Últimas Postagens de The Federal Supreme Court of Ethiopia (@fscethiopiapr) no Telegram

Postagens do Canal The Federal Supreme Court of Ethiopia

The Federal Supreme Court of Ethiopia
Federal Supreme Court is the highest court in Ethiopia. It is constitutionaly established court. It is also one of the three pillars of the federal state that assures the check and balance in & among.
10,732 Inscritos
1,807 Fotos
21 Vídeos
Última Atualização 01.03.2025 06:39

Canais Semelhantes

TIKVAH-ETHIOPIA
1,531,820 Inscritos
AACRA
10,053 Inscritos

O conteúdo mais recente compartilhado por The Federal Supreme Court of Ethiopia no Telegram


የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በተለያዮ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ሰጠ።
******
የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጥር 21/2017 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በሶስቱም ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች ላይ የቀረቡ 26 የዲስፕሊን ክሶች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ሰጥቷል።
በዚሁ መሰረት
ተ.ቁ 1 በተለያዩ መዝገቦች የዲስፕሊን ክስ የቀረበባቸው ሶስት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች፣አንድ ረዳት ዳኛ እና አንድ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ በፈጸሙት የስነ ምግባር ደንብ ጥሰት ጥፋተኛ ናቸው በማለት የወሰነ ሲሆን የቅጣት አስተያየት እንዲያቀርቡ ወስኗል።
2.ሁለት የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት ዳኞች ጥፋተኛ በተባሉበት የዲስፕሊን ክስ በቃል ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው፣
3.በሶስት የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት ዳኞች ላይ የቀረቡ የዲስፕሊን ክሶች በድጋሚ ማጣራት ተደርጎባቸው ለጉባኤው እንዲቀርብ ፣
4.በሶስቱም ደረጃ ፍርድ ቤቶች በሚገኙ 24 ዳኞች ላይ የቀረቡ 15 አቤቱታዎች ዳኞቹን የሚያስጠይቁ አይደሉም በማለት ውድቅ እንዲደረጉ፣
5.አንድ የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት ዳኛ በቀረበበት የዲስፕሊን ክስ መልስ እንዲያቀርብ ወስኗል።
በሌላ በኩል ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኝነት ለህዝብ አስተያየት መቅረብ አለብን በማለት የቀረቡ 2 ቅሬታዎች ላይ ተወያይቶ ተቀባይነት የላቸውም በማለት ወስኗል።

የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ።
መልካም በዓል

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጥር 8 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሳባ የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም በማለት የወሰናቸው መዝገቦች ዝርዝር
ተ.ቁ መዝገብ ቁጥር

1. 5439/13
2. 5522/13
3. 5546/13
4. 5557/13
5. 6077/13
6. 6104/13
7. 6106/13
8. 6112/13
9. 6113/13
10. 6115/13
11. 6132/14
12. 6134/14
13. 6141/14
14. 6159/14
15. 6199/14
16. 6210/14
17. 6218/14
18. 6221/14
19. 6237/14
20. 6482/14
21. 6555/14
22. 6556/14
23. 6559/14
24. 6561/14
25. 6562/14
26. 6563/14
27. 6736/14
28. 7235/15
29. 7457/15
30. 7540/15
31. 7604/15
32. 7605/15
33. 7623/15
34. 7820/15
35. 7834/15
36. 7969/15
37. 8070/15
38. 8309/15
39. 8496/15
40. 8500/16
41. 8524/16
42. 8546/16
43. 8670/16
44. 8706/16
45. 8740/16
46. 8970/16
47. 9027/16
48. 9069/16
49. 9321/17
*ማስታወሻ*
1. ቁጥራቸው የቅርብ ጊዜ የሆኑት ጉዳዮች ቀድመው የታዩበት ምክንያት በጉባዔው መመሪያ መሰረት ቅድሚያ አግኝተው ምርመራቸው የተጠናቀቀ (የወንጀል፣ የአካል ጉዳተኞች፣ የአሰሪና ሰራተኛ፣ ከፍ/ቤት ሪፈራል የተላኩ፣ የታገዱ መዝገቦች) መሆናቸውን እየገለፅን ከዚያ ውጭ ያሉት ግን እንደ አመጣጥ ቅደም ተከተላቸው የተስተናገዱ ናቸው፡፡
2. ከላይ የተዘረዘሩትን ውሳኔዎች የውሳኔ ግልባጭ ከሁለት ሳምንት በኋላ በጉባዔው ፅ/ቤት በመቅረብ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ

አጣሪ ጉባዔው በ55 የትርጉም አቤቱታዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እና አቅጣጫ ሰጠ።
አርብ ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም (አዲስ አበባ)

የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሐሙስ ጥር 8 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ጉባዔ በንዑስ አጣሪ ጉባዔ እና በአጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ የሕግ ተመራማሪዎች ተገቢው ምርመራ እና ማጣራት ተደርጎባቸው ከቀረቡለት የሕገ መንግሥት የትርጉም አቤቱታዎች መካከል 55 በሚሆኑት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እና አቅጣጫ ሰጥቷል።

በዕለቱ ጉባዔው ከተወያዬባቸው 55 አቤቱታዎች መካከል በቁጥር 49 የሚሆኑት ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት አልተፈፀመባቸውም ሲል እንዲዘጉ ወስኗል።
በሌላ በኩል 3 የሕገ መንግሥት ትርጉም አቤቱታዎች ላይ ደግሞ ተጨማሪ ማጣራት ተደርጎባቸው ለውሳኔ እንዲቀርቡ ጉባዔው አቅጣጫ አስቀምጧል።
በተጨማሪም በሦስት የሕገ መንግሥት የትርጉም አቤቱታ ላይ ደግሞ ተጠሪዎች ምላሽ እንዲሰጡ ጉባዔው ትዕዛዝ ሰጥቷል።


የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ

የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በተለያዮ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ሰጠ።
******
የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጥር 7/2017 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን እና አቅጣጫ ሰጥቷል።በዚሁ መሰረት
1.ከደቡብ ኢትዮጽያ ህዝቦች ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ለክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት እንዲሁም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት እጬ ዳኞች ላይ የፌደራሉ ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 81/4 አስተያየት እንዲሰጥበት በተጠየቀው ላይ ከተወያየ በኋላ አስተያየቱን ሰጥቷል፣
2.የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ዳኛ የሆኑት አቶ ጌታሁን ገ/መስቀል በፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የሙስና መከላከያ ዳይሬክቶሬት የጥቆማ ተቀባይ ክፍል ሀላፊ ሆነው እንዲሰሩ ሹመት ሰጥቷል፣
3.በፌደራል ከፍተኛ እና የመጀመሪያ ፍ/ቤት ዳኞች ምልመላ ሂደት ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ የሰጠ ሲሆን ለፌደራል የመጀመሪያ ፍ/ቤት ዳኝነት ለህዝብ አስተያየት የማለፊያ ነጥብ ወስኗል።በዚሁ መሰረት ለሴት እና አካል ጉዳተኞች 68 እና ከዚያ በላይ ለወንዶች 73 እና ከዝያ በላይ ለህዝብ አስተያየት የማለፊያ ነጥብ እንዲሆን ወስኗል።ከዚሁ ጋር በተያያዘ በውጤቱ ላይ የቀረቡ 4 ቅሬታዎችም ከእጩ ዳኞች ምልመላ መመሪያ አንጻር ከታዩ በኋላ ተቀባይነት የላቸውም በማለት ወስኗል።
የህዝብ አስተያየት የመሰብሰብ ሂደቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልጻለን።

የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ጥር 01 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሳባ የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም በማለት የወሰናቸው መዝገቦች ዝርዝር

ተ.ቁ መ.ቁ.
1. 3632/11
2. 4216/11
3. 4232/11 መረጃ ባለመሟላቱ የተዘጋ
4. 4657/11
5. 4680/12
6. 4824/12
7. 4887/12
8. 4913/12
9. 5025/12
10. 5028/12
11. 5088/12
12. 5107/12
13. 5112/12
14. 5205/12
15. 5221/12
16. 5244/12
17. 5254/12 መፍትሄ አግኝተናል በሚል የተቋረጠ
18. “ 5256/12
19. 5259/12
20. 5261/12
21. 5269/12
22. 5273/12
23. 5303/12
24. 5312/13
25. 5472/13
26. 5490/13
27. 5633/13
28. 5701/13
29. 5711/13
30. 5736/13
31. 5739/13
32. 5765/13
33. 5917/13
34. 5922/13
35. 5804/13
36. 5819/13
37. 5895/13
38. 5907/13
39. 6108/13
40. 6109/13
41. 6111/13
42. 6128/14
43. 6130/14
44. 6140/14
45. 6145/14
46. 6180/14
47. 6191/14
48. 6222/14
49. 6223/14
50. 6224/14
51. 6299/14
52. 6391/14
53. 6417/14
54. 6423/14
55. 6450/14
56. 6451/14
57. 6466/14
58. 6489/14
59. 6494/14
60. 6505/14
61. 6523/14
62. 6729/14
63. 6773/14
64. 6778/14
65. 7017/14
66. 7183/15
67. 7200/15
68. 7207/15
69. 7459/15
70. 7600/15
71. 7603/15
72. 7609/15
73. 7665/15
74. 7670/14
75. 7741/15
76. 7743/15
77. 7748/15
78. 7751/15
79. 7766/15
80. 7772/15
81. 7775/15
82. 7783/15
83. 7784/15
84. 7848/15
85. 7850/15
86. 7983/15
87. 8027/15
88. 8064/15
89. 8115/15
90. 8136/15
91. 8141/16
92. 8175/16
93. 8184/16
94. 8187/16
95. 8192/16
96. 8202/16
97. 8213/16
98. 8224/16
99. 8244/16
100. 8250/16
101. 8258/15
102. 8260/16
103. 8285/16
104. 8336/16
105. 8373/15
106. 8376/16
107. 8378/16
108. 8492/16
109. 8493/16
110. 8495/16
111. 8515/16
112. 8517/16
113. 8543/13
114. 8578/16
115. 8579/16
116. 8592/16
117. 8599/16
118. 8676/16
119. 8742/16
120. 8767/16
121. 8799/16
122. 8849/16
123. 8899/16
124. 8917/16
125. 8925/16
126. 8995/16
127. 8997/16
128. 9011/16
129. 9014/17
130. 9112/17
131. 9176/17
132. 9301/17

*ማስታወሻ*
1. ቁጥራቸው የቅርብ ጊዜ የሆኑት ጉዳዮች ቀድመው የታዩበት ምክንያት በጉባዔው መመሪያ መሰረት ቅድሚያ አግኝተው ምርመራቸው የተጠናቀቀ (የወንጀል፣ የአካል ጉዳተኞች፣ የአሰሪና ሰራተኛ፣ ከፍ/ቤት ሪፈራል የተላኩ፣ የታገዱ መዝገቦች) መሆናቸውን እየገለፅን ከዚያ ውጭ ያሉት ግን እንደ አመጣጥ ቅደም ተከተላቸው የተስተናገዱ ናቸው፡፡
2. ከላይ የተዘረዘሩትን ውሳኔዎች የውሳኔ ግልባጭ ከሁለት ሳምንት በኋላ በጉባዔው ፅ/ቤት በመቅረብ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ

ጉባዔው በ136 የትርጉም አቤቱታዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እና አቅጣጫ ሰጠ።
-----------------------------------------------------------------------------
ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም አዲስ አበባ

የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሐሙስ ጥር 1 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ጉባዔ በንዑስ አጣሪ ጉባዔ እና በአጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ የሕግ ተመራማሪዎች ሰፊ ጥናት እና ምርምር ተደርጎባቸው ለውሳኔ ከቀረቡለት የሕገ መንግሥት የአቤቱታ መዛግብት መካከል 136 በሚሆኑ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እና አቅጣጫ ሰጥቷል።

በዕለቱ ጉባዔው ከተወያዬባቸው አቤቱታዎች መካከል በቁጥር 4 በሚሆኑት ላይ ተጠሪዎች ምላሽ እንዲሰጡባቸው ትዕዛዝ ሰጥቷል።
በሌላ በኩል በመዝገብ ቁጥር 5254/.. ላይ በቀረበ ሕገ መንግሥታዊ የትርጉም ጥያቄ ላይ ተከራካሪዎቹ "መፍትሄ አግኝተናል" በማለታቸው መዝገቡ ተቋርጦ የተዘጋ ሲሆን በመዝገብ ቁጥር 4232/.. ላይ በቀረበ የትርጉም አቤቱታ ላይ የተወያዬው ጉባዔው መረጃ ባለመሟላቱ መዝገቡ ተቋርጦ እንዲዘጋ ወስኗል።
በመጨረሻም ጉባዔው በዕለቱ ከተወያዬባቸው 136 አቤቱታዎች መካከል 130 የሚሆኑት ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት አልተፈፀመባቸውም (ትርጉም አያስፈልጋቸውም) በሚል እንዲዘጉ ወስኗል።

የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሳባ የሕገ መንግሥት ትርጉም አያስፈልጋቸውም በማለት የወሰናቸው መዝገቦች ዝርዝር
ተ.ቁ መዝገብ ቁጥር
1. 3942/11
2. 4001/11
3. 4658/11
4. 5330/13
5. 5563/13
6. 5677/13
7. 5678/13
8. 5683/13
9. 5768/13
10. 5769/13
11. 5770/13
12. 5772/13
13. 5777/13
14. 5870/13
15. 5883/12
16. 6208/14
17. 6456/14
18. 6640/14
19. 6664/14
20. 6997/14
21. 7029/14
22. 7037/14
23. 7086/14
24. 7135/14
25. 7188/15
26. 7221/15
27. 7279/15
28. 7282/15
29. 7294/15
30. 7380/15
31. 7624/15
32. 7638/15
33. 7713/15
34. 7717/15
35. 7727/15
36. 7788/15
37. 7930/15
38. 7995/15
39. 8018/15
40. 8073/15
41. 8178/16
42. 8225/16
43. 8636/16
44. 8691/16
45. 8722/16
46. 8870/16
47. 8896/16
48. 8941/16
49. 9065/17
*ማስታወሻ*
1. ቁጥራቸው የቅርብ ጊዜ የሆኑት ጉዳዮች ቀድመው የታዩበት ምክንያት በጉባዔው መመሪያ መሰረት ቅድሚያ አግኝተው ምርመራቸው የተጠናቀቀ (የወንጀል፣ የአካል ጉዳተኞች፣ የአሰሪና ሰራተኛ፣ ከፍ/ቤት ሪፈራል የተላኩ፣ የታገዱ መዝገቦች) መሆናቸውን እየገለፅን ከዚያ ውጭ ያሉት ግን እንደ አመጣጥ ቅደም ተከተላቸው የተስተናገዱ ናቸው፡፡
2. ከላይ የተዘረዘሩትን ውሳኔዎች የውሳኔ ግልባጭ ከሁለት ሳምንት በኋላ በጉባዔው ፅ/ቤት በመቅረብ ማግኘት የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ

ጉባዔው በ58 የአቤቱታ መዛግብት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ፣ የውሳኔ ሐሳብና አቅጣጫ አስቀመጠ።
--------------------------------------------------------------------------------

የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሐሙስ ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም በጉባዔ ጽ/ቤቱ አዳራሽ ባደረገው ስብሰባ በንዑስ አጣሪ ጉባዔ እና በአጣሪ ጉባዔ ጽ/ቤቱ የሕግ ተመራማሪዎች አስፈላጊው ምርምር እና ማጣራት ተደርጎባቸው ከቀረቡለት የሕገ መንግሥት ትርጉም አቤቱታዎች መካከል በ58ቱ ላይ ተወያይቶ ውሳኔ፣ የውሳኔ ሐሳብ እና አቅጣጫ አስቀምጧል።

ጉባዔው በዕለቱ ከተመለከታቸው 58 የትርጉም አቤቱታ መዛግብት መካከል በመዝገብ ቁጥር 7778/15 እና በመዝገብ ቁጥር 4014/.. በተከፈቱ አቤቱታዎች ላይ ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት ተፈፅሟል በሚል የመጨረሻ የውሳኔ ሐሳቡ ለፌዴሬሽን ም/ቤት እንዲላክ ወስኗል።
በሌላ በኩል ጉባዔው በ5 የአቤቱታ መዛግብት ላይ ምላሽ እንዲሰጥባቸው ያዘዘ ሲሆን ሌሎች 2 የአቤቱታ መዛግብት ላይ ተጨማሪ ማጣራት እና ምርመራ ተደርጎባቸው በድጋሚ ለውሳኔ እንዲቀርቡ አዝዟል።

በመጨረሻም ጉባዔው በዕለቱ በነበረው ስብሰባ ከተመለከታቸው 58 አቤቱታዎች መካከል በቁጥር 49 የሚሆኑት ሕገ መንግሥታዊ ጥሰት አልተፈፀመባቸውም በሚል እንዲዘጉ ወስኗል።

የኢፌዴሪ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ

የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በተለያዮ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ሰጠ፡፡
፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨
የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዮ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላለፈ፡፡

በዚህም መሰረት ጉባኤው በእለቱ የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለክልሎቹ ጠቅላይና ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ለዳኝነት ተወዳድረው መስፈርቱን ባሟሉ ዕጩ ዳኞች ላይ አስተያየት እንዲሰጥላቸው በጠየቁት መሰረት በኢ.ፌ.ዲሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 81(4) መሰረት ለወደፊቱ ማስተካከያ እንዲደረግባቸው በሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ ማስተካከያ በማከል የድጋፍ አስተያየት ተሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል ጉባኤው በሌሎች ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡

የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ