Neueste Beiträge von Ethiopian Artificial Intelligence Institute (@ethiopianaii) auf Telegram

Ethiopian Artificial Intelligence Institute Telegram-Beiträge  

Ethiopian Artificial Intelligence Institute
This is the official Telegram channel of FDRE Artificial Intelligence Institute.
13,583 Abonnenten
2,804 Fotos
242 Videos
Zuletzt aktualisiert 11.03.2025 07:40

Ähnliche Kanäle

Ethiopia Insider
15,446 Abonnenten
RiTZY⚡️YOUTH️
8,889 Abonnenten
Borkena
7,301 Abonnenten

Der neueste Inhalt, der von Ethiopian Artificial Intelligence Institute auf Telegram geteilt wurde.

Ethiopian Artificial Intelligence Institute

21 Feb, 13:07

1,494

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በኢንዱስትሪዎች ውስጥ ምርታማነትን ከመጨመር ባሻገር በምርት ሂደት ሊገጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን ለመግታት እና ሌሎች በርካታ አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል፡፡ https://youtu.be/QHmqldF1hlE
Ethiopian Artificial Intelligence Institute

20 Feb, 12:00

604

https://youtu.be/zRpZLDe0Z80
Ethiopian Artificial Intelligence Institute

19 Feb, 12:04

1,490

በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የኤ.አይ ክበብ አባላት ኢንስቲትዩቱን ጎበኙ፡፡

በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የኤ.አይ ክበብ አባላት የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል፡፡ በጉብኝቱ ስለኢንስቲትዩቱ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ እና ስለ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ የክበቡ አባላት በጉብኝታቸው በሀገራችን ወደ ትግበራ የገቡ የቴክኖሎጂው ውጤቶችን በመገንዘባቸው ለዘርፉ ያላቸው ፍላጎት እንደጨመረው ገልጸዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ለክበቡ አባላት የአጭር ጊዜ የስልጠና መርሓ ግብር በኢንስቲትዩቱ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡ በዚህም ስልጠናዉ ላይ ሊካተቱ ስለሚገባቸዉ የተለያዩ ጉዳዮች ዉይይት ተደርጓል፡፡

ስልጠናዉ ከጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተጨማሪ ኢንስቲትዩቱ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች ላቋቋማቸው የኤ.አይ ክበብ አባላት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
Ethiopian Artificial Intelligence Institute

19 Feb, 08:09

1,475

https://youtu.be/treRFB4PixQ
Ethiopian Artificial Intelligence Institute

15 Feb, 08:16

2,738

https://youtu.be/_GvGCkqucvw
Ethiopian Artificial Intelligence Institute

14 Feb, 13:35

3,057

የአፋር ታለንት አካዳሚ ተማሪዎች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ።

አፋር ክልል ከሚገኘው አፋር ታለንት አካዳሚ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተውጣጡ ተማሪዎች በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጉብኝት አድርገዋል።

በጉብኝቱ ወቅት ስለኢንስቲትዮቱ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡ ተማሪዎቹ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ በዓለማቀፍ ደረጃ ያለበትን የእድገት ደረጃ እና የቴክኖሎጂውን አቅም በጉብኝቱ ወቅት መረዳታቸውን ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ሃገራችን በቴክኖሎጂው የደረሰችበትን አቅም በማየታቸዉ ወደፊት በዘርፉ ላይ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳሳደረባቸዉ ገልጸዋል፡፡

ኢንስቲትዩቱም ለነገ ሀገር ተረካቢ ታዳጊዎች የጉብኝት መርሓ ግብር በማዘጋጀቱ በአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ እና በአፋር ታለንት አካዳሚ ስም ምስጋና ቀርቦለታል፡፡

በጉብኝቱ የተሳተፉት ተማሪዎች የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን ፈተና በማለፍ በአፋር ታለንት አካዳሚ አዳሪ ትምህርት ቤት ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በመማር ላይ የሚገኙ ናቸዉ፡፡


ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
Ethiopian Artificial Intelligence Institute

14 Feb, 06:24

2,287

ኦፕን ኤ.አይ GPT-4.5 እና GPT-5 የተባሉ አዳዲስ የኤ.አይ ሞዴሎችን ይፋ ሊያደርግ ነው፡፡

የኦፕን ኤ.አይ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሳም አልትማን GPT-4.5 እና GPT-5 ስለተባሉ ሞዴሎች በኤክስ የማሕበራዊ ትስስር ገጹ መረጃ አጋርቷል፡፡ መረጃው ኩባንያው ሁሉንም የኤ.አይ ሞዴሎች ወደ አንድ የተዋሀደ ሥርዓት ለማምጣት እየሰራ እንደሚገኝ የሚገልጽ ነው፡፡

እንደ ዋና ስራ አስፈጻሚው መረጃ ከሆነ GPT-4.5 ወይም ኦሪዮን ተብሎ የሚጠራው ሞዴል ለሚያቀርባቸው ምላሾች ምክንያታዊነትን የማያካትት የኩባንያው የመጨረሻ ሞዴል እንደሚሆን ተመላክቷል፡፡ ይህም ከዚህ በኋላ በኦፕን ኤ.አይ ይፋ የሚሆኑ ሞዴሎች የሚያቀርቡት ምላሽ ምክንያትን ያካተት እና ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት ከፍተኛ የማሰላሰል ሂደት የሚከተሉ እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡

ከእነዚህ ሞዴሎች ይፋ መሆን በኋላ የኩባንያው ዋና ግብ ኦ-3 ተብለው የሚታወቁትን ሞዴሎች እና የጂ.ፒ.ቲ ተከታታይ ሞዴሎችን አንድ ማድረግ ነው። በውጤቱም ኦ-3ን ጨምሮ ሌሎቹንም የሚያጠቃልል GPT-5 እንደሚለቀቅና የኦ-3 ሞዴል ከዚህ በኋላ ራሱን የቻለ ነጠላ ሞዴል ሆኖ እንደማይቀጥል ታውቋል።

GPT-5 የተለያዩ ሞዴሎች አሁን ላይ የሚከውኑትን ተግባራት በአንድ የሚያጠቃልል ማዕከላዊ ሞዴል ከመሆን በሻገር በከፍተኛ የአስተውሎት ደረጃ ስራዎችን የሚከውን እንደሚሆን የዋና ስራ አስፈጻሚው መረጃ ያመላክታል፡፡

አልትማን ሞዴሎቹ የሚለቀቁበትን ቀን በግልፅ ባያስቀመጥም በሳምንታት አልያም በጥቂት ወራት ውስጥ ለተጠቃሚዎች ይፋ እንደሚሆን ታውቋል፡፡

ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
Ethiopian Artificial Intelligence Institute

13 Feb, 15:30

1,626

Delegations from Meta Visit the Ethiopian Artificial Intelligence Institute.

A delegation from Meta, led by Mr. Kojo Boakye, Vice President of Public Policy for Africa, Middle East, and Türkiye, visited the Ethiopian Artificial Intelligence Institute. They were welcomed by the institute's Director General, Worku Gachena (Ph.D.), and Deputy Director General, Taye Girma (Ph.D.). The delegation received an overview of the institute's AI-driven work from the Director General.

Mr. Kojo Boakye expressed his admiration for the institute’s progress in incorporating AI across various sectors. The delegation also relayed their positive impression of the institute's AI initiatives and expressed their desire to expand upon the existing partnership between Meta and the institute.

The visit concluded with in-depth discussions between the institute's officials and the delegation to explore further collaborative avenues.

Meta has been a long-time partner of EAII in AI and related fields.
Ethiopian Artificial Intelligence Institute

13 Feb, 12:50

1,404

በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ መስክ ዓለማቀፍ ትብብር እና ደህነነቱ የተጠበቀ ትግበራ እንዲኖር ቻይና ጥሪ አቀረበች፡፡

ቻይና ጥሪውን ያቀረበችው በሳምንቱ መጀመሪያ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ በፓሪስ ለሁለት ቀናት ሲመክር በቆየው ‘AI Action Summit’ ላይ ነው፡፡

የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ተወካይ ዣንግ ጉዋኪንግ ሰኞ ዕለት በጉባኤው ላይ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ መላው የሰው ልጆች የሚጋሩትን መጻኢ ጊዜ ለመፍጠር በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መስክ የጋራ ልማት እና ደህንነት አስፈላጊ ስለመሆኑ ተወካዩ አጽንኦት ሰጥተዋል።

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በቴክኖሎጂና ኢንዱስትሪ ሽግግር ውስጥ ቁልፍ ኃይል መሆኑን የዢ ጂንፒንግ ተወካይ አንስተዋል። ስለሆነም በዘርፉ ፈጠራ፣ አካታችነት እና አስተዳደር ረገድ ዓለማቀፍ ትበብር ሊኖር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

ቴክኖሎጂው ይዟቸው የመጡ ዕድል እና ተግዳሮቶችን በመጋፈጥ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ አስተዳደርን ለማሻሻል ዓለማቀፉ ማህበረሰብ በጋራ ሊሰራ እንደሚገባ ዣንግ ጉዋኪንግ ገልጸዋል፡፡

በጉባዔው ከ30 በላይ የሀገራት መሪዎች እና ዓለማቀፍ ተቋማት የተሳተፉ ሲሆን በማጠቃለያውም በቴክኖሎጂው አስተዳደር ዙሪያ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል።

ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም
Ethiopian Artificial Intelligence Institute

07 Feb, 15:12

1,396

ጉግል ኩባንያ ጀሚኒ 2.0 የተባለ አዲስ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ሞዴል አስተዋወቀ፡፡

ሞዴሉ ከዲፕሲክ ጋር ሊወዳደር የሚችል እንደሆነ እየተነገረ ነዉ፡፡

ይህ የኤ.አይ ሞዴል ጉግል ኩባንያ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ያለዉን ተሳትፎ ለማጠናከር የሚያስችል እንደሆነ እየተነገረለት ይገኛል፡፡

ጀሚኒ 2.0 በኩባንያው ስር ለሚተዳደረዉ ጀሚኒ ኤ.አይ ሞዴል ተጨማሪ የመፈጸም አቅም ያላብሰዋል፡፡ ሞዴሉ ጽሁፍን ብቻ መረዳት ከሚችሉ መሰል የኤ.አይ ሞዴሎች ጋር ሲነጻጸር ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን ይሰጣል፡፡

ሞዴሉ ከተጠቃሚዎች ለሚቀርብለት ጥያቄ ምላሽ እና ማብራሪያ መስጠት፣ የኮምፒዩተር ኮድ መጻፍ እና የተለያዩ ተግባራትን መከወን ይችላል፡፡

ጀሚኒ 2.0 እስከ 1.5 ሚልዮን ቃላቶችን በአንድ ጊዜ ለመተንተን የሚያስችል አቅም አለው፡፡ በተጨማሪም መረጃዎችን ከጎግል ሰርች ኢንጅን ማግኘት የሚያስችል አማራጭ አካቷል፡፡

ቴክ ክረንች በዘገባዉ እንዳስነበበዉ ሞዴሉ በቀዳሚው የጀሚኒ እና ሌሎች የጉግል መተግበሪያዎች ላይ ይገኛል፡፡

ድረ ገጽ | ፌስቡክ | ኤክስ | ዩቲዩብ | ቲክቶክ | ሊንክድኢን | ኢንስታግራም