Последние посты Estifanos Ze Mahitot Official (@estifanoszemahitot) в Telegram

Посты канала Estifanos Ze Mahitot Official

Estifanos Ze Mahitot Official
"ይህ ቻናል የተለያዩ ሀይማኖታዊ ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።"

https://t.me/+7LOhpcH8ccgxYTM0
1,472 подписчиков
690 фото
112 видео
Последнее обновление 05.03.2025 19:33

Похожие каналы

Kristina Forex Signals
28,093 подписчиков
ERA HR Development & Performance M. Team
2,895 подписчиков
Naija Crypto Gist
1,243 подписчиков

Последний контент, опубликованный в Estifanos Ze Mahitot Official на Telegram

Estifanos Ze Mahitot Official

01 Jun, 15:50

1,433

የብልጽግና ምርኩዝ አቀባይ የሆነው ምክክር ኮሚሽን ከዐማራ ሕዝብ አንፃር ገና ከጅምሩ ምኅዳራዊ እገዳ አድርጓል።

1) የዐማራ ሕዝብ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ በመሆኑ!
2) ጦርነት ላይ በመሆኑ የፖለቲካ ጥያቄዎች ለመፍታት ተኩስ አቁም አለመደረጉ!

3) የሕዝብ ጥያቄዎች የያዙት ምሁራን ፖለቲከኞች ጋዜጠኞች የወጣቶች ተወካዮች መታሰራቸው!

4) በሕዝብ ጥያቄዎች እና በአጀንዳ ቀረፃ ሊሳተፉ የሚችሉ የፖለቲካ ድርጅቶች ፈርሰዋል። የሲቪክ ተቋማት እንዳይንቀሳቀሱ ተደርገዋል!

5) በሲቪል በወታደራዊ ተቋማት ያሉ የዐማራ ምሁራን አንገት እንዲደፉ ተደርገዋል!

6) በሃገረ መንግሥት ግንባታ የላቀ ሚና በሚጫወቱ የእምነት ተቋማት ያሉ ልሂቃን እንዲበተኑ ሃገራዊ አጀንዳ እና ተሳትፎ እንዳይኖራቸው ተደርጓል!

7) አጀንዳ ቀረፃ ላይ የሕዝብ አስተያየት ለመሰብሰብ ሁሉም የመገናኛ ዘዴዎች ዝግ ተደርገዋል!

8) መዋቅራዊ ተሳትፎ የሚደረግበት ምንም ዓይነት አደረጃጀት እና ተዋረድ የለውም!

ከላይ በተዘረዘሩት እና ባልተጠቀሱት ምክንያቶች ምክክር ኮሚሽኑ ከአገሪቱ ግማሽ የሚሆነውን ሕዝብ ምህዳር (space) እንዳይኖረው አድርጓል!

ስለዚህ ምህዳር የተከለከለ ሕዝብ በሁለተኛው ሂደት አጀንዳ ቀረፃ ላይ ሊሳተፍ የሚችልበት ዕድል የለውም። አለውም ከተባለ የሕዝብ መሠረታዊ ተሳትፎ ያልተደረገበት በመሆን ይመዘገባል!

እውነተኛ አካታች አሳታፊ የሽግግር ፍትህ እና ምክክር ይደረግ ከተባለ በተለይ ለዐማራው የተዘጋው ምህዳር መከፈት አለበት።