ከዓላማ (ምክንያት)፣ ከምግብና መጠጥ ክልከላና ከጊዜ ርዝማኔ አኳያ ጾም ብዙ ዓይነት ነው፡፡
በመሆኑም በዚህ ልጥፍ (Post) ታላቁ የረመዳን ጾም (Ramadan Fast) ላይ እናተኩራለን፡፡ በመሰረቱ ረመዳን ጾም ከስፖርት ብቃት፣ ከአካል ብቃት፣ ከጤና፣ ከሰውነት አሰራር ስርዓት ሁኔታና ከመሳሰሉት አንጻር በርካታ ጥናቶች የተደረገበት ጾም ነው፡፡ ይሁን እንጂ ሰዎች የረመዳን ወር ሲደርስ እንቅስቃሴውን በማቆምና በመቀጠል መካከል ሃሳባቸው ሲከፈል ይስተዋላል፡፡
በረመዳን ጾም ወቅት የአካል ብቃት ልምምድ ማድረግ የሚያስገኛቸው ጠቀሜታዎች፦
የሰውነት ክብደት ለመቀነስ (ጾመ + እንቅስቅሴ = ሰውነታችን ስብን የበለጠ እንዲጠቀም ያደርገዋል)፤ የአካል ብቃት እንዳይቀንስ፣ በሽታ የመከላከል አቅም (immunity) ለመጠበቅና ለማሻሻል፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል (ስኳር፣ ደም ግፊት፣ ውፍረጥ....)፣ ድካም ደካም የሚለውን ስሜት ይቀንሳል - ጉልበት (energy) ከፍ ያደርጋል፤ በስራ ላይ ትኩረትንና የማስታወስ ችሎታን ይጨምራል፡፡
በረመዳን ጾም ወቅት እንቅስቃሴ ብናቋርጥ (ባንሰራ) ምን ይከሰታል?
የሰውነት ክብደት ይጨምራል (የምናገኘው ካሎሪ ከምናቃጥለው ስለሚበልጥ) ፣ የጡንቻ መጠን ይቀንሳል እንዲሁም የሰውነት አሰራር ስርዓት ጤና ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል በሳውዲ-አረቢያ በተደረገና 173 ቤተሰቦችን ባሳተፈ አንድ ጥናት 59.5 % ያህሉ በረመዳን ጾም ወቅት የሰውነት ክብደታቸው መጨመሩን አሳይቷል፡፡
በረመዳን ወቅት የአካል ብቃት ልምምድ ምክር ሃሳቦች፦
📌ጫናውን ማስተካከል፦ ቀላልና መካከለኛ ጫና ያላቸውን እንቅስቃሴዎች መስራት
📌ራስን ማዳመጥ (የተለየ አለመመቸት ወይም ህመም ካለ)
📌 ሙቅት ቦታዎች ላይ (በጸሃይ) እንቅስቃሴ አለመስራት
📌 ሳውና እና ስቲም ክፍሎችን አለመጠቀም (ውሃ ጥም ስለሚያባብሱ)
📌 በቂ እረፍት መውሰድ
📌 አዳዲስ እንቅስቃሴዎችን፣ አዲስ ግብ ወይም አዲስ ጫና አለመጀመር
📌 አመጋገብን ማስተካከል (በቂ ፕሮቲን፣ ሃይል ሰጭ ምግቦችንና ውሃ ማግኘት)
📌 የልምምድ ሰዓትና የልምምድ አይነቶችን ከሰውነት አሰራር ስርዓት ጋር በተገቢው ሁኔታ ማጣጣም
ማሳሰቢያ፦ የጤና ችግር ያለባቸውና ከዚህ በፊት እንቅስቃሴ ሰርተው የማያውቁ ግለሰቦች እንቅስቃሴ ከመጀመራቸው በፊት የህክምና ባለሞያ ማማከር ይኖርባቸዋል፡፡