۞Hikem tube۞

@et_hio_islam


آمَنَ الرَّسُولُ بِمَا أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِ وَالْمُؤْمِنُونَ ۚ كُلٌّ آمَنَ بِاللَّهِ وَمَلَائِكَتِهِ وَكُتُبِهِ أ


وَذَكِّرْ فَإِنَّ الذِّكْرَىٰ تَنفَعُ الْمُؤْمِنِينَ

ገሥጽም፤ ግሣጼ ምእመናንን ትጠቅማለችና፡፡


ሀሳብና አስታያየት በዚህ አስቀምጡልኝ @Fezekir_A

۞Hikem tube۞

21 Jan, 00:25


Hikem tube

🤍ቁረአን  የልብ  ብረሀን  ነው🤍

♤ any comments @Fezekir_A
             @et_hio_islam

۞Hikem tube۞

21 Jan, 00:25


Hikem tube
 
የታሪኩ ርዕስ፦
🇷🇺ሩሲያዊቷ ሱመያ•

      ♧ክፍል 👉8

ፀሀፊ➝عبد📖

ከዚያም ቤተሰቦቿን ለመጠየቅ ብለን ተንቀሳቀስን ደርሰን በሩን አንኳካን ቤታቸው ያረጀና እዚህ ግባ የማይባል ነው  ድህነት በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ይንፀባረቃል፡፡ ታላቅ ወንድሟ በሩን ከፈተልን ወጣትና ፈርጠም ያለ ጎረምሳ ነው ስታገኘው
እጅግ ደስ አላት፡፡ በፈገግታ ፊቷን ገልጣ ወደሱ ሄደች ሰላምታ አቀረበችለት፡፡ እሱ ግን ገና እንዳያት ፊቱ ተቆያየረ በሰላም መመለሷ ያስደሰተው ቢመስልም ሙሉ አካሏን በሚሸፍነው ልብሷ ግን ሳይገረም አልቀረም፡፡ በፈገግታ ተሞልታ ወንድሟን
አቅፋ ወደ ቤቱ ውስጥ ዘለቀች፡ ከኋላዋ ተከትዬ በመግባት ብቻዬን ሳሎን ውስጥ ተቀመጥኩኝ፡፡


እሷ ወደ ውስጥ ዘለቀች በሩሲያ ቋንቋ ታወራቸዋለች የሚያወሩትን ማወቅ አልቻልኩም፡፡ በሂደት ግን ድምፃቸው ከፍ እያለ መጯጫህ ጀመሩ ሁሉም በዚህና በዚያ እየጮሁ ያዋክቧት ጀመር ሁኔታው አለማረኝም፡፡ የሚሉት በርግጠኝነት
አላወቅኩምና ምንም ማድረግ አልቻልኩም፡፡


በሂደት ድምጹ እኔ ወዳለሁበት ክፍል እየቀረበ መጣ፡፡ አንድ ጎልማሳ ሰው ከፊት ሆኖ
ሶስት ወጣቶች ወደኔ እየጠቆሙ መጡ፡፡ መጀመሪያ አስቤ የነበረው ለልጃቸው
ያቀረብኩትን የጋብቻ ጥያቄ ይቀበሉኛል ብዬ ነበር ሆኖም ግን ወዲያው እንደ አውሬ ሰፈሩብኝ፡፡

በቅጽበትም ቡጢ፣ ጥፊ፣ እርግጫ... አከታትለው አሳረፉብኝ ለመከላከል ሞከርኩኝ፡፡ ሰዎች እንዲደርሱልኝ ብዬ ጮህኩኝ ማንም የደረሰልኝ አልነበረም፡፡ በመጨረሻም ደክሞኝ ወደቅኩኝ ይህ ቤት ለህይወት ዘመኔ መጨረሻዬ ሊሆን ነው
ብዬ አሰብኩዱላው በዛብኝ ለመሸሸ አሰብኩና በዐይኔ የገባሁበትን በር ማፈላለግ ጀመርኩ፡፡ በሩን እንዳስተዋልኩ ወደዚያው ሮጬ በሩን ከፍቼ አመለጥኩ፡፡


ተከትለው አሳደዱኝበአካባቢው ብዙ ሰው ስለነበር በሰዎች መካከል ገብቼ ተሰወርኩባቸው፡፡
ከዚያም ትንሽ አርፌ ወደነበርኩበት ማረፊያ ሄድኩኝ ከቤቱ ብዙ አይርቅም ክፍሌ ገብቼ የደረሰብኝን ለማየት ሞከርኩ ጥርሴና ከንፈሬ ደምቷል  ፊቴ በደም ተለውሷል፤ ከአፌ ደም ይፈሳል፤ ልብሴ ተበጣጥሷል ታጠብኩኝ፡፡ ከነዚያ
አውሬዎች ያስመለጠኝን አላህን አመሰገንኩ፡፡

ወዲያው ደግሞ የባለቤቴ ጉዳይ በሀሳቤ
መጣብኝ እንዴት አድርገዋት ይሆን? ፊቷ ድቅን አለብኝ፡፡ እኔን በደበደቡበት ሁኔታ ይደበድባት ይሆን! እኔ መቋቋም ያልቻልኩት ዱላ እሷ በሴት አቅሟ ትችላለች ሚስኪን ባለቤቴ። በዱላ ብዛት እጅ እንዳትሰጥና አቋሟ እንዳትለውጥ ስጋው።


       ♧ክፍል 👉9

ይ....ቀ....ጥ....ላ....ል..

♤ any comments @Fezekir_A


@et_hio_islam

۞Hikem tube۞

21 Jan, 00:24


Hikem tube

🤍ቁረአን  የልብ  ብረሀን  ነው🤍

♤ any comments @Fezekir_A
@et_hio_islam

Hikem tube

۞Hikem tube۞

21 Jan, 00:24


Channel photo updated

۞Hikem tube۞

21 Jan, 00:23


Hikem tube
 
የታሪኩ ርዕስ፦
🇷🇺ሩሲያዊቷ ሱመያ•

      ♧ክፍል 👉7

ፀሀፊ➝عبد📖


ወደኔ ዞረችና ኻሊድ ትተኛለህ? አለችኝ አዎን ደክሞናል እኮ› አልኳት፡፡ ሱብሓነላህ! የምትገርም ነህ በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እያለን መተኛት ታስባለህ? በዚህ ሁኔታ ውስጥ እኮመተኛት ሳይሆን ወደ አላህ መጠጋት፤ ወደሱ ፊታችንን ማዞር ነው ያለብን፡፡ በል ተነስና አላህን እንለምን እሱ ነው የሚሻለን› አለችኝ፡፡ ተነሳሁና የቻልኩትን
ያህል ሰገድኩ ተመልሼ ተኛሁ፡፡ እሷ ግን በሰላቷ ቀጠለች በነቃሁ ቁጥር ሩኩዕ ላይ፣ ሰጁድ ወርዳ፣ ቆማ ዱዓእ ስታደርግ፣ ስታለቅስና ስትማፀን አያታለሁ ፈጅር እስኪወጣ ድረስ በዚሁ ሁኔታ ቆየች ከዚያም ቀሰቀሰችኝ  በል ተነስ ሱብሒ
ደርሷል አብረን እንስገድ› አለችኝ፡፡ ተነሳሁና ውዱእ አደረግኩ ሰገድን ጥቂት ተኛች፡፡


ፀሐይ ስትወጣ በል ወደ ፓስፖርት ጣቢያው እንሂድ› አለችኝ፡፡ ‹እንዴ… ወዴት? ምን ልናደርግ? በምን መረጃ... የታለ ፎቶው...?› አልኳት፡፡
ሄደን እንሞክር› አለችኝ፡፡ እንሞክር ከአላህ እዝነት ተስፋ ለምን አንቆርጣለን›ሄድን፡፡ ወላሂ ጣቢያው ግቢ እንደገባንና በለበሰችው ኒቃብ እሷ መሆኗን እንዳወቁ አንደኛው ሠራተኛ ወደሷ በመምጣት አንቺ እገሌ ነሽ አይደል?› አላት፡፡ አዎን አለችው በይ ፓስፖርትሽን ውሰጂ ተሰርቶልሻል› አላት፡፡ ስታየው ከነሒጃቧ በሰጠችው ፎቶ ተስርቶላታል ደስ አላት፡፡ አላህን ለሚፈራ ሰው እሱ መውጫ
ያበጅለታል› አላልኩህም ወይ!›› አለችኝ፡፡


ለመውጣት ስንንደረደር አንደኛው ሠራተኛ ወደመጣችሁበት ከተማ በመሄድ ማህተም ማስመታት ይኖርበችኋል› በማለት አሳሰበን ወደ ትውልድ ከተማዋ ተመለስን እኔም በውስጤ ቤተሰቧን ለመጠየቅ ይህ የመጨረሻ ዕድሏ ነው አልኩኝ ከትንሿ ከተማ ደረስን ማረፊያ ቤት
ተከራየንና አረፍን ለፓስፖርቱም ማህተም አስመታን። ከዚያም ቤተሰቦቿን ለመጠየቅ ብለን ተንቀሳቀስን።...............

  ♧ክፍል 👉8

ይ....ቀ....ጥ....ላ....ል..

♤ any comments @Fezekir_A


@et_hio_islam

۞Hikem tube۞

21 Jan, 00:12


Hikem tube
 
የታሪኩ ርዕስ፦
🇷🇺ሩሲያዊቷ ሱመያ•

      ♧ክፍል 👉6

ፀሀፊ➝عبد📖

‹ካልሄድን› በሚለው አቋሟ በመጽናቷ ወደ ሞስኮ መሄዳችን ግድ ሆነ፡፡ ማረፊያ ክፍል ተከራየንና በነጋታው ወደ ፓስፖርት ጣቢያው ሄድን፡፡ የተለያዩ
ሀላፊዎች ዘንድ ገባን  በመጨረሻም ዋናው ሀላፊ ዘንድ ቀረብን ሲበዛ መጥፎ ሰው ነው፡፡ ፓስፖርቱን እያየ ፎቶውን ማገላበጥ ጀመረ፡፡ ከዚያም ወደ ባለቤቴ ቀና በማለት የዚህ ፓስፖርት ፎቶው የሷ ስለመሆኑ በምን ማወቅ እችላለሁ?› አለ፡፡


ለማመሳከር ፈልጎ ፊቷን ገልጣ እንድታሳየው ያሰበ ይመሰላል፡፡ ‹ላንተ ፊቴን አልገልጥም ሴት  ሠራተኞች ካሉ ሊያዩኝ ይችላሉአለችው ባለቤቴ፡፡

በዚህን ጊዜ ሰውዬው ክፉኛ ተቆጣ የድሮውን ፓስፖርት፣ ፎቶዎቹንና ሌሎቹን ሰነዶች ጨምሮ
ወደ ራሱ የማስቀመጫ ቦታ ወረወራቸው ትክክለኛውን የፓስፖርት ፎቶ ይዘሽ ካልመጣሽ በስተቀር ከአሁን በኋላ የበፊቱንም ሆነ አዲስ ፓስፖርት አይኖርሽም›አላት፡፡

ባለቤቴ ከሱ ጋር በማውራት ልታሳምነው ጣረች በሩሲያንኛ ነበር የሚያወሩት የሚያወሩት
አይገባኝም፡፡ ባለቤቴ ተናዳለች ምን እንደማደርግ ግራ ገብቶኛል ሀላፊው ከያዘው አቋሙ የሚመለሰ አይመስልም በፍፁም አይሆንም› አለ፡፡ እሷም
ተስፋ ሳትቆርጥ ተከራከረች፡፡ ለጥቂት ጊዜ ዝም ብላ ቆመች ወደሷ ጠጋ አልኩኝ አላህ ነፍስን ከምትችለው በላይ አያስገድዳትም፤ ችግር ላይ መሆናችንን ልብ በይ በዚህ መልኩ የምንጉላላው
እስከመቼ ነው?› አልኳት፡፡

‹አላህ እሱን ለሚፈራ ሰው መውጫ ያበጅለታል  ባላሰበውም በኩል ሲሳዩን ይለግሰዋል› አለች፡፡ እዚያው ሆነን ከኔ ጋር ብዙ ተከራከርን የጣቢያው ሀላፊ በሁኔታችን ተቆጣና እንድንወጣለት አስገደደን፡፡ ወጣን ደክሞናል በአንድ በኩል ስታሳዝነኝ በሌላ በኩል አናዳኛለች፡፡ ተቀምጠን
በሰፊው እንድናወራ በማሰብ ወደተከራየነው ክፍላችን አመራን፡፡

እኔ ላሳምናት እጥራለሁ  እሷም ልታሳምነኝ ትሞክራለ  ዕለቱ መሸ ዒሻ ሰገድን በዚህ ጉዳይ
ላይ በሀሳብ ተወጥሬያለሁ ርቦን ስለነበር ያገኘነውን በላን  ለመተኛት ብዬ ራሴን ከትራስ ጋር አገናኘሁ፡፡ ለመተኛት ማሰቤን ስታይ ፊቷ ላይ ቁጣ አነበብኩኝ..................።

   ♧ክፍል 👉7

ይ....ቀ....ጥ....ላ....ል..

♤ any comments @Fezekir_A


@et_hio_islam

۞Hikem tube۞

21 Jan, 00:09


۞Hikem tube۞ pinned «Hikem tube   የታሪኩ ርዕስ፦ •🇷🇺ሩሲያዊቷ ሱመያ•       ♧ክፍል 👉5 ፀሀፊ➝عبد📖 አስተናጋጁ ይህ ፎቶ ለፓስፖርት አይሆንም፡፡ ባለቀለም ፎቶ ነው የምንፈልገው ፀጉርና ትከሻሽ መታየት አለበት› አላት፡፡ ከዚህ ፎቶ ውጭ ሌላ እንደማትሰጥ አስረግጣ ነገረችው፡፡ በሱ በኩል የማይሳካ መሆኑን ስታውቅ ሌላ የቦታው ሠራተኛ ዘንድ ሄድን ቀጥሎም ሌላ ሀላፊ ዘንድ ሁሉም ጸጉሯ ተገልጦ…»

۞Hikem tube۞

21 Jan, 00:09


Hikem tube
 
የታሪኩ ርዕስ፦
🇷🇺ሩሲያዊቷ ሱመያ•

      ♧ክፍል 👉5

ፀሀፊ➝عبد📖


አስተናጋጁ ይህ ፎቶ ለፓስፖርት አይሆንም፡፡
ባለቀለም ፎቶ ነው የምንፈልገው ፀጉርና ትከሻሽ መታየት አለበት› አላት፡፡ ከዚህ ፎቶ ውጭ ሌላ እንደማትሰጥ አስረግጣ ነገረችው፡፡ በሱ በኩል የማይሳካ መሆኑን ስታውቅ ሌላ የቦታው ሠራተኛ ዘንድ ሄድን ቀጥሎም ሌላ ሀላፊ ዘንድ ሁሉም ጸጉሯ ተገልጦ የተነሳችው ፎቶ ካልሆነ በስተቀር አንቀበልም አሉ፡፡ ባለቤቴ በእንቢታዋ ፀናች እነርሱም በዚህ ፎቶ እንደማያስተናግዷት ገለጹላት፡፡ ፎቶውን እንዲያፀድቅላት ብለን ዋናዋ ሀላፊ ዘንድ ሄድን ብዙ ጣረች፣ አስረዳች፣
ተከራከረች፣ ሞገተቻቸው  የሚፈለገው ፊት ነው፡፡ ምንድነው ልዩነቱ? ስትፈልጉ ፎቶዎቹን አነጻጽሯቸው› አለቻቸው፡፡


ሀላፊዋም አሰራራቸው ይህን የማይፈቅድ መሆኑን አስረዳቻት በመሆኑም እንደማትቀበላት ገለፀች፡፡ ባለቤቴም ከዚህ ፎቶ ውጭ ሌላ በፍጹም አላመጣም፡፡ ባይሆን ማድረግ ያለብኝን ሌላ መፍትሔ ካለ ንገሪኝ› አለቻት፡፡


በመጨረሻም ሀላፊዋ ይህን ጉዳይሸን ሊፈታ የሚችለው ሞስኮ የሚገኘው ዋና ቢሮ
ብቻ ነው› አለችን፡፡ የፓስፖርት ጣቢያውን ትተን ወጣን፡፡ ወደ እኔ በመዞር ‹ኻሊድ ወደ ሞስኮ እንሂድ› አለኝ ተበሳጨሁ።

እነርሱ የሚሉትን ፎቶ ስጪያቸው በቃ› አልኳት
አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም፤ የቻላችሁትን ያህል አላህን ፍሩ› ነው የተባለው፡፡ የግዴታ ስለሆነብሽ ነው የተጠየቅሽውን እያደረግሽ ያለሽውፓስፖርትሽን ሊያዩ የሚችሉት ደግሞ የተወሰኑ አካላት ብቻ ናቸው፡፡

ይህም ግድ ስለሆነ ነው፡፡ ከዚያ ጊዜው እስኪያልቅ ድረስ ቤትሽ ነው የምታስቀምጪው ስለዚህእባክሽን ራስሽን አታጨናንቂ ሞስኮ ድረስ ለምን እንሄዳለን? አልኳት፡፡ አይሆንም› አለችኝ ተገላልጬማ ፈጽሞ ፎቶ ተነስቼ አልሰጣቸውም፡፡ የአላህ ዲን ካወቅኩ በኋላማ ይህ ሊሆን አይችልም በማለት ተከራከረችኝ፡፡

    ♧ክፍል 👉6

ይ....ቀ....ጥ....ላ....ል..

♤ any comments @Fezekir_A


@et_hio_islam

۞Hikem tube۞

21 Jan, 00:06


ሙስሊም ከሆንክ ብቻ እነዚህን ምርጥ ኢስላሚክ ቻናሎች ተቀላቀል 🕌 ከታች የተዘረዘሩት ሁሉንም በአንድ ፎልደር ያኛሉ።

۞Hikem tube۞

21 Jan, 00:06


💔'#ሙሽሪትን_ማን_ገደላት?' 💔
 
...ዛሬ ለየት ያለ ቀን ነበር ሰርግ'ማይደል! ሁሉም ተሰብስበው ጨዋታ እያፈኩ፣ ልጆች እየጨፈሩ ሰፈሩ ድምቅ ብላል።   ምሽት 1 ሰአት ተኩል ገደማ "እርርርርርርርይ" የሚል ድምጽ ተሰማ። ከርቀት ነበር። ጩኸቱ እየቀረበ መጣ፤ ሁሉም እየሮጠ ወጣ አንዲት ወጣት ቀሚሷ በደም እርሷል መሬት ላይ ተዘርራለች ሁሉም የሚያዩትን ማመን አቃታቸው። አንገቷ ላይ ያለው ደም መሬቱን ሞልቶታል። ሁሉም የሚያደርገውን አያቅም። እሪታው እየሞቀ ቀለጠ.......See More

ሙሉውን ለማግኘት #OPEN ይበሉ 👇👇

Wave - @semutiyeee

۞Hikem tube۞

20 Jan, 23:52


የስልክ ቁጥራቹ መጨረሻ ስንት ነው?

۞Hikem tube۞

20 Jan, 23:52


🥺 ተማሪ ኖት 🥺

۞Hikem tube۞

20 Jan, 23:52


ኢብኑል_ቀዪም ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : - ኢብኑ ተይሚያህ አንድ ጊዜ እንዲህ ሲሉ መከሩኝ —

«ቀልብህን የፈሰሰበትን ሁሉ እንደሚመጠውና ሲጨምቁትም ያንኑ እንደሚተፋው እስፖንጅ አታድርገው። ይልቁንስ እንደ መስታወት አድርገው። ብዥታዎች በገፅታው ላይ ያልፋሉንጂ ወደ ውስጡ አይገቡም። አጥርቶ ይመለከታቸዋል፣ በጠጣርነቱ ደግሞ ይመልሳቸዋል። አንተም ባንተ ላይ የመጣውን ብዥታ ሁሉ ለልብህ ካጠጣኸው የብዥታዎች መኖሪያ ይሆናል።»

📚 ۞ مفتاح دار السعادة【1/443】۞

@et_hio_islam

♤ any comments @Fezekir_A

۞Hikem tube۞

20 Jan, 23:50


Hikem tube
ኢብኑ_ተይሚያህ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«ሰውየውን መልክተኛውን ﷺ  እንዳይከተል የሚያደርጉት ሁለት ነገር ናቸው። ወይ መሐይምነቱ ነው ወይም የብልሹ አሥተሣሰብ ባለቤት መሆኑ ነው።»

📚 ۞ الفتاوي【15/93】۞
@et_hio_islam
♤ any comments @Fezekir_A

۞Hikem tube۞

20 Jan, 23:50


Hikem tube
 
የታሪኩ ርዕስ፦
🇷🇺ሩሲያዊቷ ሱመያ•

      ♧ክፍል 👉4

ፀሀፊ➝عبد📖


ኻሊድ ከሷ ጋር ለመሄድ ወሰነ እሷም ያለ ሙህሪም መሄድ እንደማትችል አመነች ብቻዋን መሄድም አልፈለገችም፡፡ የሩሲያ የአየር መንገድ
የሆነውን አውሮፕላን ተሳፈሩ ከነ ኒቃቧ ነበር    የተሳፈረችው  ከበሏ ጎን ኩራት እየተሰማት ተቀመጠች፡፡ ኻሊድ በሂጃብሽ የተነሳ ችግር እንዳያጋጥመን እፈራለሁ አላት።

እሷም ሱብሓነላህ! እነዚህን ኢ-አማኒያን እንድታዘዝና በአላህ እንድከድ ትፈልጋለህን? ወላሂ ፈጽሞ አይሆንም  አላደርገውምያሉትን ይበሉ› አለችው፡፡ሰዎች በግርምት ወደርሷ ይመለከታሉ፡፡ አስተናጋጆች ምግብ ማቅረብ ጀመሩ  ከምግቡ ጋር መጠጥ ይቀርብ ነበር፡፡ የጠጡት ሞቅ  እያላቸው ሲሄድ መናገርና እሷን በነገር መውጋት ጀመሩ  ከዚህም ከዚያም ያሾፉባት ጀመር  አንዱ ይሳለቃል፣ ሌላው ይስቃል፣ ሌላው ያላግጣል አጠገቧ ቆመው ስላሷ ያወራሉ፣ ያጣጥላሉ፡፡ ኻሊድ ይመለከታቸዋል ሆኖም ግን በራሳቸው ቋንቋ ያወሩ ስለነበር የሚሉት አይገባውም
እሷ ግን እየሰማችና እየሳቀች የሚሉትን ሁሉ ትተረጉምለታለች፡፡

በዚህን ጊዜ ኻሊድ ተቆጣ እሷ ግን እንዲረጋጋ መከረችው አይዞህ አትዘን፤ አትጨናነቅ  ሶሐቦችን ካገኛቸው ችግር አንፃር ሲታይ ይሄ በጣም ቀላል ነገር ነው፡፡ ሶሐቢያት ካለፉበት መከራ ጋር ሲነፃፀር ይህ በጣም ትንሽ ነው› አለችው፡፡ እሷም ባሏም ትዕግስትን መረጡ በመጨረሻም የተሳፈሩበት አውሮፕላን አረፈ፡፡

ኻሊድ እንዲህ ይላል፡- ሩሲያ ስንደርስ ወደ ቤተሰቦቿ ቤት በመሄድ እነርሱ ዘንድ ቀናትን ቆይተን ጉዳያችንን ጨርሰን የምንመለስ ነበር የመሰለኝ የሚስቴ ሐሳብ ግን ከዚህ ከፍ ያለ ነበር፡፡

እንዲህ አለችኝ፡- ቤተሰቦቼ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ናቸው ሃይማኖታቸውን በጣም ያጠብቃሉ፡፡ አሁን እነርሱ ዘንድ መሄድ የለብንም ማረፊያ ቤት አንከራይ እዚያው ቆይተንም
የፓስፖርቱን ጉዳይ እናስጨርስ ከጨረስን
በኋላ ሄደን ቤተሰቦቼን እንጎበኛለን፡፡› በሐሳቧ ተስማማሁ  ማረፊያ ተከራየንና እዚያው ቆየን፡፡ በነጋታው ወደ ፓስፖርት ማደሻ ማዕከል ሄድን ወደ ቢሮው ዘለቅን  አስተናጋጃችን የቀድሞውን
ፓስፖርትና ሌላ ፎቶ ጠየቀን በጥቁርና ነጭ የተነሳችውን ፎቶ አቀበለችው የፊቷ ቅርጽ ብቻ
ነበር የሚታየው፡፡

    ♧ክፍል 👉5

ይ....ቀ....ጥ....ላ....ል.

.♤ any comments @Fezekir_A

@et_hio_islam

۞Hikem tube۞

20 Jan, 23:50


ኢማሙል_አልባኒይ ረሒመሁሏህ እንዲህ ይላሉ : -

«ልክ ከአላህ ውጪ በእውነት የሚገዙት አምላክ እንደሌለ ሁሉ፥ በእውነት የሚከተሉትም የለም ረሱል ﷺ ብቻ ቢሆኑ እንጂ።»

📚 ۞ متفرقات شريط رقم【6】۞

@et_hio_islam
♤ any comments @Fezekir_A

۞Hikem tube۞

20 Jan, 23:49


♤ any comments @Fezekir_A


@et_hio_islam

۞Hikem tube۞

20 Jan, 23:48


የስልክ ቁጥራቹ መጨረሻ ስንት ነው?

۞Hikem tube۞

20 Jan, 23:46


የስልክ ቁጥራቹ መጨረሻ ስንት ነው?

۞Hikem tube۞

20 Jan, 23:40


ለፕሮፋይለዎ የሚሆኑ ቁርዓናዊ ጥቅሶችን ብቻ ለምትፈልጉ
👇👇
@only_kuran

2,429

subscribers

116

photos

94

videos