Canal Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council @eiasc1 en Telegram

Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
9,085 Suscriptores
952 Fotos
24 Videos
Última Actualización 12.03.2025 11:54

The Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council: Overview and Significance

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ከዚህ በፊት የተመለከተ የአማራ ገዢዎች አነሰ ብቃትን እንዲሰጣቸው በማስታወቂያ ንዴት ተመልከትዋል። እንደእርስዎ ያለን በኮንስትራኒ ቦታ ላይ ይችላሉ። የህዝቢ ይወስዳል ወይም የአማራ እስም ይባላል ወደ እርስዎ ማድረጓሌ ይጣይ ይበልበሉ ይቀሩሙት። ይህ ኩባንያ የእስልምና ሀብት እና የማብባለምነት አካል ይደርሳል። ይህ ዓለም ሙሉ ይወስዳል።

የእስልምና ሥርዓቶች እና የተወራዥ ተየር ወር ይሆኑ?

ይህ ድርጅት በዚህ ግን እንደ አማራ በውአል እንዲሁም ይህ የድርጅት ም/ቤት ይኖድ እንደ አማራ አለ እንዲሁም ይህ ይሰጡል ይኑዋል።

ይህ እንዲሁ አቅም ወ ይህ የፊታው ማሻሻል እስልምና ወይም ይህ ይለዋል ይለዋል።

Canal de Telegram Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት እንዴት ነው? ምን ነገር ነበር? የሚፈልጉትን ህዝብ እና ዘርፍ መሠረት ለማድረግ እየተነገረን ስለዚህ ኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የቀረበ አገልግሎት ለመቅጣት በተጎዳው የሁለትን ህዝብ ሲሆኑ ለጥሩ ተግባርነት በጽሁፍ እና በቅጥዮቹ ለማድረግ አስፈላጊ ነው። የመሰረቱን ድርጅቶች እና ውድ ግምትን በማድረግ አንድ የሚሠሩት ኦነጋዴ እና ቸገሪዎች አሉ። ወደ ቴምሰጥ የመወሰን ሀበሻዎች ሴት ልጆችን በግንብ በማጥቃት የሚሰረቱትን ደንብና የውድ ስራ እርዳን እንዲደርስ ከቴምሰጥ ጋር የምረቃ አካባቢ እና መረጃዎች እንጠቀማለን። ከዚህ በታች በመጠቀም በቴምሰጥ ሊሳይቷችን መረጋገጥ ይችላሉ።

Últimas Publicaciones de Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

Post image

መጋቢት 3፣ 2017 ዓ.ል | ረመዷን 12፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የውዱን ነብያችንን (ሰ. ዐ.ወ) ክብር የተዳፈረው ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ጠቅላይ ምክር ቤቱ በትኩረት እየሰራ ነው።
•••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ
ውዱ ነብያችን (ሰ. ዐ.ወ) ሲነኩ ከልባችን የምንታመም ቢሆንም ችግሩን የምነፈታው ግን በህጋዊ አግባብ ነው ብለዋል።

ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ አክለውም ግለሰቡ ለጊዜው ተደብቆ ቢሰወርም ተይዞ ለህግ እንዲቀርብ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የተቀናጀ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ግለሰብንና ተቋምን ለይቶ የሚረዳ በመሆኑ የተፈፀመው ትንኮሳ ከሀይማኖት ተቋማት ጋር ያለን መልካም ግንኙነት አይሻክረውም ነው ያሉት።

የሀይማኖት ተቋማት ግለሰቡ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በቅርበት ሊሰሩ ይገባል ያሉት ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም የመንግስት የፀጥታና የደህነት አካላት ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።

ተመሳሳይ ድርጊቶች ከተፈፀሙ ፈፅሞ አንታገስም ያሉት ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ ህዝበ ሙስሊሙ ግለሰቡ በህግ እንዲጠየቅ አስፈላጊው ስራ እየተሰራ መሆኑም በመገንዘብ ውጤቱን በትዕግስት እንዲጠብቅም አደራ ብለዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍን ይከታተሉ | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

12 Mar, 09:06
468
Post image

2፣ 2017 ዓ.ል | ረመዷን 11፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ              
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ዳሸን ባንክ የ6 መቶ ሚሊየን ብር የውጪ ምንዛሪ ለአሏህ እንግዶች (ለሁጃጆች) ከወዲሁ ማዘጋጀቱን ገለፀ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

ዳሸን ባንክ ለ1446/2017 ሁጃጆች መስተንግዶና አገልግሎት የሚውል የ6 መቶ ሚሊዮን ብር አቻ የአሜሪካን ዶላር ከወዲሁ ዝግጁ ማድረጉን በሸራተን አዲስ ባዘጋጀው የኢፍጣር መርሃ ግብር ላይ ይፋ አድርጓል።

በዚህ የኢፍጣር መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ የፕሬዝደንቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዑስታዝ አቡበከር አህመድ እንደተናገሩት ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከዳሸን ባንክ ጋር ጠንካራ የስራ ግንኙነት ያለው መሆኑን ጠቅሰዋል።

ዑስታዝ አቡበከር አክለውም የዳሸን ባንክ ከወለድ ነፃ አገልግሎት (ዳሸን ሸሪክ) ይህን ያህል መጠን ያለው የውጭ ምንዛሪ ከወዲሁ ማዘጋጀቱ ባንኩን ቀዳሚ ያደርገዋል ለዚህም በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስም እናመሰግናለን ብለዋል።

ባንኩ ሸሪአ መር የሆነ አገልግሎቱን ለማስፋትና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የዳሸን ሸሪክ አገልግሎቱን የበለጠ ማሳደግ ይኖርበታል ያሉት ዑስታዝ አቡበከር
ቀሪ የረመዷን ቀናቶችን አሏህ በሚወደው ስራ ላይ በማሳለፍ ተጠቃሚ ልንሆን ይገባልም ብለዋል።

ረመዷን የአንድነት፣ የመተሳሰብና የመተባበር ወር መሆኑን በመጥቀስ ባንካቸው ለደንበኞቹ ተመሳሳይ ኢፍጣር ሲያዘጋጅ መቆየቱን ያስታወሱት ደግሞ የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው አለሙ ናቸው።

የባንኩ ከወለድ ነፃ አገልግሎት ዋና መኮንን አቶ መስፍን ገዙ በበኩላቸው ዳሸን ባንክ ላለፉት አስርት  ዓመታት የማሕበራዊ አገልግሎት ኃላፊነቱን በተሻለ ሁኔታ እየተወጣ እንደሚገኝ አንስተዋል።

ዳሸን ባንክ የሸሪክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የጀመረበትን ሰባተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በልማትና በበጎ አድራጎት ተግባር ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶች ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ መለገሱን የጠቀሱት አቶ መስፍን በሶማሌ ክልል በጥቃቅንና አነስተኛ ለተሰማሩ 1 ሺህ ሴቶች የ100 ሚሊዮን ብር ከወለድ ነፃ ብድር በመስጠት ዜጎች ውጤታማ እንዲሆኑ መቻሉንም አልከዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍን ይከታተሉ | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

12 Mar, 02:53
784
Post image

29፣ 2017 ዓ.ል | ረመዷን 8፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ              
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መጋቢት 07 ለሚካሄደውን ሐገር ዓቀፍ የቁርአን ውድድር ሶስት ክልሎችና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር  የሚወክላቸውን ተወዳዳሪ አሳወቁ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አዘጋጅነት «ቁርዓን የእውቀት እና የሰላም ምንጭ» በሚል መሪ ሃሳብ መጋቢት 7/17  ዓ.ል (ረመዷን 16/446 ዓ.ሒ) በአዲስ አበባ ሀገር አቀፍ የቁርአን ውድድር ይካሄዳል።

በዚህ ሀገር አቀፍ የቁርአን ውድድር ሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ይሳተፋሉ።

የክልልና ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳይ ምክር ቤቶች ክልላቸውንና ከተማ አስተዳደራቸውን ወክለው በማጣሪያው ውድድር ላይ የሚሳተፉ ቃሪዎቻቸውን በመለየት ላይ እንደሚገኙ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የፈትዋና ምርምር ዘርፍ ተጠሪና የቁርአን ውድድሩ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሸይኽ እድሪስ ዓሊ ሁሴን ገልፀዋል።

ሸይኽ እድሪስ አሊ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ እንደገለፁት ውድድሩ ይፋ ከተደረገበት ዕለት ጀምሮ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ወደ ተወዳዳሪ ልየታ ገብተዋል።

ሼይኽ እድሪስ አክለውም እስከ አሁን የኦሮሚያ፣ የሶማሌና የሐረር ክልሎች እንዲሁም የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የማጣሪያ ውድድር ያለፉ ተወካዮቻቸውን አሳውቀዋል ብለዋል።

የተጠቀሱት ክልሎችና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር እያንዳንዳቸው ሁለት ወንዶችና አንድ ሴት የፍፃሜ ተወዳዳሪ ለይተው ማሳወቃቸውን የተናገሩት ሼይኽ እድሪስ ሌሎች ክልሎችና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቀጣይ ቀናት በማጣሪያ ውድድር የመረጧቸውን ተወካዮቻቸው እንደሚያሳውቁ ይጠበቃልም ብለዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍን ይከታተሉ | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

08 Mar, 14:50
736
Post image

የካቲት 29 2017 ዓ.ል | ረመዷን 8፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በኢስላማዊ አንድነት ላይ ሲመክር የቆየው የመካው ጉባኤ የዓለም ሙስሊሞች ለአንድነት እንዲሰሩ የሚያሳስብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ ከጉባኤው ጎን ለጎን ጠቃሚ ውይይቶችንም አድርገዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••

በዓለም ሙስሊሞች አንድነት ላይ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲመክር የቆየው የመካው ጉባኤ ትላንት ሌሊት ተጠናቋል።

በጉባኤው ላይ ከመላው ዓለም የተጋበዙ የኢስላም ሊቃውንትና የሀይማኖቱ መሪዎች የተሳተፉበት ሲሆን በጉባኤው ማጠቃለያ ከተሳታፊዎች የተነሱ ሃሳቦችን የያዘ የጋራ የስምምነት ሰነድ ተዘጋጅቶ ለሁሉም ተሳታፊዎች እንዲደርስ ተደርጓል።

የጋራ ስምምነት ሰነዱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢስላማዊ አንድነትን ለመፍጠርና ለማጠናከር እንደሚያግዝም ተስፋ ተጥሎበታል።

ጉባኤው የዓለም ሙስሊሞች ለኢስላማዊ አንድነት ቅድሚያ ሰጥተው በትኩረት መስራት እንዳለባቸው የሚያሳስብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ነው የተጠናቀቀው።

ሀገራቸውን ወክለው በመካው የሙስሊሞች አንድነት ጉባኤ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት የክብር ዶክተር ሸይኸ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ ከጉባኤው ጎን ለጎን ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከሌሎች አቻ ተቋማት ጋር አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ነጥቦች ዙሪያ ከተለያዩ ሀገራት ሙፍቲዎች፣ ኡለማዎችና ከመጅሊስ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።

ፕሬዝደንቱ በዛሬው ዕለት (ቅዳሜ) ውሏቸውም ከዓለም አቀፉ የፊቅህ ልሂቃን ጥምረት ሰብሳቢ ዶክተር ቁጥቢ ሳኖ፣ ከቡርኪና ፋሶ ፕሬዝደንት አማካሪ ዶክተር አቡበከር አብደላ፣ ከአፍሪካ ዑለማዎች ሰብሳቢ ዶክተር ሰዒድ እና ሌሎች መንፈሳዊ መሪዎች ጋር በኢስላምና ሀገራዊ ትውውቅ ዙሪያ መክረዋል።

በተጫማሪም በግንባታ ላይ የሚገኘው የንጉስ ነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ ሊፋጠን በሚችሉባቸው መንገዶች ዙሪያ ከዓለም አቀፉ ኢስላማዊ ዕርዳታ ድርጅት (ራቢጣ) ዋና ፀሀፊ የክብር ዶክተር ሙሀመድ አብዱልከሪም አልኢሳ ጋር ገንቢ ውይይት አድርገዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ/ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍን ይከታተሉ| Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1

08 Mar, 14:10
743