²³ ሳሙኤልም ወጥቤቱን፦ በአንተ ዘንድ አኑረው ብዬ የሰጠሁህን እድል ፈንታ አምጣ አለው።
²⁴ ወጥቤቱም ጭኑንና በእርሱ ላይ የነበረውን አምጥቶ በሳኦል ፊት አኖረው። ሳሙኤልም፦ ሕዝቡን ከጠራሁ ጀምሮ እስከ ተወሰነው ጊዜ ድረስ ለአንተ ተጠብቆአልና እነሆ፥ የተቀመጠልህን በፊትህ አኑረህ ብላው አለ። በዚያም ቀን ሳኦል ከሳሙኤል ጋር በላ። 1ኛ ሳሙኤል 9
🔥 ሳኦል የአባቱን ትዕዛዝ ለመፈፀም አህያ ፍለጋ ነበር የወጣው የተመለሰው ግን አህያውን ይዞ ሳይሆን ለእግዚአብሔር ህዝብ አለቃ ሆኖ የተመረጠበትን ስልጣን ነው።
🔥 አህያ ፍለጋ ተልኮ የወጣን ሰው ቀብቶ አንግሶ የሚመልስ እግዚአብሔር ብቻ ነው። ፈልገን ከወጣነው ትንሽ ነገር በላይ ጌታ ካሰበልን ትልቅ ቅባት ጋር መገናኘት ይሁንልን።
🔥 የዛሬው ያለንበት ሁኔታ የነገ ማንነታችን አይደለም። እግዚአብሔር ያልታሰበ ነገርን በህይወታችን ያደርጋል። እግዚአብሔር ካየልን እድል ፈንታ ጋር መገናኘት ይሆንልናል አሜን!!
" ከኢየሱስ ጋር መሆን ደስ ይላል "
👉 ውድ 🇪🇹 ኢትዮጵያውያን 🇪🇹 እና 🇪🇷 ኤርትራውያን 🇪🇷 ወንድሞቼ እህቶቼ ይህ እናንተን በእግዚአብሔር ቃል ለማነፅ አብሮ ለመፀለይ የተከፈተ የቴሌግራም ቻናል ስለሆነ ጆይን ያድርጉ ብሩካን ናችሁ ❤❤❤
👇👇👇👇👇👇
🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢
🟡 @elroichrist 🟡
🟡 @elroichrist 🟡
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
መልካም ቀን❤❤❤