Ethiopian Media Authority (@ethmediaauth)の最新投稿

Ethiopian Media Authority のテレグラム投稿

Ethiopian Media Authority
This channel is an official channel of Ethiopian Media Authority (EMA).
EMA is an autonomous government organization accountable to the House of Peoples’ Representatives of the FDRE.
2,967 人の購読者
2,533 枚の写真
137 本の動画
最終更新日 06.03.2025 09:13

類似チャンネル

Seyoum Teshome
22,615 人の購読者

Ethiopian Media Authority によってTelegramで共有された最新のコンテンツ

Ethiopian Media Authority

05 Mar, 16:36

215

"የንግድ መገናኛ ብዙኃን ለማህበረሰቡ የመረጃ ምንጭ ከመሆን ባለፈ በሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ ይገባል" ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር)፣ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ

ቢሾፍቱ፣ የካቲት 26/2017 ዓ.ም

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በሰላም ግንባታ ዙሪያ ከንግድ መገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ የተገኙት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር)፤ የንግድ መገናኛ ብዙኃን ለማህበረሰቡ የመረጃ ምንጭ ከመሆናቸው ባለፈ በሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ በመግለፅ፤ ትልቁ ስኬት ችግሮች ከተፈጠሩ በኋላ ለማብረድ ከመሞከር ይልቅ ከመፈጠራቸው በፊት የመከላከል ስራ መስራት አዋጭ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የንግድ መገናኛ ብዙኃን ትውልድን በመቅረጽ ረገድ ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በኃላፊነትና በአንድነት መንፈስ በሰላም ግንባታ ላይ በትኩረት መስራትና ሚናቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

በመድረኩ የንግድ መገናኛ ብዙኃን በሰላም ግንባታ ዙሪያ ያላቸው ሚና በተመለከተ እንዲሁም ህብረ ብሔራዊ አንድነት እና አሰባሳቢ ትርክት በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የመነሻ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

#ብቁ_መገናኛ_ብዙኃን_ለማህበረሰባዊ_ንቃት
#የጥላቻ_ንግግርና_ሐሰተኛ_መረጃን_በጋራ_እንከላከል
Ethiopian Media Authority

05 Mar, 08:34

289

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በሰላም ግንባታ ዙሪያ ከንግድ መገናኛ ብዙኃን ኃላፊዎች ጋር ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡
Ethiopian Media Authority

04 Mar, 11:47

369

ኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃ የሚያስተላልፉትን ትፀየፋለች!

በመሆኑም የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩትን በማጋለጥ የበኩላችንን እንወጣ!
Ethiopian Media Authority

01 Mar, 05:22

188

እንኳን ለ129ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ!
Ethiopian Media Authority

28 Feb, 15:24

278

ማንኛውም የብሮድካስት አገልግሎት ባለፈቃድ የህዝብ ጥቅምና የጋራ ሀገራዊ እሴቶች  እንዲጠናከሩ አስተዋፅኦ የሚያደርግ አገልግሎት የመስጠት ግዴታ አለበት፡፡

የህዝብ ጥቅምና የጋራ ሀገራዊ እሴቶችን ማጠናከር ይገባል!
Ethiopian Media Authority

28 Feb, 05:36

328

Disseminating hate speech is prohibited!

According to Hate Speech and Dissemination Prevention and Suppression Proclamation No 1185/2020, Article 4: “Any person disseminating hate speech by means of broadcasting, print, or social media using text, image, audio, or video is prohibited.”
Ethiopian Media Authority

27 Feb, 11:28

363

በህትመት ሥርጭት ላይ የሚገለፁ መረጃዎች

#ብቁ_መገናኛ_ብዙኃን_ለማህበረሰባዊ_ንቃት
#የጥላቻ_ንግግርና_ሐሰተኛ_መረጃን_በጋራ_እንከላከል
Ethiopian Media Authority

27 Feb, 06:00

371

የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ የቤተሰብን፣የአካባቢን ብሎም  የሀገርን ልማት የሚጎዳ እና ለትዉልድ የማይበጅ አስከፊ ተግባር ነዉ!

በመሆኑም የጥላቻ ንግግርና የሐሰተኛ መረጃ የሚያሰራጩትን በማጋለጥ የበኩላችንን እንወጣ!

#የጥላቻ_ንግግርና_ሐሰተኛ_መረጃን_በጋራ_እንከላከል
Ethiopian Media Authority

26 Feb, 11:37

378

38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔን ላስተባበሩ  ባለሙያዎች  የምስጋና መርሐ-ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19/2017 ዓ.ም (Ethiopian Media Authority)

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከአፍሪካ ህብረት ጋር በመተባበር 38ኛውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ለመዘገብ የመጡ ጋዜጠኞችን ላስተባበሩ የተቋሙ ባለሙያዎች የምስጋና መርሐ-ግብር አካሂዷል፡፡

በመርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን ዶ/ር፤ የተቋሙ ተልዕኮ እውን ከማድረግ አንፃር ባለሙያዎቹ በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመዘገብ ለመጡ ጋዜጠኞችን ከማስተባበርና ምቹ ሁኔታዎችን ከመፍጠር አንጻር ውጤታማ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

የተሰራው ስራ ገጽታ ከመገንባት አንጻር ሚናው የላቀ  መሆኑን ገልፀው፤ ለዚህ ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የተቋሙ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ቀጣይ እንደ ቷቋምና እንደ ሀገር በሚሰሩ ስራዎች ላይ ይህንን መሰል የስራ ተነሳሽነትን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም ዋና ዳይሬክተሩ አያይዘው ተናግረዋል፡፡

በመርሐ-ግብሩ ባለሥልጠኑ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔን ለመዘገብ ለመጡ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ባደረገው ተሳትፎ ዙሪያ ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ ጉባዔውን ሽፋን ለመስጠት ከ አንድ ሺህ በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ  የሚዲያ አካላትና ጋዜጠኞች  ሙሉ አገልግሎት እንደተሰጠ ተገልፃል፡፡ 

የ38ኛዉ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የሚዲያ አካላትን ላስተባበሩ የተቋሙ ባለሙያዎች የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡
Ethiopian Media Authority

26 Feb, 05:39

515

ማንኛውም ሰው የሐሰት መረጃን በማንኛውም ሁኔታ ማሰራጨት የለበትም!

ማንኛውም ሰው የሐሰት መረጃን በአደባባይ ስብሰባዎች በብሮድካስት፣ በህትመት ወይም በማህበራዊ ሚዲያዎች ወይም በሌላ ተመሳሳይ ዘዴዎች አማካኝነት በፅሁፍ፣ በምስል፣ በድምፅ ወይም በቪዲዮ ማሰራጨት የተከለከለ ተግባር ነው፡፡

#የጥላቻ_ንግግርና_ሐሰተኛ_መረጃን_በጋራ_እንከላከል