ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
የተማሪ ወላጆች እና ተማሪዎች በሙሉ
የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመጀመሪያው ወሰነ ትምህርት (First semester) ትምህርት ተጠናቆ የማጠቃለያ ፈተና መሠጠቱ ይታወቃል። በመሆኑም የፈተና ወረቀት (ውጤት) የሚመለሰው የፊታችን ሠኞ ማለትም በ26/05/17 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 - 5:30 እንደሆነ መልዕክት መተላለፉ የሚታወቅ ሲሆን በዕለቱም በመገኘት የፈተና ወረቀት (ውጤት) እንድትወስዱ እንዲሁም በሁሉም የትምህርት ዓይነት ከ100 ያላችሁን ውጤት እንድትመለከቱና እንድታረጋግጡ እናሳስባለን።
ማሳሰቢያ
በዕለቱ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስትመጡ: -
፨ የትምህርት ቤቱን ሙሉ የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) ብቻ አድርጋችሁ ብቻ ነው መምጣት የሚቻለው።
፨ የትምህርት ቤቱን መታወቂያም መያዝ እንደሚኖርባችሁ እናሳስባለን።
፨ የትምህርት ቤቱን የደንብ ልብስ (ዩኒፎርም) ሳይለብስ እንዲሁም የትምህርት ቤቱን መታወቂያ ያልያዘ ተማሪ ወደ ትምህርት ቤቱ ግቢ እንደማይገባ እንገልፃለን።
ት/ቤቱ