በአልከሶና አካባቢዋ ሰለፍዮች ግሩፕ ላይ አንድ ወንድም ባሕሩ ተካ ( አሕመድ ) ብሎ ፅፎ አሕመድ ማን ነው ? የአባቱ ስም ነው ወይ ? ወይስ ሌላ ባሕሩ ነው ? ባሕሩ ተካ ከሆነ አባቱ ሰልሟል ወይ የሚሉ ጥያቄዎች ተደጋግሞ አይቻለሁ ። ይህ ጥያቄ በብዙዎች አእምሮ ሊኖር ስለሚችል ለወንድምና እህቶች ቤተሰቦቼ በሙሉ የሰለሙ መሆኑን ላሳውቃቸው ወደድኩ ። መስለማቸው ብቻ ሳይሆን ሁሉም ቤተሰቦቼ ሰለፍዮች መሆናቸውንም አውቃችሁ ዱዓእ እንድታደርጉላቸው ላስታውሳችሁ እወዳለሁ ።
ምስጋና ለአለማቱ ጌታ የተገባ ይሁንና ከአጎቴቼ ውስጥ አብዛኞቹ ከነቤተሰቦቻቸው ሰልሟል ። የተወሰኑት ደግሞ ልጆቻቸው ሰልሟል ። አላህ ሁላችንንም ፅናቱን ይስጠን ።
http://t.me/bahruteka