بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በተፈጥሮ አደጋ የተፈናቀሉ ዜጎች በመስገጃ ቦታና በቁርዓን እጦት እየተፈተኑ እንደሆነ ተነገረ።
•••••••••••••••••••••••
አዋሽ ሱባሕ ኪሎ|
በአዋሽ ፈንታሌና በዱሊሌዓሣ ወረዳ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖች የመስገጃ ቦታና የቅዱስ ቁርዓን ቅጂ እጥረት እንደገጠማቸው የአፋር ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አባልና የስድስቱ ዞን የዳዕዋ አስተባባሪ ሼይኽ ሰዒድ አብዱልቃድር ተናገሩ።
በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በአንድ ቀበሌ እንዲሁም በዱሊሌዓሣ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ስልሳ ሺህ ያክል ሰዎች ተፈናቅለው በአሚባራ ወረዳ በተዘጋጁ ሶስት ጊዚያዊ ጣቢያዎች ተጠልለው ይገኛሉ።
የተፈጥሮ አደጋውን ተከትሎ ተፈናቃዮች ለአክፍሮተ ኃይላይ እንዳይጋለጡ ለማድረግ ጠቅላይ ምክር ቤቱ በመደባቸው አምስት ዑስታዞች አማካኝነት ሰፊ የዳዕዋ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ የገለፁት ሼይኽ ሰዒድ አብዱልቃድር ተፈናቃዮች በመስገጃና በቁርዓን እጥረት እየተፈተኑ እንደሆነ አክለዋል።
የዱሊሌዓሣ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙሐመድ አዚኬር በበኩላቸው ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለተፈናቃይ ወገኖች እያደረገ ያለው ሁለንተናዊ ድጋፍ ለሌሎች ድርጅቶች አርዓያ እንደሚሆን ተናግረው በጎ አድራጊ ድርጅቶችና ግለሰቦች ተፈናቃዮቹ ረመዷንን ተረጋግተው እንዲፆሙ የሚያስችል ድጋፍ እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13