Latest Posts from ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር (@bttsca) on Telegram

ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር Telegram Posts

ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር
መጪው ጊዜ ብሩህ ነው
1,526 Subscribers
49 Photos
2 Videos
Last Updated 01.03.2025 16:26

The latest content shared by ብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር on Telegram


ውድ አባላት ነገ 22/2017 ዓ.ም ልዩ ብድር የመጨረሻ ቀን ስለሆነ ያልተበደራችሁ መጥታችሁ እድትበደሩ እንዲሁም ለውድ አባሎቻችንም እንደተለመደው መልዕክቱን እንድታስተላልፉልን እንጠይቃለን።

ለውድ አባላት በሙሉ
ከታህሳስ 2/2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 22/2017 ዓ.ም ድረስ በአካል እየመጣችሁ የገና በዓል ልዩ ብድር መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ለምዝገባ ስትመጡ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ሂሳብ ሂሳብ ቁጥር የሌላችሁ አባላት
- የታደሰ የቀበሌ ወይም የመስሪያቤት መታወቂያ ኮፒ ከፊት ከጀርባ
- ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ ይዛችሁ እንድትመጡ እንዲሁም የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ሂሳብ ቁጥር ያላችሁ ሂሳብ ቁጥራችሁን ይዛችሁ እንድትመጡ በቅድሚያ እናሳውቃለን።

ማስታወሻ
ውድ አባላት
ነገ ማለትም ህዳር 17/2017 ዓ.ም የመጨረሻ የብድር መስጫ ቀን ሲሆን ቀጣይ ከላይ በተገለፀው ፕሮግራም መሠረት ከልዩ ብድር ክፍያ በኃላ ይቀጥላል። ስለሆነም ውድ አባላት ለየመስሪያ ቤታችሁ አባላት መረጃውን እንድታጋሩ እንናስታውሳለን።

ውድ አባላት
የ2017 ዓ.ም በዚህ ፕሮግራም መሠረት የምናስተናግድ ሲሆን እንደተለመደው ለውድ አባላት ሼር እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

ለውድ አባላት በሙሉ
ከነሀሴ 20/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 1/2016 ዓ.ም ድረስ በአካል እየመጣችሁ የእንቁጣጣሽ በዓል ልዩ ብድር መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ለምዝገባ ስትመጡ
- የታደሰ የቀበሌ ወይም የመስሪያቤት መታወቂያ ኮፒ ከፊት ከጀርባ
- ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ ይዛችሁ እንድትመጡ በቅድሚያ እናሳውቃለን።

ለውድ አባላት በሙሉ
የዓመቱን ሂሳብ ለመሥራትና ለማጠናቅ ባንክ አስገብታችሁ በጃችሁ ሪሲት ያለ አባላት ለኦዲት ስራ አስቸግሮናል በመሆኑም በአስቸኳይ ለፅ/ቤቱ እንድታስገቡልን እናሳስባለን።

የ2017 ዓ.ም ፕሮግራም በቅርቡ የምንገልፅ ሲሆን የብድር ማመልከቻ ያስገባችሁ አባላት ብቻ በሚደወልላቹ ቀን መጥታችሁ ቼኮቻችሁን እንድትወስዱ ሲሆን ለመላው ውድ አባሎቻችን ለትምህርት የምትገቡ መልካም የትምህርት ጊዜ እንዲሁ መልካም የእረፍት እዲሆንላችሁ እንመኛለን።

በድጋሚ ጥብቅ የስብሰባ ጥሪ
ሰኔ 26/2016 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤው ባለመሟላቱ ስብሰባው ለሁለተኛ ጊዜ መራዘሙ ይታወቃል።
ሆኖም በድጋሚ ቅዳሜ ሀምሌ 6/2016 ዓ.ም በተስፋ ኮከብ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከጠዋቱ 2:30 ይካሄዳል። ስለሆነም በዕለቱ ለውይይት የሚቀርቡት አጀንዳዎች

1.የማህበሩን 2017 ዓ.ም እቅድና በጀት ማፅደቅ
2.የትርፍ ትርፍ ክፍፍል መግለፅ
3.የሽምግልና ዳኞች መምረጥ
4.የአገልግሎት ክፍያን ማሳደግ
5.የመድህን ዋስትና አገልግሎት መወሰን
6.የሼር ግዢን አሳውቆ ማስወሰን መሆኑን በቅድሚያ እየገለፅን በማህበሩ ደንብ መሠረት በጉባኤው ላይ የማይገኝ አባል ብር 20 የሚቀጣ መሆኑን እናሳውቃለን።
                                             ኮሚቴው
  

ለውድ አባላት በሙሉ
ሐሙስ ሰኔ 27/2016 ዓ.ም አጣዳፊ ስራዎች ስለገጠሙን እንዲሁ ለ29/2016 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ መዘጋጀት ያለበት ጉዳዮች ስላሉብን በማንኛውም ጉዳይ እንዲሁ የሂሳብ ደብተር መሙላት  የማናስተናግድ ስለሆነ ውድ አባላት ይህንን አውቃችሁ እንዳትጉላሉ እንዲሁ ላልሰሙ አባላት መረጃውን እንድታሰራጩ እያሳወቅን በድጋሚ ከላይ በተገለፀው የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ እንድትገኙ እናሳስባለን።

ጥብቅ የስብሰባ ጥሪ ለውድ አባላት በሙሉ
ማህበር በአዋጅ ቁጥር 985/2009 መሰረት በዓመት 2 ጊዜ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ የብሩህ ተስፋ መም/ሠ/የገንዘብ ቁጠባ ብድር ኃ/የተ/ህ/ሥ/ማህበር ሰኔ 29/2016 ዓ.ም በተስፋ ኮከብ የመጀ/ደረጃ ት/ቤት ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ አባላት በሙሉ ስብሰባ እንደሚደረግ አውቆ እንዲገኝ እያሳሰብን በማይገኝ አባላት ላይ ደንቡ በሚፈቅደው ቅጣቱ ተፈፃሚ ሆኖ ከማህበሩ ሊያገኝ የሚገባውን ማንኛውንም አገልግሎት እንደማያገኝ በቅድሚያ እያሳወቅን በዕለቱ ለውይይት የሚቀርቡት አጀንዳዎች፦
1. የማህበሩን 2017 ዓ.ም እቅድና በጀት ማፅደቅ
2. የትርፍ ትርፍ ክፍፍል መግለፅ
3. የሽምግልና ዳኞች መምረጥ
4. የአገልግሎት ክፍያን ማሳደግ
5. የመድህን ዋስትና አገልግሎት መወሰን
6. የሼር ግዢን አሳውቆ ማስወሰን መሆኑን በቅድሚያ እንገልፃለን፡፡
ኮሚቴው