AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ @aljueddaawa Channel on Telegram

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

@aljueddaawa


AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

«በብዕርህ መጣራት ባትችል በሰዎች ብዕር ተጣራ»

ሀሳብ አሰተያየት ካለዎት ⇙
@AlJUDDAEWA_bot

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ (Amharic)

በብዕርህ መጣራት ባትችል በሰዎች ብዕር ተጣራ አዝናለሁ! አል–ጁድ ደዕዋ በአል–ጁድ አሜሪካዎች የሚኖሩትን አገራችን ለውጥ እና ምስራችን ዘንድ የሚያደርግ ችላጋታ ሰላም ለአገራችን ማግኘት ይችላል። የአል–ጁድ ችላጋታ ከተለያዩ አማርኛ ፊደል ላይ ያሳክላል እና መባልን ለማዋለቅ የሚረዳ፣ ወደ ጉዳዮች ለመጫን የሚጠቁ መዝገብን ለማረጋጋት ምስል የሚለው የአል–ጁድ ደዕዋ ችላጋታ ላይ ሳይሆን በአሁኑ ጊዜ ባቀረብኩት መረጃ እና መማጸን መንገዳችን ላይ የሚለውን ታሪኩን በጣም እያስቀምሳችሁ ውይዋል። እንደገና ለውጤታችን በምንመጣው በሽሉ የሚዘንጋነውን የቴሌግራም መዝገብ አቅም ቨድሮ በመሆን በእኛ የልዩ መረጃ እንቀመጣለን።

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

27 Jan, 19:20


ሰሞኑን ስናሰባስብ የነበረው ለወለዲ ከተማ ለቢላል መስጅድ ምንጣፍ በአላህ ፍቃድ በእናንተ ሰበብ ኢሄ ምንጣፉ መስጅዱ ደርሶ ማህበረሰብ በዚህ ሰዓት ማለትም (3:4ዐ) ላይ መስጅድ  በመገኘት እያነጠፉ ይገኛሉ ።

በዚህ በትልቅ ኸይር ስራ ላይ የተሳተፍቹህ በሙሉ እንኳን ደስ አላቹህ ጀዛኩሙላሁ ኸይረን

በቅርብ ወደ ከተማው ሂደን መረጃውን በደንብ እናሳውቃለን ። በዚህ ምሽት ላይ መረጃውን ሲያሳውቁኝ ደስ ብሎኝ ነው የነገርካቹህ ።

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

26 Jan, 17:39


«አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው፡፡» (ሱረቱ አል-ኢኽላስ - 2)

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

25 Jan, 19:15


“አላህ ዘንድ እሺ የተባለ ዱዓ ሁሉ የቂን ነበር መጀመሪያው። … "አላህዬ ያደርገዋል" የሚል ፅኑ እምነት። ˝

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

23 Jan, 19:13


አንድ ጊዜ ህፃናት የጎዳና ተዳዳሪዎች ቤንዚን ሲያሸቱ አየኋቸውና ስቆጣ አንዱ በዕድሜው ከፍ ያለው ❝ተዋቸው! ብርዱን ለመከላከል እንጅ ፈልገውት አይደለም።❞ አለኝ። እኔም በንግግሬ አፍሬ ሄድኩ።

ከዚያ በኋላ ሰዎች መጥፎ ነገር ላይ ወድቀው ካየሁ ከመተቸቴ በፊት ምክንያታቸው ምን ይሆን ብዬ መጠየቅን ለመድኩ። ሁሉም ሰው መጥፎ ነገር የሚሰራው ከመፈለግ ብቻ ላይሆን ይችላል። ነፍስያ አሸንፎን ወንጀል የምንሰራውን ያህል ህይወት አስገድዳቸው መጥፎ ነገር ላይ የወደቁም ብዙ አሉ።

እነዚያን ህፃናት ቤንዚን ለምን ትስባላችሁ ብዬ ከመቆጣቴ በፊት ልብስ መስጠት ከኔ ይጠበቅ ነበር። ከእኔ የሚጠበቀውን ሳልወጣ እነሱን መውቀሴ ተገቢ አልነበረም።

እንዲሁ ሰዎችንም እኛ የምንጠብቀው ደረጃ ለምን አልደረሱም ብለን ከመንቀፋችን በፊት ያለፈ ህይወታቸውን ማጥናት አለብን። ምክንያቱም የመጣንበት መንገድ ይለያያልና ሁሉም ሰው እኩል ውጤት ሊያመጣ አይችልም። ቁርሱን ሳይበላ ትምህርት ቤት የሄደና መቅሰስ ተጠቅሶለት የተላከ እኩል ትኩረት ለምን አልሰጡም ካልን ሚዛናችን ተዛንፏል።

ይሄ ምስል ታዲያ ያንን አጋጣሚ ያስታውሰኛል። በሰዎች ላይ ከመፍረድ በፊት የራስን ሃቅ መወጣት እንደሚገባ የተመከርኩበት ነው።

ከማ ቃለ ሰልማን

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

23 Jan, 17:18


«አላሁመ ሶሊ ወሰለም አላ ሀቢቢና ሙሀመድ ﷺ»

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

23 Jan, 10:17


በይቱላህ ፊ መዲነቲ ዉቢት ባቲ
#በመንገዴ_ላይ

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

23 Jan, 03:24


#ለሁሉም በሽታ መድኃኒት አለው!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿ما أنْزَلَ اللَّهُ داءً إلّا أنْزَلَ له شِفاءً.﴾

“አላህ አንድን በሽታ ከሰማይ አያወርድም። ለሷ የሚሆን መዳኛ አብሮ ቢያወርድላት እንጂ።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 5678

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

22 Jan, 19:45


«የሰማያትና የምድርም ግዛት የአላህ ነው፡፡ መመለሻም ወደ አላህ ነው፡፡» [ ሱረት አል-ኑር፣ - 42 ]

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

21 Jan, 15:14


በዛሬው እለት ጥር 13/2017 በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ሮማናት አደባባይ "ሒጃባ ክትገብር እያ፤ ትምህርታ እውን ክትማሃር እያ" በሚል በአክሱም ከተማ የተደረገው የሒጃብን ክልከላ በመቃወም የታካሄደው ደማቅ ሰልፍ በቪዲዬ።

ይህ ሰልፍ ለሒጃብ እና ሙስሊሞች የመማር ህልውና፣ ነፃነትና እና ክብር የተካሄደ ታሪካዊ ሰልፍ ነው።

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

21 Jan, 07:30


«ሒጃባችን ማንነታችን ነው»‼️

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

21 Jan, 07:27


እህቶቻችን ለእህቶቻችን

«አክሱም ሒጃብ ብቻ አይደለም የተከለከለው እሴልምና እንጂ»‼️

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

21 Jan, 06:01


"ሒጃባ ክትገብር እያ፤ ትምህርታ ውን ክትማሃር እያ" ጉዞ ወደ ሮማናት አደባባይ!

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

21 Jan, 06:00


በመቐለ ከተማ በአክሱም ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለውን በደል አስመልክቶ ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደ ይገኛል!

- ሀሩን ሚድያ በሰልፉ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃዎችን የምናደርስ ይሆናል።

© ሀሩን ሚድያ

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

13 Jan, 03:14


اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنْ الْهَمِّ وَالْحَزَنِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ الْعَجْزِ وَالْكَسَلِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ الْجُبْنِ وَالْبُخْلِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ غَلَبَةِ الدَّيْنِ، وَقَهْرِ الرِّجَالِ. 

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

12 Jan, 19:24


ይህ ወንድም ቢላል ይባላል
ለቢላል መስጅድ ዝም ከምል ነው ያለኝን ልሳተፍ ብየ ነው ብሎል  ። 68 ብር ዛሬ በዱንያ ላይ ለአላህ ቤት የተሰጠች ብድር ነች ነገ በጭንቁ ጊዜ አላህ ትርፍማ አርጎ ይስጥህ ። አላህ ይቀበልህ አላህ በሰጠሀው ነገር ላይ በረካን ይጨምርልህ


ዝም ያልን ሰወች ለአላህ የምንሰጠው አተን ነው ?

#ወለዲ_ቢላል_መሰጂድ #ምንጣፍ

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

12 Jan, 18:44


አንድ ወንድሜ 16,000 ገቢ አድርጓል። አላህ ይደሰትብህ ጀዛከላሁ ኸይር አላህየ ገንዘብህን በረካ ያድግልህ ልጆችህን ሷሊህ ያድርግልግ ዱንያ አኼራህ ያ ማረ ይሁን ያ ረብ

እርሰዎም ይሳተፉ ለአኼራዎ ይሰንቁ
ሒጅራ ባንክ 1001093660001

ንግድ ባንክ 1000361517947

አቢሲኒያ ባንክ 150615062

#ወለዲ_ቢላል_መሰጂድ #ምንጣፍ

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

12 Jan, 18:31


መጪው ጊዜ ረመዷን ነው
መስጅዶች በፆመኞች ይሞላሉ ። በርካቶቻችን ቤታችንን እናስተካክላለን የአላህ ቤት ግን ምንጣፍ ካጣ ረጂም ጊዜ ሁኖታል !

ዛሬ አካውንቴ ላይ ያለው ገንዘብ ለመስጅዴ ካሎነ ለምኔ! ደሞስ የመስጅድ ጉዳይ አጀንዳ የሚሆነው ሲፈርስ ብቻ ነው ?

ሒጅራ ባንክ 1001093660001

ንግድ ባንክ 1000361517947

አቢሲኒያ ባንክ 150615062

#ወለዲ_ቢላል_መሰጂድ #ምንጣፍ

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

12 Jan, 18:16


ይድረስ ዛሬ ላይ ካላቸው ለእውነተኛ ቤታቸው ስንቅ ለመያዝ የአላህን ውዴታ ፍለጋ ገንዘባቸውን አላህ በሚወደው ላይ ለሚያውሉ ሁሉ...

   በወለዲ ከተማ ለሚገኘው የቢላል መስጅድ ከዛሬ አስራ አምስት አመታት  በፊት ለተነጠፈው ምንጣፍ ለመቀየር ባቀረብነው ጥሪ በርካቶች ዛሬ ላይ ካላቸው ለነገው ቤታቸው በማሰብ ለአላህ ጥሩ የሆነን ትርፍማ ብድር አበድረዋል አላህ ይቀበላቸው ።

   እስከ አሁን ያለው እንቅስቃሴ በአላህ ፍቃድ በእናንተ ሰበብ የ62 ካሬ ተሸፍኖል አልሀምዱሊላህ ።


የሚቀረን 248 ካሬ ነው ?
የአንድ ካሬ ዋጋ 3200 ብር ነው


በዚህ በትልቅ ኸይር ላይ በተጠቀሱት ዘመቻወች  ተሳተፉ

793 ሰወች እያንዳንዳቸው 1000 ቢነይቱ
248 ሰወች እያንዳንዳቸው 3200 ቢነይቱ
1587 ሰወች እያንዳንዳቸው 500 ቢነይቱ
3968 ሰወች እያንዳንዳቸው 200 ቢነይቱ


ሁላችሁም በምትፈልጉት መጠን ተሳተፉ
ተጋግዘን ለአላህ ቤት ምንጣፍ እንሸፍን ።

መጪው ጊዜ ረመዷን ስለሆነ ይህንን ትልቅ እድል እንጠቀም ።

ሒጅራ ባንክ 1001093660001

ንግድ ባንክ 1000361517947

አቢሲኒያ ባንክ 150615062

#ወለዲ_ቢላል_መሰጂድ #ምንጣፍ 

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

12 Jan, 16:27


AL-Amana Arebiyan Mejlis & Furniture

ለቤትዎ ግራማ ሞገስ የሚላብሱ ምቹ መጅሊሶችን በመሰራት ልናገለግላቹህ ዝግጃታችን ጨርሰናል።

0936443838 / 0910967586

https://t.me/ALAmanaArebiyanMejlis

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

12 Jan, 14:28


በዛሬው እለት በኡስታዝ አብዱልፈታህ ሀጂዬ የሚመራው የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን መጅሊስ አመራሮች የኬሚሴ ከተማ ሶሻል ሚዲያ ተጠቀሚ የሆኑ ሙስሊም ወጣቶችን በማሰባሰብ ሚዲያን እንዴት መጠቀም እንዳለባቸው እና ሌሎችንም ምክር ሀሳቦችን ሰጥተዋል ።

በመጨረሻም የመጅሊስን ግቢ እና ያሉበትን ደረጃ አስጎበኚቷል።

"ጠቃሚ ውይይና አሰፈላጊ ምክር አገኝተናል። እንዲህ ያለው ውይይት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል። እኛም ባለን አቅም ሁሉ ተቋማችንና ኡማውን ለማገልገል ዝግጁ ነን ቢኢዝኒላህ"

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

28 Dec, 03:22


الَّذِي خَلَقَ الْمَوْتَ وَالْحَيَاةَ لِيَبْلُوَكُمْ أَيُّكُمْ أَحْسَنُ عَمَلًا ۚ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْغَفُورُ

(ሱረቱ አል-ሙልክ - 2)
ያ የትኛችሁ ሥራው ይበልጥ ያማረ መኾኑን ሊሞክራችሁ ሞትንና ሕይወትን የፈጠረ ነው፡፡ እርሱም አሸናፊው መሓሪው ነው፡፡

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

27 Dec, 11:32


ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን የወሰደውም የሰጠንም አላህ ነው፡፡ ሁሉም ነገር ከርሱ ዘንድ የተወሰነ ቀን ቀጠሮ አለው፡፡ ከአላህ የሆነን ወደናል አልሃምዱ ሊላህ

አላህ ሆይ! ለአባታችን እዝነትህን እንለምነሃለን በጀነትህ ሞሸርልን እኛንም ሰንቅ አቀባይ አድርገን ያ ከሪሙ ያ መቲን 🤲

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

22 Dec, 18:54


«ጌታዬ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ወደኔ ለምታወርደው ፈላጊ ነኝ» 🤲

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

20 Dec, 18:10


ጠያቂው፦  ሸይኽ ሰዒድ

አባቴ ፦ ለበይክ

ጠያቂው፦ ሁሌ ከሱቅ ወደ ቤት ከቤት ወደ ሱቅ በእግሩሁ ነው የምትሄዱት ለምን በባጃጅ አይሄዱም?

አባቴ፦ 1ኛ መንቀሳቀሴ ጤና ይሆነኛል
           2ኛ የባጃጁ ለልጆቼ ዳቦ ይሆነኛል
           3ኛ ዚክር ማድረጊያ ነው መንገዱ ሸፈዓ ይሆነኛል (ኢንሻ አላህ)

በአንድ ወቅት አንድ ወዳጂ ሲጠይቀው የሰማሁት ነው።  የኔ ብርቱ ዛሬማ ተረታ አላህ ሆይ! ወደ አንተው ሸሸሁ ከአንተ ውጭ ማን ረዳት አለ ያ ረሕማኑ በእዝነትህ 🤲

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

19 Dec, 16:05


የሚናራህ ታሪክ

በነቢዩ ﷺ እንዲሁም በአራቱ ኸሊፋዎች ዘመን መስጂዶች ሚናራህ አልነበራቸውም። ሙዓዚኖችም አዛን የሚያደርጉት ከበር ላይ ሆነው ወይም ከመስጂዱ ጣሪያ ላይ ወጥተው ነበር።

ሚናራህ መሰራት የጀመረው በበኑ-ዑመያዎች ዘመን እንደሆነ ይጠቀሳል። ከ40 ሒጅራ በኋላ ዑመዊዮች መቀመጫቸውን በሶርያ ደማስቆ እንዳደረጉ የሶርያ ቤተክርስቲያኖች ከቤቶቹ የተለየ ጉልላት እንዳላቸው ተመለከቱ። በዚህ ጊዜ እነሱም መስጂዶቹን ከቤቶች ለመለየት ሚናራህ አስገነቡ። ሌሎች የታሪክ ምሁራን ደግሞ ከፋርስ ቤተመቅደሶች የወሰዱት ነው ይላሉ።

ዑመዊዮች ሚናራዎቹን ይሰሩ የነበሩት ለብቻቸው ሳይሆን ከመስጂድ ጣሪያ ላይ በመቀጠል ነበር።

በዑመዊዮች ዘመን የመጀመሪያው ሚናራህ የተገነባው በ45 ሒጅራ በኸሊፋው ሙዓዊያህ ዘመን ሲሆን የገነባውም የኢራቅ በስራው አሚር ነው።

ቀጥሎም በዚሁ በሙዓዊያህ ዘመን በ53 ሒጅራ በግብፅ ካይሮ የዐምር ኢብን አል-ዓስ መስጂድ የመጀመሪያው ሚናራህ ተነገባ።

የነቢዩ ﷺ መስጂድ ለመጀመሪያ ጊዜ ሚናራህ የተሰራበት በ87 ሒጅራ በኸሊፋው አል-ወሊድ ኢብን ዐብዱልመሊክ ትዕዛዝ ሲሆን ያነፀውም በወቅቱ የመዲና አሚር የነበረው ዑመር ኢብን ዐብዱልዓዚዝ ነው።

ሚናራህ ጎልቶ የወጣውና ከመስጂዱ ተለይቶ ለብቻው መታነፅ የጀመረው በዐባስዮች ዘመን ነው።

በመስጂድ አል-ሐራም (ከዕባህ) የመጀመሪያውን ሚናራህ ያስገነባው የዐባስያው ኸሊፋ አል-መንሱር ሲሆን ዘመኑም በ139 ሒጅራ ነው።

በዐባስዮች ዘመን ከተሰሩት የመጀመሪያው ትልቁ ሚናራህ በ233 ሒጅራ የኢራቅ ሳመራ ጃሚዕ መስጂድ ሲሆን የተገነባውም በኸሊፋው አል-ሙተወኪል ነው።

ከዚያ በኋላ በየዘመኑ የተነሱት ሰልጁቆች፣ አዩቢዮች፣ መምሉኮች፣ ዑስማኒዮችና ሌሎችም ሱልጣኖች የየራሳቸውን ሚናራህ በመገንባት አሻራቸውን አሳርፈዋል።

ዑስማኒዮች ባለ 6 እሚናራህ በመገንባት የራሳቸውን መለያ ያስቀመጡ ሲሆን ከእነሱም በውበቱ የሚታወቀው በ1020 ሒጅራ የተገነባው ሰማያዊው የሱልጣን አህመድ መስጂድ ነው።

የሁሉም ነገስታት ሚናራዎች ቅርፅ የተለያየ ሲሆን የዑመዊዮች አራት ማዕዘን ሆኖ ቀጠን ያለ፣ አንደሉሶች አራት ማዕዘን ሆኖ ሰፊ፣ የዐባስዮች ክብ ሆነው ሰፊ፣ የዑስማኒኖች ደግሞ ክብ ሆነው ቀጠን ያሉ ናቸው።

በዚህ ዘመን ካሉት ሚናራዎች ትልቁ በአልጀሪያ የሚገኘው ጃሚዕ አል-ጀዛዒር መስጂድ ሲሆን ቁመቱም 265 ሜትር ነው። ሁለተኛው የሞሮኮ ካዛብላንካው አል-ሐሰን መስጂድ፥ ሶስተኛው ደግሞ የማሌዥያው የሰላሑዲን ዐብዱልዓዚዝ መስጂድ ነው።

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

19 Dec, 15:39


«አላሁመ ሶሊ ወሰለም አላ ሀቢቢና ሙሀመድ ﷺ»

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

18 Dec, 18:43


አላህ ሆይ ላንተ ስናጎነብስ ከፍ አርገን🤲
ድክመታችንን ባንተ ቁዋ ጠግንልን🤲
ህመማችንን ባንተ አዳኝነት ፈውስልን🤲
ክጃሎታችንን ባንተ አብሮነት እውን አርግልን ያረሂም🤲

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

18 Dec, 17:38


ያ ለጢፍ 🤲

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

17 Dec, 19:38


አላህ ሆይ ከእዝነትህ ውጭ ምን መሸሺያ አለን ያ ረሂሙ ኢርሃምና 🤲

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

16 Dec, 18:28


"አዩብንም (ኢዮብን) ጌታውን «እኔ መከራ አገኘኝ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ» ሲል በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡" [ ሱረቱ አል-አንቢያ - 83 ]

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

24 Nov, 20:02


#አትታገል ያንተ የሆነ ከአንተ ልሂድ አይችልም። ያንተ ያልሆነን ያንተ ለማድረግ አትታገል።

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

24 Nov, 07:01


በል አልሃምዱ ሊላህ እዚህ ባለመሆንህ በሰላም ተኝተህ በሰላም ተነሰተሃል ምንም ነገር ለማድግ ያለማንም እገዛ እያደረክ ነው። ያለ ምርጫ እየተመገብክ ነው ቤት ያፈራውን በል አልሃምዱ ሊላህ…

ያ ሻፊ ያ ከሪም ለታመሙት ሁሉ አፍያን እንለምነሃለን ያ ወዱድ 🤲

ከጥቁር አንበሳ ሆስቢታል

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

23 Nov, 15:36


የመኪና አደጋ ደርሶበት መጣ ዶክተሮች ብዙ ጣሩ ሊተርፍ ግን አልቻለም። ሰካሩ ነበር የመገጨት መንስኤው…

ዐለይከ ረበና ቢሁስኒል ኺታሚ

ጥቁር አንበሳ ሆስቢታል ሰንት ጉድ ይዟል…

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

22 Nov, 18:14


ተመን ለለው አፍያህ አልሃምዱ ሊላህ አትልም
በዚች ሰዓት በሆስቢታል የታካማዎች አልጋ ላይ የተኙ ሰንት ሰዎች አሉ!

ያ ሻፊ ለታመሙት ሁሉ አፍያን እንለምነሀለን

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

22 Nov, 03:15


አላህ ሆይ አካሌን ጤናማ አድርግልኝ፡፡ አላህ ሆይ ጆሮዬን ጤናማ አድርግለኝ፡፡ አላህ ሆይ ዓይኔን ጤናማ አድርግልኝ፡፡ ከአንተ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ አላህ ሆይ ከክህድትና ከድህነት በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ከቅብር ቅጣትም በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ከአንተ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ 🤲

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

21 Nov, 16:20


«አላሁመ ሶሊ ወሰለም አላ ሀቢቢና ሙሀመድ ﷺ»

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

17 Nov, 10:34


ሙሳ አለይሂ ሰላም ወደ ከተማው ሲደርስ
ቤት
ስራ
ሚስት አልነበረውም....
መልካም ነገር ሰራና ወደ ጥላ ቦታ ሂዶ እጆቹን ወደ ሰማይ ከፍ አርጎ ዱዓ አደረገ ።

ربي إني لما أنزلت الي من خير فقير 🤲
"ጌታየ ወደኔ ለምታወርደው ኸይር ነገር ከጃይ ነኝ"

የዛች ቀን ፀሀይ አልገባችም ነበር
ቤት .. ስራ.. ሚስት አላህ ሲሰጠው !

ይህንን ዱዓ ሞክሩት መልካም ነገር ከሰራቹህ ብኋላ ።!

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

17 Nov, 05:20


رَبِّ إِنِّي لِمَا أَنزَلْتَ إِلَيَّ مِنْ خَيْرٍ فَقِيرٌ

«ጌታዬ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ወደኔ ለምታወርደው ፈላጊ ነኝ» 🤲

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

16 Nov, 17:32


ውድ ተማሪዎቻችን የአላህ ሰላምና እዝነት ለእናንተ ይሁን

👌 እባክዎን በፍፁም ቪዲዮውን መመልክት አይርሱ

🎊በስልክ ቁጥር የነበረው የምዝገባ ሂደት ችግር በአላህ ፈቃድ የተፈታ መሆኑን እየገለፅን አሁን በተመቻቸ እና ቀላል በሆነ መንገድ በስልክ ቁጥራችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
🔗መመዝገቢያ ሊንክ
:
https://am.africaacademy.com/

ትላንትም ሆነ ዛሬ በጎግል መመዝገብ ችግር ያጋጠማችሁ ተማሪዎች በቀላል መንገድ እንዴት በጉግል መመዝገብ እንደምትችሉ በቪዲዮው ላይ በግልፅ አብራርተናል።

በቪዲዮ ላይ በሁለት መንገዶች መመዝገብ እንደምንችል በደንብ ስለሚያብራራ ሁሉም ሰው ቪዲዮውን እንዲመለከት እና የሚስማማውን የአመዘጋገብ መንገድ እንዲመርጥ እንጠይቃለን።

በተጨማሪም የግል መረጃዎትን(ስምና እና ፆታ) በትክክልና በጥንቃቄ መሙላት እንዳይረሱ።

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

16 Nov, 03:31


"ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡"  (ሱረቱ አል ዱሃ - 5)

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

15 Nov, 17:14


ይሄም ቀን ያልፋል ይሄም ሁኔታ ይቀየራል … ኢንሻ አላህ

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

15 Nov, 07:01


ربي إني لما أنزلت الي من خير فقير🤲

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

14 Nov, 17:54


ሙሳ አለይሂ ሰላም ወደ ከተማው ሲደርስ
ቤት
ስራ
ሚስት አልነበረውም....
መልካም ነገር ሰራና ወደ ጥላ ቦታ ሂዶ እጆቹን ወደ ሰማይ ከፍ አርጎ ዱዓ አደረገ ።

ربي إني لما أنزلت الي من خير فقير🤲
"ጌታየ ወደኔ ለምታወርደው ኸይር ነገር ከጃይ ነኝ"

የዛች ቀን ፀሀይ አልገባችም ነበር
ቤት ..ስራ..ሚስት አላህ ሲሰጠው !

ይህንን ዱዓ ሞክሩት መልካም ነገር ከሰራቹህ ብኋላ ።!

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

14 Nov, 16:53


«አላሁመ ሶሊ ወሰለም አላ ሀቢቢና ሙሀመድ ﷺ»

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

14 Nov, 16:50


እውነተኛ ታሪክ ነው

በጣም ይዋደዱ ይፋቀሩ ነበር። የወንድሟ የቅርብ ጓደኛ ነው ቤታቸው ይመጣል አብሮ ማ'ድ ይቀርባል እናቷም አባቷም የሚያውቁት እንደልጃቸው የሚያዩት የቅርባቸው ሰው ነው።

የው ቅርባችን ያለ ሰው አይደል የሚጠግነንም የሚሰብረንም?

እህቱና ጓደኛው የጦፈ ፍቅር ውስጥ መሆናቸውንና በቅርቡ ሽማግሌ ልኮ ሊያገባት እንደሆነ ከሌላ ከሶስተኛ ወገን ሰማ

"እንዴት ሲባል በፍፁም አይደረጋትም" ሲል ወንድም ዘራፍ አለ

እህቱን ተቆጣ አስፈራራ ዛተባት

ይህንን ለእጮኛዋ አልተናገረችም .. ጊዜው ሲደርስ የሚሆነው ይሆናል ብላ ፍቅሯን እያጣጣመች በትዕግስት እየተጠባበቀች ነው

በመጨረሻም ያ' ቀን ደረሰና ለቤተሰቦቿ ለእናት ለአባቷ አስረዳች። እሱን ማጣት እንደማትፈልግ እንደምታፈቅረው በቀጣይ ወር ሽማግሌ እንደሚልክና እንደሚጋቡ አስረግጣ ነገረች

የዚህን ጊዜ ወንድሟ ለእናቱም ለአባቱም ስለ'ሱ መጥፎ መጥፎ ነገሮችን እያነሳ እንደማይሆናት እሷን የማስተዳደር አቅም እንደሌለውም ድህነቱንም መጥፎ ባህሪውን እያነሳ እያንኳሰሰ ነገራቸው። አሻፈረኝ ብላ ሽምግልናውን ካስላከችም እንዳይቀበሉ አስረግጦ ነገራቸው

ይሄ ሲሆን ጓደኛ ከደጅ ሁኖ እየሰማ ነበር። የው ቤታቸው ይመጣል አላልኳችሁም አጋጣሚ ሲመጣ እዚህ ጨዋታ ላይ ደረሰና ሁሉንም ሰማ

ከዛቺ ደቂቃ አንስቶ "አጠገቤ እንዳትደርሺ" በምትል አንዲት text ብቻ ከህይወቱ አስወጣት

ለመነች አስለመነች ስለ ፍቅሩ ስትል ብዙ ታመመችም ተሰቃየችም እሱ ግና በፍፁም አለ። በዚህ ልክ የተዋረድኩ ሰው ሁኜ ያንችን ቤተሰብ መቀላቀል አልፈልግም ሲል ፍቅሩን ሸኛት። ተለያዩ !

ዛሬ ላይ

እሷ ኑሮዋ አውሮፓ ነው ሌላ ሰው አግብታ 3 ልጆችን ወልዳለች። ደስተኛ ትሁን አትሁን እንጃዕ/አላህ ደስተኛ ያድርጋት🤲

እሱ ግን

ብዙ ሴቶችን ወደ ህይወቱ አምጥቷል አንዲቷም ግን እንደሷ ሊሆኑለት አልቻሉም። "እሷ የሰጠችን ያከበረችን ስለ ፍቅር ስትል የተዋረደችልኝን ስለ'ኔ የታመመችልን መርሳት አልቻልኩም። ክብሬን ብዬ ፍቅሯን ገፋሁ ዛሬ ድረስ ግን ጠረኗን እናፍቃለሁ" እያለ የፀፀት ህይወትን እየኖረ አለ።

⛔️ ስለፍቅራችሁ ሲሉ የተዋረዱላችሁን ሰዎች አትርገጡ። ፊታችሁና ምላሶቻችሁ ቢደብቋቸው'ኳ ከሰዎች በተነጠላችሁ ጊዜ ልባችሁን አፍኖ የሚረግጣችሁ ህመሙን መቼም መርሳት አትችሉትም!

ፍቅር ጣዕሙ የማይገለጥ ጣፋጭ ዓለም ነው!

© ከፌስቡክ መንደር የተገኘ

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

14 Nov, 16:34


ቃለ ተዐላ፡
                                        «لَا يَضِلُّ رَبِّي وَلَا يَنسَى»
«ጌታዬ አይሳሳትም አይረሳምም»
አላህ ዘንድ ፡
     ልፋትህ ከንቱ አይሆንም
     ምንዳህም የተጠበቀ ነው
አንተ ብቻ ስራህን ለአላህና እና ለአላህ አጥራ።
#አላህ ምንኛ ያማረ ተመላኪ ሆነ

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

13 Nov, 17:36


"አንዲት ቅጠል አትወድቅም አላህ ቢያቅ እንጂ"

እንዴት ታዲያ ይሁ ሁሉ መልካም ነገር በልብህ የያዝከውስ?

ለሰወች የያዝከው ይህ ሁሉ ውዴታስ..?
የሰወች ስኬት የራስህ ስኬት ያህል የምትደሰተው ደስታህስ!
የሰወች ህመም ህመሜ ብለህ የምትታመመውስ ?
ወዳጄ :- አላህ እኛን ከላይ ያለንን አይመለከተንም ። አላህ የሚመለከተው ውስጣችንን ነው ።

ንጉሱ የሚመለከተውን ክፍል አሳምረው
በአካል ውስጥ አንዲት ስጋ አለች እሷ ከተስተካከለች ሙሉ አካላችን ተስተካከለ እሷ ከተበላሸችም ሙሉ አካላችን ተበላሸ
እሷም ልብ ነች!

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

13 Nov, 15:46


እነዚህን ሰለምቴ ቦክሰኞች ሳይ በአላህ ስራ እደነቃለሁ። እነዚህ በአንድ ቡጢ ሰው የሚዘርሩ የዓለማችን የከባድ ሚዛን ጡንቸኞች ናቸው። ግን ከእኛ በላይ ማን አለ ብለው በጉልበታቸው አልተመኩም። ይልቁንም ብዙ ቀድረ ቀሊሎች ለአላህ ለመስገድ በኮሩበት ዓለም እነሱ አላህ ከሁሉ በላይ ሃያል መሆኑን አውቀው ተንበርክከው ሰጋጆች ሆኑ። አየህ ከፍ ስትል ከፍ ያለውን ታውቃለህ። ያኔ ትተናነሳለህ።

ስማቸውን ከፈለጋችሁ እነዚህ ናቸው
♦️ ሙሐመድ ዐሊይ (ካሲየስ ማርሴለስ ክሌይ)
♦️ መሊክ ዐብዱልዓዚዝ (ማይክ ታይሰን)
♦️ ሙሐመድ ቃዊ (ዋይት ብራክስተን)
♦️ ሰዓድ ሙሐመድ (ማክስዌል አንቶኒዮ)
♦️ ዐብዱልወሐብ (ጌርቮንቴ ዴቨስ)
♦️ አንድሪው ታቴ

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

13 Nov, 09:49


አቡሁረይራ አላህ መልካም ስራቼውን ይውደድላቼው ወዳጅ የአላህ መልክተኛ ﷺ እንድህ አሉ ይለናል :ጀናዛን በመሸኘት ተቻኮሉ መልካም ነፍስ ከሆነች ወደ እርሱን ማስቀደማችሁ እሷን መልካም ነው።ከዚህም ውጭ የሆነች ነፍስ ከሆነች ደግሞ ከትከሻችሁ ላይ የምታወርዱት መጥፎ ነገር ነው።

ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግቦታል

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

13 Nov, 03:41


“በቤተሰቡ መሀል በሰላም ያደረ ሰውነቱ በሙሉ ጤነኛ ሆኖ ያነጋ የዕለት ጉርሱን ያገኘ ዱንያን በሙሉ ሰብስቧታል” ረሱሉ (ሰ·ዐ·ወ)

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

12 Nov, 11:01


"አንዳንዴ የሚያክምህ በማጉደል ውስጥ ነው።"

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

12 Nov, 05:07


የሀላል ርቀት
**
ብዙው የተማረ ሰው በቅጥር ደሞዝ የትም ስለማይደርስ በአማካሪነት ተመራማሪነት ይቀጠራል ይሰራል። ወይም ወደፖለቲካ ዘው ብሎ ይገባል። የሚያሳዝነውና አስከፊው ነገር በገባበት አለም ራሱን ሞራሉን ጥሎ እንጂ አብዛሀኛውን ጊዜ ያሰበውን ነገሮች ማግኘት አይችልም።

ሰሞኑን የ አለም ጤና ድርጅት አማካሪ ኮንሰልታት ፈልጎ ማስታወቂያ አውጥቶ ነበርና እንደለመድኩት አለሁ አልኩ። እና ፎርሙ ላይ በርካታ ባይበላስ የሚያስብሉ፣ አላህ ጋር የሚያጣሉ ጥያቄዎችን እስማማለሁ እያልክ ማለፍ አለብህ። ገና ሲጀምር ራሱ ጾታ ላይ ምርጫው ራሱ አምስት አይነት ነው። ከዛ ኋላ ያለውማ ዘግናኝ ነው...በሊዋጢ ነጻነት ታምናለህ ስትባል yes😡

ሌላው ደግሞ ይሄን ሁሉ ሀራም ይሁን ብለህ ስራውን ካገኘህ በኋላ የሚመጣው ነገር ነው። ከ ጥቂት አመት በፊት አንዱ የ UN ድርጅት Subsaharan Africa ላይ ስለሰሩት ስራ ለህብረተሰቡ ያመጣውን ጥቅም ለመገምገም ተመራማሪ ፈልገው ለምስራቅ አፍሪካ እኔን ቀጠሩኝ። እናም ስራውን ሰርቼ draft report አስገባሁ። እናም ውጤቱን ያነበቡ አሰሪዎቼ በውጤቱ ተቆጡና ስብሰባ ጠሩ። እስከ ደቡብ አፍሪካ ድረስ ያሉ አባሎች በእንጀራችን መጣህ ብለው ሊበሉኝ ተሰበሰቡ። ውጤቱን አቅርብ ተባልኩና ድርና ማጓን ሳይቀር ብትንትን አድርጌ አስረዳሁ። ውጤቱ ምን ሆኖ ነው ካላችሁኝ👉 የሰራችሁት ስራና ያወጣችሁን ሚልየን ዶላሮች ያሰባችሁትን ውጤት አላመጣም በማለቴ ነበር። አሻሽል ቢሉኝም ደረቅኩ። እነሱም ተስፋ ቆርጠው በአጭሩ ብሬን ሰጠው አሰናበቱኝ። ከዛ ጊዜ በኋላ እዛ ድርሽ አላደረጉኝም😁

አንዳንዴ ሀኪም ሆነህ ስትሰራ በሽተኛው ምን እንዳመመው በቀላሉ ታውቃለህ። በቀላሉም እንዴት እንደሚታከም ትረዳለህ። ሆኖም ክሊኒኩ ኪራይ ነው፣ ግብርም፣ የሰራተኛም ደሞዝ አለ። በቃ ሽንት ደም ሰገራ ራጅ ሁሉም ይታዘዛል.....ወይ ጣጣ

ብዙ ነጋዴዎች ጉቦ ይሰጣሉ። እናም ሸር ለመግፋት ነው ይላሉ። ጉቦ ካልሰጠ ትራፊኩ አይለቀው፣ ግብር አይቀነስለት፣ ቤቱ ስም አይዘዋወር...መገን ጣጣ

አህባቦች ሀላል መብላት ቀላል አይደለም። ገቢ አነሰን የምትሉ ሁሉ ሀላል ከሰጣችሁ ትልቅ ውለታ ነው። እንደው በደፈናው አላህ ይሁነን!

ከማ ቃለ ፕሮፌሰር Kha Abate

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

12 Nov, 02:56


የአላህ ባሮቺ ሆይ

እነዚህን ሶስት ነገሮቺ ያገኘ የገጠመው የወፈቀው

ደስታ ያገኛል በዱንያም በአሄራም

እነሱም የመጀመሪያው :-

1 በተሰጠ ጊዜ የሚያመሰግን

2 በተፈተነ ጊዜ ሶብር የሚያደርግ

3 ወንጀል በሰራ ጊዜ ተውበት የሚያደርግ

እነዚህ ሶስት ነገሮቺ የደስታ አይነቶቺ ናቸው

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

11 Nov, 17:00


እኔና አንተስ አልሃምዱ ሊላህ ለማለት ምን ያዘን!

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

11 Nov, 10:29


ለቤቴ መልክ የምሰጪው አንቺ ነሽ
ለአበቦች ቀለም እንደምትሰጪው ሁሉ ♡

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

11 Nov, 09:30


ሰራተኛን በየትኛውም መልኩ አትበድሉ። በምግብ አትቅጡ። አትምቱ። ልጆቻችሁ ሰራተኛ ላይ አይቅበጡ። በነሱ ላይ ከአላህ ጋር የሚያጣላችሁን ክፉ ቃል አትናገሩ። ራሳችሁ ላይ ቢሆን በማትፈልጉት መልኩ እንቅልፍና ረፍት አትንሱ። ከአቅም በላይ የሆነ ስራ አትስጡ። ሐቃቸውን ሳትሸራርፉ ስጡ። ሶላት እንዲሰግዱ እዘዙ። የነሱ ሐቅ በናንተ ላይ ከሚኖር፣ የናንተ ሐቅ ቢቀር ይሻላል። ደካማ ላይ ጉልበተኛ አትሁኑ። ከውጭም ይሁን ከውስጥ ልክስክስ ወንዶች ወይም ጎረምሳ ልጆች ከነሱ ጋር እንዳይባልጉ ጥንቃቄ አድርጉ። ሰበብ አድርሱ። በባህሪም ይሁን ሃላፊነትን በመወጣት በኩል ሁኔታቸው የማይጥም ከሆነ በነሱ ሰበብ ወንጀል ላይ ከመውደቅ በሰላም መሸኘት ይሻላል።

© Ibnu Munewor

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

10 Nov, 19:01


እነኚህ በኒቃብ የተዋቡ እንስቶች ከኬንያ ኢስላማዊ ዩኒቨርስቲ የተመረቁ ናቸው።

የቁጥር ቅሸባው በየቦታው ቢሆንም ኬንያ ውስጥ የሙስሊሙ ቁጥር 5.2 ሚሊዮን ብቻ ሲሆን አጠቃላይ ከሃገሪቱ ህዝብ 11%ቱን ይሸፍናሉ። በዚህ አናሳ ቁጥር በዚህ ደረጃ ኒቃባቸውን አስከብረው እየኖሩ፤ የእኛ እህቶች እንኳን ኒቃብ ማስክ እንኳ ተከልክለው ኒቃብ በመልበሳቸው ብቻ በሙስሊም ጠሎች «አሸባ'ሪና አክ'ራሪ» እየተባሉ አሁንም ድረስ እየተወነጀሉ ነው።

ኬንያ ውስጥ ሙስሊም ጠልነት ቢኖርም ግን ሙስሊሞች ከኛ በተሻለ ነው ተከብረው የሚኖሩት። ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ራሱ የሙስሊሙ ሽፋን 1.7% ሆኖ ግን እስከ ፓርላማ ድረስ ተፅዕኖ መፍጠርና መሰማት የሚችሉ ናቸው። ጠንካራ ለኡማቸው ጠበቃ የሆኑ ተቋማት አሏቸው።

እኛስ ከግማሽ በላይ ሆነን፤ እህቶቻችን በኒቃብ ሳቢያ ለበርካታ አመታት ከትምህርት ገበታና ከሥራ ሲታገዱ፣ አሁንም ይሄ ጭቆና ተጠናክሮ ሲቀጥል፣ የኛ ሰው በሠራው ተቋም ውስጥ ዓይነ ስውራን ሶላት መስገድ ተከልክለው ከፊሎች ታፍነው ሲኖሩና ያልቻሉ ጥለው ሲወጡ… አንድም መሬት የወረደና ፍሬ ያፈራ ሥራ አልተሠራም።

እኮ ለምን⁉️
ለምን ተፅዕኖ መፍጠር አልቻልንም? ለምን ተስፋ የጣልንበት ተቋማችን ተፅዕኖ መፍጠር አቃተው? በዚህ አካሄዳችን እስከ መቼ⁉️ እናንተስ ምን ትላላችሁ⁉️

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

10 Nov, 17:33


ኒካህ በጽሁፍ ይወርዳል ወይ...?

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

10 Nov, 16:06


ይህን ውብ ቲላዋ ከቲክቶክ ነው ያገኘሁት ወንድማችን ከጀግኖች ሰፈር ሆኖ ይመሰላል ዉብ አድርጎ የሚያነብልን

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

10 Nov, 12:01


ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

“የወንጀሎች ታላቅ ማለት ሰውዬው ወላጆቹን መሳደቡ ነው። አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ሰው ወላጆቹን ይሳደባልን? አሉ፦ አዎን! እሱ የሌላ ሰው አባት ይሰድባል። አባቱ ይሰደባል። የሌላ ሰው እናት ይሰድባል እናቱ ትሰደባለች።”

ቡኻሪ (5973) ሙስሊም (90) ዘግበውታል

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

10 Nov, 11:00


ለራስ ወንጀል እየሰሩ ሰዉን በኸይር ማመላከት

ሸይኽ ሙሀመድ ዘይን ዘህረዲን

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

09 Nov, 15:40


ሰፈራችን አንዲት የሚጥል በሽታ ያለባት ልጅ አለች። ዕድሜዋ አስራዎቹ ውስጥ ነው። በዚሁ በሽታ የተነሳ ከትምህርት ቀርታለች። ቁርኣን ቤት እንኳን መሄድ አልቻለችም። ብዙ ጊዜ ስለሚጥላት ከፊቷ ላይ ቁስለት አታጡም። ከቤት ብዙም ስለማትወጣ አስተሳሰቧ ጭምር እንደ ህፃን ነው። ከእኩዮቿ ያገቡም የታጩም ይኖራሉ። እሷ ግን አላህ ካላነሳላት በቀር ወደፊት ምንም ህይወት የሚኖራት አይመስልም።

ታዲያ የዚችን ልጅ ፈተና አስበውና ሌሎች ጤነኛ ሴቶች የሆነ ነገር ስለጎደላቸው ብቻ እኛም ተፈትተናል ብለው ያማርርሩ ይሆን? እላለሁ። ይች ልጅ ትልቁ ምኞቷ ጤነኛ ሆና እንደማንኛውም ሴት ዕድሏን መኖር ነው። ግን ይሄን እንኳን አልታደለችም።

አንተ ችግር የመሰለህ ለሌላው ምኞት መሆኑን እወቅ የሚባለው ለዚህ ነው። እግረኛ ሆነህ መኪና ማጣትህ ሊያስከፋህ ይችላል። ሰውነቱ ሽባ ሆኖ ለተኛው ጎረቤትህ ግን በእግር ተራምዶ መሄድ ትልቁ ህልሙ ነው።

ይህ ማፅናኛ አይደለም። ይህ እውነት ነው።

ከማ ቃለ አኺ ሰልማን

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

08 Nov, 10:17


የምንፈልገው ነገር በፈለግነው ሰአት ባይመጣ አላህ የፈለግነውን በሚያስረሳ ይተካናል በአላህ የቂን ይኑረን

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

07 Nov, 15:46


«አላሁመ ሶሊ ወሰለም አላ ሀቢቢና ሙሀመድ ﷺ»

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

07 Nov, 03:37


አላህ ሆይ! አካሌን ጤናማ አድርግልኝ፡፡ አላህ ሆይ ጆሮዬን ጤናማ አድርግለኝ፡፡ አላህ ሆይ ዓይኔን ጤናማ አድርግልኝ፡፡ ከአንተ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ አላህ ሆይ ከክህድትና ከድህነት በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ከቅብር ቅጣትም በአንተ እጠበቃለሁ፡፡ ከአንተ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡፡ 🤲

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

06 Nov, 17:20


“አንድ ሙስሊም ከመከራ ምንም አያገኘውም፤ ሌላው ቢቀር እሾኽ እንኳ ቢወጋው አላህ በሱ ሰበብ ምህረት ቢያደርግለት እንጂ።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 5640

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

04 Nov, 15:44


Channel photo updated

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

04 Nov, 14:21


ሒጃብሽን ካላወለቅሽ ማለት... በሸይኽ አብዱለጢፍ ጦሓ

#ኒቃቧንም_ትለብሳለች
#ትምህርቷንም_ትማራለች

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

03 Nov, 19:04


ሙፍቲ ዳውድ የበጎ ድርጅት በትናንተው ዕለት በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ካሉ የበጎ አድራጎት ማህበሮች በክረምት በጎ አድራጎት ስራዎች ሙፍቲ ዳውድ የበጎ አድራት ድርጅት የዋንጫ እና የሰርትፊኬት ሽልማት በዞኑ አስተዳደር ክቡር አቶ አህመድ አሊ አማካኝነት ተበርክቶለታል እናመሰግናለን።

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

03 Nov, 14:16


ሚስቱን እንደ ልዕልት የሚንከባከብ በንግስት እቅፍ ተወልዶ ማደጉን ምስክር ነው።

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

01 Nov, 13:55


በርግጥም ትዳር የበሰለች እንስትን ይሻል እንዲሁም የጥሩ ስነ-ምግባር ባልተቤት የሆነችዋንና ሚዛናዊ አእምሮ ያላትንም ይሻል በችግርና በፈተና ግዜ ሚታገስ ልብ ባልተቤት የሆነችዋንም ይሻል በነዚህ መልካም ስብእናዎች የተካነች ለመሰል ስብእና ባልተቤቶች የተገባች ናት..!

ዘመናዊነት ያጠቃትና ብስለት የጎደላት በለበሰችው የጣት ቀለበትና የሙሽራ ልሽስ ጓደኞቿ ፊት ለመኮፈስና ለመፎከር ብቻ የምትጠቀምበት በርግጥ እርሷ ለጨዋታና ቧልታ እንጅ ለትዳር የታጨች አደለችም...!

ትዳር በርግጥ ወንድ የሚለው ቃል የሚገልፀው አይነት ወንዶችንም ይሻል ይህም ማለት ለሚስቱ ክብር ያለው ፣ ተብቃቂ የሆነ፣ ሀላፊነቱን በተገቢው ሁኔታ ሚወጣ፣ ግራ ቀኝ የሚመዝንበት ሰፊ አእምሮና በህይወት ውጣ ውረዶች ራቅ ባለ እይታ የተካነ እንዲሁም በትዳር ውስጥ የረሱል (ሰ•ዐ•ወ) ወሲያ (ኑዛዜ) ተፈፃሚ የሚያደርግ ስብእና ባልተቤትንም ይሻል ...!

ትዳር ለሴት ልጅ ሳቢነትና ለወንድ ልጅ ማራኪነት ብቻና ብቻ የሚገነባ ሳይሆን...

በርግጥም ትዳር በፍቅርና በእዝነት እንዲሁም እርጋታ በተሞላበትና አላህና መልእተኛውን በመታዘዝላይ የሚመሰረት የህይወት አንድ አካል እንጂ...

ይላል ከአንድ ገፆ ያገኘሁት 😊

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

01 Nov, 12:34


"አላህም ወደ ሰላም አገር ይጠራል፡፡ የሚሻውንም ሰው ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል፡፡" (ሱረቱ ዩኑስ - 25)

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

31 Oct, 16:49


«አላሁመ ሶሊ ወሰለም አላ ሀቢቢና ሙሀመድ ﷺ»

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

31 Oct, 15:37


#ኒቃቧንም_ትለብሳለች_ትምህርቷንም_ትማራለች
የጁሙዓ ኹጥባ
ነገ ጁሙዓ ጀርመን አዳባባይ መስጂድ።.
Ustaz Abduletif Shekh Teha

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

31 Oct, 03:44


ሂጃብ(ኒቃብ) ከጨርቅ በላይ ስም፣ ከመሸፈኛ በላይ ትርጉም ያለው የእምነት ሰንደቅ ነው፡፡ በጊዜ ብዛት ማርጀት፣ በስልጣኔ ምጥቀት መቀየር፣ መከለስም ሆነ መሻሻል የሌለበት እንደ ማለዳ ፀሀይ ብሩህ ተስፋን የሚፈነጥቅ ዘመን የማይሽረው ፋሽን ነው፡፡ ትላንት በድንጋይ ዘመን ተለብሷል፣ ዛሬም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ወቅትም እየተለበሰ እንደሆነው ሁሉ፣ በማይታወቀው ነገም ሂጃብ እንደሚለበስ የሚታወቅ እውነታ ነው፡፡ አሜሪካ ይሁን አፍሪካ፣ አውሮፓ ይሁን ኤሲያ ሂጃብ ሂጃብነቱን አይለቅም፡፡ ክረምት ብርድ ስለሆነ የሚለበስ፣ በጋ ስለሞቀ የሚወልቅ ሳይሆን ልባዊ እምነትን ዘወትር በገቢር ማሳያ፣ የኢስላማዊ ማንነት መገለጫ ነው፡፡

#ኒቃቧንም_ትለብሳለች
#ትምህርቷንም_ትማራለች

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

30 Oct, 16:35


ምርጧ ሴት ባለቤቷ ቤት በማይኖርበት ጊዜ ክብሯን እና ንብረቱን የምትጠብቅ ነች

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

30 Oct, 16:34


💎 ህይወት ሚስጥር ናት
ምን እንደሚያጋጥምህ አታውቅም ።
ሁሉንም ነገር ለመቀበል እራስህን ዝግጁ አድርግ ::
➪ #መልካም ነገር ሲያጋጥምህ አመስግን
➪ #መጥፎ ነገር ሲያጋጥምህ ታጋሽ ና አመስጋኝ ሁን ከችግርም ጋር ምቾት አለ ና እራስህን አፆና።

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

30 Oct, 14:56


ተማሪዎችን ሂጃብ መከልከል???

#ኒቃቧንም_ትለብሳለች
#ትምህርቷንም_ትማራለች

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

30 Oct, 10:46


እህቴ ሆይ! ሂጃብ ተግባሩም እንደ ስሙ ነው፡፡ ከተለያዩ የማህበራዊ ህይወት ፈተናዎች በተለይም ከፆታዊ ትንኮሳ የሚጠብቅ ጋሻ ነው፡፡ በእስልምና ሴት ልጅ የሰው ልጅ ሰው እንዲሆን በመልካም ኢስላማዊ ስነ-ምግባሮች የሚታነፅበት ማዕከል ነች፡፡ የዚህ የፅድቅ እና ወርቃማ እሴቶች ጅርት የሚፈስበት መዐከል አጥሩ ሂጃብ ነው፡፡ ኢስላምን ማጥቃት የሚፈልጉ አካላትም ቀድመው ሂጃብ ላይ የሚዘምቱት ለዚሁ ነው፡፡ የሙስሊሞች ጥንካሬና ስኬት የሚወሰነው በእንስቷ ነው፡፡ ለዛም ነው ኢስላም የሂጃብ ካባን ደርቦ የኢስላም ዲፕሎማትና አምባሳደር፣ ሰንደቁን አውለብላቢ ክዋክብት አድርጎ የሾመሽ፡፡

#ኒቃቧንም_ትለብሳለች
#ትምህርቷንም_ትማራለች

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

30 Oct, 09:46


"ሰውንም ነፍሱ (በሐሳቡ) የምታጫውተውን የምናውቅ ስንኾን በእርግጥ ፈጠርነው፤ እኛም ከደም ጋኑ ጅማት ይበልጥ ወደርሱ ቅርብ ነን፡፡" (ሱረቱ ቃፍ - 16)

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

29 Oct, 03:35


«አላህ ለኛ የጻፈልን (ጥቅም) እንጂ ሌላ አይነካንም፡፡ እርሱ ረዳታችን ነው፡፡ በአላህ ላይም ምእመናን ይመኩ» በላቸው፡፡ (ሱረቱ አል-ተውባህ - 51)

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

28 Oct, 18:59


ለሴት ልጅ መራቆትን እውቅና የሰጠው የሀገራችን ህግ ነውር አካል መሸፈንን ግልፅ እውቅና መስጠት እንዴት ተሳነው ...!


#ኒቃቤን_እለብሳለሁ
#ትምህርቴን_እማራለሁ

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

28 Oct, 18:57


ሙሳኮ አላህ ለርሱ ብሎ ባህሩን እንደሚከፍልለት አያውቅም። ባህሩ ጋር የደረሰውም አስቦበት አልነበረም። ግን አንድ ነገር እርግጠኛ ነበር “ጌታው መቼም በዚያ አጣብቂኝ ውስጥ እንደማይተወው”። አቤት… የቂን፤ ዐጀብ ተወኩል ፤ “ተው(አትስጉ) ጌታዬ ከኔ ጋር ነው” የሚል ተራራ ኢማን!! ኧረ እንዲህ አይነት የቂን ሸልመን ያ ወዱድ!!

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

28 Oct, 17:47


የአላህና የመላዕክቱ እርግማን በሳሂሮች/በደጋሚዎች/ ባስደጋሚዎችም ላይ ይሁን! የስንቱን ህይወት አቃወሱት 😡

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

28 Oct, 04:15


ትዕግስት ሁልጊዜ ትክክለኛ ምርጫ አይደለም።
ሁኔታዎችን መለወጥ አንዳንድ ጊዜ በጣም ጥሩ ነው።

#መልካም_የሰራ_ሳምንት

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

28 Oct, 03:41


አፍሪካ አካዳሚ 3ኛውን ዙር የሸሪዐ ዲፕሎም ትምህርት መመዝገብ ለፈለጋችሁ ባጠቃላይ ምዝገባ መጀመሩን ያበስራችኋል።

📲 የመመዝገቢያው ኪው አር ኮድ ወይም ሊንክ
https://t.me/africaacademy_diplom3

አካዳሚውን ልዩ የሚያደርገው:
💵 በነፃ መሆኑና ለሁሉም የእድሜ ክልል ላሉ ወንዶችም ይሁን ሴቶች ምቹ መሆኑ፤
💻 በስልክ ወይም በላፕቶፕ ባሉበት ቦታና ርቀት ለመማር ምቹ መሆኑ፤
📚የትምህርት አሰጣጥ መንገዱ እጅግ ያማረና ገር መሆኑ፣ እንዲሁም በተመረጡ ዑለሞች የሚሰጥ መሆኑ፤
🗒️ለየሁሉም የትምህርት ክፍል በይሳምንቱና ትምህርቱ ሲጠናቀቅ የሚሰጡ ፈተናዎች መኖራቸው፤
🎊ላለፉ ተማሪዎች የምስክር ወረቀት የሚሰጥ መሆኑና የምርቃት ፕሮግራም የሚዘጋጅ መሆኑ፤

📖በአካዳሚው የሚሰጡ የትምህርት አይነቶች:
1 - ሲራ
2 - ዓቂዳ
3 - ፊቅህ
4 - ተርቢያ
5 - ተፍሲር
6 - ሐዲሥ

⏱️የትምህርት ቆይታው አንድ አመት ሲሆን በሁለት ሴሚስተሮች የተከፋፈለ ነው።

📋ትምህርቶቹ ለተማሪዎች የሚቀርቡት በነዚህ መልኩ ነው:
- በፒዲኤፍ (pdf)
- በቪዲዮ
- በድምፅ

(የመመዝገቢያውን ሊንክ በመጀመሪያው የኮሜንት መስጫ ሳጥንና ባዮ ላይ ያገኙታል።)

እድሉ አያምልጥዎ! በዙሪያዎም ላሉ ሁሉ ያጋሩ።

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

28 Oct, 03:24


"ሩቅንም ቅርብንም የምታውቅ፥ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ የሆንክ አላህ ሆይ የሁሉም ነገር ጌታ ነህ፡፡ የሁሉም ነገር የበላይ ተቆጣጣሪ ነህ፡፡ ከአንተ ሌላ የሚመለክ ሀይል የለም፡፡ ከነፍስ ክፉ ነገር፣ ከሸይጣንና አጋሮቹ ተንኮል፣ በራሴ ወይም በአንድ ሙስሊም ላይ ክፉ ነገር እንዳልጽምም በአንተ እጠበቃለሁ፡፡"

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

27 Oct, 18:34


❤️እውነተኛ #የትዳር አጋር ስተፈልጊ አንቺን የማጣት ሀሳብ መሸከም የማይችል ይሁን #ሰዎች ይቀይራሉ #ልቦችም ይቀየራሉ #ሁኔታዎችም ደግሞ ከኛ በላይ ጠንክራ ይሆናሉ ግን ይህ ሁሉ ሲሆን ለማስተካከል #የሚታገል እና ላንቺን #ላለማጣት ከሚታገል ጋር ሁኚ
👉ወንድሜ ሆይ አንተም በተቃራኒው እደዛው

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

27 Oct, 10:42


አላህ የምትወዱትን ነገር ካዘገየባቹህ ተስፍ አትቁረጡ
በማትፈልጉት በሚጎዳቹህ ሁኔታ እንድትኖሩ ብትገደዱም አትዘኑ።
እንደውም ትግስት አርጉና ፈገግ በሉ አላህ ሱብሐነሁ ወተላ በእዝነቱ እንዲህ ብሎ የለ ከመከራ ብኋላ ረፍት ምቾት አለ ። እናንተ በማታቁት መልኩ አላህ ሁኔታውን እያስኬደላቹህ ነው ። ምናልባት ሁኔታውን ቀድማቹህ ብታቁ የደስታ ባለቀሳቹህ ነበርና ልባችሁን አረጋጉት አብሽሩ

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

26 Oct, 12:12


ፍቅር ሀራም አይደለም ባይሆን እህቴ ማወቅ ያለብሽ ፍቅር ሙሉ የሚሆነው የአላህ ድንበር ሲጠበቅ ነው ። ለትዳር ብለሽ ሀራም የሆነ ግንኙነት አትጀምሪ ያለ ጊዜው የተቻኮለ በመከልከል ይቀጣል።

ነገሩን ለአላህ ስትይ ተይው የሚሆንሽ ትዳር አላህ በፈቀደው ጊዜ  ይመጣል ።

አትቸኩይ እህቴ ዘመኑ ላይ የምታይው ነገር እንዳይሸውድሽ ሀራም የሆኑ ግንኙነት መብዛት ሀላልነት አያስይዝም ።

ያረብ የማላገባውን እንዳታስወድደኝ
የማገባውም የምወደውን አድርግልኝ!

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

26 Oct, 03:33


"የከተማዋም ሰዎች ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ በእነሱ ላይ ከሰማይም ከምድርም በረከቶችን በከፈትንላቸው ነበር፡፡ ግን አስተባበሉ፡፡ ይሠሩት በነበሩትም ኃጢኣት ያዝናቸው፡፡" (ሱረቱ አል-አዕራፍ - 96)

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

25 Oct, 18:20


ነቢ ሙሳ(ዐሰ) በአንድ ድንገተኛ አደጋ ምክኒያት ያደጉበትን ቀዬ፥ ቤት ንብረትና ቤተሰባቸውን ጥለው ለመሰደድ ተገደው ነበር። የሰደት ጉዞው አናት በሚበሳ የበረሃ ፀሀይና አሸዋ በመሆኑ አድካሚና ተስፋ አስቆራጭ እንደሚሆን ይገመታል። መድየን ሲደርሱ ከለበሱት ውጪ የሚደርቡት፥ ለተጨማሪ ጉዞ የሚሆን ስንቅ፥ አልያም ሊያሰጠጋቸው የሚችል አልነበረም። አንድ ወንዝ አካባቢ ከሚገኝ ጥላ ሰር ተጠግተው ጥሞና ላይ ሳሉ ወደ ወንዙ ከብቶቻቸውን ሊያጠጡ ከሚመጡ አርብቶ አደሮች መካከል ሁለት እንሰቶች ከብቶቻቸውን ይዘው ራቅ ብለው ቁመው ተመለከቱ። ለምን ከብቶቻቸውን እንደማያጣጡ አስገርሟቸው ተጠግተው ጠየቁ። እንሰቶቹ አባታቸው አዛውንት በመሆኑ ከብቶቹን ማጠጣት ሰለማይችል ነበር የመጡት። ሆኖም ትንኮሳ እንዳይገጥማቸው ሌሎች አጥትተው እስኪመለሱ ጠብቀው እንደሚያጠጡ ለነቢ ሙሳ (ዐሰ) አሰረዱ። ነቢ ሙሳ (ዐሰ) ከብቶቹን እየነዱ ወደ ውሃው በማቅነት አጠጥተው ለእንሰቶቹ መለሱ።

ወደነበሩብት ጥላ ሰር ተመልሰው ጥሞናቸውን ቀጠሉ። "ጌታዬ ሆይ! ወደኔ ለምታወርደው ማንኛውም ኸይር ፈላጊ ነኝ" ሲሉ በለሆሳስ ጌታቸውን ተማፀኑ። የባሮቹን የልብ ሹክሹክታ የሚሰማው ጌታ ተማፅኖዋቸውን ሰማ። ምስጋናም ሆነ ምንዳ ሳይፈልጉ የሰሩት በጎ ስራ እጣ ፈንታቸውን አስተካከለው። ከደቂቃዎች በፊት መሄጂያ መጠጊያም ሆነ የሚበሉት የሚለብሱት ያልነበራቸው ነቢ ሙሳ (ዐሰ) እንግዳ ላድርግህ የሚል መልዕክት መጣላቸው። እንግድነቱም ልጄን ልዳርህ በሚል ግብዣ ተቀይሮ መጠጊያ፥ ቤተስብና ሀብት አገኙ። ተስፋ ከሌለው ጨለማ የተስፋ ብርሃን ፈነጠቀላቸው። ታሪካቸውን የሚቀይር ስበብ ባይኖርም ቅሉ ያለ ሰበብ መርዳት የሚችለው ጌታ ሰበብ ፈጥሮ ታሪካቸውን በቅፅበት ቀየረው።

አንዳንድ ጊዜ በሰውኛ ቀመር ስናስበው ህይወታችን ጨለማ ይመሰላል። ይረዱናል፥ ያግዙናል፥ ይደግፉናል፥ ያበረቱናል ያልናቸው ጀርባ ሰጥተውን ይገኛሉ። ህይወታችን በበጎ ይቀየር ዘንዳ መነሻ የሚሆን ሰበብ ቀርቶ ፍንጭ እናጣለን። የጥረታችን ፍሬ ድካም ይሆንና አምጠን ሶስት ወደፊት ተራምደን ባላሰብነው ምክኒያት አራት ወደኃላ ተመልሰን እንገኛለን። በመሮጫ ማሽን ላይ እንደሚከናወን ሩጫ ላብ ብናፈስም ከቦታችን ፈቀቅ አላልንም። ልፋታችን ብቻ ሳይሆን እውቀታችንም ሆነ በዙሪያችን ያሉ ትውውቆቻችን ጠብ ያደረጉልን ነገር የለም። በዚህ ሁናቴ ምሽቱ እንጂ ቀጥሎ የሚመጣው ብርሃን አይታየንም። ተስፋ መቁረጥ ተስፋችን ይሆናል። በዚህ ጊዜ ካላሰብነውና ካልገመትነው አቅጣጫ የጌታችን "ኸይር" ትወርዳለች። ሰበቡም ውጤቱም በቅጽበት ይፈጠራሉ። የሌለንን ወይንም ያጣነውን እናገኛለን። ታሪካችን ይቀየራል። የመከራ፥ ችግርና ጭንቀት ምዕራፍ ተዘግቶ የተሰፋ ምዕራፍ ይከፈታል። ያቺ ቅጽበት መቼ እንደሆነች ጌታችን እንጂ ማንም አያውቀውም። ቀኑ ጨልሞብን ማታው ብርሃን፥ ለሊቱ ረዝሞብን ማለዳው የለውጥ ንፋስ ያዘለ ሊሆን ይችላል። ህይወታችን የሚለውጠው ህይወታችን ውሰጥ ባሉ የለውጥ ሰበቦች ሳይሆን የሰበቦች ፈጣሪ በሆነው መሻት በምትመጣዋ ቅጽበት ነው።

አላህ ይግጠመን!

ተፃፈ በ Ibrahim Abdu

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

25 Oct, 04:12


أسْتَغْفِرُ اللهَ العَظِيمَ الَّذِي لاَ إلَهَ إلاَّ هُوَ، الحَيُّ القَيُّومُ، وَأتُوبُ إلَيهِ

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

24 Oct, 15:23


«አላሁመ ሶሊ ወሰለም አላ ሀቢቢና ሙሀመድ ﷺ»

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

23 Oct, 18:36


ህይወት እንቅፍት ሊያጋጥማት ይችላል
ነገር ግን አይቆምም ተስፍ ሊዳከም ይችላል
ግን አይሞትም እድሎች ሊጠፉ ይችላሉ ግን አያልቁም

ዱንያ ምንም ያህል ቢከብድህ የአላህ ብስራት ቅርብ ነዉ!❤️

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

23 Oct, 15:56


ሴቶች አንዴ ዐይናችሁን ጣል አድርጉማ ባሎችንም ይመለከታል 😊

@meh242 የሶላት ልብስ (ሸርሸፍ) በአይነት አቅርባለች ሸምቱ

phone number +251961628989
https://t.me/mandfshoping
tiktok.com/@firdinaseid

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

23 Oct, 11:11


እብሪትና እልህ አይወጥራችሁ። ካፈርኩ አይመልሰኝ አትበሉ። "ልክ ነህ ግፋበት" ብሎ የሚደልላችሁንና የውሸት ጉልበት የሚሠጣችሁን ስሜት ወዲያ ግፉ።

  አንዳንድ ጊዜ መለስ በሉና ምን ያህል ትልቅ ሰው እንዳጣችሁ እመኑ። በገዛ እጄ ለዱንያ አኺራዬ የሚጠቅመኝን ማጣት ያልነበረብኝን ሰው እኮ ነው ያጣሁት በሉ።

ለናንተው ለእልኸኞች

https://t.me/MuhammedSeidAbx

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

23 Oct, 09:26


ጥልቅ በሆነ የንፅፅር አስተምህሮት እና በተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ በሙስሊሞች ላይ የሚደርሰውን የአክፍሮት ሃይላት ተፅኖ በመታገል በሚናውቀው ተወዳጅ ኡስታዛችን ኡስታዝ ሷድቅ ሙሀመድ (አቡ ሃይደር) የ "ዓቂደቱ ጠሐዊያ" ትምህርት ዘወተር ረቡዕ እና ሀሙስ ከቀኑ 10:30 ይቀርባል።

ይከታተሉን!!  እጅግ ጠቃሚ ትምህርቶችን ከተወዳች መሻኢኾች እና ኡስታዞች ያገኛሉ።

#አፍሪካ_ቲቪ1
-------------------------------------------------------
     
አፍሪካ ቲቪ1    
ናይል ሳት 📡🛰           
ፍሪኩዌንሲ 11636⭕️    
ሲምቦል ሬት 27500    
ፖላራይዜሽን፡ ቨርቲካል

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

23 Oct, 03:27


“አላህ ሆይ በአንተ ለዚህ ማለዳ በቅተናል፡፡ በአንተ ለምሽት እንበቃለን፡፡ በአንተ ህያው ሆነና፡፡ በአንተም እንሞታለን፡፡ መመለሻ ወደ አንተ ነው፡፡ ”ቲርሙዝይ

AL–JUED DAAWA አል–ጁድ ደዕዋ

22 Oct, 12:08


ይህ እድል እንዳያመልጥዎ!

እውቅ መሻይኾችና ኡስታዞችን አካቶ የያዘው አፍሪካ አካዳሚ ለ3ኛ ዙር የሸሪዐ ዲፕሎማ መርሃ ግብር ምዝገባ መጀምሩን ሲገልፅ በታላቅ ደስታ ነው።

ፕሮግራሙን ልዩ የሚያደርጉት
ነጻ መሆኑ
💻 ሁሉም ባለበትና በተመቸው ሰአት መማር መቻሉ
👬ጾታና የእድሜ ክልል የማይገድበው መሆኑ
📚ትምህርቶቹ የሚሰጡት በእውቅ መሻይኾችና ኡስታዞች መሆኑ
🎉 እውቅና ያለው የምስክር ወረቀት መሰጠቱ።
የትምህርት ቆይታው አጭር መሆኑ

ትምህርት ህዳር 1/2017 ይጀምራል

ለመመዝገብና ትምህርቱን ለመከታተል ከታች ያለውን ቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ

https://t.me/africaacademy_diplom3

1,960

subscribers

1,173

photos

125

videos