Последние посты Addis Ababa Police Official (@addispolice) в Telegram

Посты канала Addis Ababa Police Official

Addis Ababa Police Official
Addis police
12,731 подписчиков
2,568 фото
3 видео
Последнее обновление 01.03.2025 06:25

Похожие каналы

Dr. Henok Gabisa
9,031 подписчиков
Dereje Tariku Law Office
6,483 подписчиков
Federal Prison Commission-Ethiopia
2,511 подписчиков

Последний контент, опубликованный в Addis Ababa Police Official на Telegram


የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከመደበኛ ተልዕኮው ጎን ለጎን በተጨማሪነት ያከናወናቸውን ልዩ ልዩ የለውጥና የልማት ስራዎችን አስመርቆ ሥራ አስጀምሯል፡፡
**
የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የክ/ከተማውን ፀጥታ ከማስጠበቅ ባሻገር የሪፎርሙ ውጤቶች የሆኑ በርካታ የለውጥና የልማት ሥራዎችን ማከናወኑ የሚታወቅ ነው። የካቲት 2 ቀን 2017 ዓ/ም በተጨማሪነት ያከናወናቸውን የልማትና የለውጥ ሥራዎች የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው የክ/ከተማው አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ሚጀና የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የአስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተጎብኝቶ ተመርቋል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ባስተላለፉት መልዕክት የክ/ከተማው ፖሊስ መምሪያ ከተቀበለው ተልዕኮ ባሻገር ያከናወናቸው የልማትና የሌማት ትሩፋት ሥራዎች በአርዓያነት የሚታይ መሆኑን አስታውሰው ተግባሩን አጠናክሮ ማስቀጠሉ ያስመሰግነዋል ብለዋል። አያይዘውም ተግባሩን ከቴክኖሎጅ ጋር ማስተሳሰሩ ውጤታማ እያደረገው እንደመጣ ገልጸው ለፖሊሳዊ አገልግሎት ስራው አስፈላጊ የሆኑ ልዩ ልዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በበለጠ ለማስፋፋት ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ይኖርበታል ብለዋል፡፡

ሥራዎችን በቴክኖሎጂ የማገዝ ተግባር የማስፋፋት ስራው በአስራ አንዱም ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያዎች እየተሰራበት መሆኑን ያስታወሱት ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊሰ መምሪያም በአይሲቲ ስራዎች፣ ምቹ የስራ ቦታን በመፍጠር እንዲሁም በሌማት ትሩፋት ዙሪያ የሰራቸው ስራዎች አበረታችና ለሌሎች በምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑንም ተናግረው ፖሊስ መምሪያው የጀመራቸውን ተግባራት አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ጨምረው ገልጸዋል።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ረ/ኮሚሽነር መስፍን ሰብስቤ በበኩላቸው በክ/ከተማው ህዝብ በስፋት የታደመባቸውን ልዩ ልዩ ኩነቶች ካለምንም የፀጥታ ችግር በሠላም ማጠናቀቅ የተቻለው እና እንደ ክፍለ ከተማ የወንጀል ድርጊትን መቀነስ የተቻለው በአጋጣሚ ሳይሆን የክ/ከተማው ፖሊስ አባላትና አመራሮች ደከመን ሰለችን ሳይሉ ሌትና ቀን ተግባራታቸው በቴክኖሎጂ በማስደገፍ በተሰራ ሥራ የተገኘ ውጤት ነው ብለዋል፡፡

ፖሊስ መምሪያው ከዋና የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከልና ምርመራ ተልኮው ጉን ለጎን ልዩ ልዩ የልማት ስራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው ቀደም ሲል ካከናወናቸው የልማት ስራዎች በተጨማሪ በ200ካሬ ላይ ያረፈ 4 የተለያየ ክፍሎች ያሏቸው 2 የእህል ወፍጮዎች፣ በቀን እስከ 5ሺ እንጀራ መጋገር የሚያስችል ዘመናዊ የእንጀራ ማቀነባበሪያ ፕሮጀክት ስራ ማስጀመሩንም ተናግረዋል።

በፕሮግራሙ ላይ ለፖሊስ መምሪያው ስራ ስኬታማነት ከፍተኛ አስተዋፆኦ ላደረጉ አካላት የገንዘብ፣ የሰርተፍኬት እና ጥሩ አፈጻጸም ላሳዩ ፖሊስ ጣቢያዎችም የኮምፒተር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
*
ዘገባ፦ ረ/ሳጅን አባይነህ እኔምአየሁ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

ላለፉት ሁለት ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው የአዲስ አበባ ፖሊስ ከተማ አቀፍ ስፖርት እና ፌስቲቫል ውድድር ፍፃሜውን አገኘ።
***
ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለላቀ ፖሊሳዊ አገልግሎት በሚል መሪ ቃል ከጥር 17 ጀምሮ እስከ የካቲት 1 ቀን 2017 ዓ/ም ሲካሄድ የቆየው የአዲስ አበባ ፖሊስ ከተማ አቀፍ የስፖርት እና የፌስቲቫል ውድድር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በደማቅ ሁኔታ በተካሄደ የመዝጊያ ስነ ስርዓት ተጠናቋል።

በአትሌቲክስ፣ እግር ኳስ፣ ቮሊቦል፣ ገመድ ጉተታና ጠረጴዛ ቴኒስ ከፍተኛ ፍክክር ተደርጎባቸዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፣ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስና ስፖርት ቢሮ የስራ ኃላፊዎች፣ የሰላም ሰራዊትና የደንብ ማስከበር አባላት እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በመዝጊያ ዝግጅቱ ላይ ታድመዋል።

በዕለቱ በዝግጅቱ ላይ ተገኝተው የስራ መመሪያ የሰጡት የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከተማ አቀፍ ስፖርት እና ፌስቲቫል ውድድርሩ በስኬት መጠናቀቁን ገልፀዋል። የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ከተሰጣቸው ኃላፊነት ጎን ለጎን፣ በስፖርቱ ዘርፍ የሀገርን ሰንደቅ ዓላማ ከፍ ማድረግ የቻሉ ስፖርተኞችን ማፍራት መቻላቸውን የጠቀሱት ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው የተቋሙ የሪፎርም አካል የሆነው ስፖርታዊ ውድድሩ ከአዲስ አበባ ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር መዘጋጀቱን ገልጸው በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚከናወነው የመላው ፖሊስ ስፖርት ውድድር ምርጥ ስፖርተኞችን ማግኘት እንደቻለም ተናግረዋል።

ስፖርትና ፖሊስ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸው ያሉት ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ፖሊሳዊ ተልዕኮን በብቃት ለመወጣት ስፖርት ከፍተኛ ፋይዳ ስላለው በቀጣይ እንደ ባህል እንዲዘወተር እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል። አካላዊ ቁመናው የተስተካከለ፣ ተልዕኮውን በአግባቡ የሚወጣ የፖሊስ አመራርና አባል ለማፍራት ስፖርቱን በጥብቅ ዲስፕሊን የመሩ አካላት በሙሉ ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል።

ስፖርታዊ ጨዋነትና ፖሊሳዊ ዲሲፕሊን በመጠበቅ በውድድሩ የተሳተፉ፣ ስፖርተኞችንና ለስኬታነቱ እገዛ ላደረጉ አካላት እንዲሁም ለአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ ባደረጉት ንግግር በሀገራችን ያለው የስፖርት እንቅስቃሴ እየተቀዛቀዘ መምጣቱን ተከትሎ መሰል ውድድሮች መዘጋጀታቸው ለስፖርቱ መነቃቃት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገልፀዋል። አዲስ አበባ ፖሊስ ስፖርትን የሪፎርሙ አካል በማድረግ እያከናወነ የሚገኘው ተግባር የሚደነቅ መሆኑን የገለፁት አቶ ዳዊት ትርፉ ውድድሩ በየዓመቱ እንዲካሄድና በቀጣይ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚደረገው የፖሊስ ስፖርት ውድድር ላይ አዲስ አበባ ፖሊስ ውጤታማ እንዲሆን የከተማው ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ድጋፍ አጠናቅሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የልዩ ፅ/ቤት እና ስታፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ምክትል ኮሚሽነር አህመዲን ጀማል በበኩላቸው፣ ውድድሩ በታቀደው መልኩ ስፖርታዊ ጨዋነትንና ፖሊሳዊ ዲሲፕሊንን በጠበቀ ሁኔታ መካሄዱን ገልፀዋል።

በስድስት የስፖርት ዓይነት ውድድሩ መደረጉን የጠቀሱት ኃላፊው፣ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ለስኬታማነቱ ከፍተኛ ድጋፍ ማድረጉን ገልፀው ይህም ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

ለሁለት ሳምንት ተካሃዶ በተጠናቀቀው በዘንድሮው የአዲስ አበባ ፖሊስ ከተማ አቀፍ ስፖርት እና ፌስቲቫል ውድድር፣ በአጠቃላይ ውጤት በጠረጴዛ ቴኒስ በቡድን ማዕከል፣ በነጠላ አቃቂ አሸናፊ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆኑ፣ በቮሊቦል ወንዶች የአዲስ አበባ ፖሊስ የማዕከል ስፖርት ቡድን፣ በሴቶች አራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባለድል መሆን ችሏል።

ከፍተኛ ውድድር በተደረገበት የአትሌቲክስ ስፖርት በወንዶች በአጠቃላይ ውጤት የአዲስ አበባ የማዕከል ስፖርት ቡድን የበላይነትን ሲይዝ በሴቶች ኮልፌ ቀራኒዮ የዋንጫ ተሸላሚ ለመሆን በቅቷል። በገመድ ጉተታ በወንዶች ጉለሌ እንዲሁም በሴቶች አቃቂ የዋንጫ ባለቤት ሆነዋል። በእግር ኳስ ጨዋታ በመዝጊያው ዕለት ማዕከል ከየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ተጫውተው ማዕከል ሶስት ለዜሮ በማሸነፍ የዋንጫውን ማንሳት ችሏል። አራዳ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። ማዕከልን ጨምሮ አስራ አንድ ክፍለ ከተሞች በተሳተፉበት በዚህ ስፖርታዊ መድረክ በሁሉም ውድድሮች አጠቃላይ ውጤት ማዕከል በበላይነት ሲያጠናቅቅ፣ ልደታ ሁለተኛ እንዲሁም አራዳ ሶስተኛ በመሆን የዘንድሮውን ፍክክር በስኬት አጠናቀዋል። ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በስፖርታዊ ጨዋነት ሽልማት ተበርክቶለታል።
*
ሳጅን ኤርሚያስ ዘውዴ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የታላቁ ህዳሴ ግድብን የሠላም ዋንጫ ተረከበ።
***
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አመራር እና አባላትም ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የገቢ ማሰባሰቢያ የሠላም ዋንጫን ጥር 24 ቀን 2017 ዓ/ም ከአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ተረክበዋል።

ርክክቡ የተካሄደው የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ደመና ተስፋዬ፣ የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ በየደረጃው ያሉ አመራርና አባላት በተገኙበት ነው።

በርክክቡ ስነ ስርዓት ላይ ንግግር ያደረጉት የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር ደመና ተስፋዬ ባስተላለፉት መልዕክት ፖሊስ ከመደበኛ ተልዕኮው ባሻገር በሀገራዊ የልማት ስራዎች የራሱን አሻራ እያሳረፈ መሆኑን ተናግረዋል። "ለህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ በጉልበቴ፣ በገንዘቤ እና በእውቀቴ የበኩሌን ድርሻ እወጣለሁ" በሚል መሪ ቃል ዋንጫውን ተረክበን የገቢ ማሰባሰብ ስራውን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

በዋንጫው የርክክብ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አመራር እና አባላት ለአዲስ ፖሊስ እንደ ገለጹት ታላቁ የህዳሴ ግድብ ከተጀመረ ጀምሮ ቦንድ በመግዛት እና ድጋፍ በማድረግ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን አስታውሰው የህዳሴ ግድቡ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
*
ረ/ሳጅን ዓለም ልጅዓለም 

ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀሙን ግምገማ አጠናቀቀ። ከግምገማው ማጠቃለያ በኋላ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተሰሩ የሪፎርም እና የልማት ስራዎችም ተጎብኝተዋል።
****
ጥር 21 እና 22 ቀን 2017 ዓ/ም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት በ6 ወራት የተከናወኑ ተግባራቱን ገምግሟል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፣ ምክትል ኮሚሽነሮች የክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዦች፣ የሁሉም ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊዎች በተገኙበት በተካሄደው ግምገማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎች ባለፉት 6 ወራት ያከናወኗቸውን ተግባራት በሪፖርት አቅርበዋል ።

በ2017 ዓ/ም የ6 ወራት የሥራ እንቅስቃሴ በማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት፣ በወንጀል መከላከል፣ በወንጀል ምርመራ እና በሰው ተኮር የልማት ስራዎች ስኬታማ ተግባራት እንደተከናወኑ በቀረበው ሪፖርት ላይ ተመላክቷል።

ባለፉት 6 ወራት በከተማችን አዲስ አበባ የተከበሩ ኃይማኖታዊ እና ሌሎች የአደባባይ ኩነቶች በድምቀትና በሠላም ተከብረው እንዲያልፉ ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀትና በመናበብ ውጤታማ ስራ እንደተሰራ በመድረኩ ተገልጿል ።

ህብረተሰቡን በማሳተፍ፣ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እና ስራዎችን በቴክኖሎጂ በመታገዝ በተከናወነ የወንጀል መከላከል ስራ ከባድ ወንጀሎችን በ42 ፐርሰንት መቀነስ እንደተቻለ በቀረበው ሪፖርት ላይ ተገልጿል ።

በከተማችን አዲስ አበባ በድብቅና በረቀቀ ዘዴ የተፈፀሙ የሰው መግደል ወንጀሎችን፣ የተሽከርካሪ ስርቆት እና በሌሎች ከባድ ወንጀሎች ላይ ልዩ የወንጀል ምርመራ ጥበብን በመጠቀም እንዲሁም ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ሌት ተቀን በተሠራ የምርመራና የክትትል ሥራ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።

በአንጻሩ ባለፉት 6 ወራት የመንገድ ላይ ትራፊክ አደጋ በሞት፣ በከባድ እና በቀላል የአካል ጉዳቶች አደጋው መጨመሩን በግምገማው ላይ በቀረበው ሪፖርት ላይ ተመላክቷል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በግምገማው ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት ከተከናወኑ ስኬታማ ሥራዎች ጎን ለጎን በቀጣይ የመልካም አስተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመቅረፍ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም ያልተሻገርናቸውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በማስተካከል ተገልጋዩን ማርካት በቀጣይ ስድስት ወራት በዋነኛነት የሚተገበር ጉዳይ መሆኑን ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው አሳስበዋል፡፡ በከተማች የሚፈጸሙ የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል ህብረተሰቡን በማሳተፍ በትኩረት መስራት እንደሚገባ በመግለጽ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

ተሳታፊ ከነበሩ አመራሮች ውስጥ የልዩ ጽ/ቤት ስታፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ም/ኮሚሽነር አህመዲን ጀማልን አነጋግረን በሰጡን ምላሽ የከተማውን ሠላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እንዲያስችል የስጋት ቦታዎችን በጥናት በመለየት፣ ስምሪት በመስጠት፣ ከህብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎችን መነሻ በማድረግ በተሰሩ የኦፕሬሽን ስራዎች በርካታ ለውጦች መገኘታቸውን ገልጸው ግምገማው አንዱ ክፍለ ከተማ ከሌላው ተሞክሮ የሚለዋወጡበት ነው ብለዋል።

የቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር አድማሱ ኢፋ በበኩላቸው በቴክኖሎጅ የታገዘ የወንጀል መከላከል ስራ በመስራታቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ ወንጀል እየቀነሰ መምጣቱን ጠቁመው ህብረተሰቡን ከወንጀል ስጋት ነፃ ለማድረግ የጀመርናቸውን ጥረቶች አጠንክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

ከስራ አፈጻፀም ግምገማው በኃላ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ስር የህብረተሰቡን አቅም በመጠቀም የተሠሩ የሪፎርም ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ከለውጡ አመታት ወዲህ በርካታ የልማትና የሪፎርም ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በተለያዩ ክ/ከተሞች የቴክኖሎጂ ውጤቶችን የስራ ቦታዎችን ምቹ ማድረግና የአባላት የመኖሪያ ካምፖችን ማሻሻል የተከናወኑ ከሪፎርሙ ስራዎች መካከል የሚጠቀሱ ሥራዎች ናቸው፡፡ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ /ከተማም በሪፎርሙ የተከናወኑ ልዩ ልዩ ስራዎችንና አዳዲስ ፖሊስ ጣቢያዎችን በመገንባት ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል።

የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ሽመልስ ሽፈራው ከጉብኝቱ በኃላ ለከፍተኛ አመራሮች ባደረጉት ገለጻ በግንባታ ላይ የነበሩ አዳዲስ ፖሊስ ጣቢያዎች ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት የሆኑ ሲሆን የፖሊስ መምሪያውም ህንፃ በቅርቡ ተመርቆ ሥራ እንደሚጀምር ገልፀዋል ።

የህብረተሰቡን አቅም በመጠቀም ከዚህ በፊትም ለአገልግሎት አሰጣጥም ምቹ ያልነበሩ ፖሊስ ጣቢያዎችን በማደስ እና በአዲስ በመገንባት የተሻለ የስራ ቦታን መፍጠር እንደተቻለ የገለጹት ምክትል ኮሚሽነር ሽመልስ ሽፈራው ለፖሊስ ጣቢያዎች ግንባታ በገንዘብ፣ በጉልበት እና በሀሣብ አስተዋጽኦ ያደረጉ ግለሰቦችና ተቋማትን አመስግነዋል።
*
ዘገባ፦ ዓለም ልጅዓለም
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

ጠፍተው የተገኙ ሁለት ህፃናት ቤተሰቦቻቸው እየተፈለጉ ነው  
***
ናፍሌት ንጉሱ  እና ሮዛ ዋበላ የተባሉት ሁለት ህፃናት ጥር 21 ቀን 2017 ዓ/ም ጠፍተው በአራዳ ክፍለ ከተማ  ፒያሳ አካባቢ የተገኙ እና  በህብረተሰቡ ትብብር ወደ ፖሊስ የመጡ ናቸው፡፡

የህፃናቱን ቤተሰቦች እያፈላለገ መሆኑን በመግለፅ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች እንዲገኙ ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የጠየቀው የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ፤ ቤተሰቦቻቸው ወደ ፖሊስ መምሪያው በአካል ቀርበው በማነጋገር  ህፃናቱን መረከብ እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡
*
ዘገባ፦ ኢንስፔክተር ተዘራ አብሽር

ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

የአዲስ አበባ ፖሊስ ከተማ አቀፍ ስፖርት እና ፌስቲቫል ውድድር በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።
***
ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለላቀ ፖሊሳዊ አገልግሎት በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ ፖሊስ ከተማ አቀፍ ፌስቲቫልና የስፖርት ውድድር ጥር 17 /2017 ዓ/ም በተለያዩ የስፖርት ዓይነትች መጀመሩ ይታወሳል። 5ኛ ቀኑን በያዘው በዚህ መርሀ ግብር እግር ኳስ፣ ገመድ ጉተታ፣ ጠረጴዛ ቴኒስ፣ ቮሊቮል የመሳሰሉ ስፖርቶች ከፍተኛ ፉክክር እየተደረገባቸው ይገኛል።

ነገ ጥር 22/2017 ዓ/ም የስፖርት ውድድሮቹ የሚቀጥሉ ሲሆን የምድብ እግር ኳስ ጨዋታም ይደረጋል። በምድብ "ሀ" የተመደቡት የካ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እንዲሁም አራዳ ከልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የሚገናኙ ሲሆን ሁለቱም ጨዋታዎች ልደታ ቢሪሞ ሜዳ ይካሄዳሉ።

በምድብ "ለ" የሚገኙት አዲስ ከተማ ከጉለሌ ክፍለ ከተማ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ (ማዕከል) ከኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ሳር ቤት በሚገኘው ተስፋ ሜዳ የሚጫወቱ ሲሆን በምድብ "ሐ" የተደለደሉት ለሚ ኩራ ከቦሌ ክፍለ ከተማ ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በቦሌ ቡልቡላ ሜዳ የሚጫወቱ ይሆናል።

የመጀመሪያው ጨዋታ ጠዋት 3:00 ሠዓት ሲጀምር ሁለተኛ ጨዋታ ደግሞ 5:00 ሠዓት ጀምሮ የሚካሄድ ይሆናል። በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ነገ ጥር 22 ቀን 2017 ዓ/ም ጠዋት 2:00 ሰዓት ላይ የአትሌቲክስ ስፖርት ውድድር ይጀምራል። ሌላው ተጠባቂው ውድድር በአዲስ አበባ ፖሊስ (ማዕከል) እና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ መካከል በጃል ሜዳ ጠዋት 3:00 ሰዓት የሚደረገው የቮሊቦል ጨዋታ ነው።

የመክፈቻው ዕለት በተደረጉ ውድድሮች በሴቶች ገመድ ጉተታ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የአዲስ አበባ ፖሊስ (ማዕከል)ን ያሸነፈ ሲሆን በእግር ኳስ የካ ከ አራዳ ክፍለ ከተማ ተጫውተው አንድ አቻ ተለያይተዋል። በሌሎች ውድድሮች በጠረጴዛ ቴኒስ ማዕከል አራዳን እንዲሁም ልደታ ክፍለ ከተማ አራዳን በተመሳሳይ 3 ለ 1 ያሸነፉ ሲሆን ከፍተኛ ፉክክር ከታየባቸው ጨዋታዎች መካከል አዲስ ከተማ ኮልፌን፣ ልደታ ቂርቆስን፣ ቦሌ ጉለሌ ክፍለ ከተማን በተመሳሳይ 3 ለ 2 ያሸነፉበት ይጠቀሳል።

በእግር ኳስ ማዕከል ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያን 7ለ 2 ያሸነፈበት ውጤት በውድድሩ በርካታ ጎል የተቆጠረበት ጨዋታ ሆኖም ተመዝግቧል። በገመድ ጉተታ ውድድር በወንዶች ጉለሌ እና ልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎች ምድባቸውን እየመሩ ሲሆን በሴቶች ደግሞ አቃቂና ጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያዎች በየምድቦቻቸው መሪ መሆን ችለዋል።

ውድድሩ በከፍተኛ ፉክክር መካሄዱን የሚቀጥል ሲሆን የስፖርት ቤተሰቡም ወደ ውድድር ቦታዎቹ በመሄድ ጨዋታዎቹን እንዲከታተል የውድድሮቹ አዘጋጅ ኮሚቴዎች ጋብዘዋል።
*
ዘገባ፦ ሳጅን ኤርሚያስ ዘውዴ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት የሥራ አፈፃፀሙን እየገመገመ ነው።
***
የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ በ2017 በጀት ዓመት በ6 ወራት የተከናወኑ ስራዎችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፣ ምክትል ኮሚሽነሮች የክፍለ ከተማ መምሪያ አዛዦች፣ የሁሉም ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊዎች በተገኙበት ተግባሩ እየተገመገመ ይገኛል።

በስራ አፈጻፀም ግምገማው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው  በከተማዋን ባለፈው ስድስት ወራት የተከበሩ ኃይማኖታዊ በዓላት እና የአደባባይ ኩነቶች በሠላም ተከብረው እንዲያልፉ ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።

የአዲስ አበባን ሠላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ ባለፈው ስድስት ወራት በተከናወኑ ስራዎች ላይ የነበሩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ብለዋል።

በአስራ አንዱም የክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባለፈው ስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርቶች ቀርበውም የሚገመገሙ ይሆናል።
*
ዘገባ፦ ረ/ሳጅን ዓለም ልጅዓለም

ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

በተለያዩ ቦታዎች በመንቀሳቀስና የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መስለው በተለምዶው "ሿሿ" የተባለውን ወንጀል ፈፅመዋል የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ።
***
ተጠርጣሪዎቹ ብዛታቸው 4 ሲሆን የወንጀል ድርጊቱን ፈፅመዋል ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 አካባቢ ነው።

የግል ተበዳይ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቄራ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ሄደው የጤና ምርመራ ለማድረግ ዘነበወርቅ አደባባይ ትራንስፖርት እየጠበቁ ነበር።

ግለሰቦቹም በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 B-13788 አ.አ በሆነ የቤት መኪና የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መስለውና የግል ተበዳይን ተሽከርካሪው ውስጥ ካስገቧቸው በኃላ ቄራ ድረስ ከምትሄጂ እዚሁ ቅርብ ቦታ የጤና ምርመራ ማድረግ ትችያለሽ፤ እናሳይሻለን በማለት በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ታቦት ማደሪያ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ሲደርሱ ቅያስ ውስጥ በማስገባት በእጅ ቦርሳ ውስጥ የነበረ 7900 ጥሬ ገንዘብ ይዘው ለመሰወር ሙከራ ሲያደርጉ በአየር ጤና አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ግለሰቦቹ ወንጀሉን ፈፅመው በተሽከርካሪ ለማምለጥ በሚሞክሩበት ሰዓትም አንድ ግለሰብ ላይ አደጋ ማድረሳቸውን መረጃው ይጠቁማል።

ከተያዙት 4 ተጠርጣሪዎች ውስጥ አንዷ ሴት ስትሆን አስፈላጊው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የገለፀው ፖሊስ መምሪያው ግለሰቦቹ ከዚህ በፊትም በተመሳሳይ ወንጀል በጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ፓስተር አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደነበርና ደጋጋሚ ወንጀል ፈፃሚዎች መሆናቸውን ጅምር የምርመራ መዝገቡ ያመለክታል።

የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ መስለውና የተለያዩ ማታለያ ዘዴዎችን በመጠቀም ወንጀሎችን የሚፈፅሙ ግለሰቦችን በህግ ለማስቀጣት ህብረተሰቡ የራሱን ጥንቃቄ ከማድረግ ጀምሮ ጥቆማ በመስጠት የተለመደውን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪውን እያስተላለፈ ተመሳሳይ ወንጀል የተፈፀመበት ካለ ኮልፌ በቀራኒዮ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ በመቅረብ ተጨማሪ መረጃ በመስጠትና ተጠርጣሪዎቹን በመለየት ተባባሪ እንዲሆን ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል ።
*
ዘገባ ፦ ዋና ሳጅን ዘላለም አበበ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

ጠፍታ የተገኘች የ10 ዓመት ዕድሜ ያላትን ህፃን ቤተሰቦች እያፈላለገ መሆኑን የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡  
***
ኢክረም ባዴ የተባለች በግምት የ10 ዓመት ዕድሜ ያላት  ህፃን ጥር 12 ቀን 2017 ዓ/ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ልዩ ቦታው ገዳም ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መገኘቷን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ለክፍላችን በፃፈው ደብዳቤ ጠቅሷል፡፡

ህፃኗ የመኖሪያ አድራሻዋን እንደማታውቅ እና በአሁኑ ሰዓት በህጻናት ማቆያ ተቋም ውስጥ እንደምትገኝ የገለፀው ፖሊስ መምሪያው፤ የህፃኗ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች አራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል ቀርበው በማነጋገር  ህፃኗን መረከብ እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡
*
ዘገባ፦ ኢንስፔክተር ተዘራ አብሽር

ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

ከ2300 ሊትር በላይ በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸ ቤንዚን መያዙን የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ።
***
የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ስሙ ሰንጋ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። መንግስት የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለቱ በህጋዊ መንገድ እንዲደረግና ግብይቱም በቴሌ ብር ብቻ እንዲሆን ከማድረግ ጀምሮ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

ይሁንና አንዳንድ ግለሰቦች የግል ጥቅማቸውን ብቻ ታሳቢ በማድረግ በህገ-ወጥ መንገድ ግብይት በመፈፀም ህጋዊ የግብይት ሰንሰለቱን ወደ ጎን በመተው የሀገር ሀብት የሆነውን ነዳጅ በማሸሽ በውድ ዋጋ ለመሸጥ ሲታትሩ ይስተዋላል፤ ይህንን ችግር ለመፍታት ፖሊስ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ሲሆን የዚሁ ስራ አካል የሆነው የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ ባደረገው ብርቱ ክትትል በህገ-ወጥ መንገድ በአንድ ኮንቴነር ውስጥ በጀሪካን ተሸሽጎ የነበረ 2360 ሊትር ቤንዚል ከሁለት ግለሰቦች ጋር በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ግለሰቦቹ መንግስት ያወጣውን የነዳጅ መመሪያ በመተላለፍ የሀገር ሀብት የሆነውን ነዳጅ በህገ-ወጥ መንገድ ሊሸጡ ሲሉ መያዛቸውን የፖሊስ የምርመራ መዝገብ ያስረዳል።

ህብረተሰቡ በመሰል የወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ ግለሰቦችን ሲመለከት ለፖሊስ ጥቆማ እንዲሰጥም የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።
*
ዘገባ፦ ረዳት ሳጅን ፍፁም በቀለ    
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”