Últimas Postagens de FastMereja.net2 (@fastmerejaa) no Telegram

Postagens do Canal FastMereja.net2

FastMereja.net2
FastMereja.net
1,255 Inscritos
69 Fotos
1 Vídeos
Última Atualização 06.03.2025 07:29

O conteúdo mais recente compartilhado por FastMereja.net2 no Telegram

FastMereja.net2

05 Mar, 08:18

84

ትረምፕ "አሜሪካ ተመልሳለች" አሉ
https://amharic.voanews.com/a/7998310.html

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ማክሰኞ ምሽት በአሜሪካ የሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ያደረጉትንን ንግግር "አሜሪካ ተመልሳለች" በማለት የጀመሩት ሲኾን፣ የሪፐብሊካን ሕግ አውጪዎች "ዩ ኤስ ኤ" በሚል ዝማሬ አጅበዋቸዋል።


"ከስድስት ሳምንት በፊት እዚህ ቆሜ የአሜሪካን ወርቃማ ዘመን ዐውጄ" ነበር ያሉት ትራምፕ ከዚያን ጊዜ ወዲህ በሀገራችን ታሪክ ውስጥ ታላቅ እና ስኬታማ ዘመን ለማምጣት ፈጣን እና የማያቋርጥ ተግባራት ተከናውነዋል" ብለዋል።


"አስተዳደራቸው በ43 ቀናት ውስጥ ብቻ ሌሎች ብዙ አስተዳደሮች በአራት እና ስምንት ዓመታት ውስጥ ካከናወኗቸው የበለጠ መሠራቱን" የገለጹት ትረምፕ "ገና እየጀመርን ነው" ብለዋል።


ትረምፕ እስካሁን 76 የፕሬዝደንት ማዘዣዎችን የፈረሙ ሲሆን አብዛኞቹ በፍርድቤት ክስ ተመስርቶባቸዋል።


ትረምፕ ንግግራቸውን ከጀመሩ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ በምክር ቤቱ አዳራሽ ከተሰበሰቡ ሰዎች በተሰማ የስላቅ ድምፅ ንግግራቸው በመስተጓጎሉ የተወካዮች ምክርቤቱ አፈ-ጉባኤ ማይክ ጆንሰን የምክርቤቱ ሥነ ስርዐት አስከባሪዎች፣ በቴክሳስ ዲሞክራት ፓርቲን ወክለው ለምክርቤት አባልነት የተመረጡትን አል ግሪን ከምክርቤቱ እንዲያስወጧቸው አዘዋል። ሌሎች የምክር ቤቱ አባላትም ሥነ-ስርዐት እንዲከተሉ አሳስበዋል።




ግሪን ከምክርቤቱ አዳራሽ ከወጡ በኋላ ትረምፕ ንግግራቸውን ቀጥለዋል። ተረምፕ በዚኹ የማክሰኞ ምሽት ንግግራቸው "የመጀመሪያው ወር የፕሬዝደንትነት ዘመኔ፣ በሀገራችን ታሪክ እጅግ ስኬታማው መሆኑን ብዙዎች ገልጸውታል" ያሉት ትራምፕ፣ በድንበር በኩል የሚፈፀም ሕገወጥ ሽግግርን ለማስቆም የወሰዱትን ርምጃም አብራርተዋል።


"በሀገራችን ላይ የሚፈፀመውን ወረራ ለመመከት" በደቡባዊ ድንበር ላይ ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ማወጃቸውን እና የዩናይትድ ስቴትስ ጦር በድንበር ላይ እንዲሰፍ ማድረጋቸውንም ገልጸዋል። በዚህም ምክንያት "ባለፈው ወር በሕገወጥ መንገድ ድንበር አያርጠው የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር እስከዛሬ ከተመዘገበው ዝቅተኛ ነው" ብለዋል።


በተጨማሪም ወደ ዋይት ሐውስ እንደተመለሱ የፌደራል ቅጥር ሂደቶች እና የውጭ ርዳታዎች ላይ እግድ መጣላቸውን ገልጸዋል። የፌደራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ቁጥር እና ሠራተኞችን ለመቀነስ፣ በምፅሃረ ቃሉ 'ዶጅ' በመባል የሚጠራ በኢላን መስክ የሚመራ ተቋም መመስረታቸውን የተናገሩት ትረምፕ በቢሊየኖች የሚቆጠር የመንግሥት ገንዘብ እያዳነ መሆኑንም አመልክተዋል።


ትረምፕ በንግግራቸው በዩናይትድ ስቴትስ በ48 ዓመት ውስጥ ያልታየውን የዋጋ ግሽበት ለማስተካከል ከወሰዷቸው ርምጃዎች መካከል "ወርቃማ ፈሳሽ" ሲሉ የጠሩትን የነዳጅ ጋዝ ቁፋሮ እያካሄዱ መሆኑን ተናግረዋል። "የወሳኝ እና ብርቅዬ ማዕድናት" ምርት እንደሚፋጠንም ገልጸዋል።


"ቀጣዩ የግብር ቅነሳ ነው" ያሉት ትራምፕ፣ ከገቢ ግብር፣ ከቲፕ ገንዘብ እና ከትርፍ ሰዓት ክፍያ ላይ ግብር እንደሚያነሱም ተናግረዋል።




ትረምፕ አክለው አሜሪካን "ኢ-ፍትሃዊ" ሲሉ ከገለጹት የፓሪስ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት፣ "ሙሰኛ" ካሉት የዓለም ጤና ድርጅት እና "ፀረ-አሜሪካዊ" ሲሉ ከገለፁት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ማስወጣታቸውን አብራርተዋል።


የፕሬዝደንት በዓለ ሲመት ባልተካሄደባቸው ዓመታት "ዘ ስቴት ኦፍ ዘ ዩኒየን" በመባል የሚጠራው እና የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች ለጋራ ምክርቤቱ የአሜሪካን አኹናዊ ሁኔታ በሚያብራሩበት በዚህ ንግግር፤ ትራምፕ ለዩናይትድ ስቴትስ ኢኮኖሚ እና ኢሚግሬሽን ፖሊሲ ያላቸውን ርዕይ ለሕዝብ የሚያቀርቡበት እና የፌደራል ሠራተኞችን ቅነሳ እና ከዩክሬን ፕሬዝደንት ጋራ የነበራቸውን እሰጥ አገባ አስመልክቶ የሚያብራሩበት ዕድል ፈጥሮላቸዋል።


ትረምፕ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮለድሚር ዜለንስኪ ጋራ ያደረጉትን ኃይለቃል የተሞላበት ውይይት ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የምትሰጠውን ወታደራዊ ርዳታ አቋርጣለች።


"አውሮፓውያን ዩክሬንን ከመደገፍ ይልቅ ከሩስያ ለሚገዙት ነዳጅ እና ዘይት የበለጠ አውጥተዋል" ያሉት ትራምፕ የዩክሬን ፕሬዝደንት ለሰላም ዝግጁ መሆናቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ እንደፃፉላቸው አመልክተዋል።


ትረምፕ አክለው "በተመሳሳይ ጊዜ ከሩሲያ ጋራ ጠንከር ያለ ውይይት አድርገን ለሰላም ዝግጁ መኾናቸውን የሚያሳይ ምልክቶች አግኝተናል" ብለዋል።
FastMereja.net2

05 Mar, 08:08

66

በቱኒዝያ የባህር ዳርቻ በነዳጅ ማቀነባባሪያ ለበርካታ ቀናት ያለ እርዳታ የቀሩ ስደተኞች ተገኙ
https://www.bbc.com/amharic/articles/cj92vpwveneo

ሜዲትራኒያን ባሕርን ለመሻገር የሞከሩ ኢትዮጵያዊያን አሊያም ኤርትራዊያንን ጨምሮ 32 ፍልሰተኞች በቱኒዚያ የባህር ዳርቻ ለበርካታ ቀናት ያለ እርዳታ ከቆዩ በኋላ በረድኤት ድርጅት ሕይወታቸው ታደገ።
FastMereja.net2

05 Mar, 08:07

71

ትራምፕ "በህገ ወጥ ተቃውሞ" የሚሳተፉ የውጭ አገራት ተማሪዎችን ከአገር እንደሚያባርሩ ተናገሩ
https://www.bbc.com/amharic/articles/crmjvpw74myo

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ህገወጥ" ሲሉ በጠሯቸው ተቃውሞዎች የሚሳተፉ የውጭ አገራት ተማሪዎችን ለህግ እንደሚያቀርቡ እና ከአገር እንደሚያባርሩ አስጠነቀቁ።
FastMereja.net2

05 Mar, 08:06

69

የአረብ መሪዎች ጋዛን መልሶ ለመገንባት 53 ቢሊዮን ዶላር አማራጭ እቅድ አፀደቁ
https://www.bbc.com/amharic/articles/cp3yl8pyq84o

የአረብ አገር መሪዎች "ጋዛን በመውሰድ" እና ሁለት ሚሊዮን ፍልስጤማዊያንን የሚያፈናቅለውን የፕሬዝዳንት ትራምፕ ሀሳብ የሚቀናቀን የ53 ቢሊዮን ዶላር የመልሶ ግንባታ እቅድ ግብፅ ካይሮ ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ አፅድቀዋል።
FastMereja.net2

05 Mar, 08:05

67

ዜሌንስኪ በፕሬዚዳንት ትራምፕ "ጠንካራ አመራር" ስር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናገሩ
https://www.bbc.com/amharic/articles/cedlge6en66o

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ በአገራቸው ዘላቂ ሰላም ለማምጣት በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ጠንካራ አመራር" ስር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን ተናገሩ።
FastMereja.net2

04 Mar, 23:52

79

ትረምፕ የጣሉትን ቀረጥ ተከትሎ ሜክሲኮ፡ ካናዳ እና ቻይና የአጸፋ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ አስጠነቀቁ
https://amharic.voanews.com/a/trump-tariffs/7997679.html

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትረምፕ ወደ አሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ አዲስ ቀረጥ መጣላቸውን ተከትሎ ካናዳ፣ ሜክሲኮ እና ቻይናም በየበኩላቸው የአጸፋ እርምጃ እንወስዳለን ሲሉ አስጠነቀቁ።


ዩናይትድ ስቴትስ ሁለቱ ዋና ዋና የንግድ ሸሪኮቿ ሜክሲኮ እና ካናዳ በሚልኳቸው ምርቶች ላይ የጣለችው አዲስ የ25 በመቶ ቀረጥ ዛሬ ተግባራዊ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ዛሬ የሚጀምረው እና  በቻይና ምርቶች ላይ የጣለችውን ቀደም ሲል 10 በመቶ የነበረውን ተጨማሪ ቀረጥ በእጥፍ አሳድጋው 20 በመቶ ማስገባቷ ታውቋል።


ትረምፕ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ የሚፈልሱትን ሕገ-ወጥ ስደተኞች እና ድንበር ተሻግሮ የሚጓጓዘውን ሕገ ወጥ እና አደገኛ መድሃኒት ዝውውር እንዲያግዱ የጠየቋቸው ሁለቱ የዩናይትድ ስቴትስ የቅርብ ጎረቤቶች ሜክሲኮ እና ካናዳ የተባለውን ማድረጋቸውን ይፋ ካደረጉም በኋላ አዲሱን ቀረጥ ጥለውባቸዋል።


ትረምፕ በትላንትናው ዕለት ይህንኑ ማስታወቃቸውን ተከትሎም ሦስቱ የዩናይትድ ስቴትስ ዋና ዋና የአክሲዮን ገበያዎች ከፍተኛ ውድቀት ሲያስመዘግቡ፤ ዛሬ ማለዳ በአክሲዮን ገበያዎቹ መክፈቻ ላይም እያንዳንዳችው በ2 በመቶ አዘቅዝቀው ታይተዋል።


ከሦስቱ ሀገራት በሚገቡ ምርቶች ላይ በጣሉት ከፍተኛ የቀረጥ ጭማሪ የተነሳ አሜሪካውያን ሸማቾች እና የንግድ ድርጅቶች አንዳንድ ጊዜያዊ የኢኮኖሚ ፈተና ሊገጥማቸው ይችላል’ ያሉት ትረምፕ "ነገር ግን በሦስቱ አገሮች ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ኩባንያዎች የቀረጥ ክፍያውን ለማስቀረት ሲሉ ፋብሪካዎቻቸው ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ለማዘዋወር ይገደዳሉ" ሲሉ  ተናግረል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ  ትረምፕ ለወሰዱት የቀረጥ ጭማሪ አገራቸው አፀፋ እንደምትሰጥ የተናገሩት የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሩዶ "ይህ ፍትሃዊነት የጎደለው እርምጃ በዋዛ አይታለፍም”ብለዋል። አክለውም አገራቸው 107 ቢሊዮን ዶላር በሚገመቱ የአሜሪካ ምርቶች ላይ የ25 በመቶ ቀረጥ የምትጥል መሆኗን ተናግረዋል።
FastMereja.net2

04 Mar, 23:51

72

እስራኤል ዕርዳታ ወደ ጋዛ እንዳይገባ በማገዷ የረድኤት ድርጅቶች ስጋት ገብቷቸዋል
https://amharic.voanews.com/a/humanitarians-fearful-for-gaza-as-israel-halts-aid-deliveries/7997670.html

እስራኤል ከውሃ በስተቀር ማንኛውም የሰብአዊ ዕርዳታ ወደ ጋዛ ሰርጥ እንዳይገባ ማገዷ፣ ወትሮውንም በሕይወት ለመቆየት ትግል ላይ ባሉት ሕፃናትና ቤተሰቦቻቸው ላይ አደገኛ ሁኔታ ሊፈጥር እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት  የሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) አስታውቋል።


“ትላንት በዕርዳታ ላይ የተጣለው እገዳ የሲቪሎችን ሕይወት ለመታደግ በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል” ሲሉ የቀጠናው የዩኒሴፍ ኅላፊ ኤድዋርድ ቤግበደር አስታውቀዋል።


የሕፃናትን ደህንነት ለመጠበቅ ወሳኝ የሆነው የተኩስ አቁም መቀጠሉ አስፈላጊ እንደሆነም ኅላፊው ጨምረው ተናግረዋል።


በመካከለኛው ምሥራቅ የአሜሪካ ልዑክ የሆኑት ስቲቨን ዊትኮፍ ተኩስ አቁሙ እስከ እ.አ.አ ሚያዚያ 20 ድረስ እንዲራዘም መጠየቃቸውን ያወሱት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ ይህም የረመዳን ወር እና የአይሁድ በዓላትን የሚሸፍን ሲሆን፣ በዚህ ወቅት በመጀመሪያው ቀን ሃማስ ግማሽ የሚሆኑ ታጋቾችን እንደሚለቅ፣ በመቀጠል ቋሚ የተኩስ ማቆም ሲፈጸም ደግሞ የተቀሩትን ታጋቾች እንደሚለቅ ተናግረዋል።


“ይህን ሃሳብ እቀበላለሁ፣ ሃማስ ግን እስከ አሁን እየተቃወመው ነው” ሲሉ አክለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።


እስራኤል ዕርዳታ እንዳይገባ ያገደችው ሃማስ ዕርዳታውን በመስረቁ እና ፍልስጤማውያን እንዳያገኙት በማድረጉ እንደሆነም ኔታንያሁ አስታውቀዋል። “ዕርዳታውን ለሽብር ተግባር እየተጠቀመብት ነው” ሲሉም ክስ አሰምተዋል። የተመድ ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪክ ኔታንያሁ የጠቀሱት ጉዳይ ስለመከሰቱ በሥፍራው የሚገኙ ባልደረቦቻቸው ሪፖርት እንዳላደርጉ አስታውቀዋል።
FastMereja.net2

04 Mar, 20:22

76

የስድስት ዓመት ፍልስጤም - አሜሪካዊ ሕፃን የገደለው ግለሰብ ጥፋተኛ ተባለ
https://amharic.voanews.com/a/illinois-muslim-american-verdict-reaction/7997406.html

በዩናይትድ ስቴትስ፣ ኤሊኖይ ግዛት የሚኖሩ ሙስሊም አሜሪካውያን የቅዱስ ረመዳንን የጾም ወር በጀመሩበት ወቅት፣ የስድስት ዓመቱን የፍልስጤም ተወላጅ አሜሪካዊ በመግደል በተከሰሱት ግለሰብ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ተላልፏል።


የአሜሪካ ድምጿ ኬን ፋራቦው በዚህ ዙሪያ ያደረሰንን ዘገባ፣ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።  
FastMereja.net2

04 Mar, 20:21

70

አሜሪካ ለዩክሬን የምትሰጠውን ወታደራዊ ርዳታ አቋረጠች
https://amharic.voanews.com/a/7997407.html

አውሮፓ በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማስቆም የሚደረገውን ጥረት ለመምራት በመጣደፍ ላይ ስትሆን፣ የአሜሪካው ፕሬዝደንት በበኩላቸው  ለዩክሬን የሚሰጠውን ማንኛውንም ወታደራዊ ርዳታ ትላንት ሰኞ እንዲቋረጥ አድርገዋል። ርምጃው የመጣው ትረምፕና ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ባለፈው ዐርብ በዋይት ሐውስ ውይይት ባደረጉበት ወቅት፣ ትረምፕ ዜለንስኪን ጠንከር አድርገው መወረፋቸውን ተከትሎ ነው። መላው ዓለምም በዩክሬን ባለው ግጭትና በዋይት ሃውስ በተከሰተው ጉዳይ ላይ ትኩረቱን አድርጎ ነበር።


የቪኦኤ የዋይት ሐውስ ዘጋቢ አኒታ ፓወል ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
FastMereja.net2

04 Mar, 20:20

59

 ኬንያ ውስጥ በስደተኞች የምግብ ዕደላ ወቅት በተቀሰቀሰ ግጭት ተረጂዎች ተጎዱ
https://amharic.voanews.com/a/refugees-injured-in-clashes-with-kenyan-police-during-food-ration-protests/7997332.html

ሰሜን ኬንያ በሚገኘው ካኩማ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ በተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት ፖሊስ በወሰደው ርምጃ አራት ሰዎች መቁሰላቸው ተገለጸ።


በትላንቱ የምግብ ዕደላ ላይ የተቀሰቀሰው ግጭት ለስደተኛው ከሚሰጠው የምግብ ርዳታ እጥረት ጋራ የተያያዘ መኾኑም ተመልክቷል።


ከኬንያ አጎራባቾች ደቡብ ሱዳን፣ ኢትዮጵያ፣ ቡሩንዲ እና ኮንጎ ግጭቶችን በመሸሽ እና በድርቅ ሳቢያ የሚሰደዱ ወገኖችን በሚያስጠልለው ካምፕ ውስጥ ለሚገኙት በብዙ ሺሕዎች የሚገመቱ ስደተኞች ይሰጥ የነበረው የምግብ አቅርቦት፤ በተፈጠረው የርዳታ ገንዘብ እጥረት የተነሳ የወትሮ አሠራሩ መስተጓጎሉ ተዘግቧል።


በካምፑ ለስደተኞች የሚሰጠውን ምግብ የሚያከፋፍለው የዓለም የምግብ ፕሮግራም ባለፈው ታኅሣሥ ወር ለስደተኞች ከሚሰጠው ምግብ "በገጠመው የአቅርቦት እጥረት የተነሳ ከሚያስፈልገው ከ45 በመቶ በታች እንደነበር አመልክቷል።


የዓለም የምግብ ፕሮግራም ከለጋሽ አገሮች መንግሥታት ያገኝ የነበረው መዋጮ እጥረት እንደሚገጥመው ለዓመታት ሲያሳስብ መቆየቱ ይታወቃል።