Últimas Postagens de FastMereja.net2 (@fastmerejaa) no Telegram

Postagens do Canal FastMereja.net2

FastMereja.net2
FastMereja.net
1,255 Inscritos
69 Fotos
1 Vídeos
Última Atualização 06.03.2025 07:29

Canais Semelhantes

DACKWEB 2+ ODDS
14,724 Inscritos

O conteúdo mais recente compartilhado por FastMereja.net2 no Telegram

FastMereja.net2

06 Mar, 05:59

16

አሜሪካ የታገቱ ሰዎችን በተመለከተ ከሐማስ ጋር ቀጥተኛ ድርድር ማድረጓን ገለፀች
https://www.bbc.com/amharic/articles/cx2g9gwj5qyo

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሃማስ በጋዛ ያገታቸውን እንዲለቅ "የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ" ሰጡ።
ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ማኅበራዊ ድረገጻቸው ላይ በለጠፉት ረዥም ጽሑፍ ላይ "እስራኤል የጀመረችውን ለመጨረስ እንዲያስችላት የሚያስፈልጋትን ሁሉ እየላኩ ነው። እኔ ያልኳችሁን የማታደርጉ ከሆነ አንድም የሃማስ አባል አይተርፍም" ሲሉ ተናግረዋል።
FastMereja.net2

05 Mar, 21:44

49

ቻይና የአየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም ትላልቅ የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶች ማቀዷን ይፋ አደረገች
https://amharic.voanews.com/a/news-china-announces-plans-for-major-renewable-projects-to-tackle-climate-change/7998742.html

ቻይና የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት የሚያስችሏትን ፕሮጀክቶች እንደምታዘጋጅ ዛሬ ረቡዕ አስታውቃለች። ፕሮጀክቶቹ እ.አ.አ ከ2030 አስቀድማ የካርበን ዳይኦክሳይድ በካይ ጋዝ ልቀቷን መጠን በመገደብ በ2060 ደግሞ ከካርበን ልቀት ነፃ የሚያደርጋት መሆኑን አመልክታለች።


ሙቀት አማቂ ጋዞችን በብዛት ወደ አየር በመልቀቅ ከዓለም ቀዳሚ የሆነችው ቻይና፣ በባሕር ዳርቻዎች ላይ አዳዲስ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎችን እንደምታለማ እና በበረሃማ አካባቢዎች "አዳዲስ የኃይል መሠረተልማቶችን" እንደምትገነባ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እቅድ አውጪ ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።


ሪፖርቱ አክሎ "ቻይና የካርበን ልቀትን ለመቀነስ እና በሂደት ሙሉ ለሙሉ ለማቆም በንቃት እና በጥንቃቄ ትሰራለች" ብሏል።


ሆኖም በሀገሪቱ የድንጋይ ከሰል ቁልፍ የኃይል ምንጭ ሆኖ እንደሚቀጥል ያመለከተው ሪፖርቱ፤ የካርበን ልቀትን ለመቀነስ የሚረዱ ቴክኖሎጂዎችን እያቀደች ባለችበት ወቅትም በዚህ ዓመት የድንጋይ ከሰል ምርትና አቅርቦትን ማሳደጓን እንደምትቀጥል ገልጿል። 
FastMereja.net2

05 Mar, 21:43

43

ትረምፕ በምክር ቤት ንግግራቸው የአስተዳደራቸውን የመጀመሪያ እርምጃዎች አወደሱ
https://amharic.voanews.com/a/trump-address-/7998950.html

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ትላንት ማክሰኞ  ምሽት ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤቶች ጣምራ ጉባኤ ባሰሙት ንግግር የፌዴራል መንግሥቱን መጠን እና ተጽዕኖ ለመቀነስ አስተዳደራቸው የወሰዳቸውን ቀዳሚ ርምጃዎች በማድነቅ አውስተዋል፡፡ በአሜሪካ የቅርብ የንግድ አጋሮች ላይ የጣሉትን ከፍተኛ ቀረጥ እና ዩክሬን የሩሲያን ወረራ ለመመከት የገባችውን ጦርነት እንድታቆም  የሚያደርጉትን ግፊት ጨምረው ዘርዝረዋል።


በሥነ ሥርዓቱ ላይ የታደሙ ዲሞክራት የምክር ቤቶቹ አባላት በበኩላቸው ተቃውሟቸውን ግልጽ አድርገዋል።


የአሜሪካ ድምጽ የኋይት ሀውስ ቢሮ ኃላፊ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ  ያደረሰችንን ዘገባ አሉላ ከበደ እንደሚከተለው ያቀርበዋል።
FastMereja.net2

05 Mar, 21:42

35

አሜሪካ ወታደራዊ ርዳታዋን በማቋረጧ አውሮፓ ዩክሬንን ለማስታጠቅ ትችል ይሆን?
https://amharic.voanews.com/a/us-ukraine-aid-cut-impact/7998953.html

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ለዩክሬን የሚሰጠው ወታደራዊ ድጋፍ እንዲቋረጥ ሰኞ ዕለት ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ይህም ሁሉም ወገኖች ወደ ሰላም ንግግር እንዲገቡ ለማስገደድ የታለመ ርምጃ መሆኑን አስተዳደራቸው አስታውቋል።


የቪኦኤው ሄንሪ ሪጅዌል ከለንደን በላከው ዘገባ፣ የአውሮፓ መሪዎች በበኩላቸው ለዩክሬን መሣሪያ መላክ መቀጠሉ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ አስታውቀዋል።  ዩክሬን እስከመቼ ውጊያውን መቀጠል እንደምትችል ግን እርግጠኞች አይደሉም።
FastMereja.net2

05 Mar, 21:41

30

ግብፅ ለትረምፕ የጋዛ እቅድ ያቀረበችውን አማራጭ አቅድ የአረብ መሪዎች መደገፋቸውን አስታወቀች
https://amharic.voanews.com/a/egypt-says-arab-leaders-endorse-counterproposal-to-trump-s-gaza-plan/7998939.html

የአረብ መሪዎች፤ ግብጽ በ53 ቢሊየን ዶላር ወጪ ጋዛን መልሶ ለመገንባት ያቀረበችውን ዕቅድ ትላንት ማክሰኞ  አፅድቀዋል። እቅዱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለግዛቲቱ ካቀረቡት እቅድ በተለየ ፍልስጤማውያን ከአካባቢያቸው እንዳይፈናቀሉ ለማድረግ የሚያስችል ነው።


የግብፅ እቅድ ካይሮ ውስጥ በተካሄደው የመሪዎቹ ጉባዔ የመዝጊያ ስነ ስርዓት ላይ ተቀባይነት ማግኘቱን ፕሬዝደንት አብደል-ፈታህ አል ሲሲ ገልጸዋል።


በግብፅ አስተናጋጅነት በተደረገው ስብሰባ ላይ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ የካታር አሚር እና የሳዑዲ አረብያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተገኝተዋል።


ትረምፕ  ፍልስጤማውያንን ከጋዛ ውጪ አስፍሮ  ሰርጡን መልሶ ለመገንባት ባለፈው ጥር ወር ላቀረቡት እቅድ አማራጭ ሆኖ የቀረበው የግብፅ እቅድ፣ ፍርስራሹ እስኪወገድ እና የተቀበሩ ፈንጂዎች እስከሚወጡ፣ የጋዛ ነዋሪዎች እዚያው ጋዛ ውስጥ በሰባት የተለያዩ ሥፍራዎች   በጊዜያዊ መኖሪያ ቤቶች እንዲቆዩ ይጠይቃል።


በጉባኤው ላይ የግብጹ ፕሬዝደንት ሲሲ ትረምፕ ጋዛን መልሶ ለመገንባት ስላደረጉት ጥረት አመስግነው ግብፅ ያቀረበችው እቅድ ግዛቱን በጊዜያዊነት የሚመራ የአስተዳደር አካልንም ያካተተ መሆኑን አመልክተዋል።


ዩናይትድ ስቴትስ በአሸባሪነት የፈረጀችው ሐማስ እቅዱን የተቀበለው ሲሆን፣ እስራኤል ግን ነቀፌታ ሰንዝራለች። የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፣ የአረብ ሀገራት ጉባኤ ያፀደቀው እቅድ ሐማስ እ.አ.አ በጥቅምት 7፣ 2023 ካደረሰው ጥቃት የተከተለውን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት ውስጥ ያስገባ አይደለም ብሏል። 
FastMereja.net2

05 Mar, 21:40

30

የደቡብ ሱዳን ጦር የምክትል ፕሬዝደንቱን ቤት ከቧል
https://amharic.voanews.com/a/7998843.html

ከደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝደንት ሪክ ማቻር ጋር ጥብቅ ግንኙነት ያለው የታጠቀ ቡድን፤ በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል የሚገኝ የጦር ሠፈር  መውረሩን ተከትሎ፣ የመንግሥቱ ወታደሮች ዛሬ በዋና ከተማዋ ጁባ የሚገኘውን የምክትል ፕሬዝደንቱን መኖሪያ ቤት ከበዋል፡፡ በርካታ አጋሮቻቸው በቁጥጥር ስር ውለዋል።


ማቻር፤ ባለፈው ወር የመንግሥት ባለስልጣን የነበሩ በርካታ አጋሮቻቸው  መባረራቸው እ.አ.አ በ2018 በእሳቸው እና በፖለቲካ ተቀናቃኛቸው ፕሬዝደንት ሳልቫ ኪር መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አደጋ ላይ ይጥላል ብለው ነበር። በሁለቱ ተቀናቃኞች መካከል ለአምስት ዓመታት በተካሄደው የእርስ በእርስ ጦርነት ከ400 ሺህ በላይ ሰዎች ተገድለዋል።


ለማቻር ታማኝ የነበሩት የጦሩ ምክትል አዛዥ ጀነራል ጋብሪኤል ዱፕ ላም በሰሜኑ ግዛት ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘ ትላንት ማክሰኞ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በተመሳሳይ የማቻር አጋሩ  የነዳጅ ዘይት ሚኒስትር  ፑት ካንግ ቾል ከጠባቂዎቻቸው እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር ዛሬ ረቡዕ  በቁጥጥር ስር ውለዋል። የታሰሩበት ምክንያት ግን እስካሁን አልተገለጸም።


የምዕራብ ሀገራት ልዑካን መሪዎቹ ውጥረቱን እንዲያረግቡ ባለፈው ሳምንት አሳስበው ነበር።


ደቡብ ሱዳን እ.አ.አ በ2018 የተደረሰውን ስምምነት እስካሁን ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ ያላደረገች ሲሆን ባለፈው ዓመት ሊካሄድ የነበረው ምርጫም በገንዘብ እጦት ምክንያት ለሁለት ዓመት ተራዝሟል። 
FastMereja.net2

05 Mar, 17:07

52

በኮንጎ ግጭት ምክንያት ጀርመን ለሩዋንዳ የምትሰጠውን አዲስ ርዳታ አቆመች
https://amharic.voanews.com/a/germany-stops-new-aid-to-rwanda-over-dr-congo-conflict/7998693.html

ጀርመን ለሩዋንዳ የምትሰጠውን አዲስ የልማት ርዳታ ማቆሟን እና ቃል የገባቻቸውን ድጋፎችም እየገመገመች መኾኑን ዛሬ ማክሰኞ አስታውቃለች።


ጀርመን ይህን ርምጃ የወሰደችው፣ ሩዋንዳ በጎረቤቷ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚካሄደው ግጭት ውስጥ ላላት ሚና ምላሽ ለመስጠት ነው።


የጀርመን ልማት ምኒስትር ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፣ በርሊን ውሳኔዋን አስቀድማ ለሩዋንዳ ማሳወቋን እና በምስራቅ ኮንጎ የበላይነት እያገኘ ላለው የኤም 23 አማፂ ቡድን የምትሰጠውን ድጋፍ እንድታቆም ማሳሰቧን አመልክተዋል።


ኮንጎ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባለሞያዎች እና የምዕራብ ኃያላን ሀገሮች ሩዋንዳ አማፂውን ቡድን ትደግፋለች በማለት ይከሷታል።


ክሱን የምትቃወመው ሩዋንዳ በበኩሏ በኮንጎ የቱትሲ ተወላጆችን ለመጨፍጨፍ እና ለሩዋንዳ ስጋት ለመፍጠር ከሚንቀሳቀሱ የሁቱ ተወላጅ ታጣቂዎች እራሷን እየተከላከለች እንደሆነ ትገልጻለች።


የሩዋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት የጀርመን ውሳኔ "የተሳሳተ እና አሉታዊ ውጤት ያለው ነው" ሲል ምላሽ ሰጥቷል።


መስሪያ ቤቱ ባወጣው መግለጫ "በቀጠናው በተደጋጋሚ ለሚከሰቱ አለመረጋጋቶች ታሪካዊ ኃላፊነት የተሸከሙ እንደ ጀርመን ያሉ ሀገራት ለአንድ ወገን ያደላ አስገዳጅ ርምጃዎችን ከመተግበር የተሻለ ማወቅ ነበረባቸው" ብሏል።


የጀርመን ምኒስቴር እንደገለፀው በርሊን፣ እ.አ.አ ከጥቅምት 2022 እስከ 2024 ላለው ጊዜ የ98 ሚሊየን ዶላር ርዳታ ለሩዋንዳ ለመስጠት ቃል ገብታ ነበር። 
FastMereja.net2

05 Mar, 15:08

61

ስለ አሜሪካ እና ዩክሬን የማዕድን ድርድር እስካሁን ምን እናውቃለን?
https://www.bbc.com/amharic/articles/cz9nkz4033jo

ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ አገራቸው ከአሜሪካ ጋር ስታደርግ የቆየችውን የማዕድን ድርድር ለመፈረም ዝግጁ መሆናቸውን የተናገሩት በነጩ ቤተመንግሥት በተገኙበት ወቅት ከዶናልድ ትራምፕ እና ምክትላቸው ጄዲ ቫንስ ጋር የጋለ ክርክር ውስጥ በመግባታቸው እንዲወጡ ከተደረገ ከቀናት በኋላ ነው።
FastMereja.net2

05 Mar, 15:07

60

የጉራጌን 'የክልልነት ጥያቄ' በማቀንቀን የሚታወቁት አቶ ታረቀኝ ከአንድ ዓመት እስር በኋላ ተፈቱ
https://www.bbc.com/amharic/articles/cn8r1mvlgv4o

በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳን ወክለው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ታረቀኝ ደግፌ፤ ከአንድ ዓመት ከሁለት ወር እስር በኋላ ከትናንት በስቲያ ሰኞ ከእስር ተፈቱ።
FastMereja.net2

05 Mar, 11:32

75

ህንዳዊቷ የቤት ሰራተኛ በአቡዳቢ ህጻን በመግደል ወንጀል በሞት ተቀጣች
https://www.bbc.com/amharic/articles/ckg1j04y49yo

ህንዳዊቷ የቤት ሰራተኛ የአሰሪዎቿን ህጻን ልጅ ገድለሻል በሚል ወንጀል ተከሳ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መዲና አቡዳቢ በሞት ተቀጣች።