来自 قناة أبي عبد الرحمن المرسي (@abu_abdirehman_almersi) 的最新 Telegram 贴文

قناة أبي عبد الرحمن المرسي Telegram 帖子

قناة أبي عبد الرحمن المرسي
https://t.me/Abu_Abdirehman_Almersi
2,900 订阅者
845 张照片
183 个视频
最后更新于 09.03.2025 05:57

قناة أبي عبد الرحمن المرسي 在 Telegram 上分享的最新内容

قناة أبي عبد الرحمن المرسي

22 Feb, 13:16

184

ሀቂቃ በጣም ታሳዝናለች ልብ ይነካል እህታችን አሏህ ጀነተል ፊርዶስ ይወፍቃት ልጆቿን ሷሊህ ልጆች ያግርግላት

ሞት ለማንም አይቀርም ሂወት አጭር ነች ሁላችንም ሟች ነን አላህ መጨረሻችንን ያሳምርልን💦 ከማይሆን ትዳርም አላህ ይጠብቀን 🤲

በሞት ለተለዩን አላህ ጀነትን ይወፍቀቸው🤲
قناة أبي عبد الرحمن المرسي

22 Feb, 13:03

88

🔷 የእህታች መዲና ሞት አሳዛኝ የሚያደርገው ምንድነው ?
ክፍል አንድ

እህታችን መዲና ደምሴ ለሞቷ ሰበብ የሆነው የጡት ካንሰር እንደነበር እናውቃለን ። አላህ በሰው ልጆች ላይ የፃፈው ሞት ቅሮት የለውም ። ሳአቱን ጠብቆ ይመጣል ሰበብን ከሰበቡ ባለቤት ጋር እንዲገናኝ ያደረገው አላህ ለማንኛውም ሰው ሞት ሰበብ አድርጎለታል ። የእህታችንም ከዚህ የተለየ አልነበረም ።
ይሁን እንጂ ከሞት ሰበቦች ውስጥ አንዱ ህመም ነው ። የህመሙ አይነት በጣም ቢለያይም ሰዎች በተለያየ መልኩ ህመምተኛውን ከህመሙ እንዲድን ሰበብ ያደርሳሉ ። በሰበቡ እንዲድን አላህ የፈቀደው ይድናል ። አላህ በሰበቡ እንዲድን ያልፈቀደለትና ያ ህመም ለመሞቱ ሰበብ የሚሆነው በዛው ወደ አኼራ ይሄዳል ። ነገር ግን ሰበብ በማድረሱ ቤተሰብና ዘመድ ሰበብ አድርሰናል የአላህ ውሳኔ ነውና ምንም ማድረግ አንችልም ብሎ ይፅናናል ።
በጣም በሚገርም መልኩ ብዙ ቤተሰቦች ከቤተሰባቸው ሞት ይልቅ ሰበብ ባለማድረሳቸው ሁሌም ፀፀት ሆኖባቸው ይኖራሉ ።
ወደ እህታችን መዲና ስንመለስ በሽታዋ ካንሰር መሆኑ ከታወቀ በኋላ የሚቻለው ሁሉ ሰበብ ለማድረስ ሁሉም ተረባርቧል ። ቅስም የሚሰብረውና ውስጥን የሚያደማው ግን እህታችን የጡቷ ህመም ሲጀምራት ለመታየት ሐኪም ቤት ለመሄድ አቅም ማጣቷ ነው ።
እራሳቸውም ከህይወት ጋር ትግል ውስጥ ካሉት ወንድሞቿ አንዱን ጡቴን እያመመኝ ነው ሐኪም ቤት ለመታየት ትንሽ ሳንቲም ፈልግልኝ ብትለውም ወንድሟ ሊያገኝላት ባለመቻሉ ሳትታይ ትቀራለች ። የጡቷ ህመም ግን ስር እየሰደደ አቅሙን እያዳበረ ነበር ። አደጋው እያወቀችውና እየፈራችውም ግን ለማን ትንገር እህቶቿን ማስቸገር አልፈለገችም ከህመሟ ጋር ግብግብ ቀጥላ ቀናቶች ለሳምንታት ሳምንታት ለወራቶች ቦታ እየለቀቁ ህመሟ ከአቅሟ በላይ ሲሆን ለአንድ እህቷ ትናገራለች ። እህት ደንግጣና ፈርታ ወደ ሀኪም ቤት ይዛት ትሄዳለች ስትመረመር የፈራችው አልቀረም በጣም ዘገያችሁ ወደ ካንሰርነት ተቀይራል ተባሉ ። የዚህን ጊዜ ነበር ጉዳዩ ወደኛ የደረሰው እንደምታውቁት ብዙ እህትና ወንድሞች ርብርብ አድርገው የሚቻለው ሁሉ ህክምና ተደርጎላት ነበር ። መጀመሪያ ሐኪም ቤት ለመሄድ 500 ብር ያጣችው እህታችንን ህይወት ለመታደግ እስከ 800, 000 ወጥቷል ።
እህታችን መዲና አላህ በጀነት የምታርፍ ያድርጋት እንጂ ህይወቷ በፈተና የተሞላ ነበር ። ባለትዳርና የሶስት ልጆች እናት የነበረችው መዲና የትዳር አጓርዋ የሳንቲም ድህነት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ነገር ነበር ማለት ይቻላል ። ብዙ ወንድሞች የተለያየ ከሸክም እስከ ሊስትሮ ከዘበኝነት እስከ ፅዳት ሰራተኝነት አነስተኛ ስራ እየሰሩ ቤተሰባቸውን ያስተዳድራሉ ። ይህ የሀላፊነት መሰማት ውጤት ነው ሀላፊነት የማይሰማው የሆነ አካል ችግር ሲመጣ ጥሎ ይጠፋል ። የመዲናም ባለቤት ከእነዚህ አንዱ ነበር ። በካንሰር ተይዛ ከካንሰሩ በላይ የልጆቿ ረሃብ በሽታ ሆኖ የሚያሰቃያትን ባለቤቱን ለመርዳት ከመጣር ይልቅ ጥሎ መሸሽ ነበር የመረጠው ። እናቱ ኬሞ ስትጀምር የሰውነቷ ፀጉር ሲረግፍ ያየው የመጀመሪያ ልጇ የ9 ጠኛ ክፍል ትምህርቱን ትቶ የእናቱን ሸክም ለመቀነስና ለማሳከም ሲል ሰው ቤት ተቀጠረ ።
ይሁን እንጂ ይህ ውሳኔ በእናቱ ላይ ሌላ ሸክምና ህመም የሚጨምር ነበር ። ልጇ ከእድሜው በላይ ጫና ውስጥ ገብቶ ትምህርቱን ማቋረጡ ሌላ ህመም ሆነባት ። ህመሟ በወንድሞችና እህቶች እርዳታ ህክምና ጀምራ በተለይ ከውጭ ሀገር ይምጣ የተባለው መርፌ ከጀመረች በኋላ ተስፋ ሰጪ ሁኔታ ላይ የነበረ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን ሁኔታው አስከፊ መሆን ጀመረ ። ሁለቱ ልጆቿ እድሜያቸው ገና ሲሆን ሶስተኛው አምስት አመቱ አካባቢ ነው ። እነርሱን እያየች ስታለቅሰ አጠገቧ እየተቀመጠ ጡትሽ ስለተቆረጠ ነው ወይ የምታለቅሺው አይዞሽ ይበቅላል ይላታል ። የእነዚህ ልጆቿ ሁኔታ ፊት ለፊቷ እያዘገመ እየመጣ ካለው ሞት የበለጠ እንደውጋት ቀስፎ እየያዛት በአካልና የውስጥ ህመም ውስጥ ሆነች ። ከቀናት በፊት ባለቤቴ ልትጠይቃት ሄዳ ሳለች በእንባዋ ትራሷ ርሶ አየች ምን ብላ ልታፅናናት እንደምትችል ግራ ገብቷት እያለ ትንሹ ልጇ እናቴ አትሙችብኝ ብሎ ያቅፋታል ። ከብዙ መረባበሽ በኋላ አላህዬ ያንተን ውሰኔ እቀበላለሁ ግን ለእነዚህ ልጄቼ ብኖር ደስ ይለኝ ነበር ብላ የበለጠ ተረብሻ ባለቤቴም የሚያፅናናት ሲያስፈልጋት ትታ ወጣች ።

https://t.me/bahruteka
قناة أبي عبد الرحمن المرسي

22 Feb, 12:38

154

 📔 اسم الكتاب:-➘➴➷
🖼 ❞#كيف نستقبل رمضان؟❝

📕 የሚቀራው ኪታብ ስም፦
📖 #ረመዷንን_እንደት_እንቀበለው?

🔶 إعداد وجمع:- ➘➴➷
📕الـــشـــيـــخ حـــســـيـــن بـــن مـــحـــمـــد بـــن عـــبـــد الـــلـــه الإتـــيـــوبـــي الـــســـلـــطـــي حـــفـــظـــه الـــلـــه تـــعـــالـــى

💡 አዘጋጅ:-
🔎 አሸይኽ ሑሰይን ቢን ሙሀመድ ቢን ዐብደላህ አል-ኢትዮጲ አስ-ሲልጢይ (አላህ ይጠብቃቸው!!!)
🔸الـــــمــــدرس
🎙أبو عبد الرحمن المرسي(حفظه الله)

📜የኪታብ 𝐏𝐝𝐟  ለማግኘት⇩⇩
https://t.me/Abu_Abdirehman_Almersi/3697


ሌሎች ትምህርቶችን ለማግኘት
📲⇘»https://t.me/Abu_Abdirehman_Almersi
📲⇘»https://t.me/Abu_Abdirehman_Almersi
قناة أبي عبد الرحمن المرسي

22 Feb, 11:03

248

የሙነውር ልጅ በመርከዙ ሰዎች ላይ ትችቱ የእውነት ረድ ተፈልጎበት ወይስ ለጠያቂዎች አፍ ማዘጊያ?!
—————
የሙነወር ልጅ፣ ሙሀመድ ሲራጅና ሳዳት ከማል መሰሎቻቸው:- በሱንና ላይ እያሉ፣ ለሱንና ሲታገሉ፣ ከቢድዓና ከቢድዐህ ባለ ቤቶች ሲያስጠነቅቁ፣ ባጢልን በማርከስ ሐቅን እያነገሱ፣ ለተውሒድና ለሱንና ሲታገሉ በነበረበት ወቅት የምናከብራቸውና የምንወዳቸው የነበሩ ወንድሞች ናቸው። በእልህ፣ በጀህልና እና በትቢት ተወጥረው በተምይዕ ፊክራ የተዘፈቁት። በተምይዕ ፊክራ ከተዘፈቁ በኋላ ግን (አላህ ይጠብቀንና!) የጠቀስኩላችሁን ነገሮች ሁሉ በተቃራኒው ማስኬድ ጀመሩ። ከተዘፈቁባቸው አቅጣጫ የሳቱ ነጥቦች ለአብነት ያክል:-
1, የተምይዕን ፊክራ ከተለያዩ የሙመይዐህ ዌብሳይቶች ለቃቅመው እያመጡ በሰለፊዮች መካከል በመበተን ሠለፊዮችን ብዥታ ውስጥ ለመጣል ታገሉ።

2, ቀደም ሲል ሠለፊዮች እንዲጠነቀቋቸው በከፍተኛ ደረጃ ሲያስጠነቅቁ (ከዚህ በኋላ ነጭ ነጯን እንናገራለን…) ብለው ከነበሩት (የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ) ሰዎች በመከላከል የሱንና ሰዎችን ደግሞ በመተቸት ተጠመዱ። ብሎም የመርከዙን ሰዎች ዛሬም ወደፊትም ሰለፊዮች ናቸው በማለት ሞገቱ።

3, እንደ ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ግልፅ ለወጡ የቢድዐህ ባለ ቤት (መሻይኾቻቸው) "የበሰሉ ሰዎች ናቸው…" እያሉ የተለያዩ መለሳለሶችን እያንፀባረቁ፣ በተቃራኒው ደግሞ የሱንና መሻይኾችን "የረድ ጉረኞች…" እያሉ በተለያዩ ቃላቶች እየጎነተሉ ሰዎች እንዲርቋቸውና ከሱንና መሻይኾች ት/ት እንዳይወስዱ ሲታገሉ ከርመዋል።

4, ከቢድዐህ ባለ ቤቶች መስራት ክልክል አይደለም ብለው ሲሟገቱና በርካታ ሰለፊይ የነበሩ ወንድም እህቶችም እንዲህ ባሉ ልቅ አካሄዶቻቸው ወርደው ከኢኽዋኑል ሙስሊሚን ጋር እንዲቀላቀሉ ሰበብ ሆነዋል።

5, ያለ በቂ እውቀታቸው በእልህና በትቢት ተወጥረው፣ የጀርህና ተዕዲልን ጉዳይ በፈለጉት ልክ ቀደው ሲሰፉት ከርመዋል። ሲፈልጉ "ጀርህና ተዕዲል ለማድረግ በቂ አቅም ያለው መስፈርቱን የሚያሟላ ዓሊም የለም" ሲሉ፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ በተቃራኒው "ተብዲዕና ተፍሲቅ ማድረግማ እኔና አንተም ብንሆን የሰውዬውን ሁኔታ አይተን አገሌ ሙብተዲዕ ነው አገሌ ደግሞ ሙብተዲዕ አይደለም ማለት እንችላለን…" እያሉ ተራ የመንደር ወሬ አይነት ነገር አድርገው ሲመለከቱት ተስተውሏል።

6, ግልፅ ማስረጃ የቆመበትን፣ ሸሪዓ ሙብተዲዕ ያለውን ሙብተዲዕ በሉ ሲባሉ "እኛ ሙብተዲዕ ያልነውን ካላላችሁ እያሉ እያስገደዱን ነው" ብለው ማለቃቀሳቸው ሌላኛው ጥፋታቸው ነው። እዚህጋ በጣም የሚደንቀው:- እራሳቸው የሱንና መሻይኾችን "የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሰዎች እንዴት ከሱና አይወጡም?" ብለው ሲሟገቷቸው ቆይተው መሻይኾች ደግሞ ስለ መርከዝ ኢብኑ መስዑድ ማስረጃዎችን ከሰበሰቡና ዑዝራቸውን ካስጨረሱ በኋላ "አሁንማ ከሙብተዲዕ ጋር ተቀላቅለዋል፣ ለይቶላቸወል ሙብቲዕ ናቸው" ብለው ብይን በሚሰጡ ጊዜ "መጀመሪያ እኛ እያልናችሁ ለምን ዝም አላችሁ?" ብለው በትቢትና በእልህ ተወጥረው ተብዲዓችሁን አንቀበልም ማለታቸው ነው። የሱንና ዓሊሞች አንድ አካል ላይ ማስረጃ እስኪሰበስቡ ተብዲዕ ተፍሲቅ የአኼራ ጉዳይ እንደመሆኑ በጥንቃቄ አጣርተው ዑዝሩን እስኪያስጨርሱት ድረስ መታገስ የተለመደና የሚወደስ ባህሪያቸው እንጂ የሚተቹበት ነገር አልነበረም። ደግሞ አንተ ስትነግራቸው ግልፅ ሳይሆንላቸው ቆይቶ ግልፅ ከሆነላቸው በኋላ ሐቁን በማስረጃ ማስቀመጣቸው ጥፋቱ ምኑ ላይ ነው?! ልብ በል! አንድ አካል ሙብተዲዕ በመሆኑ ግልፅ ማስረጃ ከቆመበት በኋላ ሙብተዲዕነቱን መቀበል የሚያስገድዱህ መሻይኾች ሳይሆኑ ሸሪዓዊ ማስረጃው ነው!! የተብዲዑ ጉዳይ አልተገለፀልንም እስኪገለፅልን ዝም እንላለን ባላችሁም ጊዜኮ ያስገደዳችሁ አልነበረም።

7, በተቻለ መጠን ሁሉ በሠለፊይ መሻይኾች፣ ኡስታዞችና ዱዓቶች ደዕዋ ሰለፊያን ለማስፋፋት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከመጅሊሱና ከቢድዐህ አንጃዎች ጋር በመታገል በሰፊው የሚደረገውን የሰለፊዮችን ሐቅን ግልፅ ለማድረግ ባጢልን ለማርከስ፣ ተውሒድና ሱንና የበላይ እንዲሆን ቢድዐህ እና ሺርክ እንዲረክስ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን እየተቹና እያጣጣሉ ለቢድዐህ ባለ ቤቶች እንቅስቃሴና ለሚናገሯቸው ሸሪዓን የሚፃረሩ ንግግሮች ደግሞ ዑዝር እየፈለጉ ከርመዋል።
እነዚህ የጠቀስኳቸው 7 ነጥቦች ከጥፋታቸው በጣም በጥቂቱና አደባባይ ላይ የዋሉ ናቸው።

🔸ዛሬ መለስ ብለው የሙነወር ልጅና አምሳዮቹ የመርከዝ ኢብኑ መስዑድን ሰዎች እንደ አዲስ በጨረፍታም ቢሆን ለመተቸት (ረድ) ለማድረግ መሞከራቸው እውነት ከልብ የመመለስ አዝማሚያ ነው ወይስ የተለያዩ ከእነሱ ስር የነበሩ ወንድም እህቶች ጠንከር ያለ ጥያቄ ሲያነሱ ማስተኛ ነው?!

የእውነት ተመልሰው ከቢድዐህ ባለቤቶች ረድና ታህዚር ከጀመሩ፣ ቀደም ሲል ከተውት ሐቅን የበላይ የማድረግ ባጢልንና የባጢልን ባለ ቤቶችን የማራቆት ስራ በመመለሳቸው እጅግ በጣም በልበ ሰፊነት ደስተኞች ነን!! የእውነት ከተመለሱ ከላይ የጠቀስኳቸውንና መሰል ስህተቶችንም በአደባባይ ያርሙ!!። እነዚህን ወንድሞች ከጎናችን ስናጣቸው ከተከፋነው በላይ ከተምይዕ ባህር ወጥተው ከላይ የጠቀስኳቸውንና መሰል… ስህተቶችን አስተካክለው ወደነበሩበት ሐቅ ሲመለሱ እጅግ በጣም ደስተኞች እንሆናለን!! በአላህ ፈቃድ እጅ ለእጅ ተያይዘን በምንችለው ሁሉ ሐቅን የበላይ ለማድረግ እንተጋለን!!
ነገሩ ከዚህ በተቃራኒ ሆኖ የመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሰዎች በድብብቆሽ ትተው በግልፅና በአደባባይ ከአል-ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ጋር መደመራቸውን ተከትሎ እነ ኢብኑ ሙነወር በጥሩ አቋም የነበሩ መስሏቸው ለእነ ኢብኑ ሙነወር ሲከላከሉ የነበሩ ወንድም እህቶች "በመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ላይ ያላችሁን አቋም በግልፅ ንገሩን? ይሀው ጨርሰው ከኢኽዋን ጋር ተጠቃለዋል ምን ቀራቸው?" ብለው በተለያየ መንገድ በጥያቄ ሲያጣድፏችሁ በመርከዙ ሰዎች አፍ ማዘጊያ ፅፋችሁ ከሆነ ግን ከዚህ በኋላ ሐቅ ፈላጊ ሆኖ የሚሸወድላችሁ አታገኙምና ወደ ራሳችሁ ቆም ብላችሁ ተመልከቱ!! የራሳችሁ ጉዳይ ያሳስባችሁ!! አል-ሀምዱሊላህ! ሐቅ ፈላጊ ሆነው በናንተ ብዥታ ውስጥ የወደቁ እጅግ በጣም ብዙ ወንድም እህቶች ከተለያየ አቅጣጫ እየተመለሱ ነው!!

🔸ይልቅ ለራሳችሁ ስትሉ በእልህና በትቢት ተወጥራችሁ ከገባችሁበት የተምይዕ ዋሻ ውጡና ሐቅን የባለይ ለማድረግ ታገሉ!! በእልህ (በደራ) ገብቶ ሐቅን መሳትና በባጢል መውደቅ የከሃዲያንና የመሀይማን ባህሪ ነው እንጂ ሠለፊያን የሚሞግት የሙስሊም ባህሪ አይደለም!!

إِذْ جَعَلَ الَّذِينَ كَفَرُوا فِي قُلُوبِهِمُ الْحَمِيَّةَ حَمِيَّةَ الْجَاهِلِيَّةِ

«እነዚያ የካዱት ደራይቱን የመሀይምነቲቱን ደራ (እልህ) በልቦቻቸው ውስጥ ባደረጉ ጊዜ (በቀጣናቸው ነበር)፡፡ » አል'ፈትህ 26

🔹ሠለፊይነትን የሚሞግት ሙስሊም የሆነ ሰው ሐቅን ከሁሉ ነገሩ በማስበለጥ ለሀቅ እጅ እግሩን ይሰጣል!! በዚህም የበታችነት ሳይሆን የበላይነት ይሰመዋል!!። አላህ ሐቅን አውቀው ከሚከተሉ፣ ባጢልንም አውቀው ከሚጠነቀቁና በሐቅ ላይ እስከ እለተ ሞታቸው ከሚፀኑ ባሪያዎቹ ያድርገን!!
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
#Join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa
قناة أبي عبد الرحمن المرسي

21 Feb, 22:05

175

📌አዲስ ሙሓደራ

{محاضرة بعنوان } أهمية طلب العلم

📡የሙሓደራው ርዕስ ፦{እወቀትን መፈለግ አሳሳቢነቱ}
 
🎙አቡ አብዲረህማን አብዱልቃዲር ኢብኑ ሐሰን ሀፊዘሁሏህ

08/04/ 1446

🕌 ቦታ አዳማ 01 ቀበሌ ኢብኑ ተይሚያ መስጂድ

https://t.me/abuabdurahmen
قناة أبي عبد الرحمن المرسي

21 Feb, 19:52

162

ልዩ የሙሐደራ ፕሮግራም

እነሁ የፊታችን  እሁድ በቀን 16/06/2017 ታላቅ የሙሐደራ ፕሮግራም ለየት ባለና በማረ ሁኔታ እንኳን መቅረት ማርፈድ የሚያስቆጭ ፕሮግራም  አዘገጅተን እንጠብቃቹሃላን።

በዚህ ፕሮግራም በአሏህ ፍቃድ ወሳኝ ርእሶች የሚዳሰሱበት ይሆናል


እንዲሁም በእለተ ቅዳሜ በ-15-06 በኣልቾ ልዩ ፕሮግራም ተሰናድቶ ይጠብቆታል

        ተጋባዥ  እንግዶች:-
1ኛ.ኡስታዝ  ኑራዲስ ስራጅ  ከቡታጅራ

2ኛ.ኡስታዝ አብራር አወል  ከአዲስ አበባ


3ኛ.ኡስታዝ ዶክተር  ሸምሱ ከቡታጅራ


እና ሌሎችም ኡስታዞች በአላህ ፍቃድ ይኖራሉ

አድራሻ:-ኦዶ ከተማ ትንሽ ገባ ብሎ  መስጂደል ወሊደይን/ሸረፈ ሙስጠፈ


ሰዓት:-ልክ 2:30 ይጀምራል።

ለበለጠ መረጀ ስልክ

ጀማል ኑሪ  0916293446 

  ኑሪ መሀመድ  0989606180 


   መሀመድ የሲን   ጀማል                      0982612475 

ሼርርርርርርርር
                ርርርርር
                   ርርርር
እናርግ ከጁሙዓ ቦኋላ  እናሰዉቅ።


https://t.me/+kn_NBJK5YaBkMWZk
قناة أبي عبد الرحمن المرسي

21 Feb, 17:54

174

ኩቱቦች የምትፈልጉ በውስጥ አናግሩኝ

@Umu_Abdirehman

0558634235

@Abu_Abdirehman

0563114879

https://t.me/Umu_Abdirehman_jilbab_azegaj/88?single
قناة أبي عبد الرحمن المرسي

21 Feb, 09:46

239

ልዩ የሙሀዶራ ፕሮግራም

➡️ በአይነቱ ለየት ያለ የዳዕዋ  ፕሮግራም ጥሪ   በወሎ ዩኒቨርሲቲ ሰለፊይ ተማሪወችግሩፕ (Online) ቀጥታ ሥርጭት  ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል  ⤵️
ሁሉም ሰለፍዮች ተጋብዛችኋል


  የፕሮግራሙ  አዘጋጆች

   የወሎ ዩኒቨር ሲቲ ሰለፍይ ተማሪዎች

🪑 የዕለቱ ተጋባዥ እንግዳችን

  🎙 ኡስታዝ አቡበክር ዩሱፍ
ከ(ባህር ዳር )

ርዕስ በሰዓቱ የሚገለፅ ይሆናል

🗓ፕሮግራሙ የሚካሄደው ዛሬ ጁምዓ   14/6/2017  ከኢሻ ሰላት ቡሀላ

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል  መቅረት ሳይሆን ማርፈድ ያስቆጫል


♻️ አጓጊ የሰለፊዬች ደዕዋ እንዳያልፋችሁ ከወዲሁ ጆይን ይበሉ💠↪️ፕሮግራሙን ለመከታተል ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ ።
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️

https://t.me/wollouniversty
https://t.me/wollouniversty
قناة أبي عبد الرحمن المرسي

21 Feb, 09:45

205

ሱረቱል ካህፍ)  💐📖🎧

(ሙሉ ሱራ )

#سورة_الكهف_بصوت
#ياسر_الدوسري
የቻለ ይቅራ 📖 ያልቻለ ያዳምጥ 👂🎧

የአላህ መልዕክተኛﷺእንዲህ ብለዋል

የጁመአ ቀን ሱረቱል ካህፍን የቀራ ሰው አላህ በሁለቱ ጁመዓዎች መካከል ብርሃን ያበራለታል


በነብዩ ﷺ ላይ ሰለዋት ማውረድን እናብዛ

https://t.me/daewette_asselefya_fi_mersa
قناة أبي عبد الرحمن المرسي

21 Feb, 08:48

213

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

➳ውድ ሰለፊይ ቤተሰቦቻችን በያላችሁበት አሏህ ይጠብቃችሁ እያልን ታላቅ ብስራት ይዘንላችሁ ብቅ ብለናል!!

➾ምንድን ነው? ካላችሁ ይኼው ብለናል!

<<የሰዎችን ሀጃ ማውጣት ኢባዳ ነው>>

➵<< قضاء حاجة الناس عبادة >>


➳በተሰኘ ርዕስ፦ በተወዳጁ ዑስታዛችን ዑስታዝ አቡ ፉረይሃን(ሷሊህ ውቤ)ከጉትን ለየት ያለ የዳዕዋና የንያ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል!!!

➳ቀኑ መቸነው?!!
➳ለሚለው የፊታችን ቅዳሜ ከኢሻ ሶላት በኋላ እንላችኋለን!!!

➳አድራሻ ካላችሁ!! የሱና ወንድማችንን ወንድም ሁሴን ሀሠንን እንርዳው በሚለው ግሩፕ እንላችኋለን!!
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/Wendmachinn_Enrdaw
https://t.me/Wendmachinn_Enrdaw

➳ውድ  እንግዶቻችን  የናንተን መገኘት በጉጉት እንጠብቃለን!!

➾እሰከዛው አድድድድድድ ሸርርር በማድረግም ኢስላማዊይ ሀላፍትናችንን እንወጣ!!!

#Join➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/Wendmachinn_Enrdaw
https://t.me/Wendmachinn_Enrdaw