አተ ማለት እኮ...
....
ከላይ ሲሉህ ከታች
ከታች ሲሉህ ከላይ
ታመሀል ስል ድነህ
ደናነህ ስል ታመህ
ልጠይቅህ ብየ ከቤትህ
ስመጣ
ደግም ደናነኝ አልክ አቤት ያተ ጣጣ
ትርጉምህ አልገባኝ ቀኙ ግራ ሁኖ
አልልህ ደግ ሰው ውስጠህ
እሬት ሆኖ
አተ ማለት እኮ...
ማክበር ስትችል ስድብን
መውደድ ስትችል ጸብን
ላይህ ማር ተቀብቶ
ውስጥህ ተኮል ሞልቶ
ፈቅር አትቀበል መስጠትህም ቀርቶ
አያግዙህ ነገር ልብህን
ማን አውቆ
ያለተፈታ ቅኔ ሰምና ወርቅ ሆኖ
#ገጣሚ_ዙፋን_ደጀን
@ethiopianye