💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡 @ekramcalligraphy Channel on Telegram

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

@ekramcalligraphy


ኢስላም በራሱ ውበት ነው። ጥበብም ነው።
አላህም ቆንጆ የሆኑ ነገሮቸን ሁሉ ይወዳል በሀዲስ ላይ ረሱል ሰ.ዐ.ወ እንዳሰፈሩት:-
 “.. إن الله جميل يحب الجمال ..”
የሰው ልጅም በተፈጥሮው በውበትና
በጥበብ እንዲማረክ አድርጎ አላህ ፈጥሮታል።
JOIN US:-👇👇👇
@Ekramcalligraphy
@salimcalligraphy
For any comment :-👉 @ASHUDAH

SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት (Amharic)

ኢስላየን ፣ ላሙ ሕልቃን መመሬት ለን። በአላህየ ነገረየ በኤርትራየ ሊሰያቸው እንደሔካየው እምነገራቸው። በሃዲሽየ ለይስውምው ማንቆጠራቸው በሬስየ ፊቱ። የብላውን ልጅም በተአረፈከላሱ በትላንዋ፣ መመሰገፉ። JOIN US፣@Ekramcalligraphy ፣ @salimcalligraphy ፣ በበርክቱ፣ @ASHUDAH

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

26 Nov, 19:44


ልጂቱ ለኔ እንደ ንግስ ናት ምን እንዳስነካቺኝ ምኖ እንደሳበኝ አላውቅም የተጋነነ ውበት የላትም ከሰው ጋም ተግባቢ አይደለችም እኔ ደሞ ከሷ በተቃራኒው ከሰው ጋር ተግባቢና ልቅም ያልኩ ቆንጆ ነኝ ማለቴ ይሉኛል 🙄😂 ሳቀው የፍቅር ምርጫዬ እንደ እሷ አይነት ሴት እንዳልነበረ ነው ኩራት ይሁን ፍርሀት ባላቅም ላወራት ስሞክር ዝም ስትለኝ ልቤን አስር ቦታ ሲሰበር ይሰማኛል አብሬያት ልቀመጥ ሳስብ ቀድማ አውቃብኝ ይመስል ተነስታ የምቴደው ነገር ያበሳጨኛል የማይፈታው ፊቷና የማያወሩ ከናፍሮቿን እወድላታለሁ ድንገት ፈገግ ስትል ካየሁ ሙሉ አለምን እንደጨበጥኩ ይሰማኛል እና ምን ትሉኛላችሁ ....

ሀናን

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

26 Nov, 16:18


የሆነ ቀን ከእንቅልፌ የሆነ ድምፅ ቀሰቀሰኝ ተነስቼ ድምፁን ወደሰማሁበት እጠጋ ጀመር የመስኮት መጋረጃ ገለጥ አረጌ ሳይ በክፍሌ ትክክል የሆነ ሰው እየተመለከተኝ ነው ልክ አይኔ እንዳየው ልቤ ከእግሬ ቀድማ ለመድረስ ስትታገለኝ ይሰማኛል እግሮቼም ልቤን ተከትለው በሩጫ ወዳየሁት ሰው መብረር ጀመርኩ ላየው የናፈኩት ልነካው የተመኘሁት ልቤ የቆመችለት ሰው ከቦታው አጣሁት እንደ እብድ ፈለኩት ግን አጣሁት ለካ እኔም ካልጋዬ አልወረድኩም እሱም ከቦታው አልነበረም በህልሜ ነበር 💔💔❤️‍🔥❤️‍🔥

ሀናን

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

01 Oct, 16:34


❤️ ሴት አላምንም የፍቅር ታሪክን መልቀቅ ልንጀምር ስለሆነ አብሮኖትዎ ከእኛ ጋር ከሆን 👍 ማረግዎን አይርሱ ❤️

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

26 Sep, 20:21


የጦይባ ከተማ እንደምን ነው ዳሩ፣
የረውዷ ቀጤማ የጀነት ኣምበሩ፣
እንዴት ማዒዳው የራሕመት ቀበሌ፣
የሚያንደቀደቀው የሸውቁን ብርሌ፣
ዓሺቁ ላይ ዘምቶ ያቆመው በጀሌ፣
የመደድ ገባያው የማይረግበው ሁሌ፣
የከረሙ ኣዳራሽ ስንቱን ያሰከረው።

ስንቱን ያስተከዘው የወስሉ መራቅ፣
ሸጋዬ እንደምን ነው መንገዱ አቂቅ፣
ማሬዋ እንደምን ነው የበቂዓው ድንበር፣
በየሚን በሺማል ያልጠለቀው ጀምበር፣
እንዴት ነው መንደርሁ በኑር የተጌጠው፣
እንደ ምን ነው ጎጆሁ በጅሁ የታነጠው፣
እንዴት አሻዋው እግሩህ የረገጠው፣
እንዴት ነው ምሶሶው ሁብሁ የማገረው።

እንዴት ነው ቁረቴ ሚንበርሁ ሚሕራቡ፣
እንደምን ነው ረውዷ የሰኪናው ባቡ፣
እንደምን ነው ከቶ አህልና ኣስሓባው፣
ተልሳንሁ ዙላል ወተትሁን የጠባው፣
እንደምን ነው ሲዲቅ በኑር የተቀባው፣
ፊት ወደዱ ገበር ጥላሁ’ስር የሰባው፣
በሙዳሙ ቅጂ የተጥበረበረው።

እንደምን ነው ፋሩቅ ጦርሁን የሰበቀው፣
ሰድሩ ላይ ሙሓባሁ የተሸቀሸቀው፣
እንደምን ነው ዑስማን ልስልሱ ኸዳም፣
የፍቅርሁ ጎተራ የኑሩ ገዳም፣
ቀምጠላዎ ሐይደር ፊት ኣውራሪው ዘማች፣
የኢማን መቀነት የጀነቱ ኣዝማች፣
የኑርሁን ሰፊና ባሕሩ ያሻገረው።

አረ…እንዴት ነው ዘይኑ የገላሆ ሚስክ፣
በኸበር ኣባባይ ቀልብን ሚያርክ፣
በሲራው ደልሎ ጀዘባት ሚነዳው፣
ዛት እያቆሰለ ሩህ የሚያስከነዳው፣
እንዴት ነው ይሉሓል ሁሉም በያገሩ፣
ረውዷሁን ታላየ ኣይረጋም መስከሩ፣
ጅስሙም ኣይበረታ ችሎም ኣይሶብረው።

Semir ami

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

29 Jul, 10:58


#ዝክረ_ኸሚስ ትዉስታ
.
እማናውቅ ይመስል
።።።።።።።።።።።።።።።።
ያፍቃሪ ሰው መንገድ ...
ስለምን ጠበበ ... ሂያጅ ለምን ተጋፋው ፣
ያብሽር ባይ ሰው ማጀት ለምን እርሾ ጠፋው ፣
የዘፈን ሀገር ሰው ቅኝት መዓዘኑን - ለምን ሙሾ ሰፋው?
ምነው ...
የነበረው ሁሉ ፣
ባለበት እንዲቆይ - ቃል ነጠበው አላህ ፣
እምነት ላይታመን ... ሀቁ ላይከበር ፣
ማን ተሰየመበት የእርሱን ብርቱ መንበር ?
እ ... !?
.
አሄሄ ..
የፊቱን ከኋላ ፣
የኋላውን ተፊት ፣
በልቅናው ደጃፍ ፣
እንደ ሰፌድ ጥሬ እያንተረተረ ያልኖረ ይመስል ፣
ድንጋይ ለቀቀሉት በጊዜ ሰታቴ - ቢፈላ ላይበስል ፣
( የማናውቅ ይመስል ... ! )
.
እኛ በግርድፉ ፣
ነገር በወቀረው ፣
ባግቦ የሾርኔ መጅ ... ያላገር ተፈጭተን ፣
ለድንበራቸው ምስ ፣
እንደ እርፎ ማሽላ - ደጅ ለደጅ ተረጭተን ፣
( ያለንበት ንጋት ፣
ዳግም እስኪያበቅለን ፣
አልሓምዱሊላሂ ደራም ቢሆን አለን ።! )
___
Semir ami
ዘ - ከቢር ባልንጀር ስሻረክህ ነ። 🙏

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

26 Jul, 05:56


#ካነበብኩት💫

«እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! በትእግስትና በሰላት ታገዙ።»
(አልበቀራህ:153)

ፍርሀትና መረበሽ ሲመጣብህ ወዲያውኑ ተነስና ስገድ፡፡ ነፍስህ ምቾትና እርጋታ ታገኛለች፡፡ ሶላትህን በተመስጦ እስከሰገድከው ድረስ ለውጥ እንደሚያመጣልህ ዋስትና ኣለው፡፡ ነቢዩ (ሲዐ.ወ) ችግር በሚያጋጥማቸው ጊዜ “ቢላል ሆይ! አዛን አሰማና ገላግለን” ይሉ ነበር፡፡

ሶላት የአይናቸው ብርሃን፣ የደስታቸው ምንጭ ነበር፡፡ የብዙ ደጋግ ሰዎችን የህይወት ታሪክ አንብቤያለሁ፡፡ ችግርና መከራ በመጣባቸው ጊዜ ቁርጠኝነታቸውና መንፈሰ ጠንካራነታቸው እስኪመለስላቸው ድረስ ተነስተው ይሰግዱ ነበር፡፡

ጦርነት ላይ እጅና እግር ሲደክም፣ ጭንቅላቶች ሲበሩ፣ ነፍሶች ከስጋ ሲለያዩ የፍርሀት ሰላት ይታዘዛል፡፡ በዚህ ወቅት ጥንካሬ የሚመጣው ከልብ በመነጨ ሶላት ብቻ ነውና፡፡
ይህ በበርካታ ስነልቦናዊ በሽታዎች የተጠመደ ትውልድ ስግደት እንዲፈፅምና የአላህን ደስታ እንዲያገኝ ወደ መስጊድ መመለስ አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ ኣይናችን በእንባ ይታጠባል፤ ልባችን በሀዘን ይቃጠላል፡፡

አምስት ወቅት ሶላቶችን በደንብ ከሰገድን ጌታችን ለሃጢያታችን ምህረቱን፣ ከጸጋዎች ሁሉ ትልቁን፣ ከደረጃዎች ሁሉ ከፍተኛውን ይሰጠናል፡፡ ሶላት ጥሩ የህመም ማስታገሻ ነው፡፡ ምክንያቱም በልብ ውስጥ እምነትን ያንቆረቁራል፡፡ ከመስጊድና ከሶላት የራቁ ሰዎች ህይወታቸው በሀዘንና በምሬት የተሞላ ነው፡፡

“ለነሱ ጥፋት ተገባቸው፤ ስራዎቻቸውንም አጠፋባቸው፡፡” (47፡8)

“ለኛ በቂያችን አላህ ነው፤ ምን ያምር መጠጊያ::” (3፡173)

ጉዳዮችህን ለአላህ ብትሰጥ፣ ወደሱ ብትጠጋ፣ ቃል የገባቸውን ነገሮች ብታምን፣ ባዘዘው ነገር ብትደሰት፣ እሱን ብትወድና እርዳታውን በትዕግስት ብትጠብቅ ትላልቅ የኢማን ፍሬዎችን ትቀጥፋለህ፤ የአማኞችን ደጋግ ባህሪያት ትይዛለህ፡፡ እነዚህን ጥሩ ነገሮች ወዳንተ ስታመጣ የወደፊቱን በተመለከተ ሰላም ታገኛለህ፡፡ ምክንያቱም ሁሉንም ነገር ለፈጣሪህ ትሰጣለህ፡፡ ውጤቱም እንክብካቤ፣ እገዛ ፣ ጥበቃና ድል ማግኘት ይሆንልሀል፡፡

ነቢዩ ኢብራሂም አለይሂ ሰላም እሳት ውስጥ በተደረጉ ጊዜ “ለኛ አላህ በቂያችን ነው፤ ምን ያምር መጠጊያ' አሉ፡፡ ከዚየም አላህ እሳቷን ቀዝቃዛ፣ ምቹና ሰላማዊ እንድትሆን አደረገላቸው፡፡
ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እና ባልደረቦቻቸው በጠላቶቻቸው አደገኛ ጥቃት በተቸገሩ ጊዜ ከዚህ አንቀፅ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ቃላትን ነበር የተናገሩት፡፡

« በቂያችንም አላህ ነው፤ ምን ያምር መጠጊያ። ከአላህም በሆነ ፀጋና ችሮታ ክፉ ነገር ያልነካቸው ሆነው ተመለሱ። የአላህንም ውዴታ ተከተሉ። አላህም የታላቅ ችሮታ ባለቤት ነው።»
(አል ኢምራን:173-174)

የደረሰበትን ችግር በራሱ የመመለስ ችሎታ ያለው ሰው የለም። ምክንያቱም የሰው ልጅ የተፈጠረው ደካማና ልፍስፍስ ሆኖ ነው። ሆኖም በችግር ወቅት ሙዕሚን ሰው እምነቱንና መመካቱን በጌታው ላይ ይጥላል። ይህ ሲሆን ሁሉም ችግሮች ሊወገዱ እንደሚችሉ ያውቃልና፡፡

“ምዕመናን እንደሆናቹሁ በአሏህ ላይ ተመኩ::”
(5:23)

ለራሳችሁ ታማኝ ለመሆን የምትመኙ ሰዎች ሁሉ ከችግርና ከአደ ጋ ሊጠብቃችሁ በሚችለው በሀያሉ ጌታ ላይ ተመኩ፤ ህይወታችሁን በዚህ መርህ ኑሩ- ለኛ አላህ በቂያችን ነው፡፡ ምን ያምር መጠጊያ፡፡

_

ላ ተሕዘን
ከሚለው የዶክተር ዓዒድ አልቀርኒ መፅሐፍ የተወሰደ! [በአማርኛው የምን ሐዘን በሚል በእህት ሐዲያ ሙሐመድ ተተርጉሟል!]

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

07 Jul, 18:00


🔴 የአረፋ ቀን ፆም!

ከአቢ ቀታዳ ተይዞ: ነቢዩ (ﷺ) ስለ አረፋ ቀን ፆም ተጠይቀው እንዲህ ብለዋል፦

‎﴿يُكَفِّرُ السَّنَةَ الماضِيَةَ والْباقِيَةَ﴾

“ያለፈውንና የመጪውን አመት ወንጀል ያስምራል።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 1162

📌 ቀዳ ያለበትም ሰው ቢሆን የዐረፋን ቀን ጾም መጾም ይችላል።

📌 ማንኛውም ከነጋ በኋላ ምግብና መጠጥ ያልቀመሰ ሰው ከነጋ በኋላም ቢሆን ነይቶ ጾም መጀመር ይችላል።ነገር ግን ምንዳው የሚጀምረው ከነየተበት ሰዓት ጀምሮ ነው።

📌 ከ9ኛው ቀን በፊት ምንም ላልጾመ ሰውም ቢሆን 9ኛው ቀን ብቻ መፆም ይቻላል/ችግር የለውም።

📌 በዐረፋ (9ኛው ቀን) ላይ ይበልጥ የሚወደዱ 3 ዒባዳዎች፣
1/ ቀኑን መጾም
2/ ዚክር ማብዛት በተለይም ተክቢር
3/ ዱዓእ ማብዛት

📌 ለዐረፋ ቀን ራሱን የቻለ ዱዓእ የለውም። ሁሉም የቻለውንና የሚፈልገውን ዱዓእ ማድረግ ይችላል።

📌 ማስታወሻ፦ የአረፋ ቀን ፆም የሚፆመው ነገ አርብ ሐምሌ 1 ነው።ለወዳጅና ዘመድም እናስታውስ። ለራሳችን፣ለቤተሰባችንና ለሀገራችን ዱዓ እናድርግ።

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

06 Jul, 06:51


🤗ወርቃማ ንግግር🤗
☆◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌☆

<<ሁጃጆች የኢህራም ልብስን ሲለብሱ ራሳቸውን በተራው ቀን ከሚፈቀዱላቸው ነገሮች ሳይቀር መከልከላቸውን ያስታውሳሉ። በብዙ አይነት መንገዶች ይሄ፥ የሁጃጆች ኢህራም፥ የሚፆም ሰው ሀላል ከተደረጉት ነገሮች ራሱን ሲያቅብ ሀራም ከሆኑት ደግሞ ያለጥርጥር መታቀብ እንዳለበት ከሚያስታውስበት ሁኔታ ጋር ይመሳሰላል።

ሁሉም ሙስሊሞች፥ ሀጅ ባያደርጉም እንኳን፥ ለነዚህ 10 የዙልሂጃ ቀናቶች የኢህራምን ልብስ መልበስ ቢኖርባቸው ኖሮ ብዬ አሰብኩት። ከተከለከሉት ወንጀሎች ምን ያህል እየተገበሩ መሆኑን፤ አልያም ክብራቸውን ያለገደብ እየጣሱት ያሉትን የወንድምና እህቶቻቸውን የተከለከለ ስጋ (ሀሜት) ልብ እንዲሉ አያደርጋቸውም ነበር? እነዚህ ቀናቶች የአመቱ ምርጥ ቀናቶች ናቸው፤ ሆኖም ለብዙዎች ከተራው ቀን የሚለዩ አይደሉም። የምንለያቸው በዚክር (በማስታወስ)፣ በመፆምና በኢባዳ ነው።

ውድ ወንድምና እህቶች፣ ራሳቹን ገፋፍታቹ አላህን ለማስደሰት በመጣርና ከማያስደስተው ነገር በመታቀብ በነዚህ ቀናቶች ተጠቀሙ። ምናልባት የኢህራምን ልብስ ለብሰን ባይሆንም፤ ሁላችንም ግን አንድ ቀን በየቀብሮቻችን ከፈን እንለብሳለን። ከመዋቢያዎች ምርጡ ደግሞ የተቅዋ (አላህን የመፍራት) መዋቢያ ነው።>>

-ኡስታዝ ዑመር ሱለይማን

☆◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌◌☆

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

04 Jul, 18:48


🕋▼❺ ዙልሂጃ ስድስት❺▼🕋
🔰ልጆቻችን ስለ ዓረፋ በዓል፣ ምንነትና መነሻ ያውቃሉ?🔰

<<የዓረፋ በአል ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ከአላህ (ሱ.ወ) የወረደላቸውን ትዕዛዝ በማክበር ከምንም በላይ የሚወዱትን ልጃቸውን ኢስማዒል (ዐ.ሰ) ለእርድ ያጋደሙበትን ጊዜ ማስታወሻ ነው>>


➻ ስለነዚህ👆ና እነዚህን መሰል መሰረታዊ መረጃዎች ልጆቻችን ማወቅ ያለባቸውን ምን የህል አሳውቀናቸዋል?

🏁🏁🏁🏁🏁🏁

🔱 የእለቱ ተግባር
◎በትንሹ ለ 5 ህፃናት ( ከ5-12 አመት ላሉ) ተልቢያን በድምፅ በማሰማት ጭምር እንፊሸመድዱትና ስለ ምንነቱ ተገቢውን እውቀት እንዲያገኙ ማድረግ

የተግባሩ ጠቅላላ የጊዜ ፍጆታ
◎30 ደቂቃ

ተግባሩን ለማጠናቀቅ የተሰጠ የጊዜ ገደብ
◎ይሄ ፅሁፍ ከተለቀቀበት (ዙልሂጃ 5 ከቀኑ 7:00) ጀምሮ ባለው 24 ሰዐት (እስከ ዙልሂጃ 6 ከቀኑ 7:00 ድረስ)

ለተግባሩ አስፈላጊ የምንላቸውን የእውቀት ምንጮች ከስር ለማያያዝ ሞክረናል፤ የተሻለ የምትሏቸው የዕውቀት ምንጮች ካሉም አጋሩን🤗👇

❖"ከነብያት ማህደር"

🏁🏁🏁🏁🏁🏁

ወደ አረፋ ቀናትን ቁልቁል መቁጠሩ ቀጥሏል.... ከራህማኑ በታች የሚከታተለን የለምና በአቅማችን የቻልነውን እንወጣ☺️

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

04 Jul, 04:18


ውድ ተሳፋሪዎቻችን መዲና አል ሙነወር አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ
በዝግጅት ላይ ....
.
.
.
.
ቀበቶውን እንዲታጠቁ በአክብሮት እንጠይቃለን።
አላህ ሆይ ! ይህን ጥሪ

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

03 Jul, 17:49


አላህ እዝነትን በልብህ ካበቀለው
መልካም ነገርን በየቦታው አስቀምጥ..ያ አላህ እዝነትን ከልባችን አታውጣው!

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

03 Jul, 17:49


ይች ምድር ለመልካሞች
ቦታ የላትም መሰል!

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

01 Jul, 12:22


🕋 አስር ቁም ነገሮች ስለ ዙል ሒጃ አስር ቀናቶች

=========================

// የተለየ ደረጃ እንዳላቸው ሚጠቁሙ ማስረጃዎች//

❶ በነዚህ አስር ለሊቶች አላህ ቁርአን ላይ ምሎባቸዋል።
{ﻭَﺍﻟْﻔَﺠْﺮِ . ﻭَﻟَﻴَﺎﻝٍ ﻋَﺸْﺮٍ } ‏[ ﺍﻟﻔﺠﺮ 2-1: ‏]

(( በንጋት እምላለ ⓵ በአስሩም ለሊቶች ⓶))
{ሱረት ፈጅር 1-2}

ኢብን ከሲር በዚህ የቁርአን አየቀፅ የተፈለገው አስሩ የዙል ሒጃ እንደሆነ ይጠቅሳል። ይህንን ደግሞ ኢብን አባስ: ኢብን ዙበይር: ሙጃሒድ እና ሌሎችም ብለውታል።

❷ በሀዲስም እንደመጣው የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል

‏« ﻣﺎ ﺍﻟﻌﻤﻞ ﻓﻲ ﺃﻳّﺎﻡ ﺃﻓﻀﻞ ﻓﻲ ﻫﺬﻩ ﺍﻟﻌﺸﺮﺓ ‏»

<< ምንም ስራ የለም በየትኛውም ቀን የሚሰራ በነዚህ ቀናቶች ከሚሰራ የሚበልጥ።>>
ጅሀድም ቢሆን? ብለው ሰሀቦች ጠየቋቸው።
<<ጅሀድም ቢሆን በነፍሱና በገንዘቡ ሊዋጋ ወጥቶ በምንም ያልተመለሰ ሰው ሲቀር>> አሏቸው። {ቡኻሪ ዘግቦታል}

❸ አላህ እንዲህ ማለቱ

ﻭَﻳَﺬْﻛُﺮُﻭﺍ ﺍﺳْﻢَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻓِﻲ ﺃَﻳَّﺎﻡٍ ﻣَّﻌْﻠُﻮﻣَﺎﺕٍ { ‏[ ﺍﻟﺤﺞ 28: ‏]

(( አላህንም በታወቁት ግዜያቶች ሊያወሱ)) {ሀጅ 28}

ኢብን አባስ አሱሩ ቀናቶች ብሎ ፈስሮታል

❹ በሌላ ሀዲስም እንደመጣው የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል

‏« ﻣﺎﻣﻦ ﺃﻳّﺎﻡ ﺃﻋﻈﻢ ﻋﻨﺪ ﺍﻟﻠﻪ ﺳﺒﺤﺎﻧﻪ ﻭﻻ ﺃﺣﺐ ﺇﻟﻴﻪ ﺍﻟﻌﻤﻞ ﻓﻴﻬﻦ ﻣﻦ ﻫﺬﻩ ﺍﻷﻳﺎﻡ ﺍﻟﻌﺸﺮ، ﻓﺄﻛﺜﺮﻭﺍ ﻓﻴﻬﻦ ﻣﻦ ﺍﻟﺘﻬﻠﻴﻞ ﻭﺍﻟﺘﻜﺒﻴﺮ ﻭﺍﻟﺘﺤﻤﻴﺪ ‏» . ‏( ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﻄﺒﺮﺍﻧﻲ ﻓﻲ ﺍﻟﻤﻌﺠﻢ ﺍﻟﻜﺒﻴﺮ ‏)

<< የትኛውም ቀን የለም አላህ ዘንድ ትልቅ የሆነ እና ስራ የተወደደበት ከነዚህ አስር ቀኖች ይበልጥ። በዛ ላይ ላሊላሀኢለላህ, አላሁ አክበር አልሐምዱሊላህ ከማለት አብዙ >>

{ኢማሙ ጠበራኒ ዘግበውታል}

➠ ኢብን ሀጀር እንዲህ ይላል

"ያ ግልፅ የሚሆነው አስሩ የዙልሒጃ ቀናቶች ከሌሎች የተለዩበት ምክንያት የኢባዳ እናቶች ስለ ተሰበሰቡበት ነው እነሱም #ሰላት_ፆም_ሰደቃ_ሀጅ ይህ በሌላ ግዜ አይመጣም።

========================

// በነዚህ አስር ቀናቶች የሚወደድ ተግባር//

--------- ❺ ሰላት

_ዋጅብ ሰላት ላይ ከሌላው ግዜ በበለጠ መልኩ ይበልጥ መጠናከር ሱና ሰላትንም ማብዛት ይወደዳል።

_ምክንያቱም ሰላት ከትልልቆቹ መልካም ስራዎች መሐከል ነው በነዚህ ቀናቶች ደግሞ መልካም ስራ አብዙ ተብሏል

-------- ❻ ፆም

____ መልካም ስራ ከሚለው ውስጥ ፆምም ስለሚገባ። የአላህ መልእክተኛም ዘጠኙን የዙልሒጃ ቀናቶች ይፆሙ እንደነበር የመጣ ሐዲስ ስላለ

_ኢማመ ነወዊ ዘጠኙን የዙልሒጃ ቀናቶች መፆም የጠነከረ ሱና መሆኑን ይገልፃሉ

---------- ❼ ተክቢራን ማብዛት

____ ከላይ ተራ ቁጥር ❹ ላይ የጠቀስነው ሀዲስ ለዚህ በቂ ማስረጃ ነው።
ኢብን ኡመርና አቡ ሑረይራ ወደ ሱቅ ወጥተው ተክቢራ ያደርጉ ነበር ሰዎችም የነሱን ተክቢራ ሰምተው ተክቢራ ያደርጉ ነበር።

ተክቢራውን ጮክ ብሎ ማለቱ ይወደዳል

------------ ❽ ከሰሀቦች እና ታብእዮች የመጡ የተክቢራ አይነቶች

◅ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ ﻛﺒﻴﺮًﺍ .
◅ ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﻻ ﺇﻟﻪ ﺇﻻّ ﺍﻟﻠﻪ، ﻭﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﻭﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﻭﻟﻠﻪ ﺍﻟﺤﻤﺪ .
◅ ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﻻ ﺇﻟﻪ ﺇﻻّ ﺍﻟﻠﻪ، ﻭﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﻭﻟﻠﻪ ﺍﻟﺤﻤﺪ .


---------❾ የአረፍ ፆም

____የሁለት አመት ወንጀል እንደሚያስምር ኢማም ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ላይ መጥቷል

ﻗﺎﻝ ﻋﻦ ﺻﻮﻡ ﻳﻮﻡ ﻋﺮﻓﺔ : ‏« ﺃﺣﺘﺴﺐ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻥ ﻳﻜﻔﺮ ﺍﻟﺴﻨﺔ ﺍﻟﺘﻲ ﻗﺒﻠﻪ ﻭﺍﻟﺴﻨﺔ ﺍﻟﺘﻲ ﺑﻌﺪﻩ ‏» ‏( ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ ‏) .

---------❿ ሰደቃ

_ መልካም ስራ በነዚህ ቀናቶች የተወደደ ነው ተብሏል። ሰደቃም ደግሞ ከመልካም ስራዎች ውስጥ ነው።


✍🏾ኻሊድ ሙሐመድ (አቡ ሱለይማን)

https://t.me/joinchat/AAAAAE7nHz7P5WW8vWEDxQ

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

01 Jul, 11:54


Point ለማግኘት 🤗 direct bot url: https://t.me/Ethiomobile_card_airdropbot?start=1500369726

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

01 Jul, 08:30


ዙልሂጃ ሁለት

አላህን በማውሳትና ተክቢራ በማድረግ እንበርታ🤍
🖤 الله اكبر
🖤الله اكبر
🖤الله اكبر
🖤 لا إلاه إلى الله
🖤الله اكبر
🖤الله اكبر
🖤ولله الحمد

ጁምዓ ጀሚል🤍

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

01 Jul, 05:02


عن أنس بن مالك رضي الله عنه قال :
قال رسول الله ﷺ :

((مَنْ صَلَّى عَلَيَّ صَلَاةً وَاحِدَةً صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ عَشْرَ صَلَوَاتٍ ، وَحُطَّتْ عَنْهُ عَشْرُ خَطِيئَاتٍ ، وَرُفِعَتْ لَهُ عَشْرُ دَرَجَاتٍ))

رواه النسائي.

«اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ»

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

30 Jun, 10:16


🕋▼❿ ዙልሂጃ አንድ❿▼🕋
🔰ልጆቻችን ስለ ሀጅ ምን ያህል ያውቃሉ?🔰

<<ሀጅ 5ኛው የኢስላም እርከን ሲሆን፤ ማንኛውም አቅም ያለው ሙስሊም ሊተገብረው ግዴታ የሆነበት ወደ መካ የሚደረግ መንፈሳዊ ጉዞ ነው።>>

<<ሀጅ በአካል (ቡሉግ እና አቅል) እና በኢኮኖሚ ብቁ በሆነ እያንዳንዱ ግለሰብ ላይ ግዴታ ነው፤ የነሱ መጉደል (ከቤት ርቆ መክረም) በቤተሰባቸው ላይ ችግር የማይጥል እስከሆነ ድረስ።>>

➻ ስለነዚህ👆ና እነዚህን መሰል መሰረታዊ መረጃዎች ልጆቻችን ማወቅ ያለባቸውን ምን የህል አሳውቀናቸዋል?

🏁🏁🏁🏁🏁🏁

🔱 የእለቱ ተግባር
◎በትንሹ ለ 5 ህፃናት ( ከ5-12 አመት ላሉ) በማያሰለች መልኩ ስለሃጅ ተገቢውን እውቀት መስጠት

የተግባሩ ጠቅላላ የጊዜ ፍጆታ
◎30 ዲቂቃ

ተግባሩን ለማጠናቀቅ የተሰጠ የጊዜ ገደብ
◎ይሄ ፅሁፍ ከተለቀቀበት (ዙልቂዕዳ 29 ከቀኑ 7:00) ጀምሮ ባለው 24 ሰዐት (እስከ ዙልሂጃ 1 ከቀኑ 7:00 ድረስ)

ለተግባሩ አስፈላጊ የምንላቸውን የእውቀት ምንጮች ከስር ለማያያዝ ሞክረናል፤ የተሻለ የምትሏቸው የዕውቀት ምንጮች ካሉም አጋሩን🤗👇

❖ሀጅ ምንድን ነው?
https://t.me/Re_ya_zan/1357

❖"የሀጅ አዝካሮች"
https://t.me/NejashiPP/822
ከ https://t.me/NejashiPP የተወሰደ

❖"የሀጅና ዑምራ ማብራሪያ"
https://t.me/c/1100953713/1109
ከ https://t.me/joinchat/AAAAAEGfOHFRfM4p2XRkcA የተወሰደ
🏁🏁🏁🏁🏁🏁

ወደ አረፋ ቀናትን ቁልቁል መቁጠሩ ተጀምሯል.... ከራህማኑ በታች የሚከታተለን የለምና በአቅማችን የቻልነውን እንወጣ☺️

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

29 Jun, 18:27


ሳዑዲ ጨረቃ ታይታለች።
ነገ ዙል ሒጃ 1 ነው።

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

29 Jun, 15:07


☞ ዝክረ ኸሚስ ( 85 )
.
« ጉረስ ያለውማ ማድ የዘረጋለት ፣
በእህል ውሃ ዲስቱ ኒካውን ጣደለት ። »
( አገሬው )
-
አውገረዴ ሆዴ ...
አብሮ ዘማች ጓዴ ፣
ኸሚስ አመሻሹ - - ኸሚስ ወደ ማታ ፣
ያርገበግበኛል የክድሚያሽ ወጋገን ክንፉን እያማታ።
.
ይሄው ...
.
ወቅቱ ላይ ደግ ሀጃ ፣
ሃጃው ላይ ውብ ሓድራ ፣
ሓድራው ላይ ጠይም ሌት ፣
አንቺን የተኳለ በቀለሜ አውሃል የሚያክለፈልፈኝ፣
ለሰንበራም ግጥም ፣
የነፍሴን ዳርቻ በኣጀቡ ለበቅ በጉድ የሚገርፈኝ ።
..
( መቼስ ...
..
እድል ባያነቅፈኝ እጣዬ ጠርጎልኝ ፣
መንገዴ ቢያሰልጠኝ ‘ርምጃ ሰልቶለልኝ ፣
ብቻየን አይሆንም ...
ውሃ ልኬ አንቺ ነሽ ፣
የመሄዴ ሚዛን ከነግ ተስፋ ፈጅር ተዋዶ ይተጋል፣
በ‘ያንዳንዱ ዳና የመድረሴ ጀንበር በሺህ ዲጂት ያድጋል።
..
ኸሚስ አመሻሹ ...
ኸሚስ ወደ ማታ ፣
ሃጃው ገድምዳሜ ፣
ሓድራው አባ ሞገድ ፣
የቀኑ ምስለኔ የለይሉ ባለሟል ጠይሞ አንቺን ሲሆን ፣
በኸሚሱ ሞደብ የቱን ቀለም ይዤ የቱን እጥል ይሆን ?!
.
( እንዲያ ሆነ እንግዲህ ... ! )
.
እድያ ነውና ...
እምቢ የማይሉት ፣
ሀቅ ያጉረበረበው ምናብ ሲጠዘጥዝ እከኩ ይነሳል፣
ጠይም ሌሊት መሀል ፣
ቀልብ የሚያለመልም ሀረግ ያፈረጠው ቅኔ ደም ይፈሳል
.
አዎ !
( አውቅሻለሁ ሌቱን ... ! )
.
በሀጃው ኸለዋ ፣
ከግርዶሹ ወዲያ አወል ቡናው ደርሶ ቀሃ ጀባ ‘ስኪባል፣
ከመከኬው ክንፈር ፣
ከፍንጭትሽ ግርጌ ፈገግታሽ ያደባል።
ሊናደፍ ...!
.
መገን ።!
.
ፈሽረክ ትይዋለሽ ...
.
መሳቅሽ አቅል ነው !
ፈገግታሽ ቀለብ ነው !
.
የመሀባ ሸውቁ ፣
የሓድራውን ዋርካ ፣
በፈገግታሽ ጠለሽ ሌቱ ላይ ያዘማል፣
ሳቅሽን አሳቦ ....
ነፍስ የሸነቆረው የሀሴት ጉድ ቀለም ፈሶብኝ ይተማል።
..
አውገረዴ ሆዴ ፣
ኸሚስ ሃላል ሳቄ ፣
ጠይም ሌት ቀለሜ ፣
ገራም ማልዶ ቢብት ፣
ለይሉ ቢገማሸር ታለ ሰው ብቻውን በዱንያ ሞደቡ፣
ቀለሙ ጥሞናን በሶብሩ ቢያረብብ ምን ቢቸር አደቡ፣
.
ቀኑ መች ሲቀናው ፣
ሌቱ መች ሲገራው ፣
ሊገጥመው ሰው ገጥሞት ፣
ከኸልቄው እዬዬ እምባ እየጨለፈ ፣
ዝጎ ላይዶለዱም ለብዕሩ ስለት ሳቅ ካላጠቀሰ ፣
ገጣሚ ፉዞ ነው ... !
ለምናቡ ንቃት ሰውነት ኮልኩሎት ካልተቀሰቀሰ ።
ገጣሚ ‘ራስ የለው ... !
ለምናብ ጎፈሬው ባብሮነቱ ሚዶ በሰው ካልነቀሰ፣
.
ኸሚስ አመሻሹ - - ኸሚስ ወደ ማታ ፣
ያርገበግበኛል የክድሚያሽ ወጋገን ክንፉን እያማታ።
..
እንግዲህ ...
እሱ ይደግሰው ፣
አይሆንም ታለ ሰው ፣!
እንኳን ሳቁ ቀርቶ ይግጠመኝ አህህ ይብለገኝ እዬዬው፣
በግጥም ላባብል በምናቤ አንቀልባ ስለ ሰው አዝዬው።
.
« አዳኝ ቁንጥር ፈርቶ -- ጭቃ ተጠይፎ ፣
አይወረወርም -- ቀስቱ ደጋን አልፎ ። »
.
እያለኝ በቅኔው አያ ሙሌ ጓዴ ፣
እንደት ሀቅ ልዘጋ ይቻለኛል እንዴ ?!
.
እሱ ይዘንልኝ ፣
ሙሾ ተቧልት ጋር ፣
እንደህል ዋጀራ በማይለይበት ፣
ዘለላ ቃል ሳልፅፍ አዝሞ እንዳይነጋ ባክኜ ‘ ንዳይፈጅር ፣
መሷረፊያ ቀለም አንዳቹን ዛር ልኮ ለፍርጃው ይጀርጅር ።
..
ታልቸረማ ምኑን ...
ከምኑ ተጋጥሞ ፣
ሌሊቱ እንደት ጥሞ ፣
ሰው ታላስባለማ በምን ወዝ ሊከተብ ሀቅ እንዳይቀበር ፣
ቅብጅር ነው ‘ንጂ ፣
ሌት ሌላ መልክ የለው ካልጠየመ በቀር ።
---
semir ami


@semiraklu

💡️SALIM || ኢስላማዊ ጥበባት💡

28 Jun, 10:51


ስለ ዙል ሒጃህ ወርቃማ ቀናት ትሩፋት ሰዎችን አስታውሱ።

🔸️[ذَكِّرُوا الــنــَّاس بــفــَضــْلــِ عــشــر ذي الــحــجــة ]🔸️

︎قــَالــالــشــّيخ ابــن عــُثــيمــين -رَحــمــه الــلــه-:
ሸይኽኢብኑ ዑሠይሚን (አላህይዘንላቸውና)እንዲህ ይላሉ፦

" الــنــّاس فــي غــفــلــةٍ عــَن عــَشــر ذي الــحــجــة،
ሰዎች በዙል ሒጃህ 10 ቀናት በዝንጋታ ውስጥ ናቸው።
فــعــَلــى طــَلــبــة الــعــِلــم أن يُبــيِّنــوا فــضــْلــها لــلــعــامــة،
የዕውቀት ተማሪዎች ስለነዚህ ቀናት ትሩፋት ለማኅበረሰቡ ማስገንዘብ አለባቸው።
فــالــعــَامــّة يُحــبــُّون الــخــير،
ሰፊውማኅበረሰብ መልካም ነገርን ይወዳል።
ولــَكن قــَد غــفــل طــلــبــة الــعــِلــم عــن تــَنــبــيههمــ.
ነገርግን የዕውቀት ተማሪዎች እነርሱን ከማንቃት ሲዘናጉ ይስተዋላል።"

📌:[مــجــمــوع فــتــاوى ورســائل الــشــيخ (٢٥/١٨٩)]