Latest Posts from Addis Ababa Police Official (@addispolice) on Telegram

Addis Ababa Police Official Telegram Posts

Addis Ababa Police Official
Addis police
12,731 Subscribers
2,568 Photos
3 Videos
Last Updated 01.03.2025 06:25

The latest content shared by Addis Ababa Police Official on Telegram


የአዲስ አበባ ፖሊስ ከተማ አቀፍ የፖሊስ ውድድርና ፌስቲቫል መክፈቻ "ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለላቀ ፖሊሳዊ አገልግሎት" በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሄደ።
***
ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለላቀ ፖሊሳዊ አገልግሎት በሚል መሪ ቃል የከተማ አቀፍ የአዲስ አበባ ፖሊስ ስፖርት ፌስቲቫልና ውድድር መክፈቻ ስነ-ሥርዓት ጥር 17 ቀን 2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ ስታዲየም በይፋ ተከፍቷል ።

ክቡር አቶ ሞገስ ባልቻ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ኃላፊ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የስፖርት ቢሮ በየደረጃ የሚገኙ አመራርና አባላት፣ የሠላም ሰራዊትና የደንብ ማስከበር አባላት እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በስፖርት ፌስቲቫሉ የመክፈቻ መርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተካሄደው የመክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የተገኙት የዕለቱ የክብር እንግዳ ክቡር አቶ ሞገስ ባልቻ ባደረጉት ንግግር አዲስ አበባ የተለያዩ ዓለም አቀፍና አህጉራዊ ኮንፈረንሶች የሚካሄዱባት ከተማ በመሆኗ የሠላምና ደህንነት ተምሳሌት እንድትሆን ፖሊስ ከነዋሪውና ከሌሎች የፀጥታ አካላት በጋራ ባከናወነው ተግባር ሠላምን ማረጋገጥ ተችሏል ሲሉ ተናግረዋል።

ፖሊስ በሀገራችን የስፖርት እንቅስቃሴ ታሪክ ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከተና በተለያዩ ስፖርት ዘርፎች ሀገርን ያስጠሩ ስፖርተኞች የተገኙበት ተቋም መሆኑንም ገልፀዋል። በተጨማሪም ፌስቲቫሉ ፖሊስ በስፖርት የዳበረ አካላዊ ብቃትን ተላብሶ ተልዕኮውን በላቀ ሁኔታ እንዲወጣ ያግዘዋል ሲሉ አቶ ሞገስ ባልቻ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ በላይ ደጀን በበኩላቸው ስፖርትና ፖሊስ የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ መሆናቸውን ገልፀው ፖሊስ በሀገራችን የስፖርት እድገት ውስጥ ጉልህ ሚና እንዳለው እና በዓለም አቀፍ መድረክ የሀገራችንን ክብር ከፍ ያደረጉ ስፖርተኞች የተገኘበት ተቋም መሆኑን ጠቅሰዋል።

አቶ በላይ ደጀን አያይዘው ፣ መሰል ውድድር የአባላትን ጓዳዊ ትስስር የሚያሳድግ በመሆኑ ለወደፊቱ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ለሚያከናውነው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የከተማው ስፖርት ቢሮ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አቶ በላይ ደጀን ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው፣ ባደረጉት ንግግር ለፖሊሳዊ ተልዕኮ ስኬት ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ወሳኝ መሆኑን የተረዳው ፖሊስ የሚያበረታታ መነቃቃት ላይ እንደሚገኝ ገልፀው ስፖርት የፖሊስ አባላት ህብረተሰቡን በብቃት እንዲያገለግሉ የሚያበረክተው አስተዋፅኦ ቀላል የሚባል አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

አዲስ አበባ ፖሊስ በስፖርቱ ዘርፍ በሀገር አቀፍና በዓለማቀፍ መድረክ ተሳታፊ የሆኑ ስፖርተኞችን ከማስመረጥ ባለፈ የበርካታ ሜዳሊያዎችና ዋንጫዎች ባለቤት በመሆን ውጤታማ ነው ያሉት ኮሚሽነር ጌቱ ውጤታማነቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው ከስፖርት ፌስቲቫልና ወድድሩ ጠንካራ፣ አሸናፊና ተተኪ ስፖርተኞችን ማፍራት በቀጣይ የሚጠበቅ ነው ብለዋል። አያይዘውም ለዚህ ውድድር መሳካት አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት በሙሉ ኮሚሽነሩ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ የኮሚሽን ፅ/ቤት ኃላፊና የስታፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ምክትል ኮሚሽነር አህመዲን ጀማል የዕለቱን መርሀ-ግብር ካስተዋወቁ በኃላ " ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለላቀ ፖሊሳዊ አገልግሎት " በሚል መሪ ቃል መካሄድ የጀመረው የአዲስ አበባ ፖሊስ ከተማ አቀፍ የስፖርት ፌስቲቫልና ውድድር በቀጣይ ቀናት በእግር ኳስ፣ በአትሌቲክስ፣ በገመድ ጉተታ፣ በጠረጴዛ ቴኒስ፣ በዳርትና በሌሎች የስፖርት ዓይነቶች በጠንካራ ፉክክር እንደሚቀጥል ገልፀው በቀጣይም ለ19ኛው ሀገር አቀፍ የመላው ፖሊስ ስፖርት ውድድር ከተማ አስተዳደሩን በሁሉም የስፖርት መስኮች የሚወክሉ ስፖርተኞች የሚመረጡበት እንደሚሆንም አክለው ገልፀዋል።
*
ዘገባ፦ ሳጅን ኤርሚያስ ዘውዴ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለ340 የፖሊስ እና ሌሎች የጸጥታ አካላት የመኖሪያ ቤት አስተላለፉ
***
የአዲስ አበባ ከተማ ክብርት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለ340 የፖሊስ እና ሌሎች የጸጥታ አካላት የመኖሪያ ቤት ማስተላለፋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስታውቀዋል፡፡

2ኛውን ዙር የኮሪደር ልማት ለመተግበር የፖሊሶችን ካምፕ ስንጎበኝ የሰራዊቱ አባላት ካምፕ ውስጥ ከቤተሰቦቻቸው እና ከልጆቻቸው ጋር እጅግ በማይመች ሁኔታ ውስጥ እየኖሩ መሆኑን በመረዳት ለነዋሪዎች እንዳደረግነዉ ሁሉ ለ340 ቤተሰብ ላላቸው የጸጥታ አካላት የመኖሪያ ቤቶችን አስተላልፈናልም ብለዋል ።

ፖሊስ ቅድሚያ ለህዝብ በማለት ለሀገር ደህንነት ዋጋ እየከፈለ የሚያገለግል እንደመሆኑ መጠን በቀጣይም ለሰራዊቱ ምቹ የኑሮ ሁኔታ እንዲኖረዉ ከተቋሞቻቸዉ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር የምንሰራ ይሆናል ብለዋል ከንቲባዋ በመልእክታቸው::

አዲስ አበባን ውብ እና ጽዱ እንዲሁም ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እየተሰራ ባለው ስራ ቅድሚያ የነዋሪውን ህይወት ለማሻሻል ትኩረት ተሰጥቶ መሠራቱን የተናገሩት ከንቲባ አዳነች በተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ካምፖች ሲኖሩ የነበሩ የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት የተሻለ ኑሮ መኖር እንዲችሉ ቤቶች እንዲሰጣቸው መደረጉን ተናግረዋል።

የመኖሪያ ቤቶቹን ለጸጥታ አካላት ባስተላለፉበት ወቅት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ጄነራል መላኩ ፋንታ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንዲሁም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ተገኝተዋል።

ከርክክቡ በኋላም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው ባደረጉት ንግግር የከተማ አስተዳደሩ በየጊዜው ለጸጥታ አካሉ እያደረገ የሚገኘው ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን አስታውቀው መሠል ድጋፎች በተለይም ለጸጥታ አካሉ የተልዕኮ ስኬት አጋዥ እንደሚሆን ጠቁመዋል።

አያይዘውም በዛሬው ዕለት የከተማ አስተዳደሩ ባደረገው ድጋፍ የተሠማቸውን ደስታ በመግለጽ ክብርት ከንቲባንና ካቢኔያቸውን በአዲስ አበባ ፖሊስ እና በራሳቸው ስም ምስጋና አቅርበዋል።

ምቹ ካልሆኑ ካምፖች እንዲነሱ የተደረጉት ከእነዚህ የፖሊስ አባላት ውስጥ ቤተሰብ የመሠረቱት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው የቤት ተጠቃሚ መደረጋቸውም ተገልጿል።   
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

በሙያ ስነ ምግባርና በአገልጋይነት ስሜት ህዝብን ማገልገል ታላቅ ክብር ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ። የአዲስ አበባ ፖሊስ በመደበኛ ፖሊስነት ለ29ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን የፖሊስ አባላት አስመርቋል።
***
ጥር 3 ቀን 2017 ዓ/ም ኮልፌ በሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ አካዳሚ የምረቃ መርሀ ግብሩ የተካሄደ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፤ ባደረጉት ንግግር የአዲስ አበባ ፖሊስ አገልግሎት አሰጣጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዘመነ መምጣቱን ገልፀው በተለይም ከለውጡ ወዲህ ተቋሙ በሰው ኃይል እንዲያድግና በቴክኖሎጂ ተግባራት እንዲዘምን ተደርጓል ሲሉ ተናግረዋል።

በየጊዜው እየተወሳሰበ የመጣውን የወንጀል ድርጊት ለመከላከል በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኝ የጠቆሙት ክብርት ከንቲባዋ ከለውጡ ወዲህ የፖሊስ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ የፖሊስ ጣቢያዎችን ቁጥር መጨመርና መምሪያዎችን የማስፋፋት ስራ ተሰርቷል ሲሉም ገልፀዋል። ከንቲባዋ አክለውም የአዲስ አበባ ፖሊስ የከተማችንን ሠላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ ከፀጥታ አካላትና ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ተልዕኮውን እየተወጣ እንደሚገኝ አስታውቀው የዛሬ ተመራቂ ፖሊሶችም ከህዝብ የወጣችሁ የህዝብ ልጆች እንደመሆናችሁ መጠን በስነ ምግባር፣ በክህሎት፣ በአገልጋይነት መንፈስ ህዝብን ማገልገል ከተልዕኮ በላይ ታላቅ ክብር በመሆኑ በስልጠና ያገኛችሁትን ዕውቀት በተግባር መተርጎም ይጠበቅበችኋል ብለዋል። አይይዘውም የአዲስ አበባ ፖሊስ አካዳሚን ወደ ኮሌጅ ደረጃ ለማሳደግ እየተከናወነ የሚገኘው ተግባር የሚበረታታ መሆኑን የገለፁት ክብርት ከንቲባዋ ለተቋሙ የተልዕኮ ስኬት ከተማ አስተዳደሩ በማንኛውም መልኩ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው በበኩላቸው የአዲስ አበባ ፖሊስ አካዳሚ ከለውጡ ወዲህ ለ9ኛ ጊዜ ምልምል ፖሊሶችን አሰልጥኖ ማስመረቁን ገልፀው ከተማችን አዲስ አበባ ስሟን በሚመጥን መልኩ እየዘመነችና እያደገች እንደመሆኗ መጠን እየተከናወነ የሚገኘው የልማት ስራ ውጤታማ እንዲሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ የፀጥታ ስራውን በላቀ ደረጃ እያከናወነ እንደሚገኝ ጠቁመው በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት ከባድ ወንጀልን መቀነስ እንደተቻለ አብራርተዋል።

በአዲስ አበባ ፖሊስ እየተከናወኑ ከሚገኙ የሪፎርም ስራዎች መካከል ጥራት ያለው የሰው ኃይል ማፍራት፣ የሎጀስቲክ አቅምን ማሳደግና ዘመኑን የዋጀ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መጠቀም በዋናነት እንደሚጠቀሱ ኮሚሽነር ጌቱ ጠቁመው፤ አዲስ አበባ ሦስተኛዋ የዲፕሎማት ከተማ፣ የበርካታ አለም ዓቀፍ ተቋማት መገኛ እና ልዩ ልዩ ኃይማኖታዊና ህዝባዊ የአደባባይ በዓላት የሚከበሩባት ከተማ እንደመሆኗ መጠን ይህን የሚመጥን የፖሊስ ኃይል ገንብተናል ሲሉ ኮሚሽነር ጌቱ ተናግረዋል።

የፖሊስን አገልግሎት ሁሉም በእኩልነት የሚፈልጉት ሙያ በመሆኑ የዛሬ ተመራቂዎች ይህን ለማሳካት ጠንክራችሁ ልትሰሩ ይገባልም ብለዋል። አዲስ አበባ ከተማን ሠላሟ የተረጋገጠ ለማድረግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዘመኑ የሚዋጀውን ቴክኖሎጂ ከመጠቀም ባሻገር በሰው ኃይል ተደራሽ በመሆን በሙያ የአገልግሎት ጥራትን በማረጋገጥ የበቃ ፖሊስ ለማፍራት ሌት ተቀን እየሰራ እንደሚገኝ የገለፁት የአዲስ አበባ ፖሊስ አካዳሚ ዳይሬክተር ም/ኮሚሽነር ተከታይ ያዜ ለ29ኛ ዙር ሲሰለጥኑ የነበሩ 536 ወንድ እና 238 ሴት በድምሩ 874 ምልምል የፖሊስ አባላትን ማስመረቅ እንደተቻለ ገልፀዋል። የሰልጠና አካዳሚውን ወደ ኮሌጅ ለመቀየር በርካታ ተግባራት እንደተከናወነ የገለፁት ም/ኮሚሽነር ተከታይ ያዜ የተቀላጠፈ እና ተደራሽ የሆነ ፖሊሳዊ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል ብቃት ያለው የፖሊስ አባላት ከማፍራት አንፃር አካዳሚው እያከናወነ ያለውን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
ያነጋገርናቸዉ አሰልጣኝና ተመራቂዎች በበኩላቸው የተሰጣቸውን የአካል ብቃትና ፖሊሳዊ ትምህርቶችን ወደ ተግባር በመቀየር የተሰጣቸውን ኃላፊነት በመልካም ስነ ምግባር ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።
*
ዘገባ፦ ሳጅን ኤርሚያስ ዘውዴ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥር 3 ቀን 2017 ዓ.ም ለ29ኛ ዙር ያሰለጠናቸውን መደበኛ የፖሊስ አባላትን እያስመረቀ ይገኛል።
***
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ክብርት አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እንዲሁም በየደረጃው የሚገኙ የአዲስ አበባ ፖሊስ የስራ ኃላፊዎች በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል፡፡
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

የተሰረቁ ስልኮችን እንደሚገዛ የተጠረጠረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ ።
***
ከህብረተሰቡ በመጣ ጥቆማ ህጋዊ የንግድ ፈቃድን ሽፋን በማድረግ የተሰረቁ ሞባይል ስልኮችን ይገዛል በሚል የተጠረጠረውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር በማዋል ተገቢውን ምርመራ እያጣራ መሆኑን የጉለሌ ክ/ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል ።

ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 9:00 ሠዓት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አስኮ ገብርኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ፖሊስ ከህብረተሰቡ የደረሰውን ጥቆማ መነሻ በማድረግና ተገቢውን የፍርድ ቤት የመያዣና የብርበራ ትዕዛዝ በማውጣት በተጠርጣሪው ሞባይል ጥገና ሱቅ ውስጥ ባደረገው ብርበራ የተለያየ ሞዴል ያላቸውን 30 ተቀሳቃሽ ስልኮችን እና ሁለት ታብሌቶችን ከነተጠርጣሪው ይዞ ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ ተገልጿል ።

ተመሳሳይ ወንጀል ተፈጽሞብኛል የሚል ካለ አስኮ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ በአካል በመቅረብ የተሠረቀበትን ስልክ መለየትና መረከብ የሚቻል ሆኖ ህብረተሰቡ መሠል የወንጀል ድርጊቶችን ለመከላከል በተለያዩ መንገድ የተሰረቁ ንብረቶችን ባለመግዛት ፖሊስ እየሰራ ያለውን የወንጀል መከላከል ስራ ማገዝ እንደሚኖርበትም የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን ያስተላልፋል።
*
ዘገባ፦ ሳጅን ፈለጉሽ አሻግሬ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

የ2017 ዓ/ም የገና በዓል የፀጥታ ማስከበር ተግባራትን አስመልክቶ ለጥምር የፀጥታ አካላት አመራር የሥራ መመሪያ ተሰጠ።
***
ጥምር የፀጥታ አካላት አመራር የ2017 ዓ/ም የገና በዓል የፀጥታ ማስከበር ተግባራትን አስመልክቶ ታህሳስ 25/2017 ዓ/ም በአዲሰ አበባ ፖሊስ ሠላም አዳራሽ ለአመራሩ የሥራ መመሪያ ተሰጥቷል። በመድረኩ የህግ ማስከበሩን ሥራ በውጤት ለማከናውን የሚያስችል ዕቅድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ውይይቱን የመሩትና መመሪያ የሰጡት የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ም/ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ባስተላለፉት መልዕክት በዓላት ሲከበሩ አሉታዊ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች እንደመልካም አጋጣሚ እንዳይጠቀሙበት ከሚከናወነው መደበኛ የወንጀል መከላከል ስራ ጎን ለጎን የህብረተሰቡን አቅም መጠቀም ፈፅሞ መዘንጋት የሌለበት ሥራ መሆኑን አስታውቀው ቅንጅታዊ የሥምሪት አቅጣጫን በመከተል ጠንካራ የወንጀል መከላከል ተግባር ማከናወን እንደሚገባ አስታውቀዋል። አያይዘውም የፀጥታ አካላቱ ዋና ግብ በህግ የበላይነት ሠላምና ፀጥታን ማረጋገጥ በመሆኑ ሁሉም አመራርና አባል ይህን ተገንዝቦ በዓሉ በሠላም እንዲከበር እንደ ከዚህ ቀደሙ ኃላፊነቱን በብቃት ሊወጣ እንደሚገባ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በበኩላቸው ጥምር የፀጥታ ኃይሉ ተቀናጅቶ በመስራቱ ስኬታማ መሆን እንደተቻለ ተናግረው የከተማችንን ሠላምና ፀጥታ በማረጋገጥ በኩል የድርሻውን እየተወጣ የሚገኘው የሠላም ሠራዊት እንደ ሁልጊዜው ከፀጥታ አካላቱ ጋር ተቀናጅቶ ኃላፊነቱ ለመወጣት ዝግጁ ነው ብለዋል፡፡ በዓሉ በሠላም እንዲከበር ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ለማስቻል ከማህበረሰቡ፣ ከኃይማኖት አባቶች እና የበአሉ ጉዳይ ከሚመለከታቸው አደረጃጀቶች ጋር መድረክ ተዘጋጅቶ ውይይት መደረጉንም ተናግረዋል፡፡

የመረጃ ሥርዓትን በማጠናከር የሥምሪት አቅጣጫን ከበዓሉ አከባበር ሁኔታ አንፃር በማየት የሥምሪት አቅጣጫ መከተል እንደሚገባ ያስገነዘቡት ደግሞ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው የገና በዓልን በተመለከተ ከሚከናወኑት ቅድመ ወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ሥራዎች ባሻገር ለፀጥታ ስጋት የሆኑ ቦታዎችን በጥናት በመለየት ጠንካራ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በእምነት ቦታዎች፣ በገበያ ስፍራዎች፣ በመዝናኛና በትራንስፖርት መጠበቂያ ስፍራዎች እና ሌሎች የህዝብ እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ግርግሩን እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ወንጀል ለመፈፀም የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦችን ለመቆጣጠር በቂ የፀጥታ ኃይል መመደቡን ኮሚሽነሩ ተናግረው የፀጥታ ስራው በቴክኖሎጂ እየታገዘ እንደሚከናወንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በግብይት ወቅት የሚከሰቱ የስርቆት ወንጀሎችን፣ የሀሰተኛ ገንዘብ ኖት ስርጭት እንዲሁም ህገ-ወጥ የዋጋ ንረትን ለመከላከል በሚደረጉ ጥረቶች እና በዓሉ በሠላም እንዲከበር ለማስቻል ህብረተሰቡ የተለመደ ትብብሩን ሊያደርግ እንደሚገባ ኃላፊዎቹ አሳስበዋል፡፡

አልኮል ጠጥተው የሚያሽከረክሩ አሽከርካሪዎችን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ከሚደረገው ቁጥጥር ባሻገር ለመንገድ ትራፊክ አደጋ በሚያጋልጡ ደንብ መተላለፎች ላይ ተገቢው ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራ በውይይቱ ላይ ተገልፆል።

በመጨረሻም በዓሉ የሠላምና የደስታ እንዲሆን መላው የፀጥታ ተቋማት መልካም ምኞታቸውን ገልፀው ህብረተሰቡ ለሠላም እንቅፋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-26-43-59 ፣ 011-5-52-63-02/03፣ 011-5-52-40-77፣ 011-5-54-36-78 እና 011-5-54-36-81 እንዲሁም በ987፣ 991 እና 816 ነፃ የስልክ መስመሮች ጥቆማ በመስጠትና አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፏል።
*

ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

ጤነኛ የሆነን ታዳጊ ህመምተኛ አስመስላ በማጭበርበር ስትለምን የነበረች ግለሰብ በእስራት መቀጣቷን የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
***
በከተማችን በተለያዩ ጊዜያት ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲሉ ሙሉ ጤነኛ ሆነው ሳለ ህመምተኛ በመምሰልና በማስመሰል ህብረተሰቡን ሲያጭበረብሩ የነበሩ ግለሰቦችና ተባባሪዎቻቸው በእስራት መቀጣታቸው ይታወቃል፤ በተመሳሳይም ህዳር 10 ቀን 2017 ዓ/ም በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አካባቢ ተከሳሽ እማዋይ የተባለች ግለሰብ ወንድሜ መናገርም ሆነ መንቀሳቀስ አይችልም በማለት በዊልቸር ላይ አስተኝታ ስትለምንበት በቦታው በነበሩ የደንብ ማስከበር ባለሙያዎች ተይዛ ለፖሊስ ተላልፋ ተሰጥታለች፡፡

የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያም ተጠርጣሪዋን ተረክቦ ተገቢውን ምርመራ የማጣራት ተግባር ሲከውን ቆይቷል፡፡ ፖሊስ በምርመራ መዝገቡ ላይ የግል ተበዳይ የሰባት ዓመት ታዳጊና የተከሳሽ ወንድም ሲሆን ከትውልድ አካባቢው ወደ አዲስ አበባ ትምህርት ላስተምረው በማለት አምጥታ መለመኛ ማድረጓንም ያትታል፡፡

ፖሊስ የተከሳሿን የምርመራ መዝገብ በተገቢው የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማደራጀት ለዐቃቤ ህግ በማቅረቡ የፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 3ኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሿን ያርማል ሌሎችን ከመሰል ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ያስተምራል ሲል በ6 ወር ቀላል እስራት እንድትቀጣ ወስኖባታል፡፡

በተለያዩ ቦታዎች ላይ መሠል የወንጀል ድርጊቶች እንደሚፈፀሙ ያስታወቀው ፖሊስ ህብረተሰቡ አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያይ እንደተለመደው ለፀጥታ አካላት በመጠቆም ተባባሪነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕቱን አስተላልፏል ።

ዘገባ፦ ሳጅን ፈለጉሽ አሻግሬ
*

ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

የፈረንጆች አዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ርችት እንደሚተኮስ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የደህንነትና ልዩ ኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ማስታወቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።
***
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የደህንነትና ልዩ ኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ለአዲስ አበባ ፖሊስ በላከው ደብዳቤ እንዳስታወቀው ዛሬ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ/ም የሚከበረውን የፈረንጆቹን የአዲስ ዓመት ዋዜማ በዓል ምክንያት በማድረግ ከሌሊቱ 6:00 እስከ 6:15 ሰዓት ላይ በሸራተን ሆቴል ርችት ይተኮሳል፡፡

በመሆኑም ህብረተሰቡ ተገቢው መረጃ እንዲኖረው ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
*
ዘገባ፦ ረ/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ   
*  
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

ለ42ኛ ጊዜ የተካሄደው ጆርካ የአዲስ አበባ ጃንሜዳ ሀገር አቋራጭ 1ኛ እና 2ኛ ዲቪዚዮን ውድድር ላይ የተሳተፈው የአዲስ አበባ ፖሊስ አትሌቲክስ ቡድን ውድድሩን በአጥጋቢ ውጤት አጠናቀቀ።
***
ታህሳስ 20 ቀን 2017 ዓ/ም ለ42ኛ ጊዜ የተዘጋጀው ጆርካ አዲስ አበባ  ጃንሜዳ ሀገር አቋራጭ 1ኛ እና 2ኛ ዲቪዚዮን  ሩጫ ወድድር ላይ የተሳተፈው የአዲስ አበባ ፖሊስ አትሌቲክስ ቡድን በተለያዩ ርቀቶች የተወዳደረ ሲሆን በተወዳደረባቸው የተለያዩ ርቀቶች 3ወርቅ፣ 2ብር ፣3ነሀስ ሜዳሊያና በ4ተኛ ደረጃ ሁለት የዲኘሎማ እንዲሁም ሁለት ዋንጫ በ 8ኪ.ሜ ድብልቅ ሪሌ ሁለተኛ ዲቪዚዮን እና በወንዶች በ10ኪ.ሜ  በሁለተኛ ዲቪዚዮን አንደኛ ደረጃ የዋንጫ ተሸላሚ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል።

በ5 የአትሌቲክስ ዘርፍ 49 ተወዳዳሪዎችን ይዞ የቀረበው የአዲስ አበባ ፖሊስ አትሌቲክስ ቡድን ያስገኘው ውጤት ለቀጣይ ውድድሮች ጠንካራና ደካማ ጎናችንን ያየንበት ነው ያሉት የአትሌቲክስ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ረ/ኢ/ር ጥጋቡ አሰፋ ያገኙት ውጤት አመርቂ እንደሆነም ተናግረዋል።

ተወዳዳሪዎች ውድድሩ አስደሳች እንደነበር እና ተቋማቸውን ወክለው ባመጡት ውጤት ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ቀጣይ ከዚህ በበለጠ በመስራትና በተለያዩ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ከዚህ በተሻለ ጠንክሮው በመወዳደር የተቋማቸውን ስም ከፍ ለማድረግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ በተለያዩ የስፖርት ዘርፎች ተተኪና ብቁ ስፖርተኞችን ለሀገር በማፍራት ረገድ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ እና እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን እና ለሌሎች ተቋማት ተምሳሌት እንደሆነም በአዲስ አበባ አትሌትክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ሰብሳቢ የሆኑት አትሌት ኮማንደር አበበ መኮንን ገልፀዋል።
*
ዘገባ፦ ሳጅን ጤናው ፈጠነ
*  
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”

ህፃን ልጅ ጠፍቶብኛል የሚል ግለሰብ አራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ቀርቦ መረከብ ይችላል ተብሏል
***
ዕድሜው በግምት 1 ዓመት ከ6 ወር የሚሆነው ህፃን ታህሳስ 7 ቀን 2017 ዓ/ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው አድዋ ሙዚየም አካባቢ መገኘቱን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ለክፍላችን በፃፈው ደብዳቤ ጠቅሷል፡፡

ህፃኑ በአሁኑ ሰዓት በህጻናት ማሳደጊያ ተቋም ውስጥ እንደሚገኝ የገለፀው ፖሊስ መምሪያው፤ የህፃኑ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች አራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአካል ቀርበው በማነጋገር ህፃኑን መረከብ እንደሚችሉ አስታውቋል፡፡
*
ዘገባ፦ ኢንስፔክተር ተዘራ አብሽር  
*  
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”