል አንዱ የሆነው ነቢየ እግዚአብሔር ኢሳይያስ የሚከተለውን ትንቢት ተናግሯል፡፡
"እነሆ ድንግል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች ( ኢሳ.7፥14፣ ሕዝ.44፥1) ፡፡ በኅቱም ድንግልና ተፀንሶ በኅቱም ድንግልና የተወልደው አማኑኤል ጌታ ነው፡፡ ትርጉሙም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡ነቢዩ በጎላና በተረዳ ነገር “ሕፃን ተወልዶልናል ወልድ ልጅም ተሰጥቶናል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፡ ስሙም ድንቅ መካር ኀያል አምላክ የዘለዓለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል“ በማለት የሚወለደው ሕፃን የባሕርይ አምላክ የዘለዓለም አባት የሰላም አለቃ ሥልጣን የባሕርይ ገንዘቡ እንደሆነ እና ለሥልጣኑም ወሰን ድንበር እንደሌለው ተናግሯል፡፡
👉 ከደቂቀ ነቢያት መካከል አንዱ ሚልክያስም በቤተልሔም ስለመወለዱ፡-
"የኤፍራታ ምድር አንቺ ቤተልሔም ከይሁዳ አለቆች ከቶ አታንሽም ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ ንጉሥ ከአንቺ ይወጣልና" (ሚክ.5፥2፣ ማቴ.2፥6) ብሏል፡፡
👉• ነቢየ እግዚብሔር ቅዱስ ዳዊትም "እነሆ በኤፍራታ ሰማነው ዛፍ በበዛበትም ቦታ አገኘነው እንግዲህስ ወደ እግዚአብሔር ማደሪዎች እንገባለን ብሎ የወመለዱን ምሥጢር ተናግሯል" (መዝ.131፥6)
👉• ነቢዩ ዕንባቆምም "አቤቱ ድምፅህን ሰምቼ ፈራሁ ሥራህንም ዐይቼ አደነቅሁ በሁለት እንስሶች መካከል አየሁህ ዘመኑ እንደደረሰ አድርጌ አውቅህአለሁ ዘመኑም በደረሰ ጊዜ ተገለጥክ" ብሎ በቤተልሔም በረት በተወለደ ጊዜ አድግና ላኅም እስትንፋሳቸውን እንደሚገብሩለት (ዕንባቆም 3፥1) ተናግሯል፡፡
ከዚህ በኋላ የዘመኑ ፍጻሜ ሲደርስ እግዚአብሔር መልአኩን ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ድንግል ማርያም በመላክ አብሥሯታል፡፡ “ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ።እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል" በማለት፡፡ ሉቃ. 1፡32
እመቤታችንም በብዙ ኅብረ አምሳል ትንቢት ሲነገርለት፤ ምሳሌ ሲመሰልለት፤ ሱባኤ ሲቆጠርለት የነበረውን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በቤተልሔም ግርግም ወለደችው፡፡
ይህንንም ብስራት በቤተልሔም ዋሻ መንጋቸውን ነቅተውና ተግተው ይጠብቁ ለነበሩ እረኞች መጋቤ ሐዲስ አብሣሬ ትስብዕት ቅዱስ ገብርኤል ፤ እነሆ ዛሬ መድኀኒት በዳዊት ከተማ ተወልዶላችኋል ይኸውም ቡሩክ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሚያርቅ በረከተ ሥጋ በረከተ ነፍስ የሚያድል ከዓለም በፊት ንጉሥ የነበረ ዛሬም ከዳዊት ባሕርይ /ዘር/ በቤተልሔም ዋሻ ዓለምን ለማዳን የተወለደ የዳዊት ልጅ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ ተወለደ ሲል አበሰራቸው፡፡ (መዝ.73፥12)
💥 የጌታችንን ልደት ስናነሣ ሁለት ልደታት እንዳሉት እናምናለን፡፡ እኒሁም ልደታት /ልደት ቀደማዊና/ /ልደት ደኃራዊ/ ናቸው፡፡
✔ ልደት ቀዳማዊ ፦ ቅድመ ዓለም ከአብ አካል ዘእም አካል ባሕርይ ዘእም ባሕርይ ከእግዚአብሔር አብ ያለ እናት የተወለደው ልደት ሲሆን /ነቢዩ ዳዊት እንዲህ ይገልጸዋል፡፡ "ወለድኩከ እምከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽ ባህ መዝ.109፥3 ከአጥቢያ ኮከብ አስቀድሞ ወለድኩህ ፤አንተ ልጄ ነህ እኔም ዛሬ ወለድኩህ" (መዝ.2፥7)
✔ ልደት ደኃራዊ ፦ አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ሲፈፀም በዕለት ሐሙስ ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ እንዲል ቃሉ፡፡ ቅድስት ድንግል ከምትሆን ከእመቤታችን እንበለ ዘርዓ ብዕሲ ያለ አባት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም የተወለደው ልደት ነው፡፡