Neueste Beiträge von Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council (@eiasc1) auf Telegram

Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council Telegram-Beiträge

Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት
9,085 Abonnenten
952 Fotos
24 Videos
Zuletzt aktualisiert 12.03.2025 11:54

Der neueste Inhalt, der von Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council auf Telegram geteilt wurde.

Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

16 Feb, 03:29

413

Iየካቲት 8፣ 2017 ዓ.ል | ሻዕባን 16፣ 1446 ዓ.ሒ。     
   بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ           
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
በተፈጥሮ አደጋ የተፈናቀሉ ዜጎች በመስገጃ ቦታና በቁርዓን እጦት እየተፈተኑ እንደሆነ ተነገረ።
•••••••••••••••••••••••
አዋሽ ሱባሕ ኪሎ|

በአዋሽ ፈንታሌና በዱሊሌዓሣ ወረዳ በመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት የተፈናቀሉ ወገኖች የመስገጃ ቦታና የቅዱስ ቁርዓን ቅጂ እጥረት እንደገጠማቸው የአፋር ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አባልና የስድስቱ ዞን የዳዕዋ አስተባባሪ ሼይኽ ሰዒድ አብዱልቃድር ተናገሩ።

በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳ በአንድ ቀበሌ እንዲሁም በዱሊሌዓሣ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ምክንያት ስልሳ ሺህ ያክል ሰዎች ተፈናቅለው በአሚባራ ወረዳ በተዘጋጁ ሶስት ጊዚያዊ ጣቢያዎች ተጠልለው ይገኛሉ።

የተፈጥሮ አደጋውን ተከትሎ ተፈናቃዮች ለአክፍሮተ ኃይላይ እንዳይጋለጡ ለማድረግ ጠቅላይ ምክር ቤቱ በመደባቸው አምስት ዑስታዞች አማካኝነት ሰፊ የዳዕዋ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ የገለፁት ሼይኽ ሰዒድ አብዱልቃድር ተፈናቃዮች በመስገጃና በቁርዓን እጥረት እየተፈተኑ እንደሆነ አክለዋል።

የዱሊሌዓሣ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙሐመድ አዚኬር በበኩላቸው ጠቅላይ ምክር ቤቱ ለተፈናቃይ ወገኖች እያደረገ ያለው ሁለንተናዊ ድጋፍ ለሌሎች ድርጅቶች አርዓያ እንደሚሆን ተናግረው በጎ አድራጊ ድርጅቶችና ግለሰቦች ተፈናቃዮቹ ረመዷንን ተረጋግተው እንዲፆሙ የሚያስችል ድጋፍ እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።


••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

12 Feb, 20:12

339

የሀጅ ምዝገባ ለምን እስከ ረመዷን መግቢያ ብቻ ሆነ?
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

12 Feb, 17:51

886

ሁጃጆችን ለማስተናገድ ወደ ሳውዲ አረቢያ የሚሄዱ ኻዲሞች ስራቸውን በአግባቡ እንዲሰሩ ለማድረግ ምክር ቤቱ ምን አቅዷል?
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

12 Feb, 15:55

1,179

የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት የሀጅ አብይ ኮሚቴ ኃላፊዎች ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

12 Feb, 10:19

1,472

የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት የሀጅ አብይ ኮሚቴ ኃላፊዎች ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

11 Feb, 17:22

1,641

የካቲት 4፣ 2017 ዓ.ል | ሻዕባን 13፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የሃጅ ንያ ያላቸው ምዕመናን የሳውዲ አረቢያ ሀጅ ሚንስቴር ባስቀመጠው የምዝገባ ጊዜ ፈጥኖ ሊመዘገብ ይገባል ተባለ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሀጅ አበይ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት ሀጅን በተመለከተ ከተለያዩ የመገናኝ ብዙሀን ጋዜጠኞች ለቀረቡለት ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥቷል።

ጋዜጠኞች ከሀጅ ጉዞ ጋር የተያያዙ የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተዋል። በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝደንትና የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ተጠሪ እንዲሁም የሀጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሸይኽ አብዱልአዚዝ ሸይኽ አብዱልወሊ የሀጅ ዋጋን ለመወሰን ሰፊ ጊዜ ተወስዶ በሀገር ውስጥና በውጪ ሀገር ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ በማጥናት የተወሰነ እንደሆነ አንስተዋል።

ሸይኽ አብዱልአዚዝ አክለውም ጠቅላይ ምክር ቤቱ እንደ አገልግሎት ሰጪ ተቋም የሃጅ ጉዞ ክፍያ ከህዝቡ የመክፈል አቅም ጋር የተገናዘበ እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት ያተደረገ ቢሆንም የብር የመግዛት አቅም እንዲዳከም መደረጉና ሁሉም አልጋሎቶች በውጪ ምንዛሪ የሚገኙ በመሆናቸው ክፍያው ከፍ እንዲል አድርጎታል ብለዋል።

ከዚህ በኋላ ከሀጅ ክፍያ ጋር በተያያዘ የሚለወጥ ነገር ባለመኖሩም የሀጅ ንያ ያላቸው ምዕመናን የሳውድ አረቢያ ሀጅ ሚኒስቴር ባስቀመጠውና ጠቅላይ ምክር ቤቱ ይፋ ባደረገው ጊዜ ፈጥነው መመዝገብ እንዳለባቸው ሸይህ አብዱልአዚዝ ለጋዜጠኞች በሰጡት ማብራሪያ በአጽንኦት ገልፀዋል።

በጠቅላይ ምክር ቤቱ ሥራ አስፈጻሚ እና የሀጅ አብይ ኮሜቴ የሲስተም ኃላፊ የሆኑት ኢንጂነር አንዋር ሙስጠፋ የሀጅን ጉዞ በተመለከተ ከጋዜጠኞች ለቀረቡ ጥያቄ በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያ የሀጅ ክፍያ ዋጋን ለመቀነስ ያሉትን አማራጮች በመጠቀም ዋጋው በተገለፀው ልክ ማድረስ መቻሉን አንስተዋል።

በተለይ ሁጃጆች ሳውድ አረቢያ በሚያገኟቸው አገልግሎቶች ላይ ቅነሳ እንዲደረግ የሀጅ አብይ ኮሚቴው ከፍተኛ ጥረት እንዳደረገም ኢንጂነር አንዋር ለጋዜጠኞች አብራርተዋል።

ኢንጂነር አንዋር አያይዘውም መጅሊሱ አገልግሎት ሰጪ በመሆኑ ጠቁመው ዝቅተኛ ሊባል የሚችል የአገልግሎት ክፍያ ብቻ እንደሚቀበል አስረድተዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የሀጅ ዘርፋ አብይ ኮሜቴ ፀሀፊ ሀጅ አቡዱሊዚዝ አሎ በበኩላቸው ለሀጅ አገልግሎት የሚከፈሉ ክፍያዎችን ዝርዝር የዋጋ ተመን በመጥቀስ ለጋዜጠኞች ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሀጅ አብዱልአዚዝ አክለውም ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከሁጃጆች የሚቀበለው የአገልግሎት ከፍያ ከሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አንፃር ሲታይ ዝቅተኛ ነውም ብለዋል።

እድሜያቸው ከ35 አመት በታች ለሆኑ ሁጃጆች ይጠየቅ የነበረው የማስያዣ ገንዘብም ሙሉ ለሙሉ እንዲቀር መደረጉ ለጋዜጠኞች በተሰጠው ማብራሪያ ተነስቷል።

በተጨማሪም ሁጃጆችን ለማገልገል የሚሄዱ አስተናጋጆች በሙሉ ጊዜያቸው ሁጃጆችን እንዲያገለግሉ ለማድረግ ሲባል የኢኽራም ልብስ እንዳይለብሱ እንደሚከለከሉና ከቀደሙ ዓመታት በተለየ መልኩ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግባቸውም የጠቅላይ ምክር ቤቱ አብይ ኮሚቴ ለጋዜጠኞች በሰጠው ማብራሪያ ግልፅ አድርጓል።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

11 Feb, 14:27

1,585

ሀጅ ማድረግ ለሚፈልጉ የዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ከጠቅላይ ምክር ቤቱ ሀጅና ኡምራ ዘርፍ ኃላፊ የተሰጠ ተጨማሪ ማብራሪያ
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

11 Feb, 10:11

1,664

ሁጃጆች ወደምዝገባ ሲመጡ ማሟለት ስለሚገባቸው ነገሮች አጭር ማብራሪያ በአዲስ አበባ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቱ የሀጅና ኡምራ ክፍል ኃላፊ ኢንጂነር ኢስሀቅ አብዱልዓዚዝ
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

06 Feb, 13:44

973

ጥር 29፣ 2017 ዓ.ል | ሻዕባን 7፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ            
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ለጠቅላይ ምክር ቤቱ የአምስት ዓመታት ስልታዊ ዕቅድ ለማዘጋጀት የሚረዳ የመረጃ ግብዓት ለሚያሰባስቡ ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ የቀጣይ አምስት ዓመት ለማዘጋጀት ግብዓት የሚሆነውን መረጃ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለሚያሰባስቡ ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል።

ዛሬ በጠቅላይ ምክር ቤቱ የመሠብሠቢያ አዳራሽ  የተከናወነው ሳይንሳዊ የመረጃ አሰባሰብ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሐጅ ከማል ሐሩን ንግግር ተከፍቷል።

ጠቅላይ ምክር ቤቱ ከሁለት ዓመታት ወዲህ ስራዎቹን በታቀደ መልኩ እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው ለቀጣይ አምሰት ዓመታት ስልታዊ ዕቅድም የህዝበ ሙስሊሙን ፍላጎት ማዕከል ያደረገና በጥናት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ለማድረግ ከፍተኛ የትምህርት ዝግጅትና የካበተ ልምዳ ካላቸው ምሁራን ጋር በቅርበት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ዋና ስራ አስኪያጁ አክለውም የአምስት ዓመታት ዕቅዱ ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በሚሰበሰብ ተጨባጭ መረጃ መሰረት የሚዘጋጅ በመሆኑ ዕቅዱ ሕዝበ ሙስሊሙን በተሻለ መልኩ ለማገልገል ያስችላል ብለዋል።

ለጥናትና መረጃ ለማሰባሰብ በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለሚሰማሩ ባለሙያዎች በሳይንሳዊ የመረጃ አሰባሰብ ዙሪያ ተከታታይ ስልጠና በባለሙያዎች አማካኝነት እንደሚሰጥም ተጠቅሷል።


••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc13
Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

06 Feb, 13:32

845

••••••••••••••••••••••••••••••••••••
ጥር 28፣ 2017 ዓ.ል | ሻዕባን 7፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የጠቅላይ ምክር ቤቱ የሥራ ክፍሎች የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ተገመገመ።
••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በስሩ የሚገኙት የሥራ ዘርፎች፣ የፅፈት ቤቶችና የዳሬክቶሬቶች የ2017 ዓ.ል. የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ ተካሄዷል።

በተቋሙ የሚሰሩ ስራዎች እንደይዘታቸው አይነት በተለያዩ ክፍሎች የሚፈፀሙ ቢሆኑም ስራዎችን በጋራ መገምገማችን ግን ስለ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ተመሳሳይ መረዳት እንዲኖረን ያግዛል ብለዋል የጠቅላይ ምክር ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ ሀጅ ከማል ሀሩን ግምገማውን ባስጀመሩበት ንግግራቸው።

ሀጅ ከማል አያይዘውም የስራ አፈፃፀም ግምገማው የተገኙ መልካም ልምድና ተመክሮዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠልና የተስተዋሉ ክፍተቶችን ለማረም ያግዛል ብለዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሀጅ አብዱልዓዚዝ አሎ በበኩላቸው እቅድ፣ ሪፖርት እና ግምገማ ወሳኝ የተቋማዊ አሰራር መሳሪያዎች መሆናቸውን ገልፀው ግምገማ የአሰራር ተጠያቂነትን ለማስፈንና ሰራተኛን ለማትጋት ጉልህ ሚና እንዳለው አንስተዋል።

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ስር ፕሬዝደንት ጽህፈት ቤትን ጨምሮ 20 የሚሆኑ የሥራ ክፍሎች ያሉ ሲሆን ሁሉም ክድሎች በግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ተሳትፈዋል።
•••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነትና ሚዲያ ዘርፍ
ይከታተሉን | Follow us፡
ፌስቡክ | Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council
ቴሌግራም | t.me/eiasc1
ትዊተር | https://x.com/eiasc1