بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የውዱን ነብያችንን (ሰ. ዐ.ወ) ክብር የተዳፈረው ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ጠቅላይ ምክር ቤቱ በትኩረት እየሰራ ነው።
•••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጡት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ
ውዱ ነብያችን (ሰ. ዐ.ወ) ሲነኩ ከልባችን የምንታመም ቢሆንም ችግሩን የምነፈታው ግን በህጋዊ አግባብ ነው ብለዋል።
ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ አክለውም ግለሰቡ ለጊዜው ተደብቆ ቢሰወርም ተይዞ ለህግ እንዲቀርብ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የተቀናጀ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ግለሰብንና ተቋምን ለይቶ የሚረዳ በመሆኑ የተፈፀመው ትንኮሳ ከሀይማኖት ተቋማት ጋር ያለን መልካም ግንኙነት አይሻክረውም ነው ያሉት።
የሀይማኖት ተቋማት ግለሰቡ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በቅርበት ሊሰሩ ይገባል ያሉት ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም የመንግስት የፀጥታና የደህነት አካላት ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።
ተመሳሳይ ድርጊቶች ከተፈፀሙ ፈፅሞ አንታገስም ያሉት ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ ህዝበ ሙስሊሙ ግለሰቡ በህግ እንዲጠየቅ አስፈላጊው ስራ እየተሰራ መሆኑም በመገንዘብ ውጤቱን በትዕግስት እንዲጠብቅም አደራ ብለዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍን ይከታተሉ | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1