የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ ከ6.4 ቢሊዮን ብር በላይ የግብር ዕዳ መሰብሰቡን አስታወቀ። ቢሮው ያለባቸውን “ከ3.2 ቢሊዮን ብር በላይ የግብር ዕዳ ለመክፈል ፈቃደኛ አልሆኑም” ያላቸውን 62 ግለሰቦች ሀገር እንዳይወጡ ለኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ስም ዝርዝራቸውን ማስተላለፉን ገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት ለመሰብሰብ ያቀደው ጠቅላላ የገቢ መጠን 230 ቢሊዮን ብር ነው።
የከተማ አስተዳደሩ በዘንድሮው በጀት ዓመት ከታክስ ገቢዎች ለማግኘት ያቀደው 150.1 ቢሊዮን ብር ሲሆን፤ እስከ መንፈቅ ዓመት 111.5 ቢሊዮን ብር ማግኘት መቻሉን ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ይፋ ተደርጓል።
የከተማይቱ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዚሁ ጉባኤ ላይ ባቀረቡት ሪፖርት፤ የከተማይቱ አስተዳደር “የታክስ መሰረትን በማስፋት” እንዲሁም “ብክነት እና ብልሹ አሰራርን በመከላከል” የገቢ መጠኑን ማሳደግ መቻሉን ገልጸው ነበር።
ከንቲባዋ ለዚህ በማሳያነት የጠቀሱት፤ ለግብር ስረዛ የቀረቡ ዶክመንቶች ላይ ባለፉት ስድስት ወራት በተደረገ ፍተሻ “10 ቢሊዮን ብር ማዳን መቻሉን” ነው።
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ዛሬ ሐሙስ የካቲት 27፤ 2017 በይፋዊ የፌስ ቡክ ገጹ ባወጣው መረጃ፤ ባለፈው መንፈቅ ዓመት ውስጥ ከ6.4 ቢሊዮን ብር በላይ የግብር ዕዳ መሰብሰቡን ገልጿል።
🔴ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15272/
@EthiopiaInsiderNews