Últimas publicaciones de Defence Construction Enterprise (@dce2020) en Telegram

Publicaciones de Telegram de Defence Construction Enterprise

Defence Construction Enterprise
Defense Construction Enterprise (DCE) is one of the leading construction companies in Ethiopia. We are different from other companies as we work in the most remote and difficult areas of the country. We are dedicated and devoted to build the country.
1,374 Suscriptores
971 Fotos
30 Videos
Última Actualización 06.03.2025 00:29

El contenido más reciente compartido por Defence Construction Enterprise en Telegram

Defence Construction Enterprise

31 Jan, 10:11

713

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አንዴ ማማ ከተባለ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን በእጅ ሥራ ውጤቶች ላይ ስልጠና ሰጠ፡፡

                                                                              ጥር23/2017ዓ.ም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አንዴ ማማ ከተባለ ሀገር በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር አገልግሎት በሰጡ ወረቀቶች የተለያዩ ለቤትና ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ከወረቀት የሚሰሩ የእጅ ሥራ ውጤቶችን የኢንተርፕራይዙ የቢሮ ውበትና የቢሮ አገልግሎት ከሚሰሩ የተውጣጡ ለአስራ ሰባት ሴት ሠራተኞች ለ21 ቀናት ሥልጠና ተሰጠ፡፡

የስልጠናውን አስፈላጊነት በተመለከተ በኢንተርፕራይዙ ስርዓተ ፆታ ጉዳዮች ቡድን መሪ ወ/ሪት መስታወት ንጉሴ፣ ሴቶች በተሰማሩበት የስራ ዘርፎች  ሁሉ ለሃገር እያበረከቱት ያለው አስተዋፅዖ ከፍተኛ በመሆኑም በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ማሰልጠን እና አቅማቸውን ከፍ በማድረግ የሥራ እድሎችን በመፍጠር በተሰማሩበት ዘርፍ ውጤታማ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

አንዴ ማማ የበጎ አድራጎት ድርጅት ስራ አስኪያጅ አቶ ሚካኤል ኃይሌ የበጎ አድራጎት ድርጅቱ የሚያሰለጥነው ስልጠና ጥቅም ላይ የዋሉ እና ተመልሰው ለጽሕፈት ሥራ የማይሆኑ ወረቀቶችን በመጠቀም የወረቀት ቅርጻ ቅርጾች አዘገጃጀት ላይ ነው፡፡ በመሆኑንም ሠልጣኞች ከዚህ ስልጠና በኃላ በበጎ አድራጎት ድርጅቱ በኩል የሥራ እድል እንዲያገኙ እና የገበያ ትስስር ሊፈጥሩላቸው እንደሚችሉ ተናግረዋል።

ሰልጣኞችም በበኩላቸው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የስርዓተ ፆታ ጉዳዬች ቡድን ከአንዴ ማማ በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በጋራ በመቀናጀት አገልግሎት የሰጡ ወረቀቶችን ተጠቅመው የእጅ ሥራ ውጤቶችን  አሰራር  መሰልጠናቸው የራሳቸውንም ሆነ የቤተሰባቸውን የኢኮኖሚ አቅም  መገንባት የሚያስችል ትልቅ መሠረት መሆኑን ተናግረዋል።
Defence Construction Enterprise

30 Jan, 14:55

638

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ Constraction Cost estimation and Budget እና Constraction Project management and Supervision ለመሐንዲሶች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡

ጥር 22/2017ዓ.ም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ከጥር 19-22/2017 ዓ.ም Constraction Cost estimation and Budget እና Constraction Project management and Supervision ላይ ለመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ እና ለከመከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት በምህንድስና ሥራ ላይ ለሚገኙ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በአዲስ አበባ ቱሊፕ ኦሎምፒያ ሆቴል የአቅም ግንባታ ሥልጠና ሰጠ፡፡

ሥልጠናው በሥራው ላይ ለሚገኙ የሥራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች በግንባታ ሂደት ውስጥ ፕሮጀክቶችን በተሳካ ሁኔታ ለማጠናቀቅ እና ሀብቶችን በአግባቡ ለመጠቀም፤ የፕሮጀክት ወጪዎችን መገመት እና ማስተዳደር እንዲችሉ የሚያግዝ ነው።

ሥልጠናው በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት የሥልጠና ባለሙያ በሆኑት በእጩ ዶ/ር (ኢንጂነር) ታምሩ መንግሥት እና ኢንጅነር ማቴዎስ ፀጋዬ የተሰጠ ሲሆን፣ አንድ የኮንስትራክሽን ተቋም የሚገነባቸውን የግንባታ ፕሮጀክቶች የተሻለ እንዲሆን ሳይንሳዊ  በሆነ በሰለጠነ  መንገድን እንዲመራ  ለማስቻል ነው፡፡  እንዲሁም በፕሮጀክቶች ግንባታ ላይ እየተስተዋሉ ያሉትን በጊዜ ያለማጠናቀቅ፣ የተጋገነ ወጪና የጥራት ጉድለቶችን ለመቅረፍ በሥራ ላይ ሚገጥሙ ክፍተቶችን ለመሙላት ታስቦ የተዘጋጀ ሥልጠና መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በሥልጠናው ላይ የተሳተፉ ሰልጣኞች ሥልጠናው ሥራ ላይ የሚገጥሟቸውን ክፍተቶች  በመለየት እና የጋራ መፍትሔ በማስቀመጥ በሙሉ አቅማቸን ወደ ትግበራ እንዲገቡ እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል፡፡
Defence Construction Enterprise

30 Jan, 10:55

525

ቃሊቲ ስቶር ውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት አፈጻጸም 98% መድረሱ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከሚገነባቸው ግንባታዎች መካከል የቃሊቲ ስቶር ውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት እና ተያያዥ የሳይት ሥራ አንዱ ሲሆን ግንባታው 98 % ደርሷል።

የቃሊቲ ስቶር የውስጥ ለውስጥ መንገድ እና ተያያዥ የሳይት ሥራ ባለቤትነቱ የመከላከያ ምህንድስና ዋና መምሪያ ሲሆን ግንባታውን የሚቆጣጠረውና የሚያማክረው ደግሞ መከላከያ ኮንስትራክሽን ዲዛይን ድርጅት ነው፡፡ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ለመከላከያ ሎጅስቲክ ዋና መምሪያ የሚተላለፍ ይሆናል፡፡

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ቤዛ ቀለመወርቅ እንደሚሉት፤ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ይህን ፕሮጀክት ለመሥራት በሶስት ምዕራፍ በመክፈል የተዋዋለ ሲሆን፣ የመጀመሪያው ግንባታ ዉል ጥር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ተፈርሟል፡፡ ከውሉ በኋላ ግንባታውን ለማስጀመር ከግንባታ ቦታው ጋር የሚጣጣም የዲዛይን ክለሳም ተደርጓል፡፡ ለሥራው የሚያስፈልግ የግንባታ እቃ፣ የሰው ኃይል እና ማሽነሪ በሟሟላት ግንባታው የካቲት 26 ቀን 2013 ዓ.ም እንደተጀመረ ገልጸዋል፡፡ 

ግንባታው ከተጀመረ በኋላ የመንገድ ጠረጋ ሥራ፣ የአፈር ቆረጣ እና ሙሌት ሥራ የተከናወነ ሲሆን በመቀጠልም የፍሳሽ ማስወገጃ ሥራዎች፣ የሰቤዝ እና የቤዝ ኮርስ እንዲሁም የአስፋልት ሥራዎች እና የመንገድ ቀለም ቅብ ሥራዎች ተሠርተዋል፡፡

ሁለት ትላልቅ የግምጃ ቤት ግንባታዎች፣ የውሃ መስመር፣ የእሳት አደጋ ማጥፊያ የውሃ መስመር ዝርጋታ፣ የመንገድ መብራት የኤልክቲሪክ መስመር ዝርጋታ እና የመንገድ መብራት የብረት ገጠማ እንዲሁም ለግቢው ሠራተኞች የሚያገለግሉ የመፀዳጃ ቤት ግንባታዎች ተሠርተው ተጠናቀዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ቤዛ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ የተገነባ ሲሆን የመንገዱ ስፋት ከ 10 ሜትር እስከ 20 ሜትር በሚሆን ስፋት የተገነባ ነው፡፡ ለሰው እና ተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ምቹ በመሆናቸው የመከላከያ ሎጅስቲክ ሥራን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳለጥ መልካም ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ ከፍተኛ ክብደት የሚያነሱ ክሬን የተገጠመላቸው ግምጃ ቤቶች በመገንባታቸው እቃዎችን በቀላሉ እና በአጭር ጊዜ ማንቀሳቀስ የሚያስችል መሆኑም ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ በሚፈለገው የጥራት ደረጃ ሆኖ እንዲገነባ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የተሠራ በመሆኑ የመከላካያ ሎጅስቲክስ ዋና መምሪያ የተሰጠውን ሀገራዊ ተልኮ ለመሳካት ከፍተኛ አቅም የሚፈጥርለት ይሆናል፡፡ በመሆኑም ኢንተርፕራይዙ በተያዘለት ጊዜ ግንባታውን ለማጠናቀቅ በትጋት እየሠራ ይገኛል፡፡

ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ
ፎቶግራፍ መሳይ ያደታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https:///channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
Defence Construction Enterprise

24 Jan, 17:15

962

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ አመራሮች የመስክ ምልከታ አደረጉ፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የዋናው መሥሪያ ቤት እና የግንባታ ፕሮጀክት አመራሮች በቃሊቲ ግቢ በ2400 ካሬ ላይ ሊገነባ የታሰበውን የቢሮ ሕንጻ ግንባታ ፕሮጀክት በስፍራው ተገኝተው ተመልክተዋል።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የዋናው መሥሪያ ቤት ሕንጻ ግንባታ ልዩ ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፋሲካ ንጋቱ በመስክ ምልከታው ለተገኙ አመራሮች ስለ ግንባታው ገለጻ አድርገዋል፡፡

መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የራሱ የቢሮ ሕንጻ እንዲኖረው በአጭር ጊዜ ውስጥ ግንባታ ሲፈቀድለት ገንብቶ ለማጠናቀቅ የሁሉም ፕሮጀክቶች ሁለንተናዊ ድጋፍ እና የቅርብ ክትትል ያስፈልገዋል ብለዋል፡፡

አዲስ ሊገነባ የታሰበው የዋናው መሥሪያ ቤት ሕንጻ የተለያዩ ቢሮዎች፣ ዘመናዊ የስብሰባ አዳራሽ፣ የተለያየ ደረጃ ያላቸው ካፍቴሪያዎች፣የመፀዳጃ ክፍሎች በውስጡ የያዘ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ፋሲካ ገልጸዋል።

በጉብኝቱ ተሳታፊ የነበሩ የፕሮጀክት አመራሮችም የተቋማችንን ስኬት ለማፋጠን እና ተነሳሽነትን ለመፍጠር አመራሩ በአካል ተገኝቶ ምልከታ ማድረጉ ልምድ የምንለዋወጥበት ከመሆኑም በላይ ለሚያጋጥሙ ችግሮች የጋራ መፍትሔ ለማስቀመጥ ወሳኝ ነው ብለዋል።

ለዚህም በሙያም ሆነ በቁሳቁስ ግንባታው እውን ለማድረግ ቃል ገብተዋል፡፡ የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ኢንተርፕራይዙን ስሙ ብቻም ሳይሆን የራሱ ቋሚ መለያ ያለው የግንባታ ተቋም እንዲሆን በተግባር ለመለወጥ እንደሚሰሩ በቁጭት ገልፀዋል፡፡

ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ
ፎቶግራፍ መሳይ ያደታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https:///channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
Defence Construction Enterprise

24 Jan, 12:02

708

አያይዘውም የተቋሙን ንብረትና የሰው ኃይል እንዲሁም ስራን በብቃት መምራት የዋናው መ/ቤት እና ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጆች ቀዳሚ ተግባር መሆኑ እና ተልዕኮን ውጤታማ በመሆነ መንገድ ለመፈጸም በየጊዜው ጠንካራ ድጋፍና ቁጥጥር መኖር እንዳለበት፣ ለዚህም በጠንካራ ዲስፕሊን ሥራዎችን መምራት ዋና ሥራችን ይሆናል ብለዋል።

በማጠቃለያ ውይይቱ ላይ የተሳተፉ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የዋናው መስሪያ ቤት ስራ ክፍል አመራሮች እና የሕንጻና የመንገድ ፕሮጀክት አመራሮች የበጀት አመቱ የስራ እንቅስቃሴዎች የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠል የተስተዋሉ ችግሮችን በአፋጣኝ ሁኔታ በመቅረፍ ሥራቸውን ለውጤት ለማብቃት በትኩረት መሥራት እንደሚገባ፣ ብልሹ አሰራርን በመታገል ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ መረባረብ እንደሚገባቸው የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ኮሎኔል (ኢንጂነር) ሰጠኝ አሳስበዋል፡፡

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወር የሥራ አፈጻጸም አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴን መነሻ ያደረገው ውይይት ተጠናቋል።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኮሎኔል (ኢንጂነር) ሰጠኝ ሊኪሳ በተካሄደው የስራ አፈፃፀም ውይይት የዋናው መ/ቤት፣ የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጆች እና ቡድን መሪዎች በመጀመሪያው ስድስት ወራት ውስጥ የተከናወኑ ተግባራት ሲያከናውኑ ለስራ ተግዳሮት የሚሆኑ ችግሮችን እየፈቱ መምጣታቸውን እንደ ጠንካራ ጎን በማንሳት የሚሥተዋሉ እጥረቶችን ለማስወገድ አመራሩና ሠራተኛው በቅርበት በመሥራት የበለጠ ውጤታማ መሆን የሚያስችል የስራ እቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎችን ያካተተ ስለሆነ በጥብቅ ዲፕሊን ሊመራ ይገባል፡፡ ብዙ ተቋማት እየተፈተኑ ባሉበት በዚህ ዘርፍ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ በፈተና ውስጥ የህይወት መስዋዕትነት እየከፈለ ጭምር በርካታ የግንባታ ሥራዎችን እያከናወነ የሚገኝ ተቋም መሆኑ በብዙ ባለድርሻ አካላት የሚታወቅ ሲሆን ለወደፊቱም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ የውይይት መድረኩ ተጠናቋል፡፡
Defence Construction Enterprise

24 Jan, 12:02

669

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን የስድስት ወር ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ውይይት አደረጉ::

ጥር 16/2017ዓ.ም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያውን የስድስት ወር ዕቅድ አፈጻጸም ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በመከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል ለዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ኢንስቲትዩት ውይይት አደረጉ::

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኮሎኔል (ኢንጂነር) ሰጠኝ ሊኪሳ በመድረኩ እንደገለፁት እንደ ኢንተርፕራይዝ በበጀት ዓመቱ ስኬታማ ስራዎች መከናወናቸውን አንስተው በመንገድና በሕንጻ የግንባታ ስራዎቻችን በሰው ሀብት ልማት፣ ስራዎችን በቴክኖሎጂ ታግዞ ለመስራት፣ሰራተኛን ከሥራ ጋር አገናኝቶ መስራት በበጀት አመቱ የነበረን አፈጻጸም ላይ ችግሮች የነበሩ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ለነበሩት ችግሮች አመራሩና ሰራተኛው የየራሳቸውን ድርሻ ወስደው ስህተቶች በአፋጣኝ ታርመው ወደ ትክክለኛው የሥራ መስመር በመግባት ኢንተርፕራይዙ ያሉበትን ዘርፈ ብዙ ችግሮች በመፍታት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተሻለ አፈጻጸም ደረጃ መድረስ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ሃገራችን ኢትዮጵያ አሁን እያካሄደችው ከሚገኘው ፈጣን የለውጥ እንቅስቃሴ ጋር አብሮ የሚጓዝ የኮንስትራክሽን ተቋም ማድረግ አስፈላጊ ስለሆነ በኢንተርፕራይዙ የሚገኝ ሠራተኞች የኢንተርፕራይዙን ራዕይ እውን ለማድረግ እስካሁን ይዘናቸው የመጣናቸውን ችግሮች ቁጭት ፈጥሮብን የምንመራውን ተቋም በመቀየር የሚጠበቅብንን ኃላፊነት በመወጣት በተጨባጭ መገኘት ይኖርብናል፡፡ ብልሹ አሰራርን በመታገል ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ መረባረብ እንደሚገባቸው ያሳሰቡት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አመራሩ የተቋሙን ህልውና በፅኑ መሰረት ላይ ለመገንባት በቀጣይ በሚያከናውነው ተጨባጭ የሥራ ውጤት እንደሚመዘንም አሳስበዋል።

ኢንተርፕራይዙ የለውጥ እሳቤ ውስጥ ያለ በመሆኑ አመራሩና ሠራተኛው ይህንን በመገንዘብ ሠራተኛን ከሥራ ጋር የማገናኘት፣ በአመራሩና በሰራተኛው መካከል የተግባርና የአመለካከት አንድነት ለማምጣት የውስጥ አሰራር መመሪያዎች እና ደንቦች ማሻሻያዎች ተዘጋጅተዋል፡፡ የተዘጋጁት ደንብ እና መመሪያዎች በአጭር ጊዜ ጸድቀው ወደ ተግባር እንደሚገባ እና ለዚህም የበየደረጃው ያለ አመራር የአፈጻጸም ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኮሎኔል (ኢንጂነር) ሰጠኝ በአጽንዖት ተናግረዋል።
Defence Construction Enterprise

24 Jan, 10:35

615

የኢንተርፕራይዙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በእቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በተያዘው እቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት አድርገው በቀጣይ ሥራዎች ላይም አቅጣጫ አሥቀምጠዋል።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኮሎኔል ኢንጂነር ሰጠኝ ሊኪሳ ኢንተርፕራይዙ በበጀት ዓመቱ ስኬታማ ስራዎች ማከናወኑን አንስተው በመንገድና በሕንጻ የግንባታ ስራዎች፣ በሰው ሀብት ልማት ስራዎችን በቴክኖሎጂ ታግዞ ለመስራት፣ ሰራተኛን ከሥራ ጋር አገናኝቶ መስራት የነበሩ የአፈጻጸም ላይ ችግሮች መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

ለችግሮች አመራሩና ሰራተኛው የየራሳቸውን ድርሻ ወስደው ስህተቶች በአፋጣኝ በማረም ወደ ትክክለኛው የሥራ መስመር በመግባት ኢንተርፕራይዙ ያሉበትን ዘርፈ ብዙ ችግሮች በመፍታት በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተሻለ አፈጻጸም ደረጃ ማድረስ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ሃገራችን ኢትዮጵያ አሁን እያካሄደችው ከሚገኘው ፈጣን የለውጥ እንቅስቃሴ ጋር አብሮ የሚጓዝ የኮንስትራክሽን ተቋም ማድረግ አስፈላጊ ስለሆነ በኢንተርፕራይዙ የሚገኙ ሠራተኞች የኢንተርፕራይዙን ራዕይ እውን ለማድረግ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት የሚጠበቅብንን ኃላፊነት መወጣት ይኖርብናል ነው ያሉት፡፡

በኢንተርፕራይዙ የተዘጋጁት ደንብ እና መመሪያዎች በአጭር ጊዜ ጸድቀው ወደ ተግባር እንደሚገባ እና ለዚህም በየደረጃው ያለ አመራር የአፈጻጸም ቁርጠኝነት እንደሚያስፈልግ የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኮሎኔል ኢንጂነር ሰጠኝ አጽንዖት ሰጥተዋል።

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መስሪያ ቤት ስራ ክፍል አመራሮች እና የሕንጻና የመንገድ ፕሮጀክት አመራሮች የበጀት አመቱ የስራ እንቅስቃሴዎች የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠል የተስተዋሉ ችግሮችን በአፋጣኝ ሁኔታ በመቅረፍ ሥራቸውን ለውጤት ለማብቃት በትኩረት ለመሥራትና ለማሥቀጠል ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ዘጋቢ ማርታ ተፈሪ
ፎቶግራፍ ማንመሳይ ያደታ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https:///channel/UCgcF4HWzgNZRsmMlUlb8ebQ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official
Defence Construction Enterprise

18 Jan, 18:09

1,044

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ
Defence Construction Enterprise

17 Jan, 16:33

1,004

የሥራ ቦታን ከቆሻሻ ፅዱ ማድረግ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው፡፡

ጥር 9/2017ዓ.ም

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ሠራተኞች ጽዱ የሆነ የሥራ አካባቢን ለመፍጠር መስሪያ ቤቱን ግቢ ለሥራ ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም የጽዳት ዘመቻ አካሄዱ፡፡

የሥራ ቦታን ምቹ ማድረግ ለሰዎች አካላዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኀበራዊና ሥነ - አእምሮአዊ ጤንነትንና ደኀንነትን ለመጠበቅ አስተዋጽኦ ከሚያደርጉ መሠረታዊ ፍላጎቶች አንዱ ነው፡፡  በመሆኑም ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ የሚያሳልፋት በስራ ቦታቸው ስለሆነ አንድ መስሪያ ቤት ንጽህናው የተጓደ ከሆነ በጤና ላይ ሊያስከትል የሚችለው ጉዳት በቀላሉ የሚገመት አይሆንም፡፡

ለሥራ ምቹ ያልሆነ መስሪያ ቤት ሠራተኞችን ለቅዝቃዜ፣ላልተፈለገ ሙቀት፣ለተለያዩ አደጋዎች፣ለከፍተኛ ድምፅ፣ለተለያዩ ተላላፊ በሽታዎች መፈጠርና መሠራጨት እንዲሁም ለሥነ አእምሮአዊና ማኀበራዊ ቀውስ መፈጠር ዋነኛ ምክንያት ነዉ፡፡

የመከላያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሠራተኞው ሆነ ለባለድርሻ አካላት ምቹ እና ጽዱ የሆነ የሥራ አካባቢን ለመፍጠር በቃሊቲ የሚገኘውን የመስሪያ ቤቱ ግቢ ውስጥ የጽዳት ዘመቻ አካሂዷል፡፡

የሥራ አካባቢን ጽዱ እና ምቹ ማድረግ ረጅሙን ጊዜያችንን የምናሳልፈው ስራ በምንሰራበት መስሪያ ቤት ውስጥ በመሆኑ የሥራ አካባቢን ምቹ እና ለሥራ ተስማሚ ማድረግ የሁሉም ሠራተኛ ኃላፊነት ነው፡፡ ዛሬ የተጀመረው የጽዳት ዘመቻ ቀጣይነት ያለው ሲሆን ሁሉም የሥራ መሪ እና ሠራተኛ በተመደበበት የሥራ ቦታ ላይ አካባቢውን በንጽህና መያዝ እና ማጽዳት ይጠበቅበታል።

በጽዳት ዘመቻው ከተሳተፉ ሠራተኞች መካከል የምንሰራበትን መስሪያ ቤት ውብና ጽዱ ለማድረግ የበኩላቸውን ሚና እየተወጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የጽዳት ዘመቻው በአስተባባሪዎች አማካኝነት ሠራተኛው እንዲያጸዳ በተመደበበት ቦታ ለግማሽ ቀን ተከናውኗል፡፡
Defence Construction Enterprise

06 Jan, 13:49

832

እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ!!