Alif Online @alif_online_official Channel on Telegram

Alif Online

@alif_online_official


✍️Daily Updates, detailed analysis and informed openions focusing on Ethiopia, Middle East and beyond✈️🌍

Alif Online (English)

Welcome to Alif Online, your go-to channel for daily updates, detailed analysis, and informed opinions focusing on Ethiopia, the Middle East, and beyond. Our channel, @alif_online_official, aims to provide our subscribers with the latest news, insightful commentary, and in-depth coverage of important events in these regions. Whether you are interested in politics, culture, or current affairs, Alif Online has got you covered. Stay informed and engaged with our content, written by knowledgeable experts who are passionate about the topics they cover. Join our channel today and be part of a community that values information, discussion, and learning. Alif Online - expanding your knowledge of the world, one update at a time. 📝✈️🌍

Alif Online

08 Dec, 02:17


♻️🔻🇸🇾 #ሰበር

አዲሱ የሶሪያ የሽግግር መንግስት የአሳድ አገዛዝ ማብቃቱን የሚገልጽ መግለጫ በሁሉም የሬዲዮ እና የቴሌቭዥን ጣቢያዎች በቅርብ ይፋ ያደርጋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

08 Dec, 02:08


♻️🔻🇸🇾በደማስቆ የሰይዳ ዘይነብ መካነ መቃብር እና መስጂድ አካባቢ ግጭቶች እና ተኩስ አለ - አንዳንድ የሺዓ ተዋጊዎች መካነ መቃብሩን ትተው ለመሄድ ፈቃደኛ አይደሉም።

የሰይዳ ዘይነብ መካነ መቃብር በሶስት አቅጣጫ በታህሪር አል ሻሞች እየተከበበ ነው።

ዘይነብ የዓልይ ረ.ዓ ልጅ ነች።

@Alif_Online_Official

Alif Online

08 Dec, 01:44


♻️🔻🇸🇾#ሰበር

ባሉት መረጃዎች መሰረት የሶሪያ ዋና ከተማ ደማስቆ በታህሪር አል ሻም ኃይሎች ቁጥጥር ስር ገብታለች የበሽር አል አሳድ መንግሥትም ተወግዷል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

08 Dec, 01:37


♻️🔻🇸🇾#ሰበር

የታህሪር አል ሻም ኃይሎች ደማስቆ ፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግሥት ገብተዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

08 Dec, 01:31


♻️🔻🇸🇾#ሰበር

ፕሬዚዳንት በሽር አል አሳድ ደማስቆን ለቀው መሸሻቸውን CNN አረጋግጫለሁ ብሏል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

08 Dec, 01:11


♻️🔻🇸🇾ማዕከላዊ ደማስቆ ላይ ከባድ ተኩስ እየተሰማ ነው።

@Alif_Online_Official

Alif Online

08 Dec, 01:04


♻️🔻🇸🇾የቀሩት የሶሪያ ሪፐብሊካን ጋርድ አባላት (ፕሬዚዳንታዊ ጋርዶች) ወደ ፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግስት፣ ወደ ኡመያድ መስጂድ፣ ደማስቆ ከተማ እና ደማስቆ አደባባይ ተሰማርተዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

08 Dec, 00:59


♻️🔻🇸🇾#ሰበር

የታህሪር አል ሻም ኃይሎች በሰው ልጅ የስልጣኔ ታሪክ በኢስላምም የአሸናፊነት ዘመን ትልቅ አሻራን ወደያዘችው የኡመያድ ኺላፋ መቀመጫ ወደነበረችው ደማስቆ ከተማ መግባት ጀምረዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

08 Dec, 00:56


♻️🔻🇸🇾የሶሪያ መንግሥት ወታደሮች ዩኒፎርማቸውን እየቀየሩ በደማስቆ ቦታቸውን እየለቀቁ ነው።

በአላህ ፍቃድ ተፈጽሟል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

08 Dec, 00:54


♻️🔻🇸🇾'ከዚህ በኋላ በማዕከላዊ ዕዝ ለሶሪያ መንግሥት ጦር ኃይሎች የሚተላለፉ ትዕዛዞች የሉም። ጄኔራሎች አሁን በመሰረቱ የራሳቸውን ውሳኔ እየወሰኑ ነው።'

ከቀሩት የአሳድ ታማኝ ሚሊሻዎች እና በደማስቆ ከሚገኙ የአካባቢ መከላከያ ሰራዊት አባላት በስተቀር የሶሪያ መንግሥት ጦር 'ከእንግዲህ ወዲያ የለም'፣ የትዕዛዝ መዋቅሩ 'ሙሉ በሙሉ ፈርሷል'፣ አንዳቸውም ሊዋጉ አይችሉም።'

@Alif_Online_Official

Alif Online

08 Dec, 00:45


♻️🔻🇸🇾 #ሰበር

የሶሪያ መንግሥት ጦር ከደማስቆ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ መውጣት ጀምሯል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

08 Dec, 00:03


♻️🔻🇸🇾 የታህሪር አል ሻም ኃይሎች መሪ አል-ጆላኒ ማነው፡-

አሕመድ ሁሴን አል ሻራዕ፣ “አቡ መሐመድ አል-ጁላኒ” በመባል ይታወቃል።

1982 - ሳዑዲ ሪያድ ነው የተወለደው።

በእስራኤል ከተያዘው የጎላን ኮረብታ ፌይቅ መንደር መነሻቸውን ካደረጉ ቤተሰቦች የተገኘ ነው።

ከገጠር ወግ አጥባቂ ቤተሰብ የተገኘ ነው።

በደማስቆ አል-ማዛ ሰፈር የኖረ እና በትምህርት ቤቶቿ በ1980ዎቹ መጨረሻ የተማረ ነው።

በደማስቆ ዩኒቨርሲቲ ተምሯል።

በ2000 የነበረው የፍልስጤም ኢንቲፋዳ በህይወት መንገዱ ላይ ተፅዕኖ መፍጠሩን ይገልጻል።

ከ 2001 በኋላ የኦሳማ ቢን ላደን እንቅስቃሴ ተጽዕኖ ያሳደረበት መሆኑን ይገልጻል።

በኢራቅ ውስጥ "ሳራያት አል-ሙጃሂዲንን" 2003 ላይ ተቀላቀለ።

በሶሪያ ውስጥ ለአጭር ጊዜ ታስሯል (ትክክለኛው የታሪክ ዝርዝሮች ግልጽ አይደሉም)

በኢራቅ በአሜሪካው "ቡካ ካምፕ" ውስጥ 2004-2010 ድረስ በአሜሪካ ጦር ታስሯል።

በ2011 በ"አቡበከር አል ባግዳዲ" የተሰጠውን ተልእኮ ተቀብሎ ወደ ሶሪያ ተመለሰ።

በአሜሪካ በግንባር ቀደም አሸባሪነት ተፈርጇል።

በፖለቲካዊ አረዳዱ ተራማጅነቱ እና ተግባራዊነቱ ይታወቃል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

07 Dec, 23:35


♻️🔻🇮🇷🇸🇾 ሀያት ታህሪር አል ሻም የሺዓ ሀይማኖታዊ ስፍራዎች እና ሺዓዎችን እንዲሁም ክርስቲያኖችን ጨምሮ አናሳ ሀይማኖቶችን በሶሪያ ውስጥ ለመጠበቅ ቃል በመግባት በዚህ ሳምንት ለኢራን ኢስላማዊ ሪፐብሊክ መልእክት ልኳል ሲል ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል

@Alif_Online_Official

Alif Online

07 Dec, 23:16


♻️🔻🇸🇾🇮🇷🇱🇧🇺🇸 በሊባኖስ ድንበር ላይ የምትገኘው እና የቀድሞዋ የሂዝቦላህ ጠንካራ ይዞታ የነበረችው አል-ቁሰይር ከተማ በታህሪር አል ሻም ኃይሎች ቁጥጥር ስር ውላለች - አሁንም ታህሪር አል ሻሞች ከሶሪያ ጦር  ምንም አይነት ውጊያ አልገጠማቸውም።

@Alif_Online_Official

Alif Online

07 Dec, 22:34


♻️🔻🇸🇾🇮🇷🇹🇷 የታህሪር አል ሻም ኃይሎች እጅግ ከተጠበቀው በፊት ቀድመው የሆምስ ከተማን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረዋል።

ቃል አቀባዩ ኮሎኔል ሀሰን አብዱልገኒ ሆምስን እንደተቆጣጠሩ ገልፆ 3,500 እስረኞችን ነፃ ማድረጋቸውንም አስታውቋል።

አሁን ላይ ከሁሉም አቅጣጫ ደማስቆ ተከባለች ታህሪር አል ሻሞችም በጎላን ከእስራኤል ድንበር እስከ ደቡባዊ ሊባኖስ ድንበር ትሪፖሊ ድረስ ተቀጣጥረዋል።

በደቡባዊ ሊባኖስ ጥሮፖሊ የሚገኙ ሊባኖሳዊያንም ደስታቸውን እየገለጹ ነው።

@Alif_Online_Official

Alif Online

07 Dec, 21:11


♻️🔻🇸🇾🇮🇷🇱🇧🇺🇸 የሶሪያው ፕሬዝዳንት አሳድ ጦርነቱን ለመግታት የምዕራባውያን ሀይሎች ተጽእኖ ካሳደሩ እና ስልጣን ላይ ቀጠለ "ሂዝቦላህን ጨምሮ ከኢራን ከሚደገፉ ታጣቂ ቡድኖች ጋር ያለውን ግንኙነት ለማቋረጥ" ለአሜሪካ ጥያቄ አቅርቧል።

ምንጭ፡ ብሉምበርግ

@Alif_Online_Official

Alif Online

07 Dec, 20:57


♻️🔻🇸🇾🇮🇷🇹🇷 #ሰበር

ከሶሪያ መንግሥት ጦር ጋር ግንኙነት ያለው ሚዲያ የሶሪያ መንግሥት ጦር ከሆምስ ከተማ በስተደቡብ 'ስልታዊ በሆነ መንገድ እራሱን እያዘጋጀ' ነው ብሏል - እጅግ ውድ የሆነችው ሆምስ ከተማ በይፋ በታህሪር እል ሻም ኃይሎች እጅ ገብታለች።

@Alif_Online_Official

Alif Online

07 Dec, 16:54


♻️🔻🇸🇾 የሶሪያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር:- በደማስቆ ዳርቻ ላይ በጣም ጠንካራ የሆነ የጸጥታ ጥበቃ አለ፣ ማንም ሊሰብረው አይችልም።

@Alif_Online_Official

Alif Online

22 Nov, 14:35


♻️🔻🟢 #ሰበር| አልቃሳም ብርጌድ:-

የቃሳም ተዋጊዎች በራፋህ ከተማ ቡርጅ አዋድ መገንጠያ አቅራቢያ በጠላት ወታደሮች እና ተሽከርካሪዎች ላይ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ውስብስብ የሆነ እና የተሳካ ጥቃት ማድረስ ችለዋል።

ተዋጊዎቻችን በአካባቢው በርካታ ወራሪ ወታደሮችን በጥንቃቄ ተከታትለው 4ቱን በተሳካ ሁኔታ በቃሳም "ጉል" ጠመንጃ በቀጥታ በመምታት 2 ጠላት ወታደሮች ወዲያውኑ መሞታቸውን በእርግጠኝነት አረጋግጠዋል።

እነርሱን ለመታደግ ወደቦታው የተጠጋውን የጽዮናውያን መርካቫ ታንክ በአል-ያሲን 105 ላውንቼር በመምታት በእሳት እንዲያዝ ማድረግ ተችሏል።

ከዚያ በኋላ በመንደድ ላይ ነበረውን ታንክ ለማውጣት ሌላ ወታደራዊ ቡልዶዘር ወደ ቦታው ሲቃረብ አይተው ተዋጊዎቻችን በአል-ያሲን 105 ላውንቸር አውድመዋል።

በመቀጠል ተዋጊዎቻችን በዚህ ኦፕሬሺን የተገደሉ እና የቆሰሉትን የጠላት ኃይሎች ለማንሳት ሄሊኮፕተር በቦታው ሲያርፍ አይተዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

22 Nov, 10:40


♻️🔻🟢 አልቃሳም ብርጌድ:-

የቃሳም ተዋጊዎች ከጋዛ ሰርጥ በስተ ሰሜን ከጃባሊያ ከተማ በስተ ምዕራብ በሚገኘው በአል-ሳፍታዊ ጎዳና አከባቢ በሚገኝ ቤት ውስጥ የተጠለሉትን የጽዮናውያን ኃይሎች ኢላማ በማድረግ በቲቢጂ ላውንቼር በማጥቃት የጠላት ኃይል አባላቶቹን መግደል እና ማቁሰል ችለዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

22 Nov, 04:07


♻️🔻🇺🇳⚖️ 🇬🇧 የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እና ጋላንት ላይ በወጣው የእስር ማዘዣ ዙሪያ:- ብሪታንያ የአለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ነፃነት ታከብራለች፣ በጋዛ አፋጣኝ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረስ ማድረግ ላይ እናተኩራለን።

🇨🇭የስዊዘርላንድ ፌደራላዊ የፍትህ ቢሮ:- ኔታንያሁ ወይም ጋላንት ወደ ስዊዘርላንድ ከገቡ ለአይሲሲ ተላልፈው ይሰጣሉ።

🇮🇹 የጣሊያን መከላከያ ሚኒስትር:- ኔታንያሁ ግዛታችንን ከጎበኙ በቁጥጥር ስር የማዋል ግዴታ አለብን።

🇯🇴 የዮርዳኖስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ አይማን አል-ሳፋዲ:- ፍልስጤማውያን ፍትህ ይገባቸዋልና የአይሲሲ ውሳኔ መከበር እና የእስራኤል መሪዎች የእስር ማዘዣ መተግበር አለበት።

🇮🇪 የአየርላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር:- ሁሉም ሀገራት የICCን ነፃነት እና ገለልተኝነት እንዲያከብሩ እንጠይቃለን።

እንዲሁም፣ አየርላንድ አለም አቀፍ የፍትህ እና የሰብአዊ መብቶች አሰራሮችን ለመደገፍ ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ ታረጋግጣለች።

@Alif_Online_Official

Alif Online

21 Nov, 18:15


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 ትላንት ሂዝቦላህ ዋና ዋና የእስራኤል አመራሮችን አስወግዷል!

በተለይም የ71 አመቱ እስራኤላዊ ሰፋሪ ዜቭ ኤርሊች ከእስራኤል ወራሪ ጦር ጋር ተቀላቅሎ በደቡባዊ ሊባኖስ በጀግኖቹ ሂዝቦላህ ሬድዋን ኃይሎች ተገድሏል።

- እንደ እስራኤል ጦር መረጃ ከሆነ ዘየቭ ኤርሊች ከጎላኒ ብርጌድ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ዮአቭ ያሮም ጋር በመሆን በጦሩ ታጅቦ ወደ ደቡብ ሊባኖስ ምዕራባዊ ክፍል እንዲገባ በተፈቀደለት መሰረት በአከባቢው ያሉ የአርኪኦሎጂ ቦታዎችን ለመመርመር እና ጥንታዊ ግኝቶችን ለመመራመር ስራ ጀምሮ ነበር።

በቦታው ላይ ሁለት የሂዝቦላህ አባላት ተገኝተው በወታደሮቹ ላይ ተኩስ የከፈቱ ሲሆን ከእነዚህም መካከል ተመራማሪው፣ አንድ ከፍተኛ መኮንን እና አብረዋቸው የነበሩትን ሌሎች ወታደሮችን ጨምሮ ኢላማ ተደርገው ተገድለዋል።

የእስራኤል ጦር ዩኒፎርም የለበሰው እና ሙሉ በሙሉ የታጠቀው ፕሮፌሰር ኤርሊች "የጥንታዊ እስራኤላውያን ቅሪት" አጊንቻለሁ ብሎ እንደለመደው የሊባኖስን ምድር ሊያስወርስ ሲል ራሱ ቅሪት የተደረገ ሲሆን በተጨማሪም የጎላኒ ብርጌድ አዛዥ እንዲሁም ሌሎች ጠባቂዎቻቸው በሬድዋን ኃይሎች ከጥቅም ውጪ ተደርገዋል።

የእስራኤል ባለስልጣናትም ፕሮፌሰሩ የእስራኤልን ታሪክ የያየዘ ትልቅ ምሁር መሆኑን እየገለጹ እያለቃቀሱ ነው።

@Alif_Online_Official

Alif Online

21 Nov, 16:30


♻️🔻🟢 አልቃሳም ብርጌድ:-

የእኛ ተዋጊዎች በሰሜናዊ ጋዛ ሰርጥ በበይተ ላሂያ አደባባይ 15 ወታደሮችን ካቀፈው የጽዮናውያን እግረኛ ጦር ኃይል ጋር ከቅርብ ርቀት ባደረጉት ውጊያ የጠላት ኃይሎችን አስወግደዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

21 Nov, 16:21


♻️🔻🇪🇺🇫🇷🇳🇱🇧🇪 የአውሮጳ ኅብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል የአይሲሲ ውሳኔ በሁሉም የፍርድ ቤቱ አባል ሀገራት እና የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ላይ ገዢ ነው ያሉ ሲሆን ሁሉም አባል ሀገራት ውሳኔውን ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ አለባቸው ብለዋል።

🇫🇷 የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሰጠው ምላሽም ከICC መርህ ጋር ተስማሚ የሆነ እርምጃ እንወስዳለን ብሏል።

🇳🇱 የኔዘርላንድስ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ኔዘርላንድስ የICCን መመሪያ ታከብራለች ሲል ኔታንያሁ ወይም ጋላንት በግዛታችን ላይ ካረፉ በቁጥጥር ስር ሊውሉ ይችላሉ ብሏል።

🇧🇪 የቤልጂየም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በበኩላቸው ሀገራቸው ውሳኔውን እንደምታከብር ገልፀው የአውሮፓ ሀገራት አይሲሲ ያወጣውን የእስር ማዘዣ ተግባራዊ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

21 Nov, 16:14


♻️🔻🇺🇲⚖️🇺🇳 የዶናልድ ትራምፕ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ማይክ ዋልት አይሲሲ በኔታንያሁ እና ጋላንት ላይ ላወጣው የእስር ማዘዣ በሰጠው ምላሽ:-

"ICC ምንም ተአማኒነት የለውም እና እነዚህ ክሶች በአሜሪካ መንግስት ተቀባይነት የላቸውም።

እስራኤል ህጋዊ በሆነ መንገድ ህዝቦቿን እና ድንበሯን ከዘር አጥፊ አሸባሪዎች ተከላክላለች። ለዚህ የፍርድ ቤቱ እና ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ፀረ ሴማዊ አድሏዊ ውሳኔ በጥር ወር ምላሽ እንሰጣለን።

@Alif_Online_Official

Alif Online

21 Nov, 15:36


♻️🔻🇵🇸⚫️ በኔታንያሁ እና ጋላንት ላይ የወጣውን የእስር ማዘዣ በተመለከተ የፍልስጤም ኢስላማዊ ጂሃድ (PIJ) ያወጣው መግለጫ:-

"በሄግ የሚገኘው አለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ቤንጃሚን ኔታንያሁ እና ዮአቭ ጋላንት በሰብአዊነት ላይ በፈፀሙት ወንጀል እና በፈፀሟቸው ሌሎች የጦር ወንጀሎች የእስር ማዘዣ በማውጣት ያሳለፈውን ውሳኔ ምንም እንኳን የረፈደ ውሳኔ ቢሆንም በደስታ እንቀበላለን።"

@Alif_Online_Official

Alif Online

21 Nov, 15:05


♻️🔻🇺🇳⚖️🇮🇱 ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ኔታንያሁ እና ጋላንት ላይ በጦር ወንጀሎች እና በሰብአዊነት ላይ በተፈፀሙ ወንጀሎች እንዲሁም በጋዛ ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ ተጠቅመዋል ሲል የእስር ማዘዣ አውጥቷል።

የአለም አቀፉን የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ውሳኔ ተከትሎ 124 አባል ሀገራቱ ኔታንያሁ እና ጋላንት ወደ ግዛታቸው ከገቡ የማሰር ግዴታ አለባቸው ማለት ነው።

@Alif_Online_Official

Alif Online

21 Nov, 10:47


♻️🔻🇷🇺🇺🇦 የዩክሬን አየር ሃይል ሩሲያ ዲኒፕሮፔትሮቭስክን ከኒውክሌር ውጭ በሆነ ኢንተር ኮንቲኔንታል ባሊስቲክ ሚሳኤል ኢላማ አድርጋ ደብድባለች ብሏል።

ነገር ግን፣ የሩስያ ምንጮች ይህን መረጃ ውሸት ነው ብለዋል፣ ይህ መረጃ የተሳሳተ ነው ሲሉ ጥቃቶቹ የተፈጸሙት በኢስካንደር እና ኬኤን-23 ሚሳኤሎች ነው ብለዋል።

ICBM ስለመሆኑም ሆነ አለመሆኑ እስካሁን ምንም ማረጋገጫ የለም፣ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እስካሁን መግለጫ አልሰጠም።

ብዙ ሚዲያዎች እንደሚሉት ጥቃቱ የተፈፀመው በ-ICBM ከሆነ፣ በጦርነት ታሪክ ውስጥ ICBM ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅም ላይ መዋል መጀመሩ ይረጋገጣል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

21 Nov, 09:43


♻️🔻🇷🇺🇺🇦 ከጦርነቱ መጀመሪያ ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ሩሲያ በዩክሬን ግዛት ላይ ትልቁን የአየር ጥቃት ለመሰንዘር በዝግጅት ላይ ስትሆን ከ30 በላይ TU-160 ስትራቴጂክ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖችን ይዛ በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ ትገኛለች።

@Alif_Online_Official

Alif Online

20 Nov, 16:57


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 በደቡባዊ ሊባኖስ 5 የእስራኤል ወታደሮች በሂዝቦላህ መገደላቸውን የዕብራይስጥ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

20 Nov, 16:42


♻️🔻🇺🇲🇬🇧🇺🇦🇷🇺 ባለፉት ሁለት ሰአታት ውስጥ ዩክሬን እንግሊዝ ሰራሽ የሆኑ 'Storm Shadow' አየር ላይ ተወንጫፊ የክሩዝ ሚሳኤሎችን ተጠቅማ በሩሲያ ኩርስክ ክልል ኢላማዎች ላይ ጥቃት ፈፅማለች።

ይህ የሆነው ዩክሬን ቢያንስ 6 በአሜሪካ የተሰሩ የረዥም ርቀት ክሩዝ ሚሳኤሎችን (ATACMS) ተጠቅማ በሩሲያ ብራያንስክ ክልል ኢላማዎች ላይ ትናንት ጥቃት ከፈፀመች እና በሩሲያና በኔቶ መካከል እጅግ አስፈሪ መፋጠጥ ከተፈጠረ በኋላ ነው።

ከሁለቱም የምእራቡ እና የምስራቁ ዓለም ሀገራት በርካታ ኤምባሲዎች አሁን በኪዬቭ የሚገኙትን ህንፃዎቻቸውን ለቀው እየወጡ ሲሆን ዜጎቻቸውም ሀገሪቱን እንዲለቁ ጠይቀዋል።

#ማስታወሻ በእስካሁኑ የጦርነቱ ጊዜ ሩሲያ ኒውክለር መሳሪያም ጭምር ልትጠቀም ትችላለች በሚል ስጋት ምዕራባውያኑ ለዩክሬን ከሚያቀርቡት መሳሪያ ውስጥ የረዥም ርቀት ሚሳኤሎችን ተጠቅማ ዩክሬን በሩሲያ ላይ ጥቃት እንዳትፈፅም ከልክለው የቆዩ ሲሆን በዚህ ሳምንት አሜሪካ እና ምዕራባውያኑ እነዚህን መሳሪያዎች ዩክሬን እንዳሻት እንድትጠቀም ፈቅደውላታል።

ሩሲያ ኒውክለር ጦር መሳሪያን ጨምሮ ሁሉንም አደርጋለሁ እያለች ነው።

@Alif_Online_Official

Alif Online

20 Nov, 16:32


♻️🔻🇺🇲🇺🇦🇷🇺 አሜሪካን በመከተል ግሪክ፣ ስፔን እና ጣሊያን ሁሉም በዩክሬን ላይ የሚሳኤል ጥቃት ሊደርስ እንደሚችል በመፍራት በኪዬቭ የሚገኙትን ኤምባሲዎቻቸውን እየዘጉ ነው።

@Alif_Online_Official

Alif Online

20 Nov, 16:28


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 የእስራኤል ሚዲያዎች በደቡባዊ ሊባኖስ በእስራኤል ኃይሎች ላይ አስቸጋሪ ክስተት መድረሱን ዘግበዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

20 Nov, 10:23


♻️🔻🇺🇲🇺🇦🇷🇺 በኪየቭ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ በሩስያ የአየር ጥቃት ሊደርስበት ይችላል የሚል ማስጠንቀቂያ መኖሩን ተከትሎ ለጊዜው ተዘግቷል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

19 Nov, 18:25


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 በሊባኖስ ድንበር አከባቢዎች የምድር ውጊያ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሂዝቦላህ ጽዮናውያኑ ላይ የደረሰውን ውድመት ይፋ አድርጓል

ከኖቬምበር 12 ጀምሮ በ'ሁለተኛው ምዕራፍ' በወራሪው ኃይሎች ላይ የደረሱ ጉዳቶች፡-

– ከ18 በላይ ወታደሮች ሲሞቱ መኮንኖችና ወታደሮች 32 ቆስለዋል። 

– 5 'መርካቫ' ታንኮች እና 1 ወታደራዊ ቡልዶዘር ወድሟል። 

ከኦክቶበር 1 ጀምሮ ያሉ አጠቃላይ ጉዳቶች፡-

- ከ110 በላይ ወታደሮች ሲሞቱ ከ1,050 በላይ ቆስለዋል።

– 48 'መርካቫ' ታንኮች፣ 9 ወታደራዊ ቡልዶዘሮች፣ 2 'ሃምቪ' ተሸከርካሪዎች፣ 2 [ስማቸው ያልተጠቀሰ] የታጠቁ መኪናዎች እና 2 የጦር ሃይል አጓጓዦች ወድመዋል። 

– 6 'Hermes-450' ድሮኖች እና 2 'Hermes-900' ድሮኖች እና ኳድኮፕተር ተመተው ወድቀዋል።

ይህ ቁጥር የእስራኤል ጦር በወታደራዊ ካምፖች፣ ጣቢያዎች፣ ሰፈራዎች፣ ወታደራዊ ሰፈሮች እና በተያዙት ከተሞች ላይ የደረሰበትን ኪሳራ አያካትትም።

@Alif_Online_Official

Alif Online

19 Nov, 16:33


♻️🔻🇺🇲🇵🇸 አሜሪካ ዶክተር ባሲም ናዒም እና ጋዚ ሃማድን ጨምሮ በሃማስ መሪዎች ላይ ማዕቀብ መጣሏን ቻናል 12 ዕብራይስጥ ዘግቧል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

13 Nov, 13:11


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 የእስራኤል ወታደሮች የመሸጉበት በደቡባዊ ሊባኖስ ድንበር የሚገኝ ቤት በሂዝቦላህ ጥቃት በወታሮቹ ላይ ከተደረመሰ በኋላ 7 ጽዮናዊያን ወታደሮች መወገዳቸውን የእብራይስጥ ምንጮች እየዘገቡ ነው።

@Alif_Online_Official

Alif Online

13 Nov, 12:15


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 የእስራኤል ወታደሮች በደቡባዊ ሊባኖስ በሂዝቦላህ ጥቃት ከባድ ክስተት ካስተናገዱ በኋላ ተገድለዋል።

የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን በሊባኖስ ውስጥ በጎላኒ ብርጌድ ወታደሮች ላይ ስለተፈጠረ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ እየዘገቡ ነው።

@Alif_Online_Official

Alif Online

13 Nov, 11:08


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 የእስራኤል ኃይሎች የነበሩበት በደቡባዊ ሊባኖስ ድንበር የሚገኝ ቤት በወታደሮቹ ላይ መደርመሱን የእብራይስጥ ምንጮች ዘግበዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

13 Nov, 08:40


♻️🔻🟢 በትላንትናው እለት፣ አልቃሳም ብርጌድ በርካታ ኦፕሬሺኖችን በተለይም በሰሜናዊ ጋዛ ሰርጥ መፈፀሙን አስታውቋል፣ ይህም ካለፉት ቀናት ጋር ሲነጻጸር ጉልህ ጭማሪ አሳይቷል።

ከወታደራዊ መግለጫዎቹ መካከልም:-

“መርካቫ” ታንክን ’በአል-ያሲን-105’ ላውንቼር ኢላማ በማድረግ በውስጡ የነበሩትን ወታደሮች መግደል እና ማቁሰል የቻለበትን እንዲሁም ከጀባሊያ በስተ ምዕራብ የጠላት ጦር መሳሪያ መያዙን አስታውቋል።

በበይተ ላሂያ በሚገኝ ቤት ውስጥ ሰባት የእስራኤል ወታደሮችን በ'TBG' ላውንቼር ማጥቃቱን እና ከቅርብ ርቀት በተኩስ ጥቃት ሁሉንም ማጥፋቱን አስታውቋል።

አንድ የጽዮናዊያኑን ወታደር በቀጥታ በጥይት በመምታት መምታቱን እና በጀባሊያ የሚገኘውን የእስራኤል እግረኛ ጦር በእጅ ቦምቦች በማጥቃት ሞት እና የአካል ጉዳት ማድረሱን አስታውቋል።

በሰሜነዊ ጋዛ ሁለት 'D9' ወታደራዊ ቡልዶዘሮችን እና ሌላ ታንክ ላይ ኢላማ አድርጎ አውድሟል።

ከጋዛ ከተማ በስተሰሜን ምዕራብ በሚገኝ ቤት ውስጥ የነበሩ የእስራኤል ጦር በፀረ-ሰው ላውንቼር በመምታት ጉዳት አድርሷል።

በጀባሊያ አል-ቃሲብ ሰፈር ውስጥ በሚገኝ ቤት ውስጥ የነበሩ የእስራኤል ወታደሮችን በፀረ-ሰው ላውንቼር ኢላማ አድርጎ ጥቃት መፈጸሙን ገልጿል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

12 Nov, 09:58


♻️🔻🇾🇪 የዩናይትድ ኪንግደም የባህር ንግድ ድርጅት UKMTO እንደዘገበው ከሆዴይዳ፣ የመን በስተደቡብ ምዕራብ 70 ናቲካል ማይል ርቀት ላይ በቀይ ባህር ውስጥ የነበረ መርከብ ላይ ጥቃት ደርሶበታል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

12 Nov, 09:33


♻️🔻🟢 አልቃሳም ብርጌድ:-

የአልቃሳም ተዋጊዎች በሰሜናዊ ጋዛ ጃባሊያ ካምፕ ቃሲብ ሰፈር በሚገኘው አርድ ሱሌይማን አካባቢ ወደሚገኝ ቤት 10 የጽዮናውያን ወታደሮች እንደገቡ ቤቱን በከፍተኛ ፈንጂ በማፈንዳት ሁሉንም መግደል እና ማቁሰል ችለዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

12 Nov, 04:44


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 በደቡባዊ ሊባኖስ ድንበር በሂዝቦላህ ጥቃት በእስራኤል ኃይሎች ላይ ድንገተኛ ጥቃት መድረሱን ቀጥሏል!

• በሰሜና ፍልስጤም በእስራኤል እና ሂዝቦላህ መካከል እየተካሄደ ባለው ውጊያ 10 የጽዮናውያን አሸባሪዎች መገደላቸውን እና ሌሎች መቁሰላቸውን የመጀመርያ ደረጃ የዕብራይስጥ ሚዲያ ዘገባዎች አረጋግጠዋል።

• የጸጥታ ክስተቱ በእስራኤል ሚዲያዎች "አስቸጋሪ" እና "አደገኛ" ሲሉ በድንበር የተከሰተውን ግጭት አጉልተው አሳይተዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

11 Nov, 16:25


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 በቅርብ ሰአታት በእስራኤል ሊባኖስ ድንበር በቀጠለው ውጊያ 2 የእስራኤል ወታደሮች መገደላቸውን እና 7 ሌሎች ወታደሮች መጎዳታቸውን አል አረቢያ የእስራኤል ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

11 Nov, 16:18


♻️🔻🇵🇸🇮🇱 የእስራኤል ወራሪ ጦር የ'ሎታር ኢላት' ልዩ ኦፕሬሽን ክፍለ ጦር ኤይልት ቡድን ኮማንደር የ 34 አመቱ ኢታማር ሌቪን ፍሪድማን በፍለስጤማዊያኑ ጥቃት ከተገደሉት መካከል መሆኑን አስታውቋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

11 Nov, 16:07


♻️🔻🇵🇸🇮🇱 #ተጨማሪ

በሰሜናዊ ጋዛ የፍልስጤም ኃይሎች 2 የተለያዩ የደፈጣ ጥቃቶችን የፈፀሙ ሲሆን 1 ዋና አዛዥን ጨምሮ 5 የእስራኤል አሸባሪ ወታደሮች መገደላቸው ተገልጿል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

11 Nov, 15:37


♻️🔻🇵🇸🇮🇱 #ሰበር

በሰሜናዊ ጋዛ የፍልስጤም ኃይሎች በፈፀሙት ጥቃት ቢያንስ 4 የእስራኤል አሸባሪ ወታደሮች መገደላቸውን እና ሌሎች መጎዳታቸውን የእብራይስጥ ምንጮች እየዘገቡ ነው።

@Alif_Online_Official

Alif Online

11 Nov, 15:23


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 ሂዝቦላህ ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ከባድ ነው በተባለውና ከሰኣታት በፊት በሃይፋ አቅራቢያ እና በኪሪያት ያም ላይ  በፈፀመው ከባድ የየሮኬት ጥቃት በሰፈራው ላይ የተለያዩ ከባባድ ውድመቶችን አስከትሏል።

የሂዝቦላህ የቅርብ ጊዜ ጥቃት ከደረሰ በኋላ ቡርኪናፋሶ  በርካታ የሃይፋ ዳርቻዎች እየተቃጠሉ ነው።

አሁንም ሂዝቦላህ በሊባኖስ ድንበር ከአንድ ኪሎ ሜትር ባነሰ ርቀት ላይ ሮኬቶችን ሲያስወነጭፍ ታይቷል፣ እስራኤል በተሳካ ሁኔታ ሂዝቦላህን አስወጥቻለሁ ያለችበት አዋጅም ውድቅ ሆኗል።

ጠዋት ካርሜል ላይ ሂዝቦላህ በፈመው ጥቃት ቢያንስ 6 ጽዮናዊያን የተጎዱ ሲሆን በእለቱ በተፈጸሙት ጥቃቶች ደግሞ በከባድ ሁኔታ ላይ ያሉትን ጨምሮ 28 የተጎዱ እስራኤላውያን መኖራቸው ታውቋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

11 Nov, 13:29


♻️🔻🇸🇦 የሳዑዲ አረቢያው ልዑል አልጋ ወራሽ መሀመድ ቢን ሰልማን በሪያድ የአረብ እና የሙስሊም መሪዎች ጉባኤ መክፈቻ ላይ እስራኤል በጋዛ እና ሊባኖስ የምታደርገውን ወታደራዊ ጥቃት በአስቸኳይ እንድታቆም ጠይቀዋል።

መሀመድ ቢን ሰልማን ዛሬ በጀመረው የጋራ የአረብ ሊግ እና የኢስላማዊ ትብብር ድርጅት ስብሰባ ባደረጉት ንግግር “በፍልስጤም እና በሊባኖስ ህዝብ ላይ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ” አውግዘዋል።

እስራኤል "ከተጨማሪ የጥቃት እርምጃ እንድትታቀብም" ያሳሰቡት ልዑሉ በዓለም ዙሪያ ያሉ ሀገራት ለፍልስጤም ልዓላዊነት እውቅና እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የአረብ ሀገራት ሊግ ዋና ፀሃፊ አህመድ አቡል ገይት "ቃላቶች የፍልስጤም ህዝቦችን ችግር ሊገልጹ አይችሉም" በማለት በጋዛ እና ሊባኖስ የእስራኤልን ወታደራዊ ዘመቻ በማውገዝ የመሀመድ ቢን ሰልማንን ሃሳብ ደግፈዋል፡፡

ዋና ጸሀፊው “እስራኤል በፍልስጤም ህዝብ ላይ የወሰደችው እርምጃ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት እያናጋ ነው። ዘላቂ ሰላም ማስፈን የምንችለው በፍትህ ብቻ ነው” ብለዋል።

የሳዑዲ ፕሬስ ኤጀንሲ በጋዛ እና በሊባኖስ የቀጠለው የእስራኤል "ጥቃት" "የአረብ እና ኢስላማዊ ሀገራት መሪዎች አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ አስገድዷቸዋል" ብሏል፡፡

@Alif_Online_Official

Alif Online

11 Nov, 12:54


♻️🔻🇸🇦 በጋዛ እና ሊባኖስ ላይ ትኩረቱን ያደረገው የአረብ-ኢስላማዊ ሀገራት መሪዎች ጉባኤ የሶሪያው ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድ የኢራቁ ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሺአ አልሱዳኒ የማልዲቭስ ፕሬዝዳንት መሀመድ ሙዒዙ የሞሮኮው ንጉስ መሀመድ እና ሌሎችም መሪዎች በተገኘበት መካሄድ ጀምሯል፡፡

@Alif_Online_Official

Alif Online

07 Nov, 17:50


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 ሂዝቦላህ:-

የእኛ ተዋጊዎች የእስራኤልን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከተከታተሉ በኋላ ወደ ያሩን ለመግባት የሞከረ የእግረኛ ጦር ቡድንን በደፈጣ ጥቃት ኢላማ በማድረግ በጠላት ወታደሮች ላይ በርካታ ሞት እና ጉዳት አድርሰዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

07 Nov, 14:37


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 ሂዝቦላህ ካርዮት በሚባለው የእስራኤል ሰፈራ ላይ በፈፀመው ከባድ የሮኬት ጥቃት በርካታ ጽዮናዊያን መጎዳታቸው እየተዘገበ ይገኛል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

07 Nov, 14:21


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 #ሰበር

5 የጽዮናውያን ወታደሮች በሊባኖስ ድንበር የተገደሉበት እና ሌሎች 16 ወታደሮች የተጎዱበት ከባድ የሂዝቦላህ ጥቃት መከሰቱን የጽዮናውያኑ ጦር አስታወቀ።

@Alif_Online_Official

Alif Online

07 Nov, 08:42


♻️🔻🟢 አልቃሳም ብርጌድ - ቱልከረም:-

በቱልካረም ካምፕ በአልሙራባአ መስመር ላይ የሚገኘውን የጽዮናውያን እግረኛ ጦር በደፈጣ ጥቃት ኢላማ በማድረግ በጥይት እና በፈንጂ በቀጥታ ተኩስ በመክፈት ጥቃት መፈፀሙንና ተዋጊዎቹ የጠላት ወታደሮችን ጩኸት መስማታቸውንና ሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱን አስታውቋል፡፡

ተዋጊዎቹ በቱልከረም ካምፕ ከሚገኙት ሁሉም ወታደራዊ ሃይሎች ከተውጣጡ ወንድሞቻቸው ጋር በመሆን ከአንድ ግንባር በላይ በሚገኙ ቦታዎች ላይ ወረራ ከፈጸሙት የጠላት ሃይሎች ጋር ከፍተኛ ውጊያ በማድረግ ቀድመው የተዘጋጁ ፈንጂዎችን በማፈንዳት በጽዮናውያን ጠላቶች ላይ የተረጋገጠ ቀጥተኛ ጉዳትና ሞት በማድረስ ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ተዋጊዎቹ ከሁሉንም የተቃውሞ ኃይሎች ወንድሞቻችን ጎን ለጎን በወራሪው ኃይል ላይ ባደረጉት ተከታታይ ኦፕሬሽን በቱልከረም ካምፕ በጽዮናውያን የጠላት ጦር ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት አድርሰዋል ሲል አስታውቋል፡።

@Alif_Online_Official

Alif Online

06 Nov, 17:59


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 በምዕራባዊ ገሊላ ክፋር ማስሪክ ከሊባኖስ በተተተኮሰ ሚሳኤል ስባሪ ተመቶ የሞተ አንድ እስራኤላዊ አስክሬን ተገኝቷል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

06 Nov, 17:35


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 ሂዝቦላህ ከቴላቪቭ በስተደቡብ የሚገኘውን ተርሰፊን ጦር ሰፈር  በ”ፈትህ 110” ሚሳኢሎች ለመጀመሪያ ጊዜ የመታበትን ምስል አውጥቷል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

06 Nov, 17:29


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 ሂዝቦላህ በቅርብ ሰአታት:-

የጽዮናዊያኑን መርካቫ ታንክ በፀረ ታንክ ሚሳኤል በመቱላህ ሰፈራ ውስጥ ማጋየቱን እና በውስጡ የነበሩትን ወታደሮች መግደል እና ማቁሰሉን አስታውቋል።

የጠላት ወታደሮች የመሸጉበትን ቤት በተመሩ ፀረ ታንክ ሚሳኤሎች ኢላማ በማድረግ ቀጥተኛ ጥቃት በማድረስ በውስጡ ያሉትን ወታደሮች መግደል እና ማቁሰሉን አስታውቋል።

በመቱላህ ሰፈራ የነበሩ የጠላት ጦር ሃይሎችን በ"ልዩ" ሮኬት መምታቱን አስታውቋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

06 Nov, 16:39


♻️🔻🇵🇸🇺🇲🇮🇱 ዶናልድ ትራምፕ ቢሮ ከመግባቱ በፊት ወይም ስራ እንደጀመረ የጋዛ ጦርነት ይቆማል ብዬ አስባለሁ።

@Alif_Online_Official

Alif Online

06 Nov, 16:33


♻️🔻🇮🇱ጋላንት ወደ ፀሎቱ ተመልሷል 😉

ኔታንያሁን እየረገመው ይሆን እንዴ 😂

@Alif_Online_Official

Alif Online

06 Nov, 16:11


♻️🔻🇱🇧🟡🟢 🇮🇱 ሂዝቦላህ አቪቭም በሚባለው የጽዮናዊያኑ ሰፈራ ውስጥ በፈፀመው ጥቃት በርካታ ቤቶች ፋብሪካዎች እና ሌሎች መሰረተ ልማቶችም እየወደሙ መሆኑን የከተማው አስተዳደር ገልጿል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

06 Nov, 16:07


♻️🔻🇱🇧🟡🟢 🇮🇱 ሂዝቦላህ ከሰአታት በፊት አቪቭም በሚባለው የጽዮናዊያኑ ሰፈራ ውስጥ በሚገኝ ወታደራዊ ካምፕ ላይ በፈፀመው ከባድ ጥቃት 1 የእስራኤል ወታደር መሞቱ እና ሌሎች መጎዳታቸው እየተገለጸ ነው።

@Alif_Online_Official

Alif Online

06 Nov, 15:41


♻️🔻🇱🇧🟡🟢 የሂዝቦላህ ዋና ጸሃፊ ነዒም ቃሲም ንግግር ማጠቃለያ🎙️

– ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በሂዝቦላህ አንድ ያደረገው ሀሰን ነስረላህ ሸሂድ ከሆነ ዛሬ አርባኛ ቀኑን ይዟል። እሱ ጠላትን የሚቋቋምና አገራዊ ተቋማትን የሚያጠናክር፣ በተለያዩ መስኮች ጠንካራ መዋቅር ያለው ፓርቲ ገንብቷል።

– ሂዝቦላህ በጥንካሬ፣ በድፍረት እና በሸሂድነት ላይ ባለው ጽኑ እምነት ተለይቶ ይታወቃል።

- ነስረላህ የተቃውሞው መሪ በመሆን የተከበሩ ስኬቶችን አግኝቷል; የእሱ ውርስ ይጸናል, ተቃውሞውም ይበልጥ ይጠነክራል።

– ኔታንያሁ መሪር ውጊያ እንደሚጠብቀው ሳያውቅ ሄዝቦላህን ለማጥፋት፣ ሊባኖስን ለመያዝ እንዲሁም አዲስ መካከለኛው ምስራቅን ለመቅረጽ አስቦ ነበር።

- ወረራው በሰላማዊ ሰዎች ላይ አረመኔያዊ ጥቃቶችን ይጠቀማል እና በዘመናዊ የአየር ሃይሉ ላይ ይተማመናል ነገር ግን የእኛን ተዋጊዎች በቀጥታ መዋጋትን ይፈራል።

– ሂዝቦላህ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎች ያሉት ሲሆን ጠላት ጥቃቱን እንዲያቆም በኃይል ማስገደድ ይችላል።

- በውጊያ ግንባር ላይ እርግጠኛ ነን; ወራሪው ተሸናፊ ነው። የእኛ ጥንካሬ ቀጣይነት ባለው ተቃውሞው ላይ ነው።

– ሂዝቦላህ ለእኛ ምንም ትርጉም በሌለው የአሜሪካ ምርጫ ላይ የሚመካ አይደለም። ትኩረታችን ወራሪው ግቡን እንዳያሳካ መከላከል ነው; ለአላህ እንጂ ለማንም አንሰግድም።

- ኔታንያሁ ማሸነፍ አይችልም; በሊባኖስ አፈ ጉባኤ ነቢህ ቤሪ የሚመራው ድርድር የሚካሄደው ጥቃት ከቆመ በኋላ ብቻ ነው።

- ማንኛውም ድርድር ጥቃትን ማቆም እና የሊባኖስን ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ ማክበርን ማካተት አለበት።

- የሊባኖስ ጦር የባህር ድንበሮችን እንዲጠብቅ እና በባትሩን ውስጥ ያለውን ጥሰት ምክንያቶች እንዲያብራራ እጠይቃለሁ ።

– በነስረላህ የሚመራው ተቃውሞ ጭንቅላቱን ከፍ አድርጎ ድልን ያመጣል።

- የሽንፈት ዘመን አብቅቷል; ጊዜ ቢወስድም እናሸንፋለን። ጠላት የጥፋት ጦርነትን ይፈልጋል ነገር ግን ምንም ያህል ጊዜ ቢቆይ በጠላት ላይ ስቃይ እያስከተልን ጸንተን እንቆማለን።

@Alif_Online_Official

Alif Online

06 Nov, 15:07


♻️🔻🇵🇸🟢 የአሜሪካ ምርጫን አስመልክቶ የሐማስ ይፋዊ መግለጫ🎙️

"በአዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ላይ ያለን አቋም በፍልስጤም ህዝባችን ላይ በሚያሳየው አቋም እና ተግባራዊ ባህሪ እንዲሁም በፍልስጤማዊያን ፍትሀዊ ትግል ላይ በሚኖረው አስታዋጾ ላይ የተመሰረተ ነው።

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በጋዛ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በመቃወም የራሱ የአሜሪካ ህዝብ እያሰማ ያለውን ድምጽ ማዳመጥ ይጠበቅበታል፡፡

ከፍልስጤም ህዝብ ነፃነት እና የእራሳቸውን እድል በራሳቸው የመወሰን እንዲሁ እየሩሳሌምን ዋና ከተማዋ ያደረገች ነጻ እና ሉዓላዊት ሀገረ ፍልስጤምን ከመመስረት ያነሰ ማንኛውንም መንገድ አንቀበልም።'

@Alif_Online_Official

Alif Online

06 Nov, 13:40


♻️🔻🇵🇸🇱🇧🟡🟢 🇮🇱 ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከሂዝቦላህ ጋር በሰሜናዊ ግንባር እንዲሁም በጋዛ ሰርጥ ከፍልስጤም ኃይሎች ጋር በቀጠለው ውጊያ 21 ወታደሮቹ መጎዳታቸውን የእስራኤል ወራሪ ጦር አስታውቋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

06 Nov, 10:18


♻️🔻🇱🇧🟡🟢 🇮🇱 የእስራኤል ወታደሮች ከሂዝቦላህ ጥቃት ሀገራቸውን እየጠበቁ😂

@Alif_Online_Official

Alif Online

06 Nov, 10:12


♻️🔻🇱🇧🟡🟢 🇮🇱 ሂዝቦላህ ከደቂቃዎች በፊት በቴል አቪቭ ቤንጉሪዮን አውሮፕላን ማረፊያ ላይ የሚሳኤል ጥቃት ፈፅሟል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

06 Nov, 09:37


♻️🔻🇱🇧🟡🟢 🚀🚀🚀🇮🇱 🔥

@Alif_Online_Official

Alif Online

06 Nov, 06:02


♻️🔻🇺🇲🗳️ ኢሌክቶሪያል ኮሌጅ ካርታ:-

🔴 ትራምፕ፡ 306
🔵 ሃሪስ፡ 226

✍️ ትራምፕ አሸንፏል

@Alif_Online_Official

Alif Online

06 Nov, 04:30


♻️🔻🇺🇲🗳️ ኢሌክቶሪያል ኮሌጅ ካርታ:-

🔴 ትራምፕ፡ 247
🔵 ሃሪስ፡ 186

ትራምፕ ለማሸነፍ 23 ኢሌክቶሪያል ኮሌጆችን ማግኘት በቂው ነው

@Alif_Online_Official

Alif Online

06 Nov, 04:20


♻️🔻🇺🇲🗳️ ኢሌክቶሪያል ኮሌጅ ካርታ:-


🔴 ትራምፕ፡ 237
🔵 ሃሪስ፡ 178

ትራምፕ ለማሸነፍ 33 ኢሌክቶሪያል ኮሌጆችን ማግኘት በቂው ነው

@Alif_Online_Official

Alif Online

06 Nov, 04:09


♻️🔻🇺🇲🗳️ ኢሌክቶሪያል ኮሌጅ ካርታ:-

🔴 ትራምፕ፡ 221
🔵 ሃሪስ፡ 178

ትራምፕ ለማሸነፍ 49 ኢሌክቶሪያል ኮሌጆችን ማግኘት በቂው ነው

@Alif_Online_Official

Alif Online

06 Nov, 03:06


♻️🔻🇺🇲🗳️ ትራምፕ እስካሁን በተቆጠረው ግማሽ የሚሆነው የመራጮች ድምፅ መሰረት ፔንስልቬንያ እና ዊስኮንሲን ላይም መምራት ጀምሯል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

06 Nov, 03:04


♻️🔻🇺🇲🗳️ የአሜሪካ ምርጫ የድምፅ ቆጠራ እየተካሄደ ሲሆን በተቀራራቢ ውጤትም ቢሆን ዶናልድ ትራምፕ መሪነቱን ይዟል።

በአሁኑ አካሄድ ትራምፕ ጆርጂያን እና ሰሜን ካሮላይናን ካሸነፉ፣ ካማላ ሃሪስ በሚቺጋን፣ ፔንስልቬንያ እና ዊስኮንሲን በከፍተኛ ድምፅ ማሸነፍ ይኖርበታል።

🔴 ቀይ ካርታ ላይ ያሉት ትራምፕ ያሸነፈባቸው ግዛቶች ናቸው

🔵 ሰማያዊ ካርታ ላይ ያሉት ካማላ ያሸነፈችባቸው ግዛቶች ናቸው

@Alif_Online_Official

Alif Online

05 Nov, 18:43


♻️🔻🇵🇸🇮🇱 ባለፉት አስር ሰአታት የእስራኤል ጦር ወደ ዌስት ባንክ ቱልከረም መግባቱን ተከትሎ ከሁሉም የፍልስጤም ተዋጊ ኃይሎች ጋር ውጊያ እያደረገ ነው ፍልስጤማውያኑም እጅግ ከባድ ጥቃት እየፈፀሙ ነው።

@Alif_Online_Official

Alif Online

05 Nov, 18:28


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 ሂዝቦላህ ነዒም ቃሲምን ዋና ፀሀፊ አድርጎ ሲሾም ዛሬ የተባረረው ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት "ጊዜያዊ ሹመት, ለረዥም ጊዜ የማይቆይ" ሲል ነዒም ቃሲምንም እንደሚገድሉ ዝቶ ነበር ዛሬ የእሱ ሹመት ጊዜው አለቀ።

@Alif_Online_Official

Alif Online

05 Nov, 18:24


♻️🔻🇺🇲🗳️ የአሜሪካው ምርጫ ቀጥሏል ውጤት ከመገመት ወጪ ለጊዜው አሸናፊውን የሚጠቁም መረጃ የለም።

@Alif_Online_Official

Alif Online

05 Nov, 18:13


♻️🔻🇮🇱አይሁዳዊቷ ሀገር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበረውን እስራኤል ካትዝን የጦር ሚኒስትር እንዲሁም ጌዲዮን ሳኣርን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አድርጋ ሹማለች።

@Alif_Online_Official

Alif Online

05 Nov, 18:12


♻️🔻🇮🇱ኔታንያሁ:-

ጠላቶቻችን ከሚኒስትር ጋላንት ጋር ያለንን ልዩነት ተጠቅመውበታል። በመካከላችን ያሉትን ልዩነቶች ከሚኒስትር ጋላንት ጋር ለማስተካከል ሞከርኩ፣ ነገር ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ልዩነቶቻችንን እየሰፋ ሄዱ።

@Alif_Online_Official

Alif Online

05 Nov, 18:05


♻️🔻🇮🇱#ሰበር

የእስራኤሉ መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከስልጣኑ መባረሩ ይፋ ሆነ።

@Alif_Online_Official

Alif Online

05 Nov, 16:46


♻️🔻🇲🇾🇵🇸🇺🇳🇮🇱 የጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ሀገር ማሌዢያ እስራኤል ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባልነት እንድትሰረዝ የሚጠይቅ ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ እያዘጋጀች መሆኑ ታውቋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

05 Nov, 16:08


♻️🔻🟢 አልቃሳም ብርጌድ:-

የአልቃሳም ተዋጊዎች ሰኞ እለት በሰሜናዊ ጋዛ ሰርጥ ማዕከላዊ ጀባሎያ ካምፕ በሚገኘው በአል-ሃዋጃ ጎዳና ላይ 5 ወታደሮችን ያቀፈ “የእስራኤል” እግረኛ ጦር ኃይልን በ ከቅርብ ርቀት ላይ በማሽን ጥይቶች እና የእጅ ቦምቦች ኢላማ በማድረግ ሁሉንም ወታደሮች ማስወገድ ችለዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

05 Nov, 03:50


♻️🔻🇵🇸🇮🇱🇺🇲 ባለፈው ክረምት በጋዛ በተደረገ ኦፕሬሽን 3 የአሜሪካ ወታደሮች መጎዳታቸውን እና ከእነሱ መካከል አንዱ አሜሪካዊ ወታደር ባለፈው ሳምንት መሞቱን የአሜሪካ ጦር ማስታወቁን CNN ዘግቧል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

04 Nov, 18:36


♻️🔻🇵🇸🇮🇱 ሐማስ የሳይበር ጥቃት በመፈፀም የእስራኤል ወታደሮችን ተንቀሳቃሽ ስልኮች ሰብሮ በመግባት ሚስጥራዊነት ያለው መረጃ መሰብሰቡን ቻናል 12 ዕብራይስጥ ዘግቧል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

04 Nov, 17:02


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 አንድ የእስራኤል ተጠባባቂ ወታደር በሊባኖስ የቀጠለውን ውጊያ እንዲቀላቀል በጦሩ ጥሪ ከተደረገለት በኋላ ራሱን ማጥፋቱን Kann የተባለው የእስራኤል ቻናል ዘግቧል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

04 Nov, 15:21


♻️🔻🇺🇲🗳️ ነገ የሚካሄደው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በቅርብ ሳምንታት ካማላ ሃሪስ ይዛው ከነበረው የአሸናፊነት ቅድመ ግምት አሁን ለመገመት ወደሚከብድ ተቀራራቢ የአሸናፊነት ግምት መጥቷል።

ለሙስሪሙ ዓለም በተለይም ለፍልስጤማዊያን, ሊባኖስ, የመን, ሱዳን እና ሊቢያ የትኛውም መሪ ቢመጣ ጥሩ ነገር ይዞ ይመጣል ተብሎ አይጠበቅም።

አሜሪካ እንደ ሀገር የምትከተለው ፖሊሲ አይሁዳዊነትን የመደገፍ ፖሊሲ ስለሆነ ትልቅ ለውጥ ባይመጣም የባይደን አስተዳደር በጋዛው ጦርነት ባሳየው ውሳኔ የመስጠት ድክመት ምክንያት ካማላ ሃሪስ ከተመረጠች ከባይደን አስተዳደር ቀርፋፋነት ተከትሎ የሚመጣ በርካታ ጫና ስለሚኖርባት እስራኤል ላይ ጠንካራ ጫና ልታሳድር ትችላለች።

ትራምፕ ከተመረጠ ጥሩ እድል ሊኖር ከቻለ ብቸኛ እድል የሚኖረው የሰውየው አይገመቴ አካሄድ ነው በድንገት የሚወስናቸው ውሳኔዎች ጦርነቱን ሊያስቆሙት ይችላሉ, በተለያዩ ግዛቶች ለሚገኙ ሙስሊም እና አረብ መራጮች ጦርነቱን ለማስቆም ቃል ገብቷል ጦርነቱ የሚቆመው ለማን ባደላ መልኩ ነው የሚለው ባይታወቅም።

ለባህረ ሰላጤው አረብ ሀገራት ትራምፕ ተመራጭ ነው ለኢራን ደግሞ በተቃራኒው

ለኢትዮጵያ ካማላ ተመራጭ ነች ለግብፅ ደግሞ ትራምፕ

ለሩሲያ ትራምፕ ተመራጭ ነው ለዩክሬን ደግሞ ካማላ

@Alif_Online_Official

Alif Online

04 Nov, 14:40


♻️🔻🇮🇷🇮🇱 የእስራኤል ትልቁ የአየር ጣቢያ “ኔቫቲም” አዛዥ የኢራን ወኪሎች ሳይሆኑ አይቀሩም በተባሉ ግለሰቦች የግድያ ሙከራ ከተደረገበት በኋላ ደህንነቱ ወደተጠበቀ ቦታ ተዘዋውሮ ጥበቃ እየተደረገለት እንደሆነ የእስራኤል መገናኛ ብዙሀን እየዘገቡ ነው።

@Alif_Online_Official

Alif Online

04 Nov, 08:48


♻️🔻🇵🇸🇮🇱 የእስራኤል ጦር አባል የሆነና በጋዛ ሰርጥ ውጊያ አድርጎ የተመለሰ "ሳንቲያጎ ኦቫዲያ" የተባለ አሸባሪ ወታደር ራሱን ማጥፋቱ ተገልጿል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

01 Nov, 15:58


♻️🔻🟢 አልቃሳም ብርጌድ:-

ውስብስብ በሆነው ኦፕሬሽን የአልቃሳም ተዋጊዎች በሰሜናዊ ጋዛ ሰርጥ ጀባሊያ አል-ቃሲብ አካባቢ በአል-ያሲን 105 ላውንቼር የጽዮናውያኑን ወታደሮች ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ዒላማ በማድረግ እና 12 ወታደሮች የመሸጉበትን ቤት በቲቢጂ ላውንቼር ኢላማ አድርገው በፈፀሙት ጥቃት በርካታ የጠላት ኃይሎችን መግደል እና ማቁሰል ችለዋል። 3 የጠላት  ወታደሮች ከዚህ ጥቃት ለማምለጥ በአከባቢው ወደነበረ መርከሻ ታንክ በሸሹበት ጊዜም ታንኩን በከፍተኛ ፈንጂ ኢላማ ማድረግ ተችሏል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

01 Nov, 15:18


♻️🔻🇮🇷የቀድሞው ኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአሁኑ የአሊ ኻሜኒ አማካሪ ከማል ካራዚ:-

➡️ የባላስቲክ ሚሳኤሎቻችንን ፍፁም ማድረግ እና መጨመር ይጠበቅብናል።

➡️ "የህልውና አደጋ ውስጥ እንዳለን ከተሰማን" የኑክሌር አጠቃቀም መርሆዎቻችንን የመቀየር ውሳኔ በጠረጴዛ ላይ ነው። የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎችን በቀላሉ ለማበልፀግ ሁሉም እውቀት እና የቴክኒክ ችሎታ አለን።

➡️ ለእስራኤል ጥቃት በተገቢው ጊዜ እና በተገቢው መንገድ ምላሽ እንሰጣለን።

@Alif_Online_Official

Alif Online

01 Nov, 12:19


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 ሂዝቦላህ በ "ካርሚኤል" አቅራቢያ በሚገኘው ሾራሺም ሰፈራ ላይ በፈፀመው የሮኬት ጥቃት ቢያንስ 9 ጽዮናዊያን በቀጥታ መመታታቸወን የሚገልጹ ሪፖርቶች እየወጡ ነው።

@Alif_Online_Official

Alif Online

31 Oct, 17:08


♻️🔻🇮🇷🇮🇱 የኢራን ጦር ግዙፍ ባለስቲክ ሚሳኢሎቹን ወደ አስፈላጊ ቦታዎች እያዘዋወረ መሆኑ ተገልጿል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

31 Oct, 14:53


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 ሂዝቦላህ በዋታ አል-ቂያም አካባቢ የሚገኝ የእስራኤል 'መርካቫ' ታንክ እና ሌላ ወታደራዊ ተሽከርካሪን በሁለት የተመሩ ሚሳኤሎች ኢላማ በማድረግ ማውደሙን እና በቦታው የነበሩ ወታደሮችን መግደል እና ማቁሰሉን አስታውቋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

31 Oct, 14:47


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 እብራይስጥ ቻናል 12:- የአይሁድ ደም እንደ ውሃ እየፈሰሰ ነው አለም ግን ምንም አልተሰማውም።

🤣

@Alif_Online_Official

Alif Online

31 Oct, 14:15


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 የእስራኤሉ ቻናል 13 በሃይፋ ውስጥ ከክራዮት በስተምስራቅ ሂዝቦላህ በፈፀመው የሮኬት ጥቃት 4 እስራኤላውያን መጎዳታቸውን ከነዚህም 2ቱ በአስጊ ሁኔታ ላይ ናቸው ሲል ዘግቦ ነበር።

የእስራኤል ሚዲያዎስ አሁን እንደዘገበው  ቡት ሁለቱ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።

ይህም ዛሬ በሂዝቦላህ ሮኬት ተመትተው የሞቱትን እስራኤላውያን ቁጥር 8 ያደረሰው ሲሆን መቱላ ውስጥ 6 እና 2 በክራዮት ሞተዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

31 Oct, 13:42


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 የእስራኤል ወራሪ ጦር የሞቱትን እና የቆሰሉትን ወታደሮቹን ሰብስቦ ከከተማዋ ድንበር ውጭ ወደሚገኘው የወይራ ዛፎች ጫካ ማፈግፈጉን አል ማያዲን ዘግቧል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

31 Oct, 13:22


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 #ተጨማሪ የእስራኤል ጦር አሁን በሁለት የሂዝቦላህ የደፈጣ ጥቃት ስር ከወደቀ በኋላ ከቂያም ምዕራብ እና ምስራቃዊ ዳርቻዎች በማፈግፈግ ላይ ነው።

በአሁኑ ጊዜ የነፍስ አድን ሄሊኮፕተሮች በጭስ ጋዝ ከለላ እየተሰጣቸው በአካባቢው እየተዘዋወሩ የሞቱትን እና የቆሰሉትን ወታደሮቻቸውን ለማውጣት እየሞከሩ ነው።

@Alif_Online_Official

Alif Online

31 Oct, 13:16


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 የእስራኤል ጦር ባሳለፍነው ሳምንት ሁለት ጊዜ ተመቶ ለማፈግፈግ ከተገደደ በኋላ በደቡባዊ ሊባኖስ ወደምትገኘው ወደ ቂያም መንደር እንደገና ለመጠጋት እየሞከረ ነው።

‹ኤል ሃማምስ› በመባል የሚታወቀውን ቂያም እና መቱላን የሚያሳየውን ስትራቴጂክ ኮረብታ በመከላከል ላይ በሚገኙት በወራሪው ሰራዊት እና በሂዝቦላህ ተዋጊዎች መካከል ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ ነው።

@Alif_Online_Official

Alif Online

31 Oct, 13:06


♻️🔻🇸🇦🇵🇸 የሳዑዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር:-

ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የመጀመር ሃሳብ በአሁኑ ጊዜ ያበቃለት (የተቋረጠ) ጉዳይ ነው።

@Alif_Online_Official

Alif Online

31 Oct, 13:00


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 የጽዮናውያኑ ሚዲያዎች በደቡባዊ ሊባኖስ ውስጥ "በእስራኤል ኃይሎች ላይ አስቸጋሪ የፀጥታ ክስተት" መኖሩን ዘግበዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

31 Oct, 10:55


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 የእብራይስጡ ቻናል 13 የመቱላ ማዘጋጃ ቤትን ጠቅሶ:-

"በሰሜን እስራኤል ውስጥ በላይኛው ገሊላ ከተማ ውስጥ በተፈፀመው የሮኬት ጥቃት 5 ወታደሮች ተገድለዋል"።

@Alif_Online_Official

Alif Online

31 Oct, 10:20


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 በሂዝቦላህ የሮኬት ጥቃት ቢያንስ 6 የእስራኤል ወታደሮች መጎዳታቸው ተገልጿል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

31 Oct, 10:10


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 ከሊባኖስ በተተኮሱ ሮኬቶች በመቱላ በርካታ ጉዳት መድረሱን የመጀመርያ ደረጃ መረጃዎች ያመለክታሉ። በመቱላ የእስራኤል ጦር ወታደሮች በተሰበሰቡበት ነው ሮኬቶቹ በቀጥታ ኢላማቸውን የመቱት ተብሏል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

30 Oct, 17:54


♻️🔻🇵🇸🇱🇧🟡🟢🇮🇱 ጽዮናዊው ጦር በደቡባዊ ሊባኖስ ድንበር ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ ውጊያ 22 ወታደሮቹ መጎዳታቸውን አስታውቋል።

እንዲሁም በጋዛ ብዙ ወታደሮች ኢላማ የተደረጉበት የተለየ የፀጥታ ክስተት ተከስቶ እንደነበረ የእብራይስጥ ምንጮች ቢገልጹም ጦሩ 1 ወታደሩ ብቻ ከባድ ጉዳት እንደደረሰበት ገልጾ ለወታደሩ ቢተሰቦች ማሳወቁንም  አስታውቋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

30 Oct, 17:40


♻️🔻@Alif_Online_Official

Alif Online

30 Oct, 11:51


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🎙️አዲሱ የሂዝቦላህ ዋና ፀሀፊ ነዒም ቃሲም 9:00 ላይ ንግግር ያደርጋሉ።

@Alif_Online_Official

Alif Online

26 Oct, 05:52


♻️🔻🇸🇦🇮🇷ሳዑዲ አረቢያ በኢራን ኢስላማዊ ሪፐብሊክ ላይ የተፈፀመውን ጥቃት ተቀባይነት የሌለው ስትል አውግዛለች።

ይህ ጥቃት የኢራንን ሉዓላዊነት የጣሰ እና አለም አቀፍ ህጎችን እና መመዘኛዎችን ያልተከተለ ነው ብላለች ሳዑዲ።

ሳዑዲ አረቢያ እስራኤል የቀጣናውን ሀገራት ደህንነት እና መረጋጋት አደጋ ላይ የጣለውን መባባስ ከማስፋፋት እንድትታቀብ አስጠንቅቃለች።

@Alif_Online_Official

Alif Online

26 Oct, 05:14


♻️🔻🇵🇸🇦🇪 ከፍተኛ የፍልስጤም ምንጮች ለአል-አራቢ አል-ጀዲድ:-

• የፍልስጤም አስተዳደር በጋዛ “ከጦርነቱ በኋላ” ተብሎ የቀረበውን የኤሚሬትስን እቅድ ውድቅ አድርጓል።

• የፍልስጤም አመራሮች ከጦርነቱ በኋላ በጋዛ ውስጥ የትኛውንም የኤሚሬትስ ሚና አይቀበሉም።

• የኤሚሬትስ እቅድ በዋሽንግተን በኩል ለፍልስጤም አስተዳደር እንዲደርስ ተደርጓል።

• ዕቅዱ የአረብ ጦር እና ቅጥረኞችን በጋዛ ማሰማራትን ያካትታል ነገር ግን የፍልስጤማዊያኑን ሚና አልጠቀሰም።

@Alif_Online_Official

Alif Online

26 Oct, 05:04


♻️🔻🇮🇷🇮🇱 አክሲዮስ እንዳለው የጽዮናውያኑ ባለስልጣናት ኢራንን ከማጥቃታቸው በፊት በሶስተኛ ወገን በኩል ጥቃት ሊሰነዝሩ እንደሆነ በማስጠንቀቅ አጠቃላይ ስለጥቃቱ ኢላማ ለኢራና ማሳወቃቸውን ገልጿል። ጽዮናውያኑ ይህንን ያደረጉት ቀጣዩን የኢራን ምላሽ ቀላል ለማድረግ መሆኑም ተገልጿል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

26 Oct, 04:25


♻️🔻🇮🇱የእስራኤል የጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት በሰሜናዊ እስራኤል በሬክተር ስኬል 4.9 የተለካ ትልቅ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን አረጋግጧል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

26 Oct, 04:12


♻️🔻🇮🇱በእስራኤል የመሬት መንቀጥቀጥ...

@Alif_Online_Official

Alif Online

26 Oct, 04:11


♻️🔻🇮🇷🇮🇷 የኢራን ኢስላማዊ ሪፐብሊክ አየር መከላከያ ይፋዊ መግለጫ:-

"ከዚህ ቀደም ኢራን ወንጀለኛ እና ህገ-ወጡ ጽዮናዊ አገዛዝ ምንም አይነት ጀብደኛ እርምጃዎችን እንዳይወስድ ማስጠንቀቂያ ብትሰጥም, ይህ ሀሰተኛ አገዛዝ ዛሬ ጠዋት በቴህራን, ኩዝስታን እና ኢላም ግዛቶች በሚገኙ ወታደራዊ ጣቢያዎች ላይ ጥቃት ሰንዝሯል።

የሀገሪቱ የተቀናጀ የአየር መከላከያ ስርዓት ይህንን የጥቃት ድርጊት በማክሸፍና ምላሽ በመስጠት እጅግ የተሳካ ስራ ሰርቷል።

በጥቂት ቦታዎች ላይ የተወሰነ ጉዳት ደርሷል፣ እናም የዚህ ክስተት ይዘት እየተጣራ ነው።

ውድ ዜጎቻችን እነዚህን ክስተቶች በብሔራዊ እና በይፋዊ ሚዲያዎች በኩል እንድከታተሉ እና ለጠላት ወሬ ትኩረት እንዳትሰጡ እንጠይቃለን።

@Alif_Online_Official

Alif Online

26 Oct, 02:48


♻️🔻🇮🇷🇮🇱 እስራኤል በሶስተኛ ዙር ጥቃት እድሏን እየሞከረች ነው !

@Alif_Online_Official

Alif Online

26 Oct, 02:43


♻️🔻🇮🇷🇮🇱 የኢራን ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ቀጣይ መልእክት እስኪተላለፍ ድረስ ሁሉም በረራዎች እንዲሰረዙ አዟል !

@Alif_Online_Official

Alif Online

26 Oct, 02:38


♻️🔻🇮🇷🇮🇱 ልዩነቱ ግልጽ ነው !

@Alif_Online_Official

Alif Online

26 Oct, 02:37


♻️🔻🇮🇷🇮🇱 ኢራን እጅግ የተለየ አየር መከላከያ ስርዓት እንዳላት ያየንበት ክስተት ነበር አንድም የእስራኤል ሚሳኤል መሬት ላይ አላረፈም !

@Alif_Online_Official

Alif Online

26 Oct, 02:24


♻️🔻🇮🇷🇮🇱 እስራኤል ከተጠቀመቻቸው መሳሪያዎች አንዱም ኢላማውን አልመታም, የኢራን ዝግጁነት ከተጠበቀውም በላይ ነው, ኢራን የተጠቀመችው የአየር መከላከያ ሲስተም ራሱ አይታወቅም !

@Alif_Online_Official

Alif Online

26 Oct, 02:20


♻️🔻🇮🇷🇮🇱 እስካሁን የተፈፀመው እዚህ ግባ የማይባል ተራ ጥቃት ሲሆን ምናልባት እስራኤል ዋናውን ጥቃት ልትጀምር ትችላለች !

@Alif_Online_Official

Alif Online

26 Oct, 02:15


♻️🔻🇮🇷🇮🇱 እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ጀምራለች!

@Alif_Online_Official

Alif Online

25 Oct, 17:37


♻️🔻🇾🇪🇵🇸🇱🇧 የመን ሰነዓ 📸

@Alif_Online_Official

Alif Online

25 Oct, 16:37


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 ሂዝቦላህ በዛሬው እለት በተለያዩ የድንበር ውጊያ ግንባሮች 6ኛውን የጽዮናዊያኑን መርከቫ ታንክ ማውደሙን አስታውቋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

25 Oct, 16:32


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 ሂዝቦላህ:-

በክፋር ኪላ አል ዋዛኒ ሰፈር በሚገኝ ተሽከርካሪ አጠገብ 4 የጽዮናውያን ወታደሮችን የያዘ እግረኛ ጦር ላይ ኢላማ አድርገን በፈፀምነው ጥቃት ሁሉንመ መግደል እና ማቁሰል ችለናል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

25 Oct, 16:00


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 ሂዝቦላህ:-

በኦዳይሴህ ዳርቻ 12 ወታደሮች ያሉት የጽዮናውያን እግረኛ ጦር ኃይልን በተመሩ ሚሳኤሎች ኢላማ በማድረግ የተረጋገጠ ሞት እና የአካል ጉዳት አድርሰናል።

ከ20 ደቂቃ በኋላ የእስራኤል ሀመር ወታደራዊ መኪና በውስጡ 4 ወታደሮችን ይዞ ጣልቃ በመግባት የመጀመሪያውን ሃይል ለመደገፍ ሲሞክር ሙጃሂዲኖቻችን በፀረ ታንክ ሚሳኤል ኢላማ በማድረግ ሁሉንም መግደል እና ማቁሰል ችለዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

25 Oct, 14:49


♻️🔻🇵🇸🇱🇧🟡🟢🇮🇱 የእስራኤል ጦር በሰሜናዊ ጋዛ ሰርጥ ከፍልስጤም ኃይሎች ጋር ባደረገው ውጊያ 1 መቶ አለቃን ጨምሮ 3  ወታደሮች መገደላቸውን በይፋ አስታውቋል።

ይህም ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በጋዛ እና በሊባኖስ ድንበር የተገደሉትን ወታደሮች ቁጥር ወደ 13 ያደረሰው ሲሆን ሌሎች 50 ወታደሮች መጎዳታቸውን ከነዚህም 12 የሚሆኑት ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው የጽዮናውያኑ መገናኛ ብዙሃን ገልፀዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

25 Oct, 14:41


♻️🔻🇵🇸🇱🇧🟡🟢🇮🇱 በዛሬው እለት እስካሁን ቢያንስ 13 የእስራኤል ወታደሮች መገደላቸው ተረጋግጧል, የጦሩን እለታዊ ሪፖርት እንጠብቃለን።

@Alif_Online_Official

Alif Online

25 Oct, 14:36


♻️🔻🇮🇷🇮🇱 የኢራን ባለስልጣናት፣ ሁለት የኢስላማዊ አብዮታዊ ጦሩ አዛዦችን ጨምሮ፣ እስራኤል ኢራን ላይ በምትፈፅመው ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰች፣ ከግምት ውስጥ ያሉት ምላሾች እስከ 1,000 የሚደርሱ የባላስቲክ ሚሳኤሎች ጥቃት፣ በቀጠናው በኢራን የሚደገፉ የተቃውሞ ኃይሎች የጋራ ጥቃት፣ እና በፋርስ ባህረ ሰላጤ እንዲሁም በሆርሙዝ ሰርጥ ውስጥ የሚጓዙትን የአለም አቀፍ የኃይል አቅርቦቶች እና የመርከብ ፍሰትን ማስቆም ያካተተ የተለየ ምላሽ ለመስጠት ኢራን መዘጋጀቷን ማወቅ እንደተቻለ ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

20 Oct, 19:27


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 ቤሩት 💔

@Alif_Online_Official

Alif Online

20 Oct, 19:26


♻️🔻🇱🇧🟡🟢🇮🇱 እስራኤል የሂዝቦላህን አቅም ከማዳከም በላይ የሊባኖስን ሀላል ባንክ እንቅስቃሴ ለመጉዳት እየሞከረች ነው!

የሊባኖሱ ሀላል ባንክ ድርጅት ቀርድ አል ሀሰን በሊባኖስ ዙሪያ ወደ 31 የሚጠጉ ዋና ቅርንጫፎች አሉት።

14 በቤሩት፣ 10 በደቡባዊ ሊባኖስ፣ እና 6 በባልቤክ/በካ። ትናንሽ ቅርንጫፎች እና ኤቲኤምዎች ደግሞ በበርካታ ቦታዎች አሉት።

በይፋዊ ቁጥሮች መሰረት፣ ከጥቂት አመታት በፊት፣ 1.9 ሚሊዮን ለሚሆኑ ሊባኖሳዊያን የተለያዩ ከወለድ ነፃ ብድሮችን ሰጥቷል።

በኢኮኖሚው ውስጥ ወደ 4 ቢሊዮን ዶላር የሚያንቀሳቅሰው ይህ ባንክ 300,000 በላይ ዋና ደንበኞች አሉት።

@Alif_Online_Official

Alif Online

20 Oct, 19:15


♻️🔻🇵🇸🟢🇮🇱 ኮሎኔል ብርጋዴር ጀነራል) ኢህሳን ደቅሳ በተገደለበት የአል-ቀሳም ብርጌድ ጥቃት የወራሪው ጦር 52ኛው ክፍለ ጦር ዋና አዛዥም ክፉኛ ተጎድቷል።

ምናልባት ነገ ከነገ ወዲያ ሞተ ሲባል እንሰማለን!

@Alif_Online_Official

Alif Online

20 Oct, 19:04


♻️🔻🇵🇸 በውዲቷ ፍልስጤም ምድር ላይ በቀጣይ ልክ እንደ ውዱ ሰው የህያ ሲንዋር አይነት ሚሊዮን ሲንዋሮችን እናያለን

@Alif_Online_Official

Alif Online

20 Oct, 18:51


♻️🔻🇵🇸🟢🇮🇱 ዛሬ በአል-ቀሳም ብርጌድ አስገራሚ ጥቃት የተገደለው የ401ኛው ብርጌድ ዋና አዛዥ ኮሎኔል (ብርጋዴር ጀነራል) ኢህሳን ደቅሳ በጋዛ እየተካሄደ በሚገኘው የምድር ወረራ ዋና መሪ ሲሆን የህያ ሲንዋርን ላጣንበት በራፋህ ለተፈፀመው ወረራም የመሪነት ሚና የተሰጠው አሸባሪ ነው።

መነሻው በጎላን አከባቢ ከሚኖሩ የድሩዝ አረብ አይሁድ ጎሳዎች ሲሆን ወታደራዊ ህይወቱ በሽልማት የተንቆጠቆጠ በስስት የሚመለከቱት መሪ ነበር።

አል-ቀሳም ይህን ኮሎኔል (ብርጋዴር ጀነራል) የገደለው በአሜሪካ እገዛ እስራኤል በጋዛ ላይ ካዘነበቻቸው እና ባጋጣሚ ካልፈነዱት አሜሪካ ሰራሽ ሚሳኢሎች በአንዱ ተጠቅሞ ነው።

@Alif_Online_Official

Alif Online

20 Oct, 18:36


♻️🔻🇵🇸🇱🇧🟡🟢🇮🇱 እስራኤል የሂዝቦላህ የሀብት ምንጭ ነው ባለችው ቀርድ አል-ሀሰን በተሰኘው የፋይናንስ ተቋም ንብረቶች ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት እንደምትጀምር አስጠንቅቃ ጥቃቱን ጀምራለች።

@Alif_Online_Official

Alif Online

20 Oct, 18:33


♻️🔻🇸🇦 ሳውዲ አረቢያ የኤምቢሲ ቴሌቪዥን ኃላፊን ጠርታለች።

በሳዑዲ መንግሥት የሚደገፈው ኤምቢሲ ቴሌቪዥን የፍልስጤም ተቃውሞ መሪዎችን “አሸባሪ” በማለት የፈረጀበትን ዘገባ ካስተላለፈ በኋላ ሳዑዲ አረቢያ በጣቢያው ስራ መበሳጨቷን እና ዘገባው ከህግ እና የሚዲያ ፖሊሲዎች ጋር የሚጋጭ ነው በማለት የጣቢያውን ኃላፊ ማብራሪያ መጠየቋ ተገልጿል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

20 Oct, 18:26


♻️🔻🇩🇿🇸🇦 አልጄሪያ በሳዑዲ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸውን የአል-አረቢያ እና አል-ሃደስ ቴሌቪዥን ቢሮዎችን ዘጋች።

ኢራቅን ተከትሎ የአልጄሪያ ባለስልጣናት የሳዑዲ የሚዲያ ኔትወርኮች አሳሳች እና ሙያዊ የስነምግባር መስፈርቶችን ያላከበሩ ስራዎችን በመስራታቸው ፈቃዳቸው መሰረዙን አስታውቀዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

20 Oct, 16:58


♻️🔻🇵🇸🇱🇧🟡🟢🇮🇱 በደቡባዊ ሊባኖስ ዛሬም በቀጠለው ውጊያ 3 እስራኤላውያን አሸባሪ ወታደሮች መገደላቸውን እንዲሁም በጋዛ ሰርጥ ቀደም ሲል መገደሉ ይፋ ከተደረገው ኮሎኔል በተጨማሪ 3 ወታደሮች መገደላቸውም ታውቋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

20 Oct, 16:46


♻️🔻🇵🇸🟢🇮🇱 #ሰበር

የእስራኤል ጦር 401 ኛው ብርጌድ ዋና አዛዥ ኮሎኔል ኢህሳን ደቅሳ በሰሜናዊ ጋዛ ሰርጥ ጀባሊያ በተፈፀመበት ጥቃት ተገደለ።

እንደ እስራኤል ጦር መረጃ ኮሎኔል ደቅሳ ሲጠቀምበት የነበረው ታንክ እና ሌላ ታንክ በጀባሊያ በተፈፀመው ጥቃት በፈንጂ ወድመዋል።

ኮሎኔሉ በ2006 እስራኤል ሊባኖስ ጦርነት ላይ በፈፀመው ጭፍጨፋ ከእስራኤል መንግሥት የክብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሲሆን ይሄው የ401ኛው ብርጌድ አዛዥ የጋዛው ጦርነት ከጀመረ ወዲህ የተገደለ ከፍተኛው ወታደራዊ ባለስልጣን ነው።

@Alif_Online_Official

Alif Online

20 Oct, 15:01


♻️🔻🇵🇸🟢🇮🇱 ጀባሊያ በምርጦቹ የኢስላም ልጆች እና በከሃዲው አይሁዳዊ ጠላት መካከል ከባድ ውጊያ ቀጥሏል 🔥

@Alif_Online_Official

Alif Online

20 Oct, 14:53


♻️🔻🟢 አልቃሳም ብርጌድ ባለፉት 3 ሰዓታት በጃባሊያ ካምፕ ውስጥ:-

🔻 1 ታንክ በአል-ያሲን RPG ላውንቼር አውድሟል።

🔻 በርካታ ወታደሮችን የጫኑ 3 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን በ-RPG ላውንቼር በሻዋዝ ፈንጂ እና በታንዶም ላውንቼር መምታት ችሏል።

🔻 1 ዲ-9 ወታደራዊ ቡልዶዘር በአል-ያሲን ላውንቼር አውድሟል።

🔻 2 ወታደሮች በቀጥታ በጥይት በመምታት ገድሏል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

20 Oct, 14:34


♻️🔻🇵🇸🇮🇱 #ሰበር

በሰሜናዊ ጋዛ በጀባሊያ ወረራ ላይ የሚገኘው የጽዮናዊያኑ 162ኛ ክፍለ ጦር በአል-ቀሳም ብርጌድ ከባድ ጥቃት ደርሶበታል፣ የጠላት ሚዲያዎች "እጅግ ከባድ እና ያልተለመደ የፀጥታ ችግር" መከሰቱን እና በፍልስጤማዊያኑ ጥቃት በርካታ ወታደሮቻቸው ጉዳት እንደደረሰባቸው ዘግበዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

20 Oct, 12:04


♻️🔻🇱🇧🟡🟢 🇮🇱 የዕብራይስጥ ሚዲያዎች እንደዘገቡት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 47 የእስራኤል ወታደሮች መጎዳታቸውን ከነዚህም 38 ወታደሮች ከሂዝቦላህ ጋር በተደረገ ውጊያ እንዲሁም 9 ወታደሮች በጋዛ መጎዳታቸውን ገልጸዋል።

ኦክቶበር 18 ድረስ ከእስራኤል ሚዲያ የወጣው የመጨረሻው አጠቃላይ የጉዳት ዘገባ እንደሚያመለክተው የሊባኖስ ወረራ ከጀመረ በኋላ 21 ወታደሮች ተገድለዋል እና 368 ወታደሮች ደግሞ ቆስለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የሂዝቦላህ ግምት በተመሳሳይ ቀን ከ 500 በላይ የእስራኤል ወታደሮች ተጎድተዋል እና 55 ወታደሮች ተገድለዋል።

@Alif_Online_Official

Alif Online

20 Oct, 08:19


♻️🔻🇱🇧🟡🟢 🚀🚀 🇮🇱 🔥

@Alif_Online_Official

Alif Online

19 Oct, 19:23


♻️🔻🇺🇲🇮🇱🇮🇷 ከኦክቶበር 15 እስከ 16 ባሉት ቀናት እስራኤል በኢራን ውስጥ ሰፊ ጥቃት ለማድረግ የምታደርገውን ዝግጅት የሚገልጽ ከአሜሪካ መከላከያ የወጣ የስለላ ሰነድን በዚያው የአሜሪካ የደህንነት ተቋም ውስጥ ያሉ በመረጃ የተደገፉ ምንጮች ይፋ አድርገዋል።

በሪፖርቱ መሰረት የእስራኤል አየር ሃይል (በአየር ላይ የሚተኮሱ ባሊስቲክ ሚሳኤሎችን) እንደ 'ጎልደን ሆራይዘን' (ቢያንስ 16) እና 'ROCKS' (ቢያንስ 40) በ Hatserim የአየር ማረፊያ ከጥቅምት 8 ጀምሮ ማስቀመጡ ተመላክቷል። እነዚህ ለጥቃቱ ጥቅም ላይ ከዋሉ, ትልቅ ጥቃት ይሆናል።

ከኦክቶበር 15 እስከ ኦክቶበር 16 የእስራኤል አየር ሃይል በራሞት ዴቪድ እና በራሞን አየር ማረፊያዎች ላይ በርካታ (ከአየር ወደ ላይ የሚተኩ ሚሳኤሎችን) አከማችቷል፣ ይህም ጥቃት ሊደርስ እንደሚችል ያሳያል።

በተጨማሪም፣ የእስራኤል አየር ኃይል ቢያንስ ሦስት KC-707 ታንከሮች፣ አንድ G-550 ግልፍስትሪም AWAC ጨምሮ በርካታ ቁጥር ባላቸው አውሮፕላኖች በአየር ላይ ነዳጅ መሙላት እና ፍለጋ ማድረግ እንዲሁም የነፍስ አድን ስራዎችን ለመለማመድ በጥቅምት 15 ላይ ልምምድ አድርጓል። አውሮፕላኖች, እና ምናልባትም ተዋጊ ጄቶችም ጭምር በለምምዱ ተሳትፈዋል።

ይህ ሪፖርት መነሻው የአሜሪካ የመከላከያ ዲፓርትመንት አካል ከሆነው ከናሽናል ጂኦስፓሻል-ኢንተለጀንስ ኤጀንሲ ነው።

@Alif_Online_Official

Alif Online

19 Oct, 18:52


♻️🔻🇵🇸🇮🇱 ሃድሾት ሃሞት:-

በጋዛ የእስራኤል ኃይሎች ላይ ሌላ የፀጥታ ችግር ደርሷል። ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች የተጎዱ ወታደሮችን ጭነው ሶሮቃ ሆስፒታል ደርሰዋል።

@Alif_Online_Official