来自 Addis Ababa Police Official (@addispolice) 的最新 Telegram 贴文

Addis Ababa Police Official Telegram 帖子

Addis Ababa Police Official
Addis police
12,731 订阅者
2,568 张照片
3 个视频
最后更新于 01.03.2025 06:25

相似频道

Ethio 251 Media
48,909 订阅者
CNN English News
10,560 订阅者

Addis Ababa Police Official 在 Telegram 上分享的最新内容


129ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ/ም ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚከበር ሲሆን ለበዓሉ መከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታውቋል፡፡
***
በዓሉ በሚከበር ዕለት የትራፊክ መጨናነቅ እንዳያጋጥም እና አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ እንደሚሆኑም የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ በዚህም መሰረት፡-
• በቸርችል ጎዳና በቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ባንኮ ዲሮማ መብራት
• ከአራት ኪሎ በራስ መኮንን ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ራስ መኮንን ድልድይ
• ከመነን አካባቢ እና የካቲት 12 ሆስፒታል በአፍንጮ በር ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ አፍንጮ በር
• ከእሪ በከንቱ በኤሌክትሪክ ህንፃ ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ደጎል አደባባይ
• ከአዲሱ ገበያ በሰሜን ሆቴል ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ሰሜን መብራት
• ከመርካቶ በአቡነ ጴጥሮስ ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ደጃዝማች ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ
• ከእንቁላል ፋብሪካ በቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ዮሐንስ መብራት የሚወስዱት መንገዶች ከየካቲት 22 ቀን 2017 ዓ/ም ከምሽቱ 6፡00 ሠዓት ጀምሮ እስከ የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 7፡00 ሠዓት ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች ይህንን ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና የትራፊክ ፖሊሶች የሚጠቁሟቸውን አማራጭ አቅጣጫዎችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ህብረተሰቡም ማንኛውም አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ በ 011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ መስመር 991 መጠቀም የሚቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይገልፃል።
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ  ፖሊስ መምሪያ ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የታላቁን ህዳሴ ግድብ የሠላም ዋንጫ ተረከበ።
***
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አመራር እና አባላት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የገቢ ማሰባሰቢያ የሠላም ዋንጫ የካቲት 17 ቀን 2017 ዓ/ም ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ተረክበዋል። ርክክቡ የተደረገው የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አመራርና አባላት፣ የክ/ከተማው አስተዳደር ልዩ ልዩ የስራ ኃላፊዎች፣ የኃይማኖት አባቶችና የንግዱ ማህበረሰብ በተገኙበት ነው፡፡

የኮልፌ ቀራንዮ የክፍለ ከተማ  የሠላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ያሲን መሐመድ እንደተናገሩት ታላቁ  የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሉዓላዊነታችን መገለጫና የሀገራችን መለያ በመሆኑ ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ጋር በመተባበር አስፈላጊውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡

በርክክብ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መከላከልና የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ጫንያለው ታፈሰ ባስተላለፋት መልዕክት ፖሊስ ወንጀልን ከመከላከል ተልዕኮው ጎን ለጎን በሀገር  አቀፍ የልማት ስራዎች ላይ የራሱ የሆነ አሻራ እያሳረፈ እንደሚገኝ ገልፀው የታላቁ ህዳሴ ግድባችንን "በጉልበታችንና በገንዘባችን ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን!"   በሚል መሪ ቃል የሠላም ዋንጫውን መረከባችን የግድቡ ግንባታ ከፍፃሜ እንዲደርስ ያለንን ተነሳሽነት የሚያጎለብት ነውም ብለዋል፡፡

የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ ጀምሮ  ቦንድ በመግዛት ድጋፍ ማድረጋቸውን ምክትል ዳይሬክተሩ ተናግረው የክፍለ ከተማው ፖሊስ አመራርና አባላት የተሰጣቸውን ሀገራዊ ተልኮ በብቃት ለመወጣት ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በዋንጫው የርክክብ ስነ ሰርዓት ላይ ተገኝተን ያነጋገርናቸው የክፍለ ከተማው ፖሊስ  አመራርና አባላት በሰጡት አስተያየት የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረ ጀምሮ ቦንድ በመግዛት እና ድጋፍ በማድረግ ያልተቋረጠ አስተዋፅኦ እያደረጉ እንደሚገኙ ተናግረዋል። የግድቡ ግንባታ ሙሉ በሙሉ እስኪጠናቀቅ ድረስም የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።
*
ዘገባ፡- ረ/ሳጅን ሳምሶን ሰለሞን 

ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

ጨለማን ተገን በማድረግ በተመሳሳይ ቁልፍ የቤት ሰብሮ ስርቆት ወንጀል ሲፈፅም የነበረ ተከሳሽ በሁለት መዝገብ በ11 ዓመት ፅኑ እስራትና በ5ሺህ ብር ማስቀጣቱን የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለጸ።
***
ተከሳሹ ደስይላል አበበ ይባላል የቤት ሰብሮ ስርቆት ወንጀሉን ሲፈፅም የነበረው በተለያዩ ቀናት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 አቤም አካባቢ ነው። ተከሳሽ ጨለማን ተገን በማድረግ አከራይ ግለሰብ የሌለባቸውን መኖሪያ ቤቶች በማጥናት በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ ጨለማን ተገን በማድረግ በተመሳሳይ ቁልፍ በሮችን በመክፈት የቤት ሰብሮ ስርቆት ወንጀል ሲፈፅም የነበረና የወንጀል ድርጊቶችን ሲፈፅምም ለወንጀል መፈፀሚያ ህገ-ወጥ ሽጉጥ ይዞ ሲንቀሳቀስም ነበር።                                            

ተከሳሹ ወንጀል ለመፈፀም ጨለማ ቦታ ተቀምጦ በነበረበት የአካባቢ ነዋሪዎች ተጠራጥረው ማንነቱን ለመለየት በሚሞክሩበት ወቅት በያዘው ሽጉጥ የተኩስ ድምፅ በማሰማት ያመለጠ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች በመሪና አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው አመልክተዋል።

ፖሊስም የቀረበለትን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ወንጀል ፈፃሚውን ለመለየት በተደረገ ክትትል ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር በማዋል ከዚህ በፊት የፈፀማቸውን የቤት ሰብሮ ስርቆት ወንጀሎች ያለምንም ተፅዕኖ ቦታዎቹን መርቶ ያሳየና ኤግዚቢቶቹን የማስመለስ ስራም መሰራቱን የመሪና አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ም/ኮማንደር አበራ በየነ ገልጸዋል፡፡

ፖሊስም ተገቢውን ምርመራ በማድረግና በማጠናቀቅ ማስረጃዎችን በማጠናቀር ለዓቃቤ ህግ በማቅረብ ክስ እንዲመሰረትበት አድርጓል።

ጉዳዩንም የተመለከተው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሚ ኩራ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ጥር 27 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ደስይላል አበበን ያርማል ሌሎችንም ያስተምራል በማለት በፈፀመው የቤት ሰብሮ ስርቆት 9 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲሁም ይዞት በተገኘው ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ለወንጀል ተግባር መጠቀም 2ዓመት ፅኑ እስራትና 5 ሺህ ብር ቅጣት ውሳኔ ውሳኔ አስተላልፎበታል።

የመኖሪያ ቤቶችን በመገንባት ግቢውን የሚጠብቅ በሌለበት ተከራይ ብቻ እንዲኖር በማድረግ አከራዮች ሌላ ቦታ የሚኖሩ፤ የቤት ባለንብረቶች የሚያከራዩአቸውን ተከራዮች በህጋዊ መንገድ ውል ተዋውለው ሊያከራዩና ቤታቸውንም በውክልና የሚያስተዳድር ግለሰብ በማኖር ወይም ጥበቃ በመቅጠር ግዴታቸውን ሊወጡ ይገባል። እንዲሁም በየአካባቢው ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ለፀጥታው ስራ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክሮ ሊቀጥልም ይገባል ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።
*
ዘገባ፦ ዋና ሣጅን አዳነ ደስታ 

ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

ጠፍታ የተገኘች የ10 ዓመት ዕድሜ ያላት ህፃን ከአንድ ወር ፍለጋ በኋላ ከቤተሰቦቿ ጋር ተቀላቀለች፡፡  
***
ኢክረም ባዴ በሚል ስም የተጠቀሰች በግምት የ10 ዓመት ዕድሜ ያላት ህፃን ጥር 12 ቀን 2017 ዓ/ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ልዩ ቦታው ገዳም ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ጠፍታ መገኘቷን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ለክፍላችን በፃፈው ደብዳቤ ማሳወቁን እና ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥር 19 ቀን 2017 ዓ/ም ይህንኑ መረጃ በፌስ ቡክ ገፃችን ማጋራታችን ይታወሳል፡፡

የህፃኗ ትክክለኛ ስም ደሜ አስረስ መሆኑን የተናገሩት ወላጅ እናቷ ወ/ሮ ፋጡማ ሙዳ፤ በፌስ ቡክ ገፃችን ላይ የተለጠፈውን መረጃ እና ፎቶ ግራፏን የተመለከተ ሰው ነግሯቸው የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ/ም ወደ አራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቀርበው በማነጋገር ህፃኗ ጠፍታ ከተገኘች በኋላ በጊዜያዊነት እንድትቆይ ከተደረገበት ተቋም ልጃቸውን በፖሊስ አማካይነት መረከባቸውን እና በዚህም ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል፡፡

ህፃን ደሜ አስረስን  ለማፈላለግ በተደረገው እንቅስቃሴ አስፈላጊውን ትብብር ላደረጉ እና የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ ላበረከቱ ሁሉ ፖሊስ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
*
ዘገባ፦ ኢንስፔክተር ተዘራ አብሽር

ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

የታጠፈ የደበዘዘ የተፋፋቀ እና በአጠቃላይ ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡
***
በአዲስ አበባ ከተማ በየጊዜው እየተባባሰ ለመጣው የመንገድ ትራፊክ አደጋ ልዩ ልዩ የደምብ መተላለፍ ጥፋቶች እንደ ምክንያትነት የሚገለጹ ቢሆንም ለእይታ ግልፅ ያልሆኑ የተሽከርካሪ ሰሌዳዎች መበራከት ለአደጋ ብቻ ሳይሆን የወንጀል ስጋት እየሆኑ መምጣታቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት በስድስት ወራት ውስጥ በተለያዩ የደምብ መተላለፍ ጥፋቶች ከአንድ ሚሊየን ሁለት መቶ ዘጠና ሦስት ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች በትራፊክ ፖሊስ አባላት ብቻ እርምጃ የተወሰደባቸው ሲሆን በጥር ወር 2017 ዓ/ም ብቻ ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ በተደረገ ቁጥጥር ከ2 ሺ 1 መቶ በላይ አሽከርካሪዎች እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡

በየጊዜው የታጠፈ የደበዘዘ እና የተፋፋቀ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ ቢሆንም በሚፈለገው ደረጃ ችግሩን መቅረፍ እንዳልተቻለ ያስታወቀው ፖሊስ ችግሩን ለመፍታት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ጠንካራ የቁጥጥርና የክትትል ስርዓትን በመፍጠር ህጋዊ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚገባ ታምኖበታል።

በቅርቡ ተግባራዊ በሆነው ደምብ ቁጥር 557/2016 መሰረት ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ላይ ጥፋቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ 1ሺ 5 መቶ ብር የሚያስቀጣ ደምብ መተላለፍ መሆኑን ተደንግጓል፡፡
በከተማችን አዲስ አበባ የአደጋም ሆነ የወንጀል ስጋቶችን መቀነስ የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን ያስታወቀው ፖሊስ በመደበኛነት ከሚያከናውነው የትራፊክ አደጋ መከላከል ተግባሩ ጎን ለጎን ከየካቲት16 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ በዘርፉ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የታጠፈ፣ የተቆረጠ፣ የደበዘዘ እና በአጠቃላይ ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ ሲሆን አሽከርካሪዎችም ሆኑ ባለንብረቶች ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ችግሩን በማረም የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስዱ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

የ17 አመት ታዳጊ በሆነችው አዶናይት ይሄይስ ላይ የአስገድዶ መድፈርና የግድያ ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ የሞት ፍርድ ተወሰነበት።
***
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ክልል ልዩ ቦታው 15 ሜዳ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው። የወንጀሉ ሰለባ የሆነችው የ17 አመት እድሜ ያላት አዶናይት ይሄይስ የተከሳሽ ሚካኤል ሽመልስ የፍቅረኛው ልጅ ነበረች።

መስከረም 19 ቀን 2015 ዓ/ም ከቀኑ 6:00 ሰአት ሲሆን ታዳጊ አዶናይት ይሄይስ መኖሪያ ቤቷ እያለች ተከሳሽ ለምን አስገድዶ ደፈረኝ ብለሽ ለፖሊስ ክስ መሰረትሽ በሚል ሰበብ በቢላዋ የተለያየ የሰውነት ክፍሏን 16 ቦታ በመውጋት ምንም እንዳልተፈጠረ ወደ መኖሪያ ቤቱ በመሄድ ልብሱን በመቀየር ሊሰወር ሲሞክር በአካባቢው ማህበረሰብ እና በወንጀል መከላከል ስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት ሊያዝ ችሏል።

ፖሊስም በተያዘው ተከሳሽ ላይ ባደረገው ምርመራ ከ2005 እስከ 2007 ዓ.ም ባልታወቀ ጊዜና ሰዓት ታዳጊዋ ነይ ሱቅ ልላክሽ እና ሌሎች ማታለያዎችን እየተጠቀመ በመኖሪያ ቤቱ በተደጋጋሚ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ሲፈፅምባት የቆየ መሆኑንና በወቅቱ እድሜዋ በግምት 10 አመቷ እንደነበረ የምርመራ መዝገቡ ያስረዳል፡፡

ግለሰቡ የእናቷ የፍቅር ጓደኛ የነበረ ሲሆን ይህንን አፀያፊ ድርጊት ለአንድ ሰው ብትናገሪ እናት እና አባትሽን እገላለሁ እያለ ሲያስፈራት የቆየ ስለመሆኑ የሚዘረዝረው የምርመራ መዝገቡ በተጨማሪም ሟችን በሞባይል ካሜራ ቪዲዮ ቀርጬሻለሁ በሚዲያ እና በቴሌግራም እለቀዋለሁ እያለ ለአመታት የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ሲፈፅምባት መቆየቱንና በዚህም ታዳጊዋ ከተከሳሽ በመፀነሷ ፅንሱን እንድታስወርድ ማድረጉን የተከሳሽ የምርመራ መዝገብ ያስረዳል።

ፖሊስ ባከናወነው ተጨማሪ የምርመራ ስራ ተከሳሽ ሚካኤል ሽመልስ የወንጀል ድርጊቱን መፈፀሙን አምኖ ቦታው ድረስ በመሄድ መርቶ ያሳየ ሲሆን የምርመራ መዝገቡን በማደራጀትና በማጠናቀቅ ለዓቃቤ ህግ በመላክ ክስ ተመስርቶበታል።

የወንጀል መዝገቡን ሲከታተል የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ሚካኤል ሽመልስ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ የሞት ቅጣት እንዲቀጣ እና የዘወትር ህዝባዊ መብቶቹ እንዲሻሩ ውሳኔ አስተላልፎበታል፡፡

በማህበራዊ ህይወታችን ህፃናትና ታዳጊዎችን የመጠበቅና የመንከባከብ ኃላፊነት የሁሉም ዜጋ ግዴታ ቢሆንም የቅርብ ቤተሰብ ወይም አሳዳጊዎች ኃላፊነት ከፍተኛ መሆኑን ያስታወሰው ፖሊስ መሰል የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር አዎንታዊ የጠበቀ ቁርኝት ሊኖራቸውና ከተለያዩ የወንጀል ሥጋቶችና ድርጊቶች ሊጠብቃቸው እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል።
*
ዘገባ፦ ኢንስፔክተር እመቤት ሀብታሙ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሠላም ዋንጫን ተረከበ፡፡
***
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አመራር እና አባላት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ የሠላም ዋንጫን የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ/ም ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ተረክበዋል፡፡

ርክክቡ የተካሄደው የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር መኮንን አሻግሬ፣ የክ/ከተማው ፖሊስ መምሪያና በየ ደረጃው ያሉ አመራርና አባላት እንዲሁም የኃይማኖት አባቶችና የንግዱ ማህበረሰብ በተገኙበት ነው።

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ተጀምሮ ዛሬ እስከደረሰበት ደረጃ ድረስ የአዲስ አበባ ፖሊስ እያበረከተ ያለው አበርክቶ ድርሻው ከፍተኛ አንደሆነ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ዘይነባ ጠሃ ገልፀዋል።

በርክክቡ ስነ ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የመምሪያው ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር መኮንን አሻግሬ ባስተላለፉት መልዕክት ፖሊስ ከዋና ተልዕኮው ባሻገር በልዩ ልዩ ሀገራዊ የልማት ስራዎች ላይ የነቃ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን ተናግረው፡፡ " ህዳሴ ለሠላም፣ ህዳሴ ለዲፕሎማሲ፣አፍሪካን በመብራት እናስተሳስራለን! '' በሚል መሪ ቃል የሠላም ዋንጫውን መረከባችን የክፍለ ከተማውን የፖሊስ አመራሮችና አባላትን ለማነሳሳት ትልቅ ጠቀሜታ ይኖረዋልም ብለዋል፡፡

ወንጀልን አስቀድሞ መከላከል የፖሊስ ቀዳሚ ተግባር መሆኑን ኃላፊው ጠቁመው ከዚህ ጎን ለጎን በመሰል ሀገራዊ የልማት ተግባራት ኃላፊነታችንን ለመወጣት ዝግጁዎች ነን ሲሉ ረዳት ኮሚሽነር መኮንን አሻግሬ ጨምረው ገልጸዋል።

ያነጋገርናቸው የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አመራርና አባላት በበኩላቸው ለህዳሴው ግድብ ከዚህ ቀደም ቦንድ በመግዛት ድጋፍ ሲያደርጉ እንደነበር አስታውሰው ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልፀዋል።
*
ዘገባ፦ ዋና ሳጅን ጤናው ፈጠነ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

የባለቤቱን ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ያጠፋው ተከሳሽ የሞት ፍርድ ተወሰነበት።
***
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ክልል ልዩ ቦታው አርሴማ ፀበል እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ነው። ሟች ወ/ሮ አልማዝ እሸቱ ተከሳሽ ፀሀዬ ቦጋለ ከተባለው ግለሰብ ጋር ትዳር መስርተው የሚኖሩ ጥንዶች ነበሩ።

ነሀሴ 27 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ 5:00 ሰአት ሲሆን ተከሳሽ ሟች አልማዝ እሸቱን ከሌላ ወንድ ጋር ትገናኛለሽ ስልክ ትደዋወያለሽ በሚል ጥርጣሬ ተነሳስቶ ሟች ለጉዳይዋ ከቤት ለመውጣት ልብስ ለብሳ ጫማ ለማሰር ባጎነበሰችበት ወቅት በሊጥ መዳመጫ እንጨት ማጅራቷን በመምታት ህይወቷ እንዲያልፍ በማድረግ የሟችን አስክሬን በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ ባለው መጸዳጃ ቤት ውስጥ በማስገባት የግራ እግሯን ከዳሌዋ እስከ ባቷ ያለውን የሰውነት ክፍሏን በመቁረጥ፣ ስጋዋን በመመልመልና በመክተፍ የመጸዳጃ ሲንክ ውስጥ ውስጥ በመክተት ቀሪውን የሰውነት ክፍሏን ደግሞ መፀዳጃ ቤት ውስጥ ይደብቃል፤ የፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ ፀጋዬ ቦጋለ የአልማዝ መጥፋት ላሳሰባቸው ለቤተሰቦቿ እና ለስራ ባልደረቦቿ ገዳም እንደሄደች ለማሳመን ሞክሯል።

ሆኖም በመኖሪያ አካባቢው የተለየ ሽታ መከሰቱ ያሳሰባቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ለፖሊስ ያቀረቡትን አቤቱታ መነሻ በማድረግና ወደ አካባቢው በመሄድ የሟችን አስክሬን በማንሳት ወንጀል ፈፃሚውን በቁጥጥር ስር ያውለዋል፡፡ ተከሳሹ ላይ የሚቀሩ የምርመራዎችንና ተጨማሪ ማስረጃዎችን በማሟላት የወንጀል ድርጊቱን መፈፀሙን በሰጠው ቃል ከማረጋገጡም ባሻገር የወንጀል አፈፃፀሙን የሚመለከታቸው የሕግ ባለሙያዎችና ታዛቢዎች በተገኙበት መርቶ አሳይቷል።

ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ነሃሴ 28ቀን 2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ፀሀዬ ቦጋለ ጥፋተኛ ሆኖ በማግኘቱ በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ከተወሰነ በኋላ ውሳኔውን በመቃወም ጉዳዩን ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ቀርቦ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ጥር 12 ቀን 2017 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ተከሳሽ እንዲቀጣ ወስኖበታል።
*
ዘገባ:-ኢንስፔክተር እመቤት ሀብታሙ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የታላቁን ህዳሴ ግድብ የሠላም ዋንጫን ተረከበ፤ "የግድቡ ቀሪ ስራዎች እስኪጠናቀቁ ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን " ሲሉ የክ/ከተማው ፖሊስ አመራርና አባላት ገልፀዋል።
***
የአዲስ አበባ ፖሊስ አመራርና አባላት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ቦንድ በመግዛት እና የግንባታው ስፍራ በመሄድ ሰራተኞችን በማነቃቃት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ሲያበረክት ቆይቷል፡፡ የግድቡ ቀሪ ስራዎች እንዲጠናቀቁ ለማስቻል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሠላም ዋንጫን በሁሉም ፖሊስ መምሪያዎች እንዲዘዋዋር በማድረግ ላይ ነው፡፡

የካቲት 5 ቀን 2017 ዓ/ም የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አመራርና አባላት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሠላም ዋንጫን ከልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በደማቅ ስነ-ስነርአት ተረክበዋል።

በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር አራጌ እሸቴ ዋንጫው ከስያሜው አንስቶ ሠላምና ልማትን የሚሰብክ መሆኑን ተናግረው ፖሊስ ሠላምና ፀጥታ ከማስፈን ዋና ተልዕኮው ባሻገር በመሰል አገራዊ የልማት ስራዎች ላይ በንቃት እየተሳተፈ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የተቋሙ አመራሮችና አባላት ለግድቡ ግንባታ ባላቸው አቅም አሻራቸውን እንዲያኖሩ ለማስቻል የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሠላም ዋንጫ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በሚኖረው ቆይታ ልዩ ልዩ የግንዛቤ ማስጨባጫ ስራዎችን በመስራት የፖሊሱን ተሳትፎ ይበልጥ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ኮማንደሩ አስታውቀዋል፡፡

የጉለሌ ክፍለ ከተማ የህዳሴ ግድብ ማስተባባሪያ ኃላፊ አቶ ተሾመ ክብረት በበኩላቸው ፖሊስ ለየትኛውም ሀገራዊ ጉዳይ ግንባር ቀደም መሆኑን ጠቅሰው አመራር እና አባላቱ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ቦንድ በመግዛት ያደረጉትን አስተዋፅኦ አድንቀው ፖሊስ መምሪያው ግንዛቤ ለመፍጠር የሚሰራቸው ስራዎች ስኬታማ እንዲሆኑ የክፍለ ከተማው አስተዳደር ተገቢውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡

በዋንጫው የርክክብ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አመራሮች ታላቁ የህዳሴ ግድብ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ በተከታታይ ያለማቋረጥ ቦንድ በመግዛት በቻሉት መጠን የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑን ገልፀዋል።

ያነጋገርናቸው አመራርና አባላት በበኩላቸው በደማቅ ስነ-ስርዓት የታላቁን ህዳሴ ግድብ የሠላም ዋንጫን መረከባችን ፖሊስ፣ ህዝብና መንግስት የጣለበትን ኃላፊነት በስኬት በመወጣት ለሀገሩ ያለውን ፍቅር በተግባር የሚያሳይበት አጋጣሚ በመሆኑ ደስተኞች ነን ብለዋል፡፡ ቀሪ የግድቡ ስራ እስከሚጠናቅ ተሳትፏችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
*
ዘገባ፦ ሳጅኝ ፈለጉሽ አሻግሬ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የጀሞ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ደረጃቸውን የጠበቁ ቢሮዎች አስገብቶ አስመረቀ።
***
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ስትራቴጂክ መኮንኖች ፣ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ም/ኮሚሽነር ሽመልስ ሽፈራው እና የክ/ከተማው አስተዳደር በየደረጃው ያሉ አመራሮች በተገኙበት ነው የተመረቀው።

በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ፖሊስ ተቀዳሚ ተግባሩ ወንጀልን አስቀድሞ መከላከል ተፈፅሞ ሲገኝም ፈፃሚውን በመያዝ በህግ አግባበብ እንዲጠየቅ ለማድረግ እና ለሌሎች አገልግሎት አሰጣጦችም ምቹ ሁኔታን መፍጠር ጊዜው የሚጠይቀው ተግባር ነው ብለዋል፡።

የተሻለ የፖሊስ አገልግሎት ለመስጠት እና ፖሊስም ተረጋግቶ በመስራት አካባቢውን መቆጣጠር እንዲችል ምቹ የስራ ቦታና ሁኔታን መፍጠር ወንጀልን ከመቀነስ አንፃር የሚኖረው አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሚሆን ኮሚሽነር ጌቱ ገልፀው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የጀሞ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ለዚህ ተግባር አንዱ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።

የክ/ከተማውና የጣቢያው የፖሊስ አመራሮች ሌት ተቀን የአካባቢያቸውን በጎ ፈቃደኛና የህዝብን አቅም በመጠቀም በቁርጠኝነት በመምራታቸው እና አባሉም የህዝብ ጉዳይ የኔ ጉዳይ ነው በማለት ተግቶ በመስራቱ አካባቢው ላይ የነበሩ የወንጀል ስጋቶችን አስቀድሞ በመከላከል ወንጀልን ከመቀነስ ባሻገር ደረጃውን የጠበቀ ፖሊስ ጣቢያ በመገንባቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል፡፡

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ም/ኮሚሽነር ሽመልስ ሽፈራው በክፍለ ከተማው የጀሞ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያን ጨምሮ ህብረተሰቡን በማሳተፍ 11 ፖሊስ ጣቢያዎችን በማፍረስ እንደ አዲስ ደረጃቸውን የጠበቁ ቢሮዎችን መገባት ተችሏል ብለዋል።

ከዚህም ባሻገር ለአባሉ ምቹ ማረፊያ ይሆን ዘንድ ደረጃቸውን የጠበቁ ሁለት የአባላት መኖሪያ ካምፖች መሰራቱን የገለፁት ም/ኮሚሽነር ሽመልስ ዘመናዊ ህንፃ ከመገባት ባሻገር ቴክኖሎጂን በማስተሳሰር ቅድመ ወንጀል የመከላከል ስራዎችን እየሰራን እንገኛለን ካሉ በኋላ ይሄንኑ አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ አክለው ገልፀዋል።

በተለምዶ ሱቄ ቅድስት ማርያም ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ወንጀሎች የሚበዙት አካባቢ እንደነበር የገለፁት የጀሞ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ኢ/ር ግርማ ደስታ እና የማህበረሰብ አስተባባሪ ሆኑት አቶ ፀጋዬ ባርክልኝ እንደገለፁት እነዚህን ወንጀሎች በመተባበር መቀነስ ቢቻልም ደረጃቸውን የጠበቁ ቢሮዎች ባለመኖራቸው ለማገልግለም ሆነ ለመገልገል ፈታኝ ሆኖብን ቆይቷል ብለዋል።

አያይዘውም እንደገለፁልን ዛሬ ላይ 12 ደረጃቸውን የጠበቁ ቢሮዎችን መገባት ተችሏል ብለው በቀጣይ ወንጀልን ተባብሮ ከመከላከል ባሻገር ለአካባቢው ማህበረሰብ እና ለፖሊስ አባላት ግልጋሎት የሚሰጡ በፖሊስ ጣቢያው ውስጥ የከርሰ ምድር ውሀ የማውጣት እንዲሁም የዳቦ ማምረቻ ማሽኖችን በመግዛት ሥራ የማስጀመር እቅዶች እንዳላቸው ኢ/ር ግርማ እና አቶ ፀጋዬ ባርክልኝ ጨምረው ተናግረዋል።
*
ዘገባ፦ ረ/ሳጅን አባይነህ እኔምአየሁ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”