#ዐብይ_ጾም ፦ማለት ምን ማለት ነው በመጀመሪያ ‹‹ዐቢይ›› የሚለው ቃል ‹‹አበየ›› ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ትርጓሜውም ‹‹ከፍ አለ›› ማለት ነው፡፡
የዐብይ ጾም የተለያየ ስያሜዎች ዐብይ ጾም ከቀኑ ርዝማኔ በተጨማሪ ጾሙ የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡
#ጾመ_ሁዳዴ፡- ሁዳድ ማለት ሠፊ (ትልቅ) የእርሻ ቦታ ማለት ነው፡፡ ይህም ጾም ደግሞ በቀኑ ብዛት ትልቅ (ሠፊ) በመሆኑ የሁዳዴ ጾም ይባላል፡፡
#የካሳ_ጾም፡- እንዲህ የተባለበት ምክንያቱ ደግሞ አዳምና ሔዋን በዲያቢሎስ ግዞት እያሉ ክርስቶስ ደሙን በመክፈል (በመካስ) ነጻ ስላውጣቸው የካሳ ጾም ተብሎሏል
#የድል_ጾም ፡-ይህም ደግሞ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ጾም ሰይጣንን ድል ያደረገበት በመሆኑ የድል ጾም ተብሏል፡፡
#የመሸጋገሪያ_ጾም ፦ጌታችን ከሕገ ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል ሊያሸጋግረን የጾመው ጾም በመሆኑ የመሸጋገሪያ ጾም ተብሏል።
#ጾም_አስተምህሮ፡- ይህ ጾም ‹‹ጾም አስተምህሮ›› የተባለበት ምክንያት ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማስተማር የጾመው በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ የተለያዪ ስያሜዎች አሉት
‹‹የመሸጋገሪያ ጾም ››
‹‹የስራ መጀመሪያ ጾም ››
ይህ ፆም ታላቅ መባሉም ለ55 ቀናት ያህል መፆሙና ከሌሎቹ አፅዋማት ጋር ሲነፃፀር በቁጥር
መብለጡ ብቻ ሳይሆን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ
ቆሮንቶስ መፆም ሳይገባው ለእኛ አርአያና ትልቅ ምሳሌ ለመሆን የፆመው ፆምም
በመሆኑ ነው።
ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች እንዲሁም ደግሞ ሶስቱ ርዕሰ ኃጢአት የሚባሉት
#ትዕቢት፣
#ስስት
#ፍቅረ_ነዋይ
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ድል የተመቱበት ስለሆነ ይህ ጾም አብይ (ታላቅ) ተብሏል፡፡
የአብይ ጾም ሳምንታት 8 ናቸው፤
1. #ዘወረደ
2. #ቅድስት
3. #ምኩራብ
4. #መጻጉዕ
5. #ደብረዘይት
6. #ገብርሔር
7. #ኒቆዲሞስ
8. #ሆሣዕና
አቢይ ጾም ሦስቱ ክፍሎች
1. ዘወረደ (ጾመ ሕርቃል)፤ ይህም ጾሙ ከሚገባበት ሰኞ ጀምሮ እስከ እሑድ ያረስ ያለው 7 ቀን ነው።
2. የጌታ ጾም፤ ይህም ከቅድስት ሰኞ እስከ ሆሣዕና ዋዜማ ዓርብ ድረስ ያለው 40 ቀን ነው።
3. ሕማማት፤ ይህም ጌታችን በአልዓዛር ቤት ለማዕድ ከተቀመጠበት የሆሳዕና ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ሥዑር ቅዳሜ ያለው መከራን የተቀበለበት 8 ቀን ሕማማት ነው።
ይህም 7+40+8 = 55 ቀን ማለት ነው።
የዲያብሎስን ሥራ ሊያፈርስየተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅም በፆም ድል ማድረግን ለእኛ አስተምሮናል። እኛምበዚህ በአብይ ፆም የለመነውና የጠየቅነው ነገር ሁሉ ከኃጢአት በስተቀርእንዲከናወንልን ፆምን ገንዘባችን እናድርግ። በፆም የተጠቀሙ ቅዱሳን አባቶችና ቅዱሳንእናቶች እንዳሉን እናስተውል።
ጾም ጸሎታችን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቀበልልን አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር