Últimas publicaciones de Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council (@eiasc1) en Telegram

Publicaciones de Telegram de Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
9,085 Suscriptores
952 Fotos
24 Videos
Última Actualización 12.03.2025 11:54

El contenido más reciente compartido por Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council en Telegram

Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

12 Mar, 09:06

468

መጋቢት 3፣ 2017 ዓ.ል | ረመዷን 12፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የውዱን ነብያችንን (ሰ. ዐ.ወ) ክብር የተዳፈረው ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ጠቅላይ ምክር ቤቱ በትኩረት እየሰራ ነው።
•••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ
ውዱ ነብያችን (ሰ. ዐ.ወ) ሲነኩ ከልባችን የምንታመም ቢሆንም ችግሩን የምነፈታው ግን በህጋዊ አግባብ ነው ብለዋል።

ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ አክለውም ግለሰቡ ለጊዜው ተደብቆ ቢሰወርም ተይዞ ለህግ እንዲቀርብ ጠቅላይ ምክር ቤቱ የተቀናጀ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ግለሰብንና ተቋምን ለይቶ የሚረዳ በመሆኑ የተፈፀመው ትንኮሳ ከሀይማኖት ተቋማት ጋር ያለን መልካም ግንኙነት አይሻክረውም ነው ያሉት።

የሀይማኖት ተቋማት ግለሰቡ በህግ ቁጥጥር ስር እንዲውል ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ጋር በቅርበት ሊሰሩ ይገባል ያሉት ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም የመንግስት የፀጥታና የደህነት አካላት ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።

ተመሳሳይ ድርጊቶች ከተፈፀሙ ፈፅሞ አንታገስም ያሉት ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ ህዝበ ሙስሊሙ ግለሰቡ በህግ እንዲጠየቅ አስፈላጊው ስራ እየተሰራ መሆኑም በመገንዘብ ውጤቱን በትዕግስት እንዲጠብቅም አደራ ብለዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍን ይከታተሉ | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

12 Mar, 02:53

784

2፣ 2017 ዓ.ል | ረመዷን 11፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ              
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ዳሸን ባንክ የ6 መቶ ሚሊየን ብር የውጪ ምንዛሪ ለአሏህ እንግዶች (ለሁጃጆች) ከወዲሁ ማዘጋጀቱን ገለፀ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

ዳሸን ባንክ ለ1446/2017 ሁጃጆች መስተንግዶና አገልግሎት የሚውል የ6 መቶ ሚሊዮን ብር አቻ የአሜሪካን ዶላር ከወዲሁ ዝግጁ ማድረጉን በሸራተን አዲስ ባዘጋጀው የኢፍጣር መርሃ ግብር ላይ ይፋ አድርጓል።

በዚህ የኢፍጣር መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የጠቅላይ ምክር ቤቱ የፕሬዝደንቱ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዑስታዝ አቡበከር አህመድ እንደተናገሩት ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከዳሸን ባንክ ጋር ጠንካራ የስራ ግንኙነት ያለው መሆኑን ጠቅሰዋል።

ዑስታዝ አቡበከር አክለውም የዳሸን ባንክ ከወለድ ነፃ አገልግሎት (ዳሸን ሸሪክ) ይህን ያህል መጠን ያለው የውጭ ምንዛሪ ከወዲሁ ማዘጋጀቱ ባንኩን ቀዳሚ ያደርገዋል ለዚህም በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስም እናመሰግናለን ብለዋል።

ባንኩ ሸሪአ መር የሆነ አገልግሎቱን ለማስፋትና የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የዳሸን ሸሪክ አገልግሎቱን የበለጠ ማሳደግ ይኖርበታል ያሉት ዑስታዝ አቡበከር
ቀሪ የረመዷን ቀናቶችን አሏህ በሚወደው ስራ ላይ በማሳለፍ ተጠቃሚ ልንሆን ይገባልም ብለዋል።

ረመዷን የአንድነት፣ የመተሳሰብና የመተባበር ወር መሆኑን በመጥቀስ ባንካቸው ለደንበኞቹ ተመሳሳይ ኢፍጣር ሲያዘጋጅ መቆየቱን ያስታወሱት ደግሞ የዳሸን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው አለሙ ናቸው።

የባንኩ ከወለድ ነፃ አገልግሎት ዋና መኮንን አቶ መስፍን ገዙ በበኩላቸው ዳሸን ባንክ ላለፉት አስርት  ዓመታት የማሕበራዊ አገልግሎት ኃላፊነቱን በተሻለ ሁኔታ እየተወጣ እንደሚገኝ አንስተዋል።

ዳሸን ባንክ የሸሪክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የጀመረበትን ሰባተኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በልማትና በበጎ አድራጎት ተግባር ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶች ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ መለገሱን የጠቀሱት አቶ መስፍን በሶማሌ ክልል በጥቃቅንና አነስተኛ ለተሰማሩ 1 ሺህ ሴቶች የ100 ሚሊዮን ብር ከወለድ ነፃ ብድር በመስጠት ዜጎች ውጤታማ እንዲሆኑ መቻሉንም አልከዋል።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍን ይከታተሉ | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

08 Mar, 14:50

736

29፣ 2017 ዓ.ል | ረመዷን 8፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ              
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
መጋቢት 07 ለሚካሄደውን ሐገር ዓቀፍ የቁርአን ውድድር ሶስት ክልሎችና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር  የሚወክላቸውን ተወዳዳሪ አሳወቁ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አዘጋጅነት «ቁርዓን የእውቀት እና የሰላም ምንጭ» በሚል መሪ ሃሳብ መጋቢት 7/17  ዓ.ል (ረመዷን 16/446 ዓ.ሒ) በአዲስ አበባ ሀገር አቀፍ የቁርአን ውድድር ይካሄዳል።

በዚህ ሀገር አቀፍ የቁርአን ውድድር ሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ይሳተፋሉ።

የክልልና ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳይ ምክር ቤቶች ክልላቸውንና ከተማ አስተዳደራቸውን ወክለው በማጣሪያው ውድድር ላይ የሚሳተፉ ቃሪዎቻቸውን በመለየት ላይ እንደሚገኙ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የፈትዋና ምርምር ዘርፍ ተጠሪና የቁርአን ውድድሩ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሸይኽ እድሪስ ዓሊ ሁሴን ገልፀዋል።

ሸይኽ እድሪስ አሊ ለጠቅላይ ምክር ቤቱ ህዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ እንደገለፁት ውድድሩ ይፋ ከተደረገበት ዕለት ጀምሮ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ወደ ተወዳዳሪ ልየታ ገብተዋል።

ሼይኽ እድሪስ አክለውም እስከ አሁን የኦሮሚያ፣ የሶማሌና የሐረር ክልሎች እንዲሁም የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የማጣሪያ ውድድር ያለፉ ተወካዮቻቸውን አሳውቀዋል ብለዋል።

የተጠቀሱት ክልሎችና ድሬደዋ ከተማ አስተዳደር እያንዳንዳቸው ሁለት ወንዶችና አንድ ሴት የፍፃሜ ተወዳዳሪ ለይተው ማሳወቃቸውን የተናገሩት ሼይኽ እድሪስ ሌሎች ክልሎችና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቀጣይ ቀናት በማጣሪያ ውድድር የመረጧቸውን ተወካዮቻቸው እንደሚያሳውቁ ይጠበቃልም ብለዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍን ይከታተሉ | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

08 Mar, 14:10

743

የካቲት 29 2017 ዓ.ል | ረመዷን 8፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በኢስላማዊ አንድነት ላይ ሲመክር የቆየው የመካው ጉባኤ የዓለም ሙስሊሞች ለአንድነት እንዲሰሩ የሚያሳስብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቀቀ።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዝደንት ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ ከጉባኤው ጎን ለጎን ጠቃሚ ውይይቶችንም አድርገዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••

በዓለም ሙስሊሞች አንድነት ላይ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲመክር የቆየው የመካው ጉባኤ ትላንት ሌሊት ተጠናቋል።

በጉባኤው ላይ ከመላው ዓለም የተጋበዙ የኢስላም ሊቃውንትና የሀይማኖቱ መሪዎች የተሳተፉበት ሲሆን በጉባኤው ማጠቃለያ ከተሳታፊዎች የተነሱ ሃሳቦችን የያዘ የጋራ የስምምነት ሰነድ ተዘጋጅቶ ለሁሉም ተሳታፊዎች እንዲደርስ ተደርጓል።

የጋራ ስምምነት ሰነዱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢስላማዊ አንድነትን ለመፍጠርና ለማጠናከር እንደሚያግዝም ተስፋ ተጥሎበታል።

ጉባኤው የዓለም ሙስሊሞች ለኢስላማዊ አንድነት ቅድሚያ ሰጥተው በትኩረት መስራት እንዳለባቸው የሚያሳስብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ነው የተጠናቀቀው።

ሀገራቸውን ወክለው በመካው የሙስሊሞች አንድነት ጉባኤ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት የክብር ዶክተር ሸይኸ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ ከጉባኤው ጎን ለጎን ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከሌሎች አቻ ተቋማት ጋር አብሮ መስራት በሚቻልባቸው ነጥቦች ዙሪያ ከተለያዩ ሀገራት ሙፍቲዎች፣ ኡለማዎችና ከመጅሊስ አመራሮች ጋር ተወያይተዋል።

ፕሬዝደንቱ በዛሬው ዕለት (ቅዳሜ) ውሏቸውም ከዓለም አቀፉ የፊቅህ ልሂቃን ጥምረት ሰብሳቢ ዶክተር ቁጥቢ ሳኖ፣ ከቡርኪና ፋሶ ፕሬዝደንት አማካሪ ዶክተር አቡበከር አብደላ፣ ከአፍሪካ ዑለማዎች ሰብሳቢ ዶክተር ሰዒድ እና ሌሎች መንፈሳዊ መሪዎች ጋር በኢስላምና ሀገራዊ ትውውቅ ዙሪያ መክረዋል።

በተጫማሪም በግንባታ ላይ የሚገኘው የንጉስ ነጃሺ ኢስላማዊ ማዕከል ግንባታ ሊፋጠን በሚችሉባቸው መንገዶች ዙሪያ ከዓለም አቀፉ ኢስላማዊ ዕርዳታ ድርጅት (ራቢጣ) ዋና ፀሀፊ የክብር ዶክተር ሙሀመድ አብዱልከሪም አልኢሳ ጋር ገንቢ ውይይት አድርገዋል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ/ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍን ይከታተሉ| Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

08 Mar, 08:03

985

#የረመዷን_መልዕክቶች
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

07 Mar, 15:53

1,389

የካቲት 28 2017 ዓ.ል | ረመዷን 7፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ቅርንጫፋዊ በሆኑ ነገሮች ከመለያዬት ወጥተን እንደ ኢስላም አንድ ሆነን ልንቆም ይገባል ― ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋ በሳውድ አረቢያ መካ ከተማ እየተካሄደ ባለው በኢስላማዊ አንድነት ዙሪያ በሚመክረው መድረክ ላይ የሀገራቸው መልካም ተመክሮ ለተሳታፊዎች አጋርተዋል።

ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም የሀገራቸውን ተመክሮ በገለፁበት ልግግራቸው የኢትዮጵያ ዑለማእ የስምምነት ሰነድን በዋቢነት ጠቅሰዋል።

ሙስሊሞች በመዝሃባዊና ጥቃቅን የሀሳብ ልዩነቶች ከመከፋፈል ይልቅ አንድ በሚያደርጉን የኢስላም መሰረቶች ዙሪያ በመሰባሰብ ጠክረን ልንቆም ይገባል ብለዋል።

የሚያስተሳስረንን የአላህ ገመድ በጋራ በመያዝ ጠላት ወደ ውስጣችን ሰርጎ እንዳይገባ ልናደርግ ይገባል ያሉት የክብር ዶክተር ሸይኽ ሀጅ ኢብራሂም ሙስሊሞች እንደ ሀገርም ሆን እንደ ዓለም አንድ ሆነን ልንቆም ይገባል ብለዋል።

ለሁለት ቀናት የቆየው ጉባኤ በዛሬው ዕለት በተለያዩ መርሀ ግብሮች የሚጠናቀቅ ይሆናል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ/ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍን ይከታተሉ| Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

27 Feb, 19:05

288

የካቲት 20፣ 2017 ዓ.ል | ሻዕባን 29 ፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጨረቃ አርብ ምሽት ከታየች የ1446 ዓ.ሒ የታላቁ ረመዷን ፆም ቅዳሜ ካልታዬች ግን እሁድ እንደሚሆን ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ገለፀ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የፌደራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት ለጠቅላይ ምክር ቤቱ በላከው መግለጫ ጨረቃ አርብ የካቲት 21/17 ( ሻዕባን 29/1446) ከታየች የ1446 ዓ.ሒ የታላቁ ረመዷን ፆም ቅዳሜ የካቲት 22/17 ዓ.ል የሚጀመር ሲሆን፤ ካልታየች ግን የረመዷን ፆም እሁድ የካቲት 23/17 ዓ.ል እንደሚጀምር ገልጧል።

ለተከበረው የረመዷን ወር ፆም በሰላም ላደረሰን አሏህ ምስጋና እናቀርባለን ያለው የጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤቱ መግለጫ ህዝበ ሙስሊሙ በፆም ወቅት ኢስላማዊውን የመደጋገፍና የመረዳዳት ተግባር የበለጠ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤቱ አደራ ብሏል።

በመጨረሻም ለሐገራችን እና ለመላው ዓለም ህዝበ ሙስሊም ፆሙ የጤና፣ የሰላምና የፍቅር እንዲሆን ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤቱ መልካም ምኞቱን ገልጿል።
••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

27 Feb, 17:36

631

የካቲት 20፣ 2017 ዓ.ል | ሻዕባን 28፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት አጀንሲ ከዳሸን ባንክ የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አገኘ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የልማት ክንፍ የሆነው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ ለህዝብ ባበረከተው የማህበራዊ አገልግለት ከዳሸን ባንክ የሸሪክ ከወለድ ነፃ አገል አገልግሎት የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደርጎለታል።

የገንዘብ ድጋፉን የተቀበሉት የልማት ኤጀንሲው የፕሮግራም ዴቨሎፕመንትና ኳሊቲ አሹራንስ ማናጀር አቶ ኸይረዲን ኢማና ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለፁት ኤጀንሲው የሰው ሃይሉን እንደ አዲስ ካዋቀረበት ካለፉት ሶስት ወራት ወዲህ ለህዝቡ ተስፋ ሰጪ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

ኤጀንሲው ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ምክንያቶች ለሕዝበ ሙስሊሙ ማበርከት ያለበትን ያህል አስተዋፅኦ ማበርከት ተስኖት መቆየቱን ያወሱት አቶ ኸይረዲን አዲሱ የኤጀንሲው ስራ አመራር የተጣለበትን ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት ከዓለምና ሐገር አቀፍ ድርጅቶች በቅርበት እየሰራ ነውም ብለዋል።

ደሻን ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የጀመረበትን 7ኛ ዓመት በማስመልከት ለ31 ሀገር በቀል ግብረ ሰናይና የልማት ድርጅቶ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን የልማት ኤጀንሲው ባሳየው የተሻለ የስራ አፈፃፀም ከፍተኛውን የ2 ሚሊዬን ብር ድጋፍ ለመውሰድ ችሏል።

የልማት ኤጀንሲው በአፋር ክልል በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ከቀያቸው ተፈናቅለው ለማህበራዊ ቀውስ ለተዳረጉ ወገኖች በቅርቡ የምግብ ግብዓቶችን ማከፋፈሉ የሚታወስ ነው።
••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ/ምክር ቤትን ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍን ይከታተሉ| Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

27 Feb, 15:45

804

የካቲት 20፣ 2017 ዓ.ል | ሻዕባን 28 ፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ዳሸን ባንክ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲን ጨምሮ ለ31 የግብረ ሰናይ እና የልማት ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

ዳሸን ባንክ ሸሪክ በሚል ስያሜ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የጀመረበትን 7ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ለ31 ሐገር በቀል የግብረ ሰናይ እና የልማት ድርጅቶች ከአምሰት መቶ ሺህ እስከ 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ።

ባንኩ ድጋፉን ያደረገው በበጎ አድራጎትና ልማት ዘርፍ የተሻለ ውጤት አስመዝግበዋል ላላቸው ድርጅቶች ስለመሆኑ የባንኩ የከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ቺፍ ኦፊሰር አቶ መስፍን በዙ ተናግረዋል።

የበጎ አድራጎትና የልማት ድርጅቶች የባንኩ የሸሪዓ አማካሪዎች ባዘጋጁት መስፈርት እንደተመረጡም አቶ መስፍን አክለዋል።

ከተመሠረተ ሃያ ዘጠኝ ዓመታትን ያስቆጠረው ባንኩ ሸሪዓ መር የሆነውን የከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት በማስፋት አሁን ላይ ካሉት 860 ቅርንጫፎች ውስጥ በ7 መቶ 74 ቱ የመስኮት እንዲሁም በ86 ቅርንጫፎቹ ሙሉ ለሙሉ የከወለድ ነፃ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑንም ቺፍ ኦፊሰሩ ተናግረዋል።

ባንኩ በዛሬው የልገሳ መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲን ጨምሮ ለ31 የግብረ ሰናይና የልማት ድርጅቶች ከ22 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የልማት ኤጀንሲ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የልማት ክንፎች አንዱ መሆኑ ይታወቃል።
••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

27 Feb, 09:04

1,011

የካቲት 20፣ 2017 ዓ.ል |  ሻዕባን 28 ፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ             
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የክብር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ
የመሩት ልዑክ የወሊሶን የሕፃናት መንደር የስራ
እንቅስቃሴ እየጎበኘ ነው።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት   ፕሬዝደንት የክቡር ዶክተር ሼይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የመሩት ልዑክ ወሊሶ የሕፃናት መንደር ሲደርስ አቀባበል ተደርጎለታል።


ልዑኩ የጠቅላይ ምክር ቤቱ የልማት ክንፍ አንዱ በሆነው የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት የወሊሶ ቅርንጫፍ የህፃናት መንደርን የስራ ቅስቃሴ በመጎብኘት ላይ ይገኛል።

በጉብኝቱ ላይ የጠቅላይ ምክር ቤቱ ተቀዳሚ ምክትል
ፕሬዝዳንት ሼይኽ አብዱልከሪም ሼይኽ በድረዲን፣ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት የክብር ዶክተር ሼይኽ ሱልጣን አማን ኤባ፣ የኦሮሚያ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼይኽ ጋሊ ሙኽታር እና የአወሊያ ዕርዳታና ልማት ድርጅት የቦርድ አባላት ተሳትፈዋል።
...........................................
የሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ክፍላችን ተጨማሪ መረጃዎችን የሚያደርሳችሁ ይሆናል።