******
የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ጥር 21/2017 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በሶስቱም ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች ላይ የቀረቡ 26 የዲስፕሊን ክሶች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ሰጥቷል።
በዚሁ መሰረት
ተ.ቁ 1 በተለያዩ መዝገቦች የዲስፕሊን ክስ የቀረበባቸው ሶስት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች፣አንድ ረዳት ዳኛ እና አንድ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ በፈጸሙት የስነ ምግባር ደንብ ጥሰት ጥፋተኛ ናቸው በማለት የወሰነ ሲሆን የቅጣት አስተያየት እንዲያቀርቡ ወስኗል።
2.ሁለት የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት ዳኞች ጥፋተኛ በተባሉበት የዲስፕሊን ክስ በቃል ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው፣
3.በሶስት የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት ዳኞች ላይ የቀረቡ የዲስፕሊን ክሶች በድጋሚ ማጣራት ተደርጎባቸው ለጉባኤው እንዲቀርብ ፣
4.በሶስቱም ደረጃ ፍርድ ቤቶች በሚገኙ 24 ዳኞች ላይ የቀረቡ 15 አቤቱታዎች ዳኞቹን የሚያስጠይቁ አይደሉም በማለት ውድቅ እንዲደረጉ፣
5.አንድ የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት ዳኛ በቀረበበት የዲስፕሊን ክስ መልስ እንዲያቀርብ ወስኗል።
በሌላ በኩል ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኝነት ለህዝብ አስተያየት መቅረብ አለብን በማለት የቀረቡ 2 ቅሬታዎች ላይ ተወያይቶ ተቀባይነት የላቸውም በማለት ወስኗል።
የፌደራል ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ