Neueste Beiträge von ☝️ፈፊሩ ኢለላሂ☝️ "ወደ አላህም ሽሹ"🇪🇭 (@fafiru_illahi) auf Telegram

☝️ፈፊሩ ኢለላሂ☝️ "ወደ አላህም ሽሹ"🇪🇭 Telegram-Beiträge

☝️ፈፊሩ ኢለላሂ☝️ "ወደ አላህም ሽሹ"🇪🇭
1,893 Abonnenten
599 Fotos
33 Videos
Zuletzt aktualisiert 06.03.2025 09:34

Der neueste Inhalt, der von ☝️ፈፊሩ ኢለላሂ☝️ "ወደ አላህም ሽሹ"🇪🇭 auf Telegram geteilt wurde.

☝️ፈፊሩ ኢለላሂ☝️ "ወደ አላህም ሽሹ"🇪🇭

28 Feb, 11:49

200

ዛሬ ሻዕባን 29-1446 ሂጅሪ ነው።

ቴሌስኮፖዋች ተወልውለው እየተገጠሙ ነው !! ዛሬ ከዐስር በኃላ አይኖች ሁሉ ጨረቃን በፍቅር እና በናፍቆት ጥበቃ ይማትራሉ።
ውድ እና የረቀቁ ቴሌስኮፖች ተገጣጥመው ሰአቱን እየጠበቁ ሲሆን ጨረቃ ዛሬ ከታየች ማታ ተራዊህ ይሰገድና ነገ ረመዳንን ፆም የምንጀምር ሲሆን ካልታየች ደግሞ ኢንሻ አላህ ነገ ቅዳሜ ማታ ተራዊህ እንጀምራለን። ፆማችንም እሁድ ይሆናል ኢንሻአ አላህ ።

@fafiru_illahi
@fafiru_illahi
☝️ፈፊሩ ኢለላሂ☝️ "ወደ አላህም ሽሹ"🇪🇭

27 Feb, 19:16

165

ነገ አላህ ካለ የረመዷን ጨረቃ ምርመራ ይደረጋል ... አላህ ካለም ነገ ሊሆን ይችላል...እና...

አላህ በሰላም አድርሶ ከሚፆሙት ያድርገን!

@fafiru_illahi
@fafiru_illahi
☝️ፈፊሩ ኢለላሂ☝️ "ወደ አላህም ሽሹ"🇪🇭

26 Feb, 06:37

224

ከሁሉም ሙስሊም ቤት የሚዘልቀውን እንግዳ ለመቀበል ሰው ሁላ ሽርጉድ ይላል። እኛም ቤት የተለየ ነገር አልተፈጠረም። በግ፣ ተምር፣ ለሚጠባበሱ ምግቦች ዱቄት የመሳሰሉትን ፣ ለቤቱ ፍካት መጋረጃ መቀየር፣ የትራስ ልብስ ማሰፋት… ኢድ ነገ የሚሆን ይመስል ሁሉም ቦታ አዲስ ድባብ ይፈጠራል። ይህን ድባብ ከሌለ ረመዷኑ ረመዷን አይመስለንም፣ ከቤታችን የምናስፈጥረው እንግዳ ከሌለን ረመዷን አይመስለንም፣ ፊጥራ ላይ ሾርባ፣ አሳንቡሳ፣ ቡስኩትና ሌሎች ብዙ አይነት ምግቦች ካልቀረቡ ሸህሩ ራህማ የደረሰ አይመስለንም፣ እኔም ጭምር አይመስለኝም #ነበር… አዎ ነበር! አሁን ረመዷን ለኔ ይህ አይደለም። ይህን ሀሳብ ያስቀየረኝ የአንድ ሰው ንግግር ነው። ኡስታዝ ሙሀመድ ሆብሎስ… ማንኛውም ሰው እንደሚያደርገው ለረመዷን የምቀይረው የስልክ ጥሪ ነሽዳ በመፈለግ ላይ በስህተት የተከፈተ ቪድዮ ላይ፣ ስለ ረመዷን አጿጿማችን ነበር ስሜታዊ ሁኖ የሚናገረው። ሰላምታና በነብያችን ﷺ ላይ ሰለዋት አውርዶ የሚከተለውን ተናገረ።

< አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ከሁሉም በጣም አዛኙ፣ ሀያሉ፣ ረዛቁ… ጌታ ነው። እኛ ነን እዝነቱን ሽሽት የምንሄደው፤ ምህረቱን ችላ ብለን የምንኖረው፣ እኛ ነን ምርጫ ተሰጥቶን ስህተት የሆነውን ምንገድ በምርጫችን የምንከተለው። ነብያት፣ መፅሀፍን አውርዶልና መመሪያ ይሆነን ዘንድ እኛ ችላ ብለን የተውነው። እርሱ ግን የተውበት በሮችን ክፍት አድርጎ እኛን በመጠበቅ ላይ ነው። መጪው ቀን ጥሩ እድልን ያመቻችልናል። ሱሀቦች ረመዷን በተቃረበ ጊዜ በጣም በጉጉት ይጠብቁ ነበር። ይህ ወር ዘንግተነው የኖርነውን ዲን ለማስታወስ፣ የደረቀ ልባችንን ለማርጠብ፣ ያመጸ ነፍሲያችንን ለማስተካከል የሚመጣ እዝነት የሚወርድበት የአመቱ ልዩ ወር ነው። የፆመ ሰው ሁለት ዒዶች ይኖሩታል። የመጀመሪያው ኢድ ቤተሰቦቹ ጋ ሁኖ የሚያከብረው ሲሆን የሁለተኛው ግን አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ፊት ቁሞ የስራውን ውጤት(ሽልማት) ሲመለከት ነው። ታዳ ይህን ወር ሌላውን ወር እንደምናሳልፈው ማሳለፍ ትፈልጋላችሁን? ረመዷን የቁርአን፣ የሰደቃ፣ የተሀጁድ፣ የተራዊህ፣ የዱኣ፣ የኢዕቲካፍ ወር ነው። በረመዷን ከዱንያ በቻልነው ርቀን ወደ አላህ የምንቃረብበት ወር ነው። ነገር ግን አሁን ረመዷንን የበዓል ወር ካደረግነው ቆይተናል። የኢባዳውን ወር የመተኛ ፣ የፆሙን ወር ምግብ የሚደፋበት፣ ተሀጁድ የመስገጃውን ወርን ሌሊቱን የአመፅ አድርገነዋል። ለዚህ ነው ናፍቆናል የምንለው?
የጀነት በሮች ክፍት ሁነው በተዘጋጁልን ወቅት፣ የጀሀነም በሮች በተዘጉበት፣ ሸያጢኖች በታሰሩበት በዚህ ግዜ ወደ አላህ ካልተጠጋን መች ነው የምንጠጋው? ለኢፍጣር ቤተሰብ ጋ መሰባሰብ ደስ ይለናል፣ ፊጥራ ስንገባበዝ ደስ ይለናል፣ መጥፎ ነው እያልኩ አይደለም። ነገር ግን በዛን ወቅት ማነው መግሪብን መስጂድ ጀመዓ ለመስገድ የሚያስበው! ማነው ስለ ኢሻና ተራዊህ የሚጨነቀው? ለአስራ አንዱ ወር ያልተውነውን ለረመዷን ኢፍጣር ሲባል እንተዋለን! አንብያ፣ ሶሀቦች፣ ሰለፎች ሂወታቸውን ሰጥተው ለኛ ያስተላለፉትን ዲን ሌላው ቀርቶ ረመዷንን እንኳን እንዴት እንደምፆመው ቢያዩ ምን ይሉንስ ነበር? ወንዶሞቼ ይህ ነው እድላችን ከጀሀነም እሳት ነጃ የምንወጣበት።

ብዙዎቻችን ዘንድ የኢድ ጣዕሙ ጠፍቷል። ኢድ ላይ ያለን ጉጉት ጠፍቷል። ለምን ይመስላችኋል? ረመዷኑን ሙሉ በየአይነት ምግብ ስንበላ፣ ቤተሰብ ጋ ስንገባበዝ ስንዘያየር፣ እቃ ስንቀያይር ውለን ምኑ አዲስ ሁኖብን ኢድ ብርቅ ይሆንብናል? ውድ ሙስሊም ወንድምና እህቶቼ ወሩ የፆም ነው፣ ወሩ የኢባዳ ነው፣ ወሩ ያንተ፣ ያንቺ ነው። ፈተና በምትሆኑበት ጊዜ ቀናችሁን በፕሮግራም መድባችሁ ሰአት እንዳታባክኑ እንደምትጠነቀቁት ሁሉ የረመዷንንም ወር ተጠቅማችሁበት ይለፍ። አምና ያባከነው ረመዷን ቁጭቱ ይሰማን፣ ለኸይር እንሽቀዳደም ይህ እድል ዳግም ላይመለስ ይችላልና… ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ>
ይህን ደዕዋ ከሰማሁ በኋላ ነሺዳውን መፈለግ ትቼ እንዴት እቅድ ማውጣት እንዳለብኝ ፕሮግራም አወጣሁ። ኢንሻአላህ ቀኑ ተቃርቦ አንድ ብዬ ልጀምር ተቃርቢያለሁ። አላህ በትክክል የምሰራበት ወር ያድርግልኝ!
:
ስንት ረመዷን አባክነናል? ከቡሉግ በኋላ ስንተ ረመዷን ፁመናል? 3፣5 ፣10፣15 ስንት? ስንት ረመዷን ፁመን ሳንፆም አባክነናል? ስንት? አሁንም አንድ እንኳን የሳራንበት ረመዷን እንዲኖር አትፈልጉምን? አሁንም ምሽቱን በፊልም፣ ቀኑን በእንቅልፍ፣ ሌሊቱን በመብላት ብቻ አሳልፈነው እንዲያልቅ ትመኛላችሁን? ኑ በእድሜያችን ቢያንስ አንድ ጊዜ እንኳ በትክክል የፆምነው ረመዳን ይኑረን! ኑ አጅሩን በአግባቡ እንጠቀም! ኑ የእዝነቱን ወር ወደ አዛኙ እንቃረብነት!
<(እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ) ያ በርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድና (እውነትን ከውሸት) ከሚለዩም ገላጮች (አንቀጾች) ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡>
(2:185)

@fafiru_illahi
@fafiru_illahi
☝️ፈፊሩ ኢለላሂ☝️ "ወደ አላህም ሽሹ"🇪🇭

26 Feb, 05:11

172

• አላህ .. የሰዎች ብሶት አዳማጭ፣ ችግራቸዉን ፈች፣ ለመከራቸው ደራሽ፣ ዕዳቸዉን ከፋይ፣ ጭንቀታቸዉን ተጋሪ፣ ህመማቸዉን ታማሚ፣ ሐዘናቸዉ ተካፋይ፣  ...ያደረገህ እንደሆን በርግጥም የወደደ ስለመሆኑ ምልክት ነው። በዚህ ሁኔታህ ላይ የኖርክ እንደሆነ ከፍ እንዳልክ ትኖራለህ ይላሉ ኢማም ኢብኑል ቀይም።
@fafiru_illahi
☝️ፈፊሩ ኢለላሂ☝️ "ወደ አላህም ሽሹ"🇪🇭

25 Feb, 17:33

207

💛ቁምነገር አዘል የሆነች ምርጥ ኢስላሚክ ቻናል ተጋበዙልኝ 🤗

🕌ወላሂ ሀቂቃ ማስታወቂያ ነው🕌
☝️ፈፊሩ ኢለላሂ☝️ "ወደ አላህም ሽሹ"🇪🇭

25 Feb, 12:51

18

♻️የቁርዐኑ ወር ረመዷን ስንት ቀን እንደቀረው ያውቃሉ

🌕ስለረመዳን ብቻ የሚዘገብበትና በሳምንት ውስጥ 1⃣ ሺ ተከታይ ያፈራውና የተወደደውን ቻናል ተጋበዙልኝ

🌟ወላሂ ሐቂቃ ማስታወቂያ ነው🌟
☝️ፈፊሩ ኢለላሂ☝️ "ወደ አላህም ሽሹ"🇪🇭

25 Feb, 10:55

22

👳‍♂🧕ሙስሊሞች ከነዚህ መካከል የቱን ትፈልጋላችሁ


ŵανєя:::➡️@Waver_boy1
☝️ፈፊሩ ኢለላሂ☝️ "ወደ አላህም ሽሹ"🇪🇭

25 Feb, 06:19

180

አንድ ፈተና ቢደርስብኝ አራት ጊዜ አመሰግናለሁ : -
አንድ ከዚህ የባሰ ፈተና ስላልፈተነኝ ሁለት : ታጋሽ እንድሆን ስላደረግኝ
ሶስት : ምንዳ ወደማግኘት እንድመለስ ስለረዳኝ እንዲሁም
አራተኛ : ፈተናውን በዲኔ ባለማድረጉ አመሰግናለሁ የሚሉ ቀደምት ሰለፎች አልፈዋል። አላህ ይርሀማቸውና🖤
@fafiru_illahi
☝️ፈፊሩ ኢለላሂ☝️ "ወደ አላህም ሽሹ"🇪🇭

22 Feb, 19:20

238

.
🤍 ከጌታህ ዘንድ የማትችለዉ ነገር አይሰጥህም።
...ክብደትና አለመቻል ለየቅል ናቸዉ።
.......የፈተኑህ ነገሮች ከበዱህ እንጂ መች አቃቱህ?


@fafiru_illahi
@fafiru_illahi
☝️ፈፊሩ ኢለላሂ☝️ "ወደ አላህም ሽሹ"🇪🇭

22 Feb, 19:08

231

ለወንድምህ ዱዓእ አድርግለት!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿دُعاءُ الأخِ لأخِيهِ بِظَهرِ الغيْبِ لا يُرَدُّ﴾

“ወንድም ለወንድሙ በሌለበት የሚያደርገው ዱዓ አይመለስም። (ተቀባይነት አለው)።”

📚 ሶሂህ አልጃሚዕ: 3379

@fafiru_illahi
@fafiru_illahi