بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጠቅላይ ምክር ቤቱ በህዳሴው ግድብ አቅራቢያ ለሚገነባው ራህማ መስጂድ የፌሮ ብረት ድጋፍ አደረገ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ባምዛ ቀበሌ ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ በቅርብ እርቀት ለሚገነባው ራህማ መስጂድ አራት ሚሊዮን ብር ወጪ ያደረገበትን 235 ኩንታል የፌሮ ብረት ድጋፍ አድርጓል።
በድጋፍ ርክክቡ ወቅት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ስራ አስፈፃሚ አባልና የተቋማት ዘርፍ ተጠሪ ሼይኽ አልመርዲ አብዱላሂ አሽዌይ እንደተናገሩት ከሆነ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከበወረት ድጋፍ በተጨማሪ የመስጂዱ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ህዝበ ሙስሊሙን የማስተባበር ሚና እየተጫወተ ነው።
በታላቁ የረመዷን የመጀመሪያ ጁምዓ በቤንሸጉል ጉምዝ ክልል ከታላቁ ህዳሴ ግድብ በቅርብ እርቀት ለሚገነባው አል ራሕማን መስጂድ የገቢ ማሠባሰቢያ መርግብር በሀገር አቀፍ ደረጃ ስለሚካሄድ ህዝበ ሙስሊሙ ድጋፍ እንዲያደርግም ሸይህ አልመርዲ አብዱሏሂ ጥሪ አቅርበዋል።
የፌሮ ብረቱን ከጠቅላይ ምክር ቤቱ የተረከቡት የአል ራሕማን መስጂድ ተወካይ አቶ ኩራባቸው ዓለዊ በበኩላቸው የመስጅዱ የመሰረት ደከንጋይ ህዳር /09/ 2017 በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም መቀመጡን አስታውሰው ከህዳር 24 2017 ጀምሮ መስጅዱ በግንባታ ላይ መሆኑን ገልፀዋል።
አቶ ኩራባቸው አክለውም ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለመስጅዱ ግንባታ የፌሮ ብረት ድጋፍ ማድረጉ የመስጅዱን ግንባታ በማፋጠን በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ያግዛል ብለዋል።
ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለራህማ መስጅድ ግንባታ ላደረገው የብረት ድጋፍ በክልሉ ሙስሊምና በመስጂዱ ኮሚቴ ስም አመስግነው ከዚህ በፊትም ከተውፊቅ (ፍል ውሐ)፣ ከሰላም (ቄራ)፣ ከአቡ ሁረይራ (ወሎ ሰፈር) እና ከታላቁ ንጎስ ነጃሺ (አፍሪካ ህብረት) መስጂዶች ከህዝበ ሙስሊሙ ለመስጅዱ ማሰሪያ ገንዘብ መሰብሰቡን አስታውሰዋል።
በቀጣይም በታላቁ የረመዷን ወር የመጀመሪው ጁምዓ አዲስ አበባ ላይ በሚገኙ መሳጂዶች ድጋፍ ለማሰባሰብ ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13