Последние посты Estifanos Ze Mahitot Official (@estifanoszemahitot) в Telegram

Посты канала Estifanos Ze Mahitot Official

Estifanos Ze Mahitot Official
"ይህ ቻናል የተለያዩ ሀይማኖታዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።"

https://t.me/+7LOhpcH8ccgxYTM0
1,472 подписчиков
690 фото
112 видео
Последнее обновление 05.03.2025 19:33

Последний контент, опубликованный в Estifanos Ze Mahitot Official на Telegram

Estifanos Ze Mahitot Official

05 Sep, 10:57

1,457

ጳጉሜን ፩:- የማዕተብ ቀን
ጳጉሜን ፪:- የክብረ ክህነት ቀን።
ጳጉሜን ፫:- የፊደል ገበታ ቀን።
ጳጉሜን ፬:- የሰንደቅ ዓላማና
ጳጉሜን ፭:- የቅድስት ቤተክርስቲያን ቀን።

🙏
Estifanos Ze Mahitot Official

05 Sep, 05:49

1,316

በሉ ወዳጅነታችሁን ግለጡ!

“መስከረም ሚዲያን በመስከረም” ዘመቻን ይቀላቀሉ።

Subscribe and share

https://youtube.com/channel/UCzzbnGov2lpY2yqEl8akJLw?si=zOTAiRmcuq_cXN7v
Estifanos Ze Mahitot Official

23 Aug, 10:36

1,412

ቅኖና የመደንገግ የዖዛን ቅንነት

የአሚናዳብ ልጅ ዖዛንን በእስራኤል በተመረጡ 32ሺ ሰዎች መሃል ለቀናት በቤታቸው የሰነበተችውን ታቦተ ጽዮንን ከሚያመጡ ሰዎች መሃል ነበር።

ታቦተ ጽዮን የከበረችበትን ሰረገላ ከወንድሙ ጋር ይነዳ ነበር። ነገር ግን የሰረገላውን ድንገት መንገጫገጭ ያሳሰበው ዖዛን ለቀናት በአባቱ ቤት የሰነበተችውን ታቦተ ጽዮን "ከሰረገላ እንዳትወድቅ" በሚል እጁን ዘርግቶ ደግፎ ሊያጸናት ሞከረ።

ከእዘህ በኃላ ያለው ውጤት ሲጠቃለል"“የእግዚአብሔርም ቍጣ በዖዛ ላይ ነደደ፥ እግዚአብሔርም ስለ ድፍረቱ በዚያው ቀሠፈው፤ በእግዚአብሔርም ታቦት አጠገብ በዚያው ሞተ።
  — 2ኛ ሳሙ 6፥7" ሲል ይዘገዋል።

አሁን ላይ በቅንነትም ይሁን ሆን ተብሎ(በተዋሕዶ ስም የተሃድሶ እና ቅባት ተወካዮች ስላሉ) በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የአገልጋይነትን ስያሜ የወሰዱ ሰዎች በድፍረት ስርዓተ ቤተክርስቲያን ላይ ጨክነው አዲስ በር ሲከፍቱ እናያለን።

"ስትሰብክ ለምን ነጠላ ለብሰህ፣መስቀልህን እያሳየህ፣ በስመ አብ በወልድ... ብለህ አትጀምርም" የሚል ጥያቄ የተነሳበት አንድ ቲክቶከር "ዘመኑን አይመጥንም እንደዛ ብዬ አልጀምርም" የሚል ጥቅል መልስ አይነት ሲሰጥ ሰማው።

ቤተክርስቲያን የማትናገራቸው፣ከመቅደሱ ያልዋለ፣ከኦርቶዶክሳዊነት  የስብከት ምንጭ ያልፈለቀ ወንጌል በቤተክርስቲያን ስም እዚህ እና እዛ ቆመው እየተፋጩ ወተት ለሚፈልገው ምዕመን አጥንት ሊያስግጡ ይሞክራሉ።

ዛሬ ደግሞ እንደ ላቲን እና ካቶሊክ ስእለ ማርያምን እንደ ኦሪቱ ጽላት አክብረው የሚዞሩ ወጣቶች አዲስ የቅዱሳት ስእላት የመገልገል ቅኖና ድንጋጌ ሰርተዋል። እንደ ወረርሽን የመስፋት እድሉ ሰፊ እንደሆነ እንጠብቃለን።

እንግዲህ በጎም ሆነ መጥፎ ትላንት የቅድስት ቤተክርስቲያን ስርዓት እና ልምድ ያልሆኑ ልምምዶችን ላይ መድፈር ማቆም አለብን።

እንደ ታቦተ ጽዮን አዘነበሉ ብለን ለእግዚአብሔር ብለን ነው በሚል ቅንነት ልንነካው የማይቻለን  ስርዓቶች አሉን።

አዳዲስ ልምምዶች ስርዓት እንዲሆኑ፣ነባሮች እንዲለወጡ(እንዲሻሻል) የመደንገግ እና ልምምድ ውስጥ እንዲገቡ የውሳኔ ልዕልና ያለው አንድ ጉባኤ አለን። ግብሩም ቅዱስ ስሙም ሲኖዶስ ይባላል።

@Kune Demelash kassaye
Estifanos Ze Mahitot Official

31 Jul, 14:53

1,845

የባንዳው መፅሐፍ በPDF
Estifanos Ze Mahitot Official

23 Jul, 16:44

2,118

የሟቾች ቁጥር 230 ደርሷል!

የሞሮኮ መንግስት አንድ ህፃን ልጅ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ ታፍኖ እሱን ለማውጣት የሃገሪቱ መንግስት ያደርግ የነበረውን ርብርብ እንደ አለም ዋንጫ በየሶሻል ሚዲያው ላይቭ ስንከታተል የነበርን ህዝቦች እነሆ ዛሬ ከእኛው ሃገር ላይ በደቡብ ክልል ጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት ምክንያት እስከአሁን ከ230 ሰዎች በላይ ሞተው ተገኝተዋል።

በአደጋው እስከአሁን ብዙ ተጎጂዎች ከተዳፈኑበት እንዳልወጡ እየተነገረም ነው። አሁን ባለው ሁኔታ አደጋው የተከሰተበት ቦታ አስቸጋሪ በመሆኑ አስክሬን በሰው ኃይል ለማንሳት አስቸጋሪ ሆኖአል።

ሂሊኮፍተር እና ማሽኖች በአከባቢው በአስቸኴይ መድረስ አለበት። ህብረተሰቡ በዶማ ነው ሬሳ እያፈላለገ ያለው!    
Estifanos Ze Mahitot Official

21 Jun, 18:05

2,645

ያስተምራሉ ፣ ይቀድሳሉ ፣ ያቆርባሉ ፣ ያስጠምቃሉ ፣ ያስታርቃሉ ፣ ያርሳሉ ፣ ይዘራሉ ፣ ያጭዳሉ።

አቡነ ይስሃቅ
ወላይታ ሆይ ደስስስ ይበልሽ❗️
Estifanos Ze Mahitot Official

19 Jun, 07:16

1,764

እንዲህ ያለ የሞራል ልዕልና ላይ ለመቀመጥ አማራ ሆኖ መገኜትን ይጠይቃል። ረሀባቸው ቢያመኝም የሞራል ከፍታቸው ህመሜን አክሞታል!

ኦህህህ የኔ ጀግኖች👌🙏💚💛
Estifanos Ze Mahitot Official

19 Jun, 06:49

1,377

ፋኖነት የደም ውርስ ነው!!
Estifanos Ze Mahitot Official

07 Jun, 18:44

2,023

ዛሬ ደግሞ ታቦት አክብሮ (ተሸክሞ)ስልክ የሚጎረጉር "ካህን" መጥቶላቹሃል🙄

ከእሱ የባሰ ደግሞ ከታቦቱ ፊት ተዘርፍጠው የሚታዩት ስመ "ካህናት" 😭

  አንደኛ ታቦት ቆሞ እሱ መቀመጡ ሳያንስ ጭራሽ ከታቦቱ ፊት ተዘረፈጠ🙄

ለነገሩ የእግዚአብሔርን ታቦት በመከለል ከታቦቱ ፊት በድፍረት ዝርፍጥ የሚሉ እልፍ ሁነዋል።

"የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ ታደርገዋለህ ፤ እኔም የምሰጥህን ምስክር በታቦቱ ውስጥ ታኖረዋለህ። በዚያም ከአንተ ጋር እገናኛለሁ ፤ የእስራኤልንም ልጆች ታዝዝ ዘንድ የምሰጥህን ነገር ሁሉ፥ በምስክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁለት ኪሩቤል መካከል፥ በስርየት መክደኛውም ላይ ሆኜ እነጋገርሃለሁ!"ዘጸ. 25፤21-22

አንዳንዶች  "ካህናት በክብረ በዓላት ማኅሌት ቆመው ስለሚያድሩና ስለሚደክማቸው ነው የሚቀመጡት!" ትሉ ይሆናል። የቀድሞ ጳጳሳትና ካህናትስ አይደክማቸውም ነበረ ወይ? "ከእግዚአብሔር ክብር የሚበልጥ የለም!" ብለው ድካማቸውን ስለሚቋቋሙት ነው እንጅ እኮ የቀድሞዎቹ እውነተኞቹ ጳጳሳትና ካህናትም እኮ ሳይደክማቸው ቀርቶ አይደለም "ታቦት ቆሞ አንቀመጥም!" ብለው ታቦት እስኪገባ ድረስ የሚቆሙት። እርግጥ ነው ሕማም ያለባቸውና እርጅና የተጫጫናቸው መቆም አይችሉ ይሆናል። እነዚህ መቆም የማይችሉ አባቶች መቆም የማይችሉ ከሆኑ ፊት ለፊት ተዘርፍጠው እየታዩ መሰናከያ ከመሆን ግን መታቀብ አለባቸው። መቆም ካልቻሉ ታቦቱ በሚቆምበት አካባቢ መታየት የለባቸውም። ከዚያ ዞር ማለት አለባቸው።
Estifanos Ze Mahitot Official

01 Jun, 16:40

1,728

እንደ ጲላጦስ ፍትህ ያሴረ ሁሉ እየከበረ ነው
***

ከመፈንቅለ ፓትርያሪክ እስከ ቁልቢ ገብርኤል የሐብት ክፍፍል ድረስ ጽላት አስቁመው በልበ ሙሉነት ያሴሩት አባት ጉዳይ አጀንዳ ሆኖ በቅዱስ ሲኖዶስ መታዬት ሲገባው ....ችግር የፈጠረው አካል እራሱ አጀንዳ ያዢ ከሆኑት ሰብስብ ውስጥ አካል ሆኖ ተሾሙ።

ነገ ከነገወዲያ ይህ ንግግር ሥጋ ለብሶ ቤተክርስቲያንን እንደሚሰነጥቃት እየታወቀ ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ውሎ ለፈንቃዩ አካል ህዝብ እና አብያተክርስቲያናት ለሐሳባቸው እንዲተባበሯቸው ጭምር ይመስል ተጨማሪ የሚያስተዳድሩትን ሀገረስብከት ጨምረው ወደ 7 ከፍ አድርገዋል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ አሁን አሁን የመንፈስ ቅዱስ መንበር የተነጠቀ ይመስላል። የእረኝነት ውሳኔ ጠፍቶ የምንደኝነት ሐሳቦች እየገነኑ ነው።

እንደ ጲላጦስ ፍትህ የዛተ ያሴረ የተተናኮለ ሁሉ እየተሸለመ ነው።

Kune Demelash kassaye