来自 ትምህርተ ኦርቶዶክስ (@diyakonae) 的最新 Telegram 贴文

ትምህርተ ኦርቶዶክስ Telegram 帖子

ትምህርተ ኦርቶዶክስ
ውድ የ ትምህርተ ኦርቶዶክስ ቻናል ተከታዮች በሙሉ በዚህ ቻናል ሙሉ በሙሉ የኦርቶዶክስ ሀይማኖት ትምህርቶችን በቻ የምንለጥፍ መሆኑን ለመግለፅ እነዳለሁ ለሌሎችም በማጋራት (ሼር ) አገልግሎቱን ይደግፉ
3,696 订阅者
61 张照片
3 个视频
最后更新于 13.03.2025 02:57

ትምህርተ ኦርቶዶክስ 在 Telegram 上分享的最新内容

ትምህርተ ኦርቶዶክስ

30 Nov, 08:40

773

ኅዳር ጽዮን
"ጽዮን" ማለት "ጸወን አምባ፣ መጠጊያ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል፡፡

ኅዳር ፳፩ ቀን በታቦተ ጽዮን የተፈጸሙ ታላላቅ ተአምራት የሚታሰቡበት ቀን ነው፡፡ በዚህ ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የታቦተ ጽዮንን ተአምራት እግዚአብሔር ቃል ቅድስት ድንግል ማርያምን ታቦቱ አድርጎ ከፈጸማቸው ታላላቅ የድኅነት ሥራዎች ጋር በማነጻጸር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በነገረ ድኅነት ውስጥ ያላትን ድርሻ በስፋት ታስተምራለች፡፡

ነቢዩ ሙሴ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጸልዮና ጹሞ ዐሥርቱ ቃላት የተጻፈበትን ጽላት ከእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑን ታቦት ‹ታቦተ ጽዮንን› እንደተቀበለ መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል፡፡

ታቦተ ጽዮን ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸችበት ምክንያት የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ንጽሕና ለማመልከት ነው፡፡ በውስጥም በውጪም በጥሩ ወርቅ የተለበጠች መሆኗ ደግሞ የእመቤታችን ድንግል ማርያም ቅድስናዋንና በሁለት ወገን ድንግል የመሆኗ ምሳሌ ነው፡፡

ንጉሥ ዳዊት የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ጽዮን ከተማ ባስመጣበት ወቅት በታቦቷ ፊት በሙሉ ኃይሉ በደስታ እየዘለለ ለእግዚአብሔር በዝማሬ ምስጋና አቅርቧል፡፡ ‹‹ለንጉሥ ዳዊትም “እግዚአብሔር የአቢዳራ ቤት የነበረውን ሁሉ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ባረከ” ብለው ነገሩት፡፡

ዳዊትም ሄዶ የእግዚአብሔርን ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ራሱ ከተማ በደስታ አመጣት፡፡ ከእርሱም ጋር የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ሰባት መሰንቆ የሚመቱ መዘምራን ነበሩ፤ በሬዎችንና በጎችን ይሠዉ ነበር፡፡ ዳዊትም በእግዚአብሔር ፊት በገና ይደረድር ነበር›› እንዲል፤ ነቢዩ ዳዊት በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት የተቀኘው ለሰው ልጆች ሁሉ የመዳናችን ምክንያት የሆነችውን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሲያመስገን ነው፡፡ (፪ሳሙ.፮፥፲፪-፲፬)

ታቦተ ጽዮን እስራኤል የዮርዳኖስን ባሕር ለመሻገር በተቸገሩ ጊዜ ነቢዩ ኢያሱ እግዚአብሔር አምላክ በነገረው መሠረት ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት ይዘው በሕዝቡ ፊት ወደ ዮርዳኖስ እንዲሄዱ ነገራቸው፤ እነርሱም እንደታዘዙት አደረጉ፤ ታቦቱን የተሸከሙት የካህናቱ እግሮች በውኃው ዳር ሲጠልቁ ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል በደረቅ መሬት ጸንተው ቆመው ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው እስኪሻገሩ ድረስ እስራኤል ሁሉ በደረቅ መሬት ተሻገሩ፡፡ (ኢያ. ፫፥፩-፲፯)

እስራኤላውያን በመካከላቸው የቃል ኪዳኑ ታቦት በያዙ ቁጥር በጦርነታቸው ሁል ጊዜ ያሸንፉ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ልዑል እግዚአብሔር ሕዝበ እስራኤል ስለበደሉት እንዲሁም የኤሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ በደላቸውና ክፋታቸው ስለበዛ ታቦተ ጽዮን ተማርካ ወደ ፍልስጥኤም ሄደች፡፡ በዚያ በአሕዛብ ምድርም ልዩ ልዩ ተአምራትን እያደረገች ፍልስጥኤማውያንን ስለአስጨነቀቻቸው የፍልስጥኤማውያን አለቆች የቃልኪዳኑን ታቦት ልዩ ልዩ ገጸ በረከቶችን አስይዘው ወደመጣችበት በሠረገላ አድርገው በክብር ሸኝተዋታል፡፡ (፩ኛ.ሳሙ. ፭፥፩-፲፭)
ሀገራችን ኢትዮጵያም በንግሥተ ሳባ አማካኝነት ለታቦተ ጽዮን መቀመጫ እንድትሆን የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኗል፡፡ ይህም እንዲህ ነበር፤ ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ጥበብ ለማድነቅ ምድረ እስራኤል ድረስ መጓዟን ተከትሎ ከንጉሡ ቀዳማዊ ምኒልክን ፀነሰች፡፡

ቀዳማዊ ምኒልክ ከአደገ በኋላ አባቱን ሊጠይቅ ሂዶ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ አብረውት አንድ ሺህ ሁለት መቶ እስራኤላውያን የበኩር ልጆች፣ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት በአዛርያስ የሚመሩ ሌዋውያን ካህናትም አብረውት ለጉዞ ተነሡ፡፡ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትንና ሌሎች በርካታ ቁሳቁሶችን ይዘውም ነበር።

ነገር ግን ታቦተ ጽዮንን አዛርያስና ካህናቱ ተማክረው ቀዳማዊ ምኒልክ እንኳን ሳይሰማ በምሥጢር ይዘዋት ሊመጡ ተስማሙ፡፡ ዕቅዳቸውን ለማሳካት በታቦተ ጽዮን አምሳያ ሌላ ታቦት አዘጋጅተው ለመሄድ በሚነሡበት ዕለት ሌሊትም ወደ ቤተ መቅደስ ይዘውት ሄዱ፡፡

ከቤተ መቅደስ ሲደርሱም የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበርና የቤተ መቅደሱ በር ተከፍቶ እና ውስጡም በብርሃን ተሞልቶ ታቦተ ጽዮንም ከመንበሯ በመነሣት ከፍ ብላ አገኟት። በዚህም የአምላክን ፈቃድ ተረድተውና እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በፍጥነት ይዘዋት ወጡ፡፡ በአምሳያዋ የሠሩትንም ቅርፅ በመንበሩ ላይ አስቀምጠው ሄዱ።

የንጉሡ ወታደሮች በፍጥነት ቢጓዙም ቀዳማዊ ምኒልክ እና አዛርያስ ታቦተ ጽዮንን ይዘው ሲጓዙ እጅግ ፍጣን ስለበር ሊደርሱባቸው አልቻሉም። መጽሐፈ ክብረ ነገሥት ይህንን ሲጠቅስ ‹‹ከመሬት አንድ ክንድ ያህል ከፍ ብለው ይሄዱ ነበር›› በማለት ይገልጸዋል። ባሕረ ኤርትራን ከተሻገሩና ግብፅ ከደረሱ በኋላ ዕረፍትን ባደረጉ ጊዜ አዛርያስ ለቀዳማዊ ምኒልክ ታቦተ ጽዮንን ይዘዋት እንደመጡ ነገረው፡፡

አያይዞም ‹‹አንተም ብትሻ ታቦቷንም ወደ ሀገሯ ልመልሳት ብትል አትችልም፤ አባትህ ሰሎሞንም ሊወስዳት ቢመጣ አይሆንለትም›› አለው። ከቦታ ቦታ ይዣት እንቀሳቀሳለው ቢልም ያለ ፈቃዷ ምንም እንደማያደርግና ሁሉ ነገር በአምላክ መልካም ፈቃድ እንደሚፈጸም ነገረው። ቀዳማዊው ምኒልክም ይህን ሲሰማ ተደሰተ፤ ሕዝቡና ሠራዊቱ በሙሉ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ከግብፅ ምድር ወጥተው እስከ ኢትዮጵያ በታላቅ እልልታና ሆታ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መጡ።

ኅዳር ፳፩ ቀን አክሱም በደረሱ ጊዜም እናቱ ንግሥተ ሳባ ተቀበለችው፤ ደስታና እልልታውን ተመልክታ ያገኙት ነገር እንዳለ ብትጠይቀው ታቦተ ጽዮንን እንዳመጧት ነገራት፡፡ የእርሷም ደስታ እጥፍ ድርብ ሆነ። ታቦቷንም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስቀመጡአት፡፡

ከዚያም ዘመን ጀምሮ በየዓመቱ ኅዳር ፳፩ ቀን ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም በታቦተ ጽዮን የተፈጸሙ ታላላቅ ተአምራትን በማሰብ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታከብራለች፡፡
         ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፤
ክብረ ነገሥት ተርጓሚ ሥርግው ገላው (1994 ዓ.ም)
መዝገበ ታሪክ ቊጥር 1 (መምህር ኅሩይ ኤርምያስ)
ትምህርተ ኦርቶዶክስ

17 Nov, 04:14

165

🧲 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቻናል

📚 ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት ብራና እና ወረቀት በpdf
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ እና መልስ
📜 ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞች
የግእዝ ቋንቋ ትምህርት
🎶 የኦርቶዶክስ የመዝሙር ግጥሞች
📙 ተከታታይ ትምህርቶች
📘 ስንክሳር የእየለቱ
📗 ብሂለ አበው
📓 መንፈሳዊ ተረኮዎች
📔 የአበው ምክር
📚 የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች
🤵‍♂የመምህር ምህረተአብ አሰፋ ቻናል

የፈለጉትን መርጠው ይቀላቀሉ

🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖
ትምህርተ ኦርቶዶክስ

15 Nov, 11:10

1,048

በዓለ ደብረ ቁስቋም
እንኳን አደረሰን

ደብረ ቁስቋም በደቡብ ግብፅ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ደብረ ቁስቋም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲሁም ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን ይዛ ከስደት ሲመለሱ ያረፉበት ቦታ ነው፡፡

ይህም በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈ ሄሮድስ ክርስቶስን ለመግደል በፈለገ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለአረጋዊው ዮሴፍ በሕልሙ ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ›› ባለው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ (ማቴ. ፪፥፲፫-፲፭)

የክርስቶስ ስደቱ ቀድሞ በነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹. . . እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል፡፡ የግብፅም ጣዖታት በፊቱ ይዋረዳሉ›› ተብሎ በተነገረው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ ነቢዩ ፈጣን ደመና ያለው ጌታችን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ጀርባ ላይ ሆኖ ወደ ግብፅ መውረዱን ለመግለጽ ነው፡፡ (ኢሳ. ፲፱፥፩) በስደቱም ጣዖታተ ግብፅ እየተሰባበሩ ሲወድቁ፤ በእነርሱም አድረው ሰውን ሲያስቱ የነበሩ አጋንንትም ሲሸሹ ታይተዋል፡፡

ደግሞም ጌታችን ዳግማዊ አዳም ነውና በምክረ ከይሲ (ዲያብሎስ) ምክንያት ተሰዶ የነበረው ቀዳማዊ አዳምን ለመካስ ተሰደደ፤ በዚህም አጋንንትን ከሰው ልቦና አውጥቶ አሳደደ፡፡

እመቤታችንም ልጇን ይዛ ከስደት ስትመለስ ያረፈችበትን ተራራ ደብረ ቁስቋምን ባረከችው ቀደሰችውም፤ ይህ ተራራ የተቀደሰ ተራራ ስለመሆኑ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ታኦፊሎጎስ በድርሳነ ማርያም እንዲህ አለ፤ ‹‹ይህም ከሀገሮቹ ሁሉ ተራሮች የሚበልጥ (የተለየ) ከፍ ያለ ተራራ ነው፡፡ በውስጡ ቅዱስ አግዚአብሔር ያድራል፡፡ ይህንን ተራራ የእግዚአብሔር ልጅ ወዶታል፤ አክብሮታልምና፤ ከዓለም ሀገሮች ሁሉ ከተቀደሰች እናቱ ጋር አድሮባታልና፡፡ ከመላእክት ቤት ያድር ዘንድ አልወደደም፤ ቢታንያንም አልመረጠም፡፡
ከተራራው ላይ ባለች ገዳም ቤት ውስጥ አደረ እንጂ፤ ነቢዩ ዳዊት፤ የጽዮንን ተራራ ወደደ፤ በአርያምም መቅደሱን ሠራ እንዳለ፡፡››
‹‹አንተ ተራራ ሆይ የእግዚአብሔር ማደሪያ በሆንህ ጊዜ በኪሩቤልና በሱራፌል መካከል ፍጹም ደስታ ተደረገ፡፡ የመላእክት ሠራዊት ቅዱስ የሆነ ፈጣሪያቸውንና ጌታቸውን ይታዘዙ (ያገለግሉ) ነበር፡፡

አንተ ተራራ ሆይ ያደረብህ ጌታችን ስለሆነ ከተራሮች ሁሉ ከደብረ ሲናም ይልቅ ከፍ ከፍ አልህ፤ ጌታችን በደብረ ሲና ባረፈ ጊዜ ፍጹም ደስታ፣ ታላቅ ብርሃንም በሆነ ጊዜ መቅረብና መመልከት ከሙሴ በቀር የቻለ የለም፡፡

እርሱም ቢሆን ፊቱን ማየት አልቻለም፡፡ ሥጋ ለባሽ ሁሉ እርሱን ዐይቶ በሕይወት መኖር የሚቻለው የለምና፡፡ እኛ ግን አየን፤ ከዚህ ማደሩንም ተረዳን፤ ዳግመኛም ንጽሕት በሆነች በማርያም ዘንድ አየነው፡፡ ቅድስት ከሆነች ከእመቤታችን ማርያም ዘንድ በቤተልሔም ስለ እኛ በተዋሐደው ሥጋ በጨለማና በሞት ጥላ ሥር ያለን እኛን ከቸርነቱና ሰውን ከመውደዱ የተነሣ መጥቶ አዳነን፤ ከዓለም ሁሉ ይልቅ ጣዖትን በማምለክ ሲበድሉም ወደ ግብፅ  ሀገር ወርዶ በእነርሱ ላይ የመለኮትነት ብርሃኑን በማብራት ታላቅ የሆነ ክብሩን ገለጠ››፡፡ (ድርሳነ ማርያም)
ኅዳር ፮ ቀንን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛም በኋላ ዘመን ሐዋርያትን በደብረ ቁስቋም ሰብስቦ፤ ታቦትንና ቤተ ክርስቲያኑን አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙን እንደ ሰጣቸው፤ እኛንም ለዚህ ክብር የበቃን እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፤ አሜን፡፡

ምንጭ፤ ድርሳነ ማርያም መጽሐፍ ትርጉም
https://t.me/DIYAKONAE
ትምህርተ ኦርቶዶክስ

09 Nov, 10:18

761

👳‍♂አባቶች ይህንን ይመክሩናል
            እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን

ለኦርቶዶኮስ አማኞች ብቻ የተከፈተ ቻናል ።
    ክርስትናችን እንዳንኖረው የሚያደርጉን ምክንያቶች በእውኑ ታውቋቸዋላችሁ⁉️
ለዚህ ችግር አባቶች ምን አሉ⁉️
የምትፈልጉትን ለማግኘት ወደ ቻናላችን ተቀላቀሉ

ይህ ምክረ አበው ነው ሁላችሁም ተቀላቀሉ ትጠቀሙበታላችሁ open የሚለውን በመንካት ይቀላቀሉን👇👇👇👇👇👇👇
    ⬜️◻️◽️▫️ⓄⓅⒺⓃ⬛️⬛️⬛️⬛️
    ⬜️◻️◽️▫️ⓄⓅⒺⓃ▪️◾️◼️⬛️
    ⬜️⬜️⬜️⬜️ⓄⓅⒺⓃ▪️◾️◼️⬛️

https://t.me/addlist/Hnzdad45XskzMTM8

https://t.me/addlist/Hnzdad45XskzMTM8
ትምህርተ ኦርቶዶክስ

05 Oct, 06:38

1,124

❤️እንኳን ለጽጌ ፆም አደረሳቹ?

መልካም ጾም እያልኩኝ እንዚህን ከታች የምታዩዋቸውን ቻናሎች ጋበዝኳችሁ!

https://t.me/addlist/uXhiFffRAV5mYTk8
ትምህርተ ኦርቶዶክስ

23 Jul, 15:50

2,247

.          መስቀል ለምን እንሳለማለን

መስቀል ስንሳለም ምዕመኑ ይፍቱኝ ይባርኩኝ ብለን በፍጹም ትህትና በእምነት ሆኖ ወደ ካህኑ እንቀርባለን ካህኑም በመስቀሉ የላይኛው ክፍልና በታችኛው ክፍል ግንባራችንና አፋችንን አሳልመው ይባርኩናል።
ግንባሩን ማስነካታቸው በአዕምሮ የተሰራውን ከንፈሩን ማስነካታቸው በመናገር የተሰራውን ኃጥያት እግዚአብሔር ይተውላችሁ ማለታቸው ነው።ቀዳሲያኑ ለቅዳሴ መምህሩ ለማስተማር ዘማሪው ለመዘመር ሲነሱ በማዕረግ ከፍ ካሉት ካህን መስቀል የሚሳለሙት።
ኃጢያት በሶስት መንገድ ይሰራል
፩. በገቢር (በመስራት)
፪.በነቢር (በመናገር)
፫.በኅልዩ (በማሰብ)
ታዲያ በገቢር በመስራት የተፈጸመውን ኃጢአት ለማስተሰረይ ጊዜ ሰጥቶ ወደ ንስሐ አባት ቀርቦ በኑዛዜ ቀኖና መቀበልና ቀኖናውን መፈፀም ይገባል። ለዚህ ነው አሁን አሁን በከተሜው ዘንድ እምብዛም ባይታይም ወንጌሉ የገባቸው ክርስቲያኖች ካህን ባዩ ቁጥር መስቀል ለመሳለም የሚጓጉት። ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ማድረጋችሁን አትዘንጉ
እያወቅን በድፍረት ሳናውቅ በስሕተት የሰራነውን ኃጢአት ይቅር ይበለን ።
https://t.me/DIYAKONAE
ትምህርተ ኦርቶዶክስ

14 Jul, 03:26

1,543

#እንኳን #ለቅድስት #ሥላሴ #በዓል #አደረሳችሁ
አብርሃም ይስሐቅን ለመሰዋት ወደተራራ ወስዶት ነበር። እግዚአብሔር ግን በይስሐቅ ፈንታ በግን በዕፀ ሳቤቅ አወረደለት። ያ በግ ከሦስቱ አካላት የአንዱ የወልድ ምሳሌ ነው። ለጊዜው ይስሐቅ ከሞት የዳነው በዚያ በግዕ ቤዛነት ነው። የሰው ልጅ ሁሉ ከሞት የዳነበት ሕያው በግዕ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ዕፀ ሳቤቅ የድንግል ማርያም ምሳሌ ነው። ክርስቶስ ለእኛ ቤዛ ሆኖ በመስቀል ተሰቅሎ አዳነን።

"አብርሃም ወሰዶ ለይስሐቅ ወልዱ ከመ ይሡዖ።
አውረደ ሎቱ ቤዛሁ በግዐ"።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ።
ትምህርተ ኦርቶዶክስ

13 Jul, 08:33

1,331

🧲 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቻናል

📚 ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት ብራና እና ወረቀት በpdf
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ እና መልስ
📜 ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞች
የግእዝ ቋንቋ ትምህርት
🎶 የኦርቶዶክስ የመዝሙር ግጥሞች
📙 ተከታታይ ትምህርቶች
📘 ስንክሳር የእየለቱ
📗 ብሂለ አበው
📓 መንፈሳዊ ተረኮዎች
📔 የአበው ምክር
📚 የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች
🤵‍♂የመምህር ምህረተአብ አሰፋ ቻናል

ይቀላቀሉ

🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖
ትምህርተ ኦርቶዶክስ

13 Jul, 05:55

1,274

"ቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት ጾምና ምሕላ አወጀ።

ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)

ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የምሕላ ጸሎት እንዲደርስ ታውጇል።

የቋሚ ቅዱስ ሲኖዶሱ ሙሉ መልእክት እንደሚከተለው ቀርቧል።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ  አሜን

ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ  በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የሚፈጸመውን የምሕላ ጸሎት አስመልክቶ ከቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

‹‹ተማሕለሉ ወሰአሉ ኃበ አቡክሙ ሰማያዊ እስመ አብ ይሁበክሙ ኵሎ ዘሰአልክሙ…አባታችሁ የምትለምኑትን ሁሉ  ይሰጣችኋልና ወደ ሰማይ አባታችሁ ለምኑ፣ ምሕላንም አውጁ›› ኢዩኤል 1፤14 ቅዱስ ያሬድ

በሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ  በጾም በጸሎት በመወሰን፣ምሕላን በማወጅ ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ሁሉን ማድረግ ወደሚችለው አምላካችን አግዚአብሔር ምልጃን ማቅረብ የሚያስፈልግ መሆኑን ከሀገራችን ሊቃውንት መካከል የመጀመሪያ  የሆነው  ቅዱስ ያሬድ ከሰማያውያን ዐውደ ማህሌት ሰምቶ በቀሰመው ጣዕመ ዜማ  አበክሮ ይነግረናል፡፡

በመሆኑም ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷልና በእውነት የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ እግዚአብሔር መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር አንድነት፣ ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ከአንድነት ገዳማት ኅብረት በቀረበው ጥያቄ መነሻነት ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በሁሉም የሀገራችን ክፍልና በሌሎችም አህጉራተ ዓለም የምትገኙ መነኰሳትና መነኰሳይያት  ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት የገዳማት ኅብረቱን ጥሪ ተቀብላችሁ የምሕላ ጸሎት እንድታደርሱ፣ በጤና ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀር እስከ ዕርበተ ፀሐይ በመጾም ሱባኤ እንድትይዙ፣ ቋሚ ሲኖዶስ በኅብረተ መንፈስ ቅዱስ ከአደራ ጋር ያሳስባል፡፡

ሁሉም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮችና  ምእመናን  ሀገራዊ ሰላምን፣  መረጋጋትንና ፍቅር አንድነትን ለማስፈን ጾምና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን  ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

‹‹እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ››
ሐምሌ 5 ቀን 2016 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ትምህርተ ኦርቶዶክስ

07 Jul, 09:32

1,028

🧲 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቻናል

📚 ኦርቶዶክሳዊ መጽሐፍት ብራና እና ወረቀት በpdf
መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄ እና መልስ
📜 ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞች
የግእዝ ቋንቋ ትምህርት
🎶 የኦርቶዶክስ የመዝሙር ግጥሞች
📙 ተከታታይ ትምህርቶች
📘 ስንክሳር የእየለቱ
📗 ብሂለ አበው
📓 መንፈሳዊ ተረኮዎች
📔 የአበው ምክር
📚 የተለያዩ መንፈሳዊ ትምህርቶች
🤵‍♂የመምህር ምህረተአብ አሰፋ ቻናል

ይቀላቀሉ

🇹 🇪 🇼 🇦 🇭 🇪 🇩 🇴
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖
📖█▓▒░►𝑶𝑷𝑬𝑵◄░►𝑶𝑷𝑬𝑵▒▓█📖