ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ のテレグラム投稿

"ይህ ቻናል የጅ/ዩ/ዋ/ግ/ግ/ጉ ሲሆን በጅማ ዋና ግቢ ለሚማሩ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ተማሪዎች በግ/ጉ ሚትላለፉትን መልዕክት፣ት/ቶች፣ስነ ጽሁፎች እና ሌሎችም ለማድረስ የተከፈተ ቻናል ነው።"
ለማንኛውም አስተያየት
👉 @AsegidT
👉 @SuraMoD
👉 @Shalule
ለማንኛውም አስተያየት
👉 @AsegidT
👉 @SuraMoD
👉 @Shalule
2,415 人の購読者
2,467 枚の写真
42 本の動画
最終更新日 06.03.2025 09:38
ጅማ/ዩ/ ዋና ግቢ - ግቢ ጉባኤ によってTelegramで共有された最新のコンテンツ
✝✝✝ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች የሳምንቱ ትምህርታዊ ስነ ጽሑፍ እነሆ✝✝✝
💐ቅድስት💐
ቤተ ክርስቲያናችን በሠራችልን የጾም ሥርዓት መሠረት ሁለተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት “ቅድስት” በመባል ይጠራል። ይህም ቅዱስ ያሬድ በጾመ ድጓው የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ጾም ከፋፍሎ በዜማ ደርሶ ባስቀመጠልን መሠረት ነው። ሳምንቱ የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት ይሁን እንጂ ጌታችን በገዳመ ቆሮንቶስ ለጾመው ጾም ወይም ጾመ ዐርብዓ የመጀመርያው ሳምንት ነው።
ቅድስት ስንል "የተመረጠች፣ ልዩ የሆነች፣ የከበረች" ሳምንት እያልን ነው። (መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ መዝገበ ቃላት ገጽ ፯፻፹፬) ቅዱስ ያሬድም ይህችን ሳምንት ቅድስት ብሎ መጥራቱ፡-
፩. ጌታችን ጾሙን የጀመረባት የመጀመሪያዋ ሳምንት በመሆንዋ ነው። በዮርዳኖስ ወንዝ የጥምቀትን ሕግ ከሠራልን በኋላ በመብል ምክንያት የመጣውን የሕግ መተላለፍ ጾሞ የረኃብን፣ የስስትን እና የትዕቢትን ፈተናዎች ያጠፋልን ዘንድ ከሰው ርቆ በበረሃ ለዐርብዓ ቀን እና ሌሊት ጾሞ፣ ጸልዮ ከክብሩ ዝቅ ያለውን የሰው ልጅ ሊያከብረው የጾመበትን ሳምንት ለማዘከር ማኅሌታይ ቅዱስ ያሬድ ሳምንቱን “ቅድስት” ብሎ ጠርቶታል። (ማቴ.፬፥፩-፲፩)
፪. ሰንበት ላይ በመዋሉ ነው፤ አምላካችን እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን በነቢዩ ሙሴ በኩል ከሰጣቸው ዐሥርቱ ትእዛዛት መካከል አንዷ ክብረ ሰንበትን እንዲጠብቁ ነው። "የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ" እንዲል፡፡ (ዘጸ.፳፥፰) ይህን ያልንበትም ምክንያት በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ነው።
የመጀመሪያው ፈጣሬ ፍጡራን፣ አምጻኤ ዓለማት ቅዱስ እግዚአብሔር ይህችን ዓለምና በውስጧ የሚኖሩትንም ፍጥረታት ከአለመኖር ወደ መኖር በቃሉ ፈጥሮ፣ የሰውን ልጅም በእጁ ከምድር አፈር አበጃጅቶ ከጨረሰ በኋላ ከሥራው ሁሉ ያረፈባት ዕለትና ለእስራኤል ዘሥጋ እንዲጠብቋት የተሰጠች የዕረፍት ቀን በመሆንዋ ነው፡፡ (ቀዳሚት ሰንበት) (ዘፍ.፪፥፫)ይህችውም ዕለት በአይሁድ ዘንድ እጅግ የተከበረች እና ልዩ የዕረፍት ቀን ተደርጋ ትከበራለች። በዚች ዕለት ከቆሙ ሳይቀመጡ፣ ከዘረጉ ሳያጥፉ ሥራቸውን ሁሉ በመካተቻይቱ ቀን (ዓርብ ዕለት) ፈጽመው በዚህች ቀን ያርፉ ነበር። እስራኤል ዘነፍስ ለሆንን ለሐዲስ ኪዳን ምእመናንም ይህችን ዕለት ከሥጋ ዕረፍት እናርፍባት ዘንድ ሕግ ተሠርቶልናል።
ሁለተኛዋ የዕረፍት ቀን ደግሞ የትንሣኤያችን በኩር ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሞትን መውጊያ ሰብሮ፣ የመቃብርን ሆድ ባዶ አስቀርቶ፣ ሰላም አጥቶ በእሳት ዛንዥር ይሠቃይ ለነበረው ለአዳም እና ለልጆቹ የሰላም ስብከት በሰበከበት፣ በትንሣኤውም ሞትን ድል ባደረገበት፣ በሚመጣውም ዓለም በትንሣኤ ዘጉባኤ ዳግሞኛ ለፍርድ በሚመጣባት የሐዲስ ኪዳኗ ሰንበት “ሰንበተ ክርስቲያን” ላይ ይህ የጌታ ጾም ስለሚጀምር የመጀመሪያዋን ሳምንት “ቅድስት” ብሎ ጠራት።
ይህች ዕለት ከዕለታት ሁሉ የከበረች፣ ከፍ ከፍም ያለች ናት። ጥንቱን ዓለም በእርሷ መፈጠር ጀምረ፤ የሰው ልጅ ትንሣኤውን በእርሷ አየ፤ ፍጻሜውም (ህልቀተ ዓለም) በእርሷ ይሆናል። በዚያችም ቀን ወደ ተዘጋጀችልን የደስታ መኖሪያችን ወደ መንግሥተ እግዚአብሔር እንገባባታለን።
ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ
✝✝✝የጅማ ዩንቨርሲቲ ዋና ግቢ ግቢ ጉባኤ ት/ት ክፍል ትምህርታዊ ስነ ጽሑፍ ንዑስ ክፍል🙏✝✝✝

“እኔን ያዘጋጀኝ ለዚህ ቀን ነበር ለካ?”
ዲ/ን ዶ/ር መገርሳ ዓለሙ የቀዶ ጥገና ሰብ ስፔሻሊስት
የካቲት ፳፫/፳፻፲፯ ዓ.ም
በማኅበረ ቅዱሳን የ13ኛው የግቢ ጉባኤ ዓለም አቀፍ ሴሚናር በከሰዓት መርሐ ግብር የልምምድ ልውውጥ ተደርጓል።
ከተጋባዥ አገልጋዮች መካከል አንዱ የሆኑትና የቀዶ ጥገና ሰብ ስፔሻሊስቱ ዲ/ን ዶ/ር መገርሳ ከምርቃት በኋላ ወደ አምቦ እና አጋሮ ለሥራ መመደባቸውን ተናግረው የእግዚአብሔርንም መልእክት የተረዳሁበት ነው ይላሉ።
በተለይም በአጋሮ ቆይታቸው በአካባቢው ወደ 22 አብያተ ክርስቲያናት እንደነበሩና ከ3 ወይ 4 የማይበልጡ አብያተ ክርስቲያናት ብቻ ክፍት ነበሩ ይላሉ።
አክለውም ወደ አካባቢው ስሄድ አባቶች ምእመናን የሚያስተምራቸው አጥተው ሊበተኑ ነው እባክህ ትንሽ ከቻልህ አስተምርልን አሉኝ። እኔ በግቢ ጉባኤ ብማርም መድረክ ይዤ አስተምሬ ስለማላውቅ ደነገጥሁ። ነገር ግን ከሚበተኑ ብዬ ከሕክምና ሥራዬ በተጨማሪ ወንጌል መስበክ ጀመርሁ።
የበለጠ ብዙ ቦታ ለመድረስም ሞተር ሳይክል ገዛሁና በቻልሁት ያወቅሁትን እውነት አስተማርሁ።
ዲ/ን ዶ/ር መገርሳ ለካስ እግዚአብሔር በግቢ ጉባኤ አስተምሮ ያስጨረሰኝ ለዚህ ቀን አስቦኝ አዘጋጅቶኝ ነበር? ለካ እኛን የሚጠብቁ በየቦታው አሉ? ብዬ ራሴን ጠየቅሁ ይላሉ።
እናም የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች እንዲህ ያሉ የቤተ ክርስቲያን ክፍተቶችን ለመሙላት መዘጋጀት አለብን በማለት መልእክት አስተላልፈዋል።
በመርሐ ግብሩ ልምዳቸውን ያካፈሉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር ዶ/ር ወርቁ ደጀኔ እና የማኅበረ ቅዱሳን ሥራ አመራር አባል ወ/ሮ የእሱነሽ ተሾመም የግቢ ጉባኤ ተማሪዎች በግቢ ሕይወታቸው ራሳቸውን ከውጫዊና ውስጣዊ ፈተናዎች በመጠበቅ ለሀገርና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዲዘጋጁ አሳስበዋል።

🎉🎉የዚህ ሳምንት አሸናፊዎች🎉🎉
🥇 Saron – 6 (14.4 sec)
🥈 @Kidanemercyy – 6 (15.5 sec)
🥉 @Et12211922nb – 6 (53.9 sec)
የተሳተፋችሁ በጠቅላላ እግዚአብሔር ያክብርልን መልካም ምሽት😊
🥇 Saron – 6 (14.4 sec)
🥈 @Kidanemercyy – 6 (15.5 sec)
🥉 @Et12211922nb – 6 (53.9 sec)
የተሳተፋችሁ በጠቅላላ እግዚአብሔር ያክብርልን መልካም ምሽት😊
🎲 Quiz ''የአርብ ጥያቄ' ኒቆዲምስ ጥያቄና መልስ '
ይህ በየሳምንቱ አርብ ምሽት2:30 ላይ በጅማ ዩኒቨርስቲ ዋና ግቢ ግቢ ጉባኤ ትምህርትና ሐዋሪያዊ አገልግሎት እየተዘጋጀ የሚቀርብ የጥያቄና መልስ ውድድር ነው በዚህ ውድድር በመሳተፍ መንፈሳዊ እውቀቶን ያሳድጉ!
🖊 6 questions · ⏱ 45 sec

❌ውድ የግቢ ጉባኤያችን ቤተሰቦች ✅
👉ሳምንታዊው በትምህርት ክፍል የሚዘጋጀው የጥያቄና መልስ መርሃግብር ሊጀምር ነው ተዘጋጁ