Latest Posts from የኛ ግጥም 😍😄❤🥰🥺 (@ethiopianye) on Telegram

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺 Telegram Posts

የኛ ግጥም 😍😄❤🥰🥺
እንኳን ደና መጡ🙏
በዚህ ቻናል
#ግጥሞች
#ቀልዶች
እንዲሁም ሀገርኛ ወጎችን አዝናኝ መረጃዎችን በለዛ እናገኛለን
ለማንኛውም አስተያየት እንዲሁም ስራዎን ማቅረብ ከፈለጉ ወይም cross ከፈለጉ
በዚህ ያናግሩኝ 👉 @berii34
እዚህ ለይ ደሞ👇
@ethiopianye👈join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ

for any comment👉 @berii34
2,332 Subscribers
284 Photos
90 Videos
Last Updated 07.03.2025 00:50

The latest content shared by የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺 on Telegram

የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

04 Mar, 16:33

196

ሀሰት በከበባት ኢ ፍትሀዊ አለም ተከሳሽ በሙሉ ወንጀለኛ አይደለም

አይገርምም ...?

የሚታዘዙለት ሳርና ንፋሱ ሀጢአት የሌለባት ንፁህ ሳለች ነፍሱ
ወንጀለኛ ተብሎ ፤

ተከሳሽ ነበረ ክርስቶስ እራሱ፡፡

By Eyob Z Mariam

@ethiopianye
@ethiopianye
የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

02 Mar, 12:03

331

አድዋ

እስኪ ተናገሪ አንቺ የአድዋ መሬት፣
ውጊያው እንዴት ነበር የሚዘረር ጠላት፣
ደማቅ ታሪክ ሲፃፍ ኢትዮጵያ ስትነግስ፣
ህዝበ አለም ሲደነቅ የነጭ ደም ሲፈስ፣
ገበየሁ ሲሰዋ ባልቻ ደግሞ ሲቀስ፣
ምን አሉ ምኒሊክ ምን አለች ኢትዮጵያ፣
ወንድነት ሲዘራ ጠላት ሲሆን ትቢያ፣
እልፍ አእላፍት አልፈው፣
አጥት ከስክሰው፣
ንፁህ ደም አፍሰው፣
ትክ የለሿን ህይዎት ለሀገር ገብረው፣
ታሪክን ፃፉልን፣
በክብር አነገሱን፣
ያን ሰሰለት ያን ተራራ፣
ቋጥኝ አለቱ ሳይፈራ፣
ጋሻ መክተው፣
ጦር አንካሴ ወርውረው፣
ፋሽሽት አውድመዋል፣
ሀገርን አስከብረዋል፣
ታንክ ቢስለመለም፣
ጀቱ ቢዝገመገም፣
ባሩድ በምድር ቢረጭ ማንም አልፈራውም፣
አድዋ ስታጌጥ በደም ስትከበር፣
እልፍ አዳም ሲጨነቅ ነጭ አገት ሲቀብር፣
ጥቁሮች ቀና ሲሉ ታሪኩ ሲቀየር፣
ምን አለች ኢትዮጵያ ምንስ ብላ ነበር፣
አድዋ ደማችን፣
አጥት ነፍሳችን፣
የኛነት ምሰሶ ክብር ሞገሳችን፣
በደም ያፀናነው በነፍስ ያቀበጥነው፣
አጥት ገድግደን ጠላት የቀበርነው፣
እኛ ነን አድዋ፣
ቦታው ነው አድዋ፣
ዜጋው ነው አድዋ፣
ህዝቡ ነው አድዋ፣
ሳር ቅጠሉ ሁሉ ጋራው ሸንተረሩ፣
እሱ ነው አድዋ ብዙ ነው ሚስጥሩ፣
እወቁን እንግዲህ ደማቅ ታሪክ አለን፣
ድንበር አናስነካም ህይወትን ገብረን፣
ታሪክ የከተበው፣
ትውልድ የዘከረው፣
የነፃነት ችቦ የተቀጣጠለው፣
የአእላፍ ሰዎች ህይዎት ገብረን ነው፣
አድዋ ሁሌም ናት፣
ዝንተ አለም ኗሪናት፣
ጋራው ምድሩ አይጠፋም፣
ታሪኩም አይነጥፍም፣
በደም ያጌጥንበት ከቶም አይረሳም፣
ልባችን ጀግኖ፣
አንድነት ገንግኖ፣
ጠላትን ቆላነው፣
አንጀቱን በሳንጃ ደረቱን ወጋነው፣
ከንቱ ያለመውን በከንቱ አስቀረነው፣
እንዲህ ነን እኛማ የአድዋ ባለቤት፣
የካራ ማራና ለጥቁሮች ተምሳሌት፣
የይቻላል መምህር የነፃነት አባት፣
ለዚህም እኮ ነው እኛ አድዋ የሆን፣
አለም የሰገደው ዛሬም የሚያከብረን።
           02/06/2016

@ethiopianye
የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

02 Mar, 08:04

268

እንኳን አደረሳችሁ ኢትዮጵያውያን🔥🫡
የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

02 Mar, 06:33

268

ከዳመናው መሀል ይፈልቃል ኃያል ጢስ
ድል ለሀገሬ ሊሰጥ
በፈረሱ ይነጉዳል የአራዳው ጊዮርጊስ
ይዘምታል በሰማይ አማኝ ህዝቡን ከልሎ
የአምላክ ውብ ምድር
ቅድስት ኢትዮጵያ አትደፈር ብሎ

ይጎርፋል ሰው
ጦር ጋሻውን በእጁ አንጠልጥሎ
ምንሽር አልቤኑን በጀርባው ላይ አዝሎ
በባዶ እግሩ ጋሬጣውን ረቶ
እንዴትስ ይቀራል
ከንጉሱ ከንፈር የማርያም ስም ወጥቶ

ልክ እንደ ጦር እቃ ታቦት ተሸክሞ
ልክ እንደ አዘቦት ቀን በጾም ተሸልሞ
ቅንጣት እህል ሳይጎርስ በእምነቱ ቁሞ
ቅዳሴውን ሳይሽር በሰዓቱ ተገኝቶ
‹‹አሀዱ›› ሲል በህብረት አንድነት ገንብቶ
የዋለ ገበሬ የዋለ ሰራዊት
ድል አፍሶ ቢመለስ ይደንቃል ወይ ጥቂት?
(አይደንቅም)

አቡነ ማቲዎስ እምነትን አግዝፈው
ለሰራዊት ሲባል
‹‹ጾም ይሻር›› የሚል ትእዛዝ ተላልፈው
ከንጉስ ተሟግተው
በመስቀል አሳልመው
ባርከው ተዋጊውን ቢልኩ ወደ ውጊያ
ሰው በእህል ሳይሆን
በእምነት እንደሚረታ
ምስክር ትሆን ዘንድ አሸነፈች ጦቢያ

እኔ ግን
የድል ታሪክ ይዤ
ቆሚያለሁ ፈዝዤ
ተኝቻለሁ ደንዝዤ
አልስራ ጀብድ አልፈጽም ገድል
እንዴት ያቅተኛል
መዘከር እንኳን የአባቶቼን ድል?
ቢገባኝ ኖሮ የነጻነት ክብር
የካቲት ጊዮርጊስ
ስዕለት ባስገባሁ ለመቆሜ ተአምር

በባዶ እግር ሄዶ ጫማ ያለበሰኝ
ከአራቱም አቅጣጫ
ለአንድ አላማ ዘምቶ ሀገር ያወረሰኝ
በዘር ጎጠኝነት
ተከፋፍዬ ቢያይ በእንባው በወቀሰኝ
‹‹ ከአንድነት እርካብ ቁልቁል ተፈጥፍጠህ
በቁንጽል ማንነት ራስክን ለውጠህ
የምትኖር ሁላ አድዋን አስታውሰህ
ሁን እንደ ጥንቱ ፍቅርን ተንተርሰህ
አሻፈረኝ ካልክ ግን
‹‹ማርያምን!›› እፋረድኃለው በሰማይ
በሀገሬ ጀርባ ላይ ፈልተኃል እንደ ተባይ ››
ብሎ ባወጀብኝ
ሽልብታዬን አይቶ
እብደቴን ታዝቦ ከሞቴ ባነቃኝ
ጾም ጸሎትን ትቼ
አርብ ሮብን ረስቼ
ቅዳሴ ሰዓታት
ማህሌት ኪዳንን እኒህን ዘንግቼ
ለሆዴ አድሬ ስኖር እንደ አሳማ
ይደንቃል ወይ እውነት
ተረግጬ ብቀር ልክ እንደ ቄጤማ?
ተንኜ ብቀር ልክ እንደ ጤዛ?
ተሸንፌ ብታይ ወድቄ እንደ ዋዛ?
(አይደንቅም)

ዋ ለእኔ!
ዋ እኔ!
ርግብ ጋር ዘምቼ
ለቀረሁኝ ሞቼ

#ኤልዳን
@eldan29

@ethiopianye
የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

01 Mar, 18:10

263

እስኪ ይቺን ልጋብዝሽ

ተባረክ አባቴ
እስኪ ልመርቅህ ሽቅብ አንጋጥጬ፣
ከሰው ልጆች ሁሉ አንተን አስበልጬ፣
አንተማ ለልጅህ፣
ብዙ ወጥተህ ወርደህ፣
ከስተህና ጠቁረህ፣
ተዝቆ የማያልቅ እውቀትን መግበህ፣
ለዚህ አበቃኸኝ፣
ሰውም አደረከኝ፣
አንተማ የኔ አባት እንዲህ ትለኝ ነበር...
ልጄ ሀገር ማለት፣
ልጄ መንደር ማለት፣
አፈር ምድሩ አይደለም፣
ሰው በሙላ ነው ሙሉውን ህዝበ አዳም፣
ብለህ ያስተማርከኝ፣
ዛሬም ሰው አድርጎኝ፣
ሁሉን እወዳለሁ ከነግሳግሱ፣
አንድም ነገር ሳይቀር አሰሱ ገሰሱ፣
እንደ ዘመኑ ሰው ብሄር ቋንቋ አልልም፣
በማንነት በዘር በእምነት አልነጥልም፣
በሃብት በድህነት በፆታ በቀለም ብየ አልከፋፍልም፣
እያንዳንዱን ዜጋ እኔ እወደዋለሁ ከነምናምኑ፣
ለኔ በቂየ ነው ብቻ ሰው መሆኑ፣
ያኔ በልጅነት አባቴ ሲመክረኝ፣
ከስሩ አስቀምጦ ሀገርን ሲያሳየኝ፣
እኛነት ኩራት ነው፣
አንድነት ሃይል ነው፣
ልዩነት ውበት ነው፣
እኛን ያደመቀን የሀገር ቀለም ነው፣
ብሎ ይጀምራል እኔም እሰማለሁ፣
ልቤም በሩን ከፍቶ አዳምጠዋለሁ፣
ገና በማለዳ ፀሃይዋ ሳትፋጅ፣
እኔም ሳልገረጅፍ ሳልወጣ ከሰው እጅ፣
የተማርኩት ጥበብ ዛሬ ሳያጠበኝ፣
ትምክት ወለድ ሳልሆን በሰውኛ አስኪዶኝ፣
ውስጤም ደስተኛ ነው ልቤም ባለርካታ፣
ደግነት ነው ምግቤ ጠዋት እስከ ማታ፣
ተባረክ አባቴ፣
አንተ መሰረቴ፣
የጠዋት ድምቀቴ፣
የዛሬው ኩራቴ፣
ተባረክ ተባረክ አሁንም ተባረክ ...
ብየ ልመርቅህ፣
ይሄው ሰው አርጎኛል ያባትነት ወግህ።
             25/12/2016
@maedote27

@ethiopianye
የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

01 Mar, 08:06

280

ቃለኛ ናት ለእግዜር ወጉ
ልባም ትጉህ
ኪዳን አዛይ ልበ ብርቱ
ዳር እስከ ዳር ከአስረቱ
ንቃ አተኛም ለሰዓቱ

ወተቲቱ!

ለ ሶስት ለስድስቱ
ለዘጠኝ ሰዓቱ
ቁሞ ጠላይ ለእግዜር
ነጣላ አንጋቢቱ
ተንበርካኪ ካፈር ከስነ ስዕሉ
አሜን ቃለ ከንፈር ለመረቃት ሁሉ
ጦም ኣዳሪ አትወላውል
አታውቀውም የላት ስልቱ
ወድቃ ማትገዛ ለነገረ ከንቱ

ወተቲቱ!

ዮኒ
ኣታን
@ethiopianye
የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

28 Feb, 17:00

317

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮቻችን መልካም የረመዳን ፆም እንዲሆንላችሁ እንመኛለን❤️

         ረመዳን ከሪም 🌛

@ethiopianye
የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

28 Feb, 05:17

385

አይ ፍቅር

እክት፣
እክትክት፣
ስብር፣
ስብርብር፣
ልበልልሽ አልኳት፣
ፍቅሬን ላለማጣት፣
ሽጥና ዳሌዋ፣
አይኗ ፈገግታዋ፣
ፀጉር ተረከዟ፣
ውበት እና ወዟ፣
ቀድመው ቢማርኩኝ፣
እጅ ወደላይ ሲሉኝ፣
ልከትልሽ አልኳት፣
ስብር ልበል አልኳት፣
ልድቀቅልሽ አልኳት፣
አይ ያፈቀረ ሰው፣
የማይሆነው የለው፣
ይነክታል ይፈጫል፣
ይወድቃል ይነሳል፣
ይምል ይገዘታል፣
እላይ እታች ብሎ፣
ስንት አለት ፈንቅሎ፣
ይተኛል ለፍቅር፣
እክት ይላል ስብር፣
ፍቅር ሞገደኛው፣
ጀግና የሚያስተኛው፣
እንዲህ አድርጎኛል፣
ይፈጭ ያደቀኛል።
       2016

@maedote27

@ethiopianye
@ethiopianye
የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

25 Feb, 05:37

479

**
ፍቅር እንደ እቃቃ፣
እንደ ቀልድ አበቃ!

ጨዋታው ፈረሰ ዳቦው ተቆረሰ፣
በሳቅ ተጀምሮ በእንባ ተጨረሰ!

#ኤዶምገነት_ፃፈችው

@ethiopianye
የኛ ግጥም 😍😄🥰🥺

25 Feb, 05:36

476

ብዙ ኖሬ ነበር
ፍቅር በሚመስል
  በሰጠኸኝ ቅዠት
ጠልቄ እየዋኘው
ተመስገን.....
አንተን ያጣሁው ለታ 
እራሴን አገኘው

         ፅጌሬዳ✍️
@ethiopianye
@ethiopianye