Последние посты Fit Corner Sport- ፊት ኮርነር ስፖርት (@fitcorner) в Telegram

Посты канала Fit Corner Sport- ፊት ኮርነር ስፖርት

Fit Corner Sport- ፊት ኮርነር ስፖርት
Will provide different Training & Consultancy on fitness & wellness industry.
1,415 подписчиков
1,372 фото
30 видео
Последнее обновление 01.03.2025 03:02

Похожие каналы

Abay Media አባይ ሚዲያ
7,043 подписчиков
Iran Wushu
5,326 подписчиков

Последний контент, опубликованный в Fit Corner Sport- ፊት ኮርነር ስፖርት на Telegram


የአድዋ ድል ሙዚዬም ጉብኝት -
ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም - አዲስ አበባ

**
ገብርየ ቢሞት ተተካ ባልቻ፤
መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ
፡፡” (ኢትዮጵያዊያን)

የፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ ጂም አባላትና ሰራተኞች የአድዋ ድል ሙዚዬምን ጎበኙ፡፡ በፒያሳ እምብርት ላይ የሚገኘው ይህ ሙዚየም የአድዋ ጦርነት ታሪክን ከመነሻው እስከ ፍፃሜው ያሉውን ሂደት በዝርዝር የሚያስቃኝ ነው፡፡ የነገስታቱ አልባሳት፣ ቁሳቁስና የጦር መሳሪያዎች አሁንም ድረስ ከነ ግርማ ሞገሳቸው በሙዚዬሙ ይገኛሉ፡፡ ኢንስትራክተር ነፃነት ካሳን ጨምሮ፣ አሰልጣኞችና ሰልጣኞች በጉብኝቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡

ክብደት መቀነስ ለሚፈልግ ሰው ካርቦሃይድሬት ዋና ጠላቱ ይሆን እንዴ?
🥗🍌🍇🍓🍍🌽🥬🥖🥯🧀🥩🎂🍰
የሰውነት ክብደትን ስለመቆጣጠር ሲወሳ አመጋገብና እንቅስቃሴ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታወች ናቸው። ካርቦሃይድሬትን የሚመለከተው ስጋት የሚመዘዘው ግን ከተፈጥሯዊ ባህሪው ነው። በካርቦሃይድሬት የበለፀገ ምግብ ከተመገብን በኋላ ወዲያውኑ ወደ ግሉኮስ ይቀየራል። ይህም ዋነኛ የጉልበት ምንጭ ነው። ሰውነት ከሚፈልገው በላይ የሆነ ግሉኮስ ካለ ወደ ጉበት (liver) ይወሰድና በግላይኮጅን (glycogen) መልክ ይቀመጣል፤ ቀሪው ደግሞ በኢንሱሊን እርዳታ ወደ ስብ (fatty acid) ይቀየርና በተለያዩ የሰውነት ክፍሎች በስብ መልኩ ይከማቻል። ይህም በሰውነት የስብ መጠን ላይ ቀጥተኛ አስተዋፅዖ አለው። ይሁን እንጂ የሰውነት ክብደት ከመቀነስ አንፃር ስንመለከተው ዋናው ነገር በየዕለቱ ከሁሉም የምግብ አይነቶች የምናገኘው ጉልበት (energy) መጠን መብዛትና ማነስ -  በየቀኑ ከምናወጣው የጉልበት መጠን ጋር ያለው ሚዛን ነው። ለዚህም ነው ሰዎች ''ካርቦሃድሬትን'' ብቻ ነጥለው ''በጠላትነት'' መፈረጃቸው በብዙ ጥናቶች ዘንድ ተቀባይነት የሌለው። የካርቦሃይድሬት ምንጮችን መለየት ግን በጣም አስፈላጊ ነው። የሰውነት ክብደትን ለማስተካከል ጣፋጭ ነገሮችን🍰🍦🍭 በእጅጉ መቀነስ፤ የተፈጥሮ ይዘታቸውን የጠበቁ የእህልና ጥራጥሬ ምርቶችን (አጃ፣ ገብስ፣ ስንዴ፣ ሩዝ...)፣ አትክልትና ፍራፍሬዎችን በተገቢው መንገድ አመጣጥኖ መመገብና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አዘውትሮ መስራት ዋና መፍትሄዎች ናቸው።

👇ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጫን በዩቱብ ከእኛ ጋር ቤተሰብ ይሁኑ! በየጊዜው መረጃ እናቀብልወታለን።
👇👇
ዩቱዩብ: https://youtube.com/@netsisport?si=GY0w80TrUxw12rjU

Baga Ayyaana Irreechaan Nagaan Geessan!

እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሰዎ!
መልካም በዓል!

የቦርጭ መንስዔና መዘዙ!
🎯🎯
ቦርጭ ከእንግሊዝኛው “abdominal obesity” ጋር አቻ ትርጉም ያለው ሲሆን በሆድ አካባቢ ከመጠን በላይ የሆነ ስብ መከማቸት ማለት ነው፡፡ ይህ ከፍተኛ የሆነ የስብ ክምችት በጤና ላይ ውስብስብ ጉዳት አለው፡፡ ምክንያቱም በሆድ አካባቢ ጣፊያ፣ ጉበት፣ ጨጓራ፣ አንጀትና የመሳሰሉት የሰውነት ክፍሎች ስለሚገኙ እና ተፅዕኖ ስለሚያርፍባቸው ነው፡፡
በሃገራችን ኢትዮጵያም 🇪🇹 ቦርጭ ያላቸው ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ጥናቶች አመላክተዋል፡፡ በቅርብ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተደረጉ ጥናቶች መካከል ዝቅተኛ ሁኖ የተገኘው  37.31% ሲሆን ከፍኛው 61.27% የሚሆኑ ተጠኝኞች ቦርጭ ያላቸው መሆኑን ያመላከተ ነበር፡፡ 
የቦርጭ መንስዔዎች:- እንቅስቃሴ አለማድረግ፣🍻አልኮል ማዘውተር፣ ጭንቀት፣ ዘረመል (Genetics)፣ እንቅልፍ ማጣት፣ ማጨስና አመጋገብ ሲሆኑ የሚያስከትለው ዋና ዋና ችግሮች ደግሞ የልብ በሽታ፣ ስኳር (Type II diabetes)፣ ደም ግፊት፣ ካንሰር፣ አስም፣ የጀርባ ህመምና የመሳሰሉት ይጠቀሳሉ፡፡
ቦርጭን ለማጥፋት አይነተኛ መፍትሔዎች አዘውትሮ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መስራትና የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከል ናቸው፡፡

🙋 ለከረባት መደገፊያ እንዲሆን ቦርጭ እንዲኖርዎት ይፈልጋሉ? (ሃሳብዎን በአስተያየት መስጫው ላይ ያካፍሉን)

ከታች ያለውን ''Link'' በመጫን በፌስቡክ፣ በቴልግራም፣ በቲክቶክ፣ በዩቱብና በኢንስታግራም ከእኛ ጋር በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ! በየጊዜው መረጃ እናቀብልወታለን።
https://qrco.de/bfPmrI

ዲጄ ሸዋ ከኢንስትራክተር ነፃነት ጋር! አዝናኝ ቆይታ!

https://youtu.be/owse0No_hdU?si=04GTUUwZEwr743UT

ለምን ቴስቶስቴሮን (testosterone) ይኽን ያህል ተፈላጊ ሆነ?
የተለያዩ ሰዎች የቴስቶስቴሮን ሆርሞን በሚዋጥ (ክኒን💊) ወይም በመርፌ 💉ሲዎስዱ አይተው ያውቃሉ? ይህንን የሚያደርጉት ለምን ይመስልወታል?
ቴስቶስቴሮን የፆታ -ሆርሞን ሲሆን ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ላይ በብዛት ስለሚገኝና የወንዳወንድ ባህርያትን የሚያላብስ በመሆኑ “የወንዶች ሆርሞን” በመባል ይታወቃል፡፡ ወንዶች ጺም፣ ደረት፣ ወፍራም ድምጽ ወዘተ… እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡
ከዚህም ባሻገር በሰውነት ውስጥ በርካታ ተግባራት አሉት፡፡ ዋና ዋናዎቹም የፆታዊ ፍላጎት (libido)፣ የአጥንት መጠንና ጥንካሬ በመጨመር፣ የስብ ክምችት በመቀነስ፣ የጡንቻ መጠንና ጥንካሬ በመጨመር፣ ቀይ-የደም ህዋሳት (red blood cells) እና የዘር ፈሳሽ (sperm) እንዲመረቱ በማድረግ ቁልፍ ሚና አለው፡፡  ይኸው ሆርሞን በሴቶችም ውስጥ የሚገኝ ሲሆን  የአጥንት ጥንካሬያቸውን በመጨመር፣ የእንቁላል (ovary) ምርትን በማስተካከል፣ ጤናማ የፆታዊ ፍላጎት (libido) እንዲኖራቸው በማድረግ ወዘተ… አስተዋጽዖ አለው፡፡
ለዚህም ነው ሰዎች በተለይም የሰውነት ግንባታ የሚሰሩ (body builders) እና የዚህ ሆርሞን መጠን በተለያዩ ችግሮች የቀነሰባቸው ሰዎች ሰው ሰራሽ የቴስቶስቴሮን (Synthetic testosterone)🧪🧪 የሚጠቀሙት፡፡ ነገር ግን በሰው ሰራሽ መንገድ በሰውነት ውስጥ ከልክ በላይ ሲገኝ በርካታ ውስብስብ ችግሮች አሉት፡፡ 
በጤናማ መልኩ የቴስቶስቴሮንን መጠን ለማሳደግ የጥንካሬ እንቅስቃሴዎችን መስራት ዋነኛው ሲሆን የሰውነት ክብደትን ማስተካከል፣ በቂ እንቅልፍ ማግኘት፣ አለማጨስ፣ አልኮል አለማዘውተር (አለማብዛት) በእጅጉ ይረዳሉ፡፡

ከእኛ ጋር በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ!👇
https://qrco.de/bfPmrI

የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እዲሰሩ የሚመከሩት ለምንድን ነው?
🏃🚶‍♂⛹‍♀🚴‍♀🏊‍♂
የስኳር በሽታ (Diabetes Mellitus):- ሥር የሰደደ የሜታቦሊክ በሽታ (metabolic disease) ሲሆን በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ከሚገባው በላይ ከፍ በማለቱ የሚከሰት ነው፡፡ ይህም በጊዜ ሂደት በልብ፣ በደም ሥሮች፣ በአይን፣ በኩላሊት እና በነርቭ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል፡፡ የስኳር በሽታ የሚከሰተው የሰውነት ሕብረ ህዋሳት(Cells) ለኢንሱሊን ምላሽ አለመስጠት ወይም አለመግባባት (type 2) ወይም በሰውነት ውስጥ ኢንሱሊን በበቂ ሁኔታ (ጭራሽ) አለመኖሩ ነው (type 1)፡፡ በጣም የተለመደው የስኳር በሽታ ዓይነት አይነት -2 (type 2) ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ በአለም ላይ 422 ሚሊዮን ሰዎች የስኳር በሽታ ያለባቸው ሲሆን አብዛኛዎቹ ታማሚዎች የሚገኙት ደግሞ በማደግ ላይ ባሉ ሃገራት ነው፡፡ በየአመቱ 1.5 ሚሊዮን ሰዎች በዚሁ በሽታ ምክንያት ይሞታሉ (WHO፡ 2024)፡፡
የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አዘውትሮ መሥራት ታዲያ ለስኳር ታማሚዎች የሚከተሉትን ዋና ዋና ጠቀሜታዎች ያስገኛል፡፡
👉በሰውነት ውስጥ የሚገኝ የስኳር መጠን ይቀንሳል፤
👉በሰውነት ሕብረ-ህዋሳት እና በኢንሱልን መካከል ተግባቦት እንዲፈጠር ያደርጋል፤
👉የHbA1c መጠን ከ7.0% በታች እንዲቀንስ ያደርጋል፤
👉የስኳር በሽታ የሚያመጡ ችግሮችን (ውፍረት፣ ቦርጭ ….) ይቀንሳል፤
👉በበሽታው ምክንያት የሚመጡ የአካላዊ ውስንነቶች (ህመሞች) ይቀንሳል፤
👉የልብና የደም ዝውውር ስርዓትን ያሻሽላል፤

እነዚህን ጠቀሜታዎች ለማግኘት የስኳር ታማሚዎች የትንፋሽ (aerobic)፣ የጥንካሬ (resistance) ወይም በጥምር (aerobic & resistance combined) እቅስቃሴዎችን መስራት ይችላሉ፡፡

“ህብራችን ለአንድነታችንና ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መሪ ቃል በተስፋ ሜዳ ደማቅ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተከናወነ፡፡
ጳጉሜ 04/2016 ዓ.ም
ሳርቤት፤ ተስፋ ሜዳ፤ አዲስ አበባ

🏃🏿‍♀️🌼🌼🏃🏿‍♂️🌼🌼🏃🏿
ፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ ከኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር “ህብራችን ለአንድነታችንና ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መሪ ቃል ሳርቤት በሚገኘው የተስፋ ሜዳ ደማቅ የአካል ብቃት እንቅስቀሴ ተካሄደ፡፡

በዚህ ደማቅ መርሃ ግብር ላይ በም/ፕሬዚደንት ማዕረግ የተከበሩ አቶ አዲሱ አረጋ፣ የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ማቴዎስ ብሩ፣ የፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንስትራክተር ነፃነት ካሣ፣ የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ሰራተኞችና ሌሎች ጥሪ የተደረገለቸው እንግዶች ተሳትፈውበታል፡፡

የተከበሩ አቶ አዲሱ አረጋ ለመላው ኢትዮጵያዊያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን መጭው የ2017 ዓ.ም አንድነታችን የምናጠናክርበት፣ በህብር የምንኖርበትና ሠላማችንን የምናረጋግጥበት ጊዜ እዲሆን ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡

አቶ ማቴዎስ ብሩ በበኩላቸው መላው የኦሮሚያ ሰራተኞች እንደ ሁል ጊዜው ሁሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን አዘውትረው በመስራት ጤናቸውን እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ኢንስትራክተር ነፃነት ካሣ ሁላችንም አዲሱን ዓመት ጤናችንን በአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለመጠበቅ የምንተጋበትና ጤናችንን ጠብቀን በሕብር የምኖርበት ዓመት እዲሆን ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡
🏃🏿‍♀️🏃🏿‍♂️🌼🌼🌼🌼🏃🏿🏃🏿‍♀️
#ፊት ኮርነር ስፖርት አማካሪ
#የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
# ጳጉሜ 4 - የሕብር ቀን

በቅርብ ቀን በኢ.ቢ.ሲ ይጠብቁን!!