Последние посты AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ (@aljueddaawa) в Telegram

Посты канала AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ
AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

«በብዕርህ መጣራት ባትችል በሰዎች ብዕር ተጣራ»

ሀሳብ አሰተያየት ካለዎት ⇙
@AlJUDDAEWA_bot
1,921 подписчиков
1,223 фото
126 видео
Последнее обновление 09.03.2025 02:28

Похожие каналы

Abu Hiba (አቡ ሒባ)
6,122 подписчиков
Fuad Shemsu || ፋአድ ሸምሱ
2,428 подписчиков

Последний контент, опубликованный в AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ на Telegram

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

06 Feb, 02:00

227

ታላቁ ሰው ፉደይል ኢብ ኢያድ እንድህ ይል ነበር

《እነዚህ ሰደቃን ሚጠይቁ(ሚለምኑ)ሰዎች ምንኛ ያስደሳሉ የኛን ስንቅ ያለ ምንም ክፍያ ተሸክመው አላህ ዘንድ ያደርሱልናል》

كان الفضيل بن عيّاض رحمه الله تعالى يقول
《 نعم السائلون؛ يحملون أزوادنا إلى الآخرة بغير أجرة! حتى يضعوها في الميزان بين يدي الله تعالى》

ኒያችንን ብቻ ማሳመር ነው ያለብን የምንሰጣት ሰደቃ ለሚስኪኖች የምናደርገው ድጋፍ አላህ ዘንድ ሁጃ ይሆንልናል።

አላህ ያገኘሀውን ገንዘብ ከየት አመጣህ የትስ አዋልከው ብሎ ሲጠይቀን መልሳችን ምን  ይሆን?

አዎ አሁን ጤና እያለን ገንዘብ እያለን ጊዜ እያለን ኸይር ስራ እንስራ ደካሞችን አለንላችሁ እንበላቸው እነሱን አስደስተን አላህ በኛ የመደሰትን ትልቅ እድል እንጎናፀፍ አብሽሩ ሰደቃ ስለሰጠን ገንዘባችን አይቀንስም።

ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል 《 አላህ ሶስት ነገር ላይ ምሏል ከዛም ውስጥ  ሰደቃ በመስጠት ገንዘብ አይቀንስም》 ብለዋል ።


"የአንድ ቤተሰብ የረመዷን አስቤዛ ፓኬጅ 3500 ብር"

በባንክ ገቢ ለማድረግ

♢ ንግድ ባንክ  1000388115444
♢  አዋሸ ባንክ       01425412116600
♢ ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ  1000085221616
♢ ኦሮሚያ ኢንተርናሺናል ባንክ 1493281700001
♢ ሒጅራ ባንክ  1001097420001
♢ ዘምዘም ባንክ    0019001920101

የአካውንት ሰም ፦ ሙፍቲ ዳውድ የከሚሴ ወጣቶች የልማትና የበጎ አድራጎት ማህበር

#ረመዷንን_ከሚሰኪኖች_ጋር_6 #ለ600_አባወራዎች #ሙፍቲ_ዳውድ_ቲም
AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

05 Feb, 16:47

171

💲 ሰደቃ ከገንዘብ ላይ አታጎድልም!

አላህ (ሱ•ወ) እንዲህ ይላል፦

“ጌታዬ ሲሳይን ከባሮቹ ለሚሻው ሰው ያሰፋል፡፡ ለእርሱም ያጠብባል፡፡ ከማንኛውም ነገር የምትለግሱትን እርሱ ይተካዋል፡፡ እርሱም ከሲሳይ ሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው” በላቸው፡፡۝

📖 ምዕራፍ ሰበእ: 39

"የአንድ ቤተሰብ የረመዷን አስቤዛ ፓኬጅ 3500 ብር"

በባንክ ገቢ ለማድረግ

♢ ንግድ ባንክ 1000388115444
♢ አዋሸ ባንክ 01425412116600
♢ ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 1000085221616
♢ ኦሮሚያ ኢንተርናሺናል ባንክ 1493281700001
♢ ሒጅራ ባንክ 1001097420001
♢ ዘምዘም ባንክ 0019001920101

የአካውንት ሰም ፦ ሙፍቲ ዳውድ የከሚሴ ወጣቶች የልማትና የበጎ አድራጎት ማህበር

#ረመዷንን_ከሚሰኪኖች_ጋር_6 #ለ600_አባወራዎች
#ሙፍቲ_ዳውድ_ቲም
AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

05 Feb, 11:00

178

አንድ ወንድሜ የአንድ ቤተሰብ 3,500 ብር ገቢ አድርጓል። አላህ ይጨምርለት አላህ ይደሰትበት ጀዛከላሁ ኸይር

እርሰዎም በሚችሉት ይሳተፉ

"የአንድ ቤተሰብ የረመዷን አስቤዛ ፓኬጅ 3500 ብር"

#ረመዷንን_ከሚሰኪኖች_ጋር_6 #ለ600_አባወራዎች #ሙፍቲ_ዳውድ_ቲም
AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

05 Feb, 08:43

152

አባ ሥራ ልሄድ ነው ብየ ግንባሩን ስሜ ዱዓውን ተቀብየ የሚሸኘኝ አባት ነበረኝ ይሄን ሰሜት ትረዱታላቹህ?

ከአባየ ህልፈት ቦሇላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለስራ እየወጣሁ ነው…

ዱንያ ላይ ምንም ዘውታሪ የሆነ ነገር የለም። ሁሉም በቀኑ በተራው ይጓዛል።

“የቱንም ያህል ብትኖር ሟች ነህ የፈለከውን ውደድ ትለየዋለህ”

ከየትኛውም ጉዳያቹህ በፊት ወላጆቻችሁን አስቀድሙ ሁሌም ለነሱ ቅርብ ሁኑ ያ ጥቁር ቀን ይመጣል ለዳማና ቁጭትን ይዞ

አላህ ሆይ! ያቺን በህይወቱ ሁሉ ስለኛ ደስታ ሰለኛ ምቾት ያሰበች የተጨነቀችን ነፍስ ከቀብር መከራ ከመህሸር ቀን ጭንቅ ነፃ በላት ያ ከሪም 🤲

አላህ ሆይ! ባንተ ልቅና የሚያምን ባንተ እዝነትም የሚተማመን ባሪያህ ነበር አላህ ሆይ አታሳፍረው
አላህ ሆይ! ያንተ እዝነት ከሱ ስህተትና ጥፋት የሰፋ ነው አባታችንን በሰፊው እዝነትህና በማያልቀው አውፍታህ አካበው ያ ረሕማኑ ያ ረሒሙ ያ ወዱድ 🤲
AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

05 Feb, 04:48

163

ሙፍቲ ዳውድ የበጎ አድራጎት ድርጅት ለ1446 ሒጅራ ረመዷን ለ600 አባወራዎች የረመዷን አስቤዛ ለማበርከት አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ ነው። በዚህ በትልቅ ኸይር ላይ ተሳተፉ

አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ አለ፦

الَّذِينَ يُنفِقُونَ أَمْوَالَهُم بِاللَّيْلِ وَالنَّهَارِ سِرًّا وَعَلَانِيَةً فَلَهُمْ أَجْرُهُمْ عِندَ رَبِّهِمْ وَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ

“እነዚያ ገንዘቦቻቸውን በሌሊትና በቀን በድብቅም በግልጽም የሚለግሱ ለእነርሱ በጌታቸው ዘንድ ምንዳቸው አላቸው። በእነርሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም እነርሱም አያዝኑም።” (አል-በቀራ 2፤ 274)

ከሶደቃ የሚጠቀመው የመጀመሪያው ሰው ሶደቃ አድራጊው ነው። ምክንያቱም ከስስት ታጠራዋለች። ከኃጢያትም ትጠብቀዋለች። ከመከራም ትከላከልለታለች…

የአቅማችን ያክል በመለገስ የወገኖቻችን ችግር እንቅረፍ
የአንድ ቤተሰብ ማሰፈጠሪያ 3,500 ብር

በባንክ ገቢ ለማድረግ ↷

♢ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000388115444

♢ አዋሸ ባንክ 01425412116600

♢ ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 1000085221616

♢ ኦሮሚያ ኢንተርናሺናል ባንክ 1493281700001

♢ ሒጅራ ባንክ 1001097420001

♢ ዘምዘም ባንክ 0019001920101

#ረመዷንን_ከሚሰኪኖች_ጋር_6 #ለ600_አባወራዎች #ሙፍቲ_ዳውድ_ቲም
AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

05 Feb, 04:44

150

ሀጅ ልሂድ ወይስ ልቅር🙄 ?
******
በ 2013 PhD ልማር ብየ ገባሁ። በዛ ወቅት 3 ልጅ ነበረኝ። እና ዩኒቨርስቲው ለምርምር የምሰጣችሁ 60 ሺ ብር ብቻ ነው ብሎ ቸክ ሰጠን። እኔም በዚህ ብር ምኑን ተመራመርኩት እያልኩ ቼኩን ተቀብየ ከተማ ስወጣ የሀጅ ማስታወቂያ አየሁ። ክፍያውንም 56 ሺ ብር ይላል። ነሻጣየ ድንገት ገንፍሎ መጅሊሶችን የሚቀርብ አንድ ሷሂቤን ጠርቼ ነገ አስመዝግበኝ አልኩት። ይሄን 60 ሺ ከየወሩ ደሞዜ ብቀንስ መሙላት ለምርምሩ አያቅተኝም አልኩት። እሺ ብሎኝ ተለያየን።

ሆኖም አዳሬ ጥሩ አልነበረም..እንቅልፍ አሳጣኝ። ሸይጧን በምድር ላይ ያለውን ጦር በሙሉ ሰብስቦ አዘመተብኝ። ቁርአን እንዳለው>> ሸይጧን በድህነት ያስፈራራችኋል<< ነገሩ ሆነ። ሀጅ ለመሄድ በመወሰኔ የሚያጋጥመኝን የድህነት አይነት ደረደረልኝ። ከዛም አልፎ የቤተሰቤን ድህነት የሰፈሩን ችግር በሙሉ ተራ በተራ እየነገረ ውሳኔህ የጥጋብ ነው የራስወዳድነት ነው እያለ ደሊል ደረደረልኝ። የሚገርመውኮ ሀጅ ብቀር አንድም ብር ላለው ነገሮች አልሰጥም። ከሁሉም ምክንያቱ ያሳመነኝ >>ባለቤትህ እርጉዝ ዘጠነኛ ወር ሆኗት መሄድህ ጭካኔ ነው<< የሚል መረጃ ያቀረበበት ነው። ብቻ ነፍስያም ተጨምራ ለሊቱን ሲወቅጡኝ አደሩ። ለራሴ ድጋፍ ደሊል የሆነኝ በዚያ አመት በረመዳን ወራት በህልሜ ለበይክ እያልኩ ከእባን ስዞር ያየሁትን መናም እንደማስረጂያ መቁጠሬ ነው።

አይነጋ የለ ነግቶ ሷሂቤ ደወለ። ሰፈር መኪና ይዞ ቆሟል። አፍሬ ተነሳሁና መጣሁ አልኩ። ተውኩት እንዴት ይባላል። ባለቤቴን ስነግራት "ወላሂ ሂድ ይገባሀል አለችኝ"። እየታሸሁም በፊትና በግድ ሄድኩና ተመዝግቤ ስከፍል ሸይጧን የምድር ጦሩንም ይሁን አየርሀይሉን ይዞ አፈገፈገ። ልቤን ቀስፎ የያዘው ሁሉ ሸክም ለቀቀኝ። የሆነው ሆነ። ይህንን ታሪክ የጻፍኩት ምናልባት የገጠማችሁ ካላችሁ እንድትበረታቱ እንዳትሸነፉ ለማለት ነው። ምክር ስጠይቁም ከሚያበረታችሁ ብቻ ይሁን። እንጂ የዛን ወቅት ይቅርብህ የሚል ቢመጣ በተለይ ከቤተሰብ ከባድ ነበር። ለሁሉም የነገርኩት አውሮፕላን ላይ ስወጣ ነበር።

በዙል ሂጃ 3ኛው ቀን መካ አልቤክ ተኝቼ ሳለ ለሊት 9 ሰአት ሜሴጅ ደረሰኝ። ባለቤትህ ሴት ልጅ በሰላም ተገላግላለች ይላል። አገሩም ወራቱም የተከበረ ጀሊሉም የላቀ ነውና "አላሁ አክበር አላሁ አክበር እያልኩ ተነሳሁ። ወላጆቿ በሌሉበት ጥያት መጥቻለሁ በደንብ ካድማት እያልኩ ሁኔታዋ ለዱአ ተመችቶኝ ነበር። ውዱእ አድርጌ ለሽኩር ጠዋፍ ላድርግ ብየ በለሊቱ ወደ ሀረም (ከእባ) ወጣሁ። በእግሬ ብቻየን በጭርታው አስፓልት ስጓዝ አንድ ነጭ መኪና ቆመ። ታክሲ ይሆናል ብየ "ሀረም" "ከም" አልኩት። በ ሀሳቤ 2 ሪያል ከሆነ እሄዳለሁ እያልኩ ሳስብ "ቢሸርጥ አንተድአ ሊ" ዱአ የምታደርግልኝ ከሆነ በነጻ ነው አለኝ። እኔም " በልደቱን ጠይበቱን ወረቡን ገፉር" ብየው ገባሁ። ሰውየው በደስታ ሳቀና ከበረ። ሀረም ወስዶ ጣለኝ..ሀረም በ ባብ ፈህድ ገብቼ ሺዎቹን በጠዋፍ ማእበል ለሽኩር ተቀላቀልኩ።

ንጋት ላይ ሷሂቦቼ ሙሬና ጀሜ ቢንዳውድ ፊት ለፊት ሜዳው ላይ ፈልገው አገኙኝ። ሱብሂ ላይ ከዶርም ስጠፋባቸው ደውለው ደስታየን ነግሬያቸው ተከትለውኝ ነበር። እርጎና ቁርስ ፉል ይዘው መጠው ካደሙኝ። ከድሮ ጀምሮ ሲካድሙኝ ይመቸኛል። እዛ ሜዳ ላይ ቁጭ ብለን እያለ ጀሊሉ ምን ያህል በፈድሉ እንዳከረመኝ ታስቦኝ ልጅቱን "ኢናያ" ብየ ስም አወጣሁላት።

እና ሀጅን ስታስቡ ሸይጧን አይፈትነንም ብላችሁ አትጠብቁ። ለመወሰን ያለ ውጣ ውረድ ከባድ ነው። ከወጀበባችሁ ነፍስያን ታግላችሁ በደጋጎች ተገፍታችሁ መሄድ ነው። አርካን ሚን አርካኒል ኢስላም ነው። ዛሬ ነገ ስትሉ ሚልየን ይገባል። በሀያት እያሉ ለአላህ በሚያወጡት ጨከን ማለት ያስፈልጋል። ዛሬ ላይ የሀጅ ጉዞው ፈተናው የዱንያ ፍቅር ነው። እንደድሮዎቹ በእግር በሶ ጭነን 6 ወር ተጓዙ ሳንባል እዚህ ካደረሰን ደጉ ነገር መጓዝ ነው።

ያልነገርኳችሁ ነገር የሚና ገበያ ያዋጣል። አረፋ ላይ የጠየቁት ሁሉ ይገኛል። የዛኔ የጠየቅኩት ሀጃ ሲወጣ አመትም አልዞረም። አላህ ያስረዳንና። ለሀጅ አላህ ከሰጠህ 625 ሺ ብዙ አይደለም። ሀጃ ላያልቅ ዋጅባት ላይ እየደከምን እድሜያችን እንዳያልቅ።

© ከማ ቃለ ፕሮፌሰር Kha Abate
AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

03 Feb, 18:22

177

የኑሮ ሁኔታ ሁሉም ዘንድ ከብዷል። ወትሮም በድጋፍ ለነበረው እጅጉን ከብዷል። ይሄን ጊዜ በመተዛዘን ካላሳለፍነው አሰከፊ ነው።

ረመዷን ቀኑን ፁሞ ውሎ ማፍጠሪያ ማጣት…

ካለን እናካፍን ሰደቃች ለነገ ለአኼራች ጥላችን ትሆናለች ኢንሻ አላህ

"የአንድ ቤተሰብ የረመዷን አስቤዛ ፓኬጅ 3500 ብር"

#ረመዷንን_ከሚሰኪኖች_ጋር_6 #ለ600_አባወራዎች #ሙፍቲ_ዳውድ_ቲም
AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

03 Feb, 08:43

225

"ፆመኛን ያስፈጠረ ከፆመኛው አጅር ምንም ሳይቀነስ የፆመኛውን አምሳያ ያህል አጅር አለው።"
ረሱል - ﷺ -

"የአንድ ቤተሰብ የረመዷን አስቤዛ ፓኬጅ 3500 ብር"

#ረመዷንን_ከሚሰኪኖች_ጋር_6 #ለ600_አባወራዎች #ሙፍቲ_ዳውድ_ቲም
AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

03 Feb, 03:12

196

አስር ዓመት ያልሞላቸው ታዳጊዎችን ፈጀር ሶፈል አወል ማገኘት እንዴት ያስደሰታል ምንኛ ያማረ ተርቢያ
AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

02 Feb, 18:16

210

Waldaa Misoomaaa fi Tola Oltummaa Dargaggoota Mufti  Daawwuud Kamisee

"Ramadaana Miskiina /Harka qalleeyyii waliin!" jechuun Waldaan kuni sooma Ramadaanaa marsaa shanaffaa bara 2017 namoota harka qalleeyyii 600 tahaaniif baasi ji'a ji'aa isaanii dandahuuf sochii  taasisaa jira.

Deeggarsi ji'aa ramadaana kanaaf maatii tokkoof taasifamuu qarshii 3500 yommuu tahu ramadaana kana harka qalleeyyii /miskiinota 600f taasifama.

Ergamaan Rabbii Rasuuli keenya (SAW)

Namni nama soomanaan oolee faxarsiise, miindaan (ajiriiin) isaa akka nama soomana sana soomeetti isaaf lakkaa'ama; ajiriin irraa hin hiir'atu.

Hundi keessan hojii kheeyrii kanatti makamtanii hirmaachuudhaan, miskiinota (harka qalleeyyii) kanneen soomana sooman faxarsiisaa.

Baankii Daldalaa Itoophiyaa 1000388115444

♢ Baankii Awaash  01425412116600

♢ Baankii Waldaa Hojii Gamtaa Oromiyaa 1000085221616

♢ Baankiii Oromiyaa 1493281700001

♢ Baankii Hijraa 1001097420001

♢ Baankii Zamzam 0019001920101

#ረመዷንን_ከሚሰኪኖች_ጋር_6 #ለ600_አባወራዎች #ሙፍቲ_ዳውድ_ቲም