Latest Posts from Fit Corner Sport- ፊት ኮርነር ስፖርት (@fitcorner) on Telegram

Fit Corner Sport- ፊት ኮርነር ስፖርት Telegram Posts

Fit Corner Sport- ፊት ኮርነር ስፖርት
Will provide different Training & Consultancy on fitness & wellness industry.
1,415 Subscribers
1,372 Photos
30 Videos
Last Updated 01.03.2025 03:02

The latest content shared by Fit Corner Sport- ፊት ኮርነር ስፖርት on Telegram


አዲስ የስልጠና ክፍለ ጊዜ - በፊት ኮርነር ስፖርት - አድዋ ጂም!
🧘‍♂️🧘🏾‍♀️🧘🏾‍♀️🧘🏿🧘‍♂️
የዓብይ ፆም እና የረመዳን ፆምን ምክንያት በማድረግ ለጂም አባሎቻችን አማራጭ የስልጥና ፕሮግራም ለመስጥት በማሰብ በዮጋ ኢንስትራክተር ዘወትር ማክሰኞና ሐሙስ ጠዋት ከ2፡30 - 3፡30 ሠዓት ድረስ የዮጋ ልምምድ መጀመራችን ስንገልጽ በደስታ ነው።
🧘‍♂️🧘🏾‍♀️🧘🏾‍♀️🧘🏿🧘‍♂️

ልዩ ከቤት ውጭ የስልጠናና የመዝናኛ ፕሮግራም ተካሄደ
የካቲት 03/2017 ዓ.ም - ፊት ኮርነር ስፖርት

*****
ፊት ኮርነር ስፖርት - አድዋ ጅም አባላት ልዩ ከቤት ውጭ የስልጠናና የመዝናኛ ፕሮግራም በጉብኝት፣ በሃይኪንግና በልዩ ልዩ አዝናኝ ጨዋታዎች ታጅቦ ተከናውኗል፡፡
የዚህ መርሃ ግብር ዋና ዓላማ የጅም አባላትን ማህበራዊ አንድነት ማጠናከር፣ የቡድን ስራን ለማጠናከር፣ የስልጠና ተነሳሽነትን ማሳደግ፣ አዕምሯዊና ሰነ-ልቦናዊ ክህሎትን ለማሳደገ እና ስፖርታዊ ክህሎቶችን የአካል ብቃት ስልጠና አካል ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን የፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንስትራክተር ነጻነት ካሣ ገልጸዋል፡፡

ከምግብ በኋላ እንቅስቃሴ መስራት ጠቀሜታ እንዳለው ያውቃሉ?
***
ከምግብ በኋላ የሚሰራው እንቅስቃሴ የድህረ-ምግብ እንቅስቃሴ /Postprandial exercise/ ይባላል፡፡ ይህም እንቅስቃሴ የተለመደው ቀላል-እና-መካከለኛ ጫና ያለው ሲሆን የስርዓተ-ምግብ ልመት (digestion system) ለማሳለጥ፣ በደም ውስጥ የሚገኝ የስኳር መጠንን (blood sugar) ለመቆጣጠር እና አጠቃላይ ጤናን ለማሻሻል ይረዳል፡፡ በተጨማሪም የሰውነት አጠቃላይ አሰራር ስርዓት /Metabolism/ ለማሻሻል፣ ከምግብ በኋላ የትራይግላይሰራይድ /triglyceride/ መጠንን ለመቆጣጠር እና የሰውነት ክብደት መጠንን ለመቆጣጠር ይረዳል፡፡

ይህም ለስኳር በሽታ እና ለተለያዩ የልብና የደም ዝውውር ችግሮች የመጋለጥ ሁኔታን ይከላከላል፡፡ በተለይም የስኳር በሽታ ያለባቸው፣ ውፍረት ያለባቸውና ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች አዘውትረው እንዲሰሩት ይመከራል፡፡

የድህረ-ምግብ እንቅስቃሴ ዓይነቶች
የትንፋሽ፦ እርምጃ (ከ10 እስከ 30 ደቂቃ)፣ ቀለል ያለ ሳይክል
ዮጋ፦ ቀለል ያል
የጥንካሬ ልምምድ፦ ቀለል ያለ (ከ15 እስከ 30 ደቂቃ)

ድህረ-ምግብ እንቅስቃሴ መቸ እና በምን ያህል ጫና የሰራል?
ጊዜ፦ ከምግብ በኋላ ከ10 እስከ 15 ደቂቃ በኋላ እና ከ30 ደቂቃ በፊት ይጀመራል።
ጫና፦ ከቀላል-እስከ-መካከለኛ ጫና መሆን ይኖርበታል።

ማሳሰቢያ፦ ከፍተኛ ጫና ያላቸው እንቅስቃሴዎችን ከምግብ በኋላ ወዲያውኑ መስራት የደም ዝውውርን ከስርዓተ-ልመት (digestion system) እንዲርቅና ስራ-ላይ-ወዳለው-ጡንቻ (working muscle) እንዲሄድ ስለሚያደርገው አለመመቸት ይፈጥራል፡፡ በመሆኑም ከባድ ጫና ያለውን እንቅስቃሴ ከመስራታችን በፊት ቢያንስ 30 ደቂቃ መቆየት አስፈላጊ ነው።

🎉🎉Congratulations on your wedding day bro and best wishes for a happy life together!
🎉❤️የአብርሃምና የሳራ ትዳር ያርግላችሁ::
# Fit corner Adewa gym

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!

መልካም የገና በዓል!

ፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ

የምሽት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በውቧ ፒያሳ ተካሄደ።
ታህሳስ 24/2016 ዓ.ም፤ ፒያሳ፤ አዲስ አበባ
*****
በትናንቱ የረቡዕ ምሽት ከ12:00 ሰዓት ጀምሮ ደማቅ የማህበረሰብ አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ውብ ሁና በተሰራቸው ፒያሳ ተካሂዷል።
ይኽ በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ፊት ለፊት የተከናወነው የምሽት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መርሃ ግብር በኢንስትራክተር ነፃነት ካሳ የተመራ ሲሆን ሌሎች አሰልጣኞችና የአካል ብቃት አሰልጣኞች፣ ሰልጣኞችና ፒያሳ አካባቢ ነዋሪዎች ተሳትፈውበታል።
ህብረተሰቡ ያለምንም ገደብና ያለክፍያ ከፍተኛ ልምድ ባላቸው የአካል ብቃት አሰልጣኞች የታገዘ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ እና ንቁ የአኗኗር ዘይቤ እንዲከተሉ የሚያበረታታ ቋሚ መርሃ ግብር መሆኑ ተገልጿል።
===//====

https://vm.tiktok.com/ZMk6beF4h

አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዝየም ፊትለፊት የምሽት እንቅስቃሴ፤
ታህሳሰ 9/ 2017 ዓ.ም፤
ረቡዕ ምሽት
**
'' ስፖርት ለሁሉም በሁሉም ቦታ''

በውቢቷ ፒያሳ በአድዋ ጂም የሚገኙ የፊት ኮርነር ስፖርት አባላት እና በፒያሳና አከባቢው ያሉ ነዋሪዎች የተሳተፉበት የምሽት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ።

ይህ የምሽት የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም ፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ ከአድዋ ድል መታስቢያና ከአ/አ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በትብብር የተዘጋጀ ነው:: በቀጣይም ማህበራዊ ኃላፊነታችንን ለመውጣት በየአስራ አምስት ቀኑ በነፃ የምሽት አካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ ተወስኖዋል::

===//===
# ፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ
# ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
# አድዋ ድል መታስቢያ

የአካል ብቃት እና የጂም ስልጠናዎችን በሰለጠኑ ባለሞያዎች እንዲሰጡ ለማድረግ የሚያስችል ሁኔታ እየተፈጠረ ነው።
ህዳር 24/2017 ዓ.ም፤ አዳማ
📖📖📖**📰📰
የአካል ብቃት ስልጠና አሰልጣኞችን ለማብቃትና ሳይንሳዊ ስልጠናን የሚተገብሩ ለማድረግ የሚያስችል የአሰልጣኞች ማሰልጠኛ ሰነዶች ዝግጅት እየተከናወነ ነው።

የአካል ብቃት አሰልጣኞች ግልጽና አለም አቀፍ ግብብነት የሚፈጥር የሙያ ደረጃን ጨምሮ ሌሎች አስፈላጊ ሁኔታወችን ለማሟላት የሚያስችል ሁኔታ የሚያማላ መሆኑ ታውቋል።

ይህንን የሙያ ደረጃ ለማዘጋጀት ፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴርና ከስራና ክህሎት ሚናስቴር ጋር በመተባበር በመስራት ላይ ይገኛል።

ለአካል ብቃት አሰልጣኞች ተገቢው የንድፈ ሃሳብና የተግባር ብቃትን ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግና በሳይንሳዊ መንገድ የተፈተሸ የስልጠና ሂደትን ለመተግበር የሚያስችል መሪ ሰነድ ለማዘጋጀት ከፍተኛ ልምድ ያላቸው የዩኒቨርሲቲ መምህራን፣ የአካል ብቃት ኢንስትራክተሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈውበታል።
===//====

ፆም አንድም ለነፍስ፤ አንድም ለስጋ ነው!
**
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፆም በርከት ያሉ ሲሆኑ በዓመት እስክ 252 ቀናት ይደርሳሉ፡፡ እንደሚፆመው ግለሰብ እድሜ፣ ፆታ፣ ሃይማኖታዊ እርከን ወይም ሌላ ሁኔታ በቀን ለሰዓታት ከመፆም ጀምሮ ለቀናት እስከ መፆም ሊደርስ ይችላል። የምግብ ክልከላው ግን ተመሳሳይና ወጥ ነው። ምንም አይነት የእንስሳት ተዋፅዖ መመገብ አይቻልም፤ ተከታታይ የጉልበት (calorie intake) ገደብና የሰዓት ገደብ አለው። ስለዚህ የኦርቶዶክስ ጾም ‘’ረጅም ፆም (intermittent fasting)’’ ብቻ አይደለም። ይህም በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ከሚገኙ አጽዋማት ሁሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ጾም ጥብቅ መሆኑ ይገለጻል፡፡

የሆነው ሁሉ ሁኖ ጾም አንድም ለነፍስ አንድም ለስጋ ይጠቅማል፡፡ ለነፍስ ያለውን ጥቅም ለአባቶች እናቆየውና ሌሎች ጠቀሜታዎች ላይ እናትኩር፡፡

ከመፆም ጠቀሜታዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ:-
ክብደትን (ውፍረትን) ለመቀነስ (ውፍረት ለብዙ በሽታዎች መንስዔ ነው)፣ በደም ውስጥ የሚገኝ የስኳር መጠንን ለመቆጣጠር ( by reducing insulin resistance) ፣ የደም ግፊትን ለመቀነስ፣ ካንሰርን ለመከላከል፣ የልብ ጤናን ለማሻሻል (በተለይም በዕረፍት ጊዜ የልብ-ምት ፍጥነት ዝቅ ለማድረግና ደም የመርጨት አቅም ለመጨመር) ፣ የአዕምሮ ጤናን ለማሻሻል፣ የኒውሮን (neurons) እክልን ለመከላከል፣ የእድገት ሆርሞን (Human Growth hormone /HGH/) መጠን ለመጨመር፣ በሽታ የመከላከል አቅምን ለመጨመር፣ ጉዳት የደረሰበት አካል ለመጠገን (የHGH መጨመር የሚያስገኘው አንዱ ጥቅም ነው)፣ የስብ መጠንን ለመቀነስ፣ የስኳር በሽታን ለመከላከል ወዘተ ... ይጠቅማል።
ለአብነት ያህል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የገና ፆምን መሰረት አድርጎ በተደረገ ጥናት፦ ጿሚዎች ከገና ፆም መጠናቀቅ በኋላ 3.3 ኪ.ግ ክብደት፣  1.09 BMI፣  1.01% የሰውነት ስብ መቀነስ ችለዋል (አለማየሁ እና ቃለአብ ፥ 2023)፡፡
የአካል ብቃት ልመምድ ከማድረግ አንፃር ስንመለከተው የኢ/ኦ/ተዋህዶ አማኞች የፆም ሁኔታ የምግብ ገደብ፣ የሰዓት ገደብና የምናገኘው ጉልበት መጠን ገደብ ተዋህደው ያሉበት በመሆኑ ልምምድን በአግባቡ ማቅድ ያስፈልጋል፡፡

በገና ጾም ወቅት የአካል ብቃት አእንቅስቃሴ ልምምድ ምክረ ሃሳቦች፦
1.  ጫናውን ማስተካከል (ቀላልና መካከለኛ ጫና ያላቸውን እንቅስቃሴዎች መስራት)
2.  ራስን ማዳመጥ (የተለየ አለመመቸት ወይም ህመም ካለ)
3.  ልምምዱን ከጾም ሰዓት ውጭ (ከሰዓት በኋላና ማታ ማድርግ/በተለይም ከበድ ያሉ ተግባራትን)
4.  ለሰውነት ግንባታ (body building) እና የጥንካሬ ተግባራት የሚሰሩ ግለሰቦች ያላቸውን መጠበቅ ላይ ማተኮር (በጾሙ በቂ/ተፈላጊ/የተሟላ ፕሮቲን /complete amino acids/ ስለማይገኝ)
5.  በቂ እረፍት መውሰድ
6.  የልምምድ ስዓትና የልምምድ አይነቶችን ከሰውነት አሰራር ስርዓት ጋር በተገቢው ሁኔታ ማጣጣም ያስፈልጋል፡፡