Dernières publications de የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት (@aasundayschool) sur Telegram

Publications du canal የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
ይህ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ልሳን ነው።
10,161 abonnés
3,317 photos
37 vidéos
Dernière mise à jour 05.03.2025 22:10

Le dernier contenu partagé par የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት sur Telegram

የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

31 Jan, 14:27

1,927

ይቅርታ እየጠየቅን ቀኑ ተቀይሯል
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

21 Jan, 05:13

3,612

በዓላችን ያለምንም የጸጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ እንዲውል ለማድረግ የመንግስት የጸጥታ ተቋማት በተለይም የጸጥታና የደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል፣ የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽንና ሌሎች የጸጥታ ተቋማት ያለመታከት ላደረጉት አስተዋጽኦ
ቅድስት ቤተክርስቲያን የተሰማትን ደስታ በመግለጽ ምስጋ
ናዋን ታቀርባለች።

በተያያዘ የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የበዓል አከባበር ሂደቱን በቅርበት በመከታተልና እንቅፋቶች እንዳይፈጠሩ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ በመስራትና የታቦታት ማለፊያ ቦታዎችን በማጽዳት ያበረከተው አስተዋጽኦን ቅድስት ቤተክርስቲያን የምታደንቀውና ምስጋናም የምትቸረው ነው።

በዓላችን በመላ አገራችን በልዩ ድምቀትና ውበት ተከብሮ መዋል ይችል ዘንድ  በየ ክልሉ የሚገኙ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች መዋቅራቸውን በመጠቀም ታቦታት የሚጓዙበትን ቦታዎች በሚገባ ዝግጁ በማድረግ ለታቦታት ማክበሪያ የሆኑ ይዞታዎችን በመፍ
ቀድና በሰነድ የተረጋገጠ የባለቤትነት መብትን በማጎናጸፍ  እንዲሁም በዓሉ በምልዓተ ሕዝብ በሰላም ተከብሮ እንዲውል ላደረጉት ድጋፍና ትብብር ቅድስት ቤተክረስቲያን ምስጋናዋን ታቀርባለች።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበው የጥምቀት በዓል የአገራችን ኢትዮጵያና የመላው ሕዝባችን በዓል መሆኑን በተግባር በማረጋገጥ ደረጃ በተለይም ሙስሊም ወንድሞቻችን ያሳያችሁት ፍቅርና አንድነትን የሚገልጽ ተግባር በእጅጉ የሚያስመሰግን አንድነትና አብሮነትን የሚያጠናክር በመሆኑ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ላሳያችሁት ፍቅርና ክብር በልዑል እግዚአብሔር ስም ልባዊ ምስጋናዋን ታቀርባለች።

በአጠቃላይ የዘንድሮ የከተራ፣የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ  በዓላት በመላ አገራችን እጅግ ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበበት ሕዝበ ክርስቲያን በአደባባይ ተገኝቶ  በልዩ ውበት በሰላም ያከበራቸው  መሆኑን ከመላ አገራችን የደረሰን ሪፖርት የሚያመለክት ሲሆን በዚህ ልክ በዓላቶቻችን በሰላም ተከብረው መዋላቸው ደግሞ በእጅጉ የሚያስደስትና ለአገራችን የቱሪዝም እድገትና የገጽታ ግንባታም ላቅ ያለ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ቤተክርስቲያን ታምናለች።

ስለሆነም በዓላቶቻችን  በዚህ መልኩ ተከብረው መዋል እንዲችሉ ለማድረግ አቅማችሁን በማስተባበር ዋጋ ለከፈላችሁ ልጆቻችን በሙሉ እግዚአብሔር አምላክ ዋጋችሁን እንዲከፍላችሁ ቤተክርስቲያን የዘወትር ጸሎቷ መሆኑን ስትገልጽ በልጆቿ መንፈሳዊ ተጋድሎ ከፍተኛ ደስታ የተሰማት መሆኑን በመግለጽ ጭምር ነው።

           የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
                 መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት
                      ጥር ፲፪ ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም
                          አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
Eotc
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

21 Jan, 05:13

2,788

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የከተራ፣የጥምቀትና የቃና ዘገሊላ በዓላት በመላ አገራችን ከፍተኛ ቁጥር ባስመዘገበ ምልዓተ ሕዝብ በሰላም ተከብሮ በመዋሉ ለልዑል እግዚአብሔር
ምስጋናዋን ታቀርባለች።

የ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም የጥምቀት በዓል በመላ አገራችን በድምቀት ተከብሮ መዋል ይችል ዘንድ በማዕከልም ሆነ በአህጉረ ስብከት ደረጃ በሊቃነ ጳጳሳት ተቋቁመው ሥራቸውን በሚገባ የተወጡ የሥራ ኃላፊዎችና የጥምቀት በዓል ዝግጅት አስተባባሪዎች፣
ካህናት፣የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣በዓሉ በድምቀት እንዲከበር አደባባዮችን በማስዋብና ሥነሥርዓትን በማስከበር ትልቁን ሚና የተጫወቱ ኦርቶዶክሳዊያን ወጣት ልጆቻችን ምዕመናንና ምዕመናት በሙሉ በዓላቶቻችን ያለአንዳች ችግር በሰላም ተከብረው እንዲውሉ ስላደረጋችሁ ቅድስት ቤተክርስቲያን ልባዊ ምርጋናዋን ታቀርብላችኋለች።

በተለይም በመዲናችን አዲስ አበባ ጃን ሜዳ የተከበሩት ሦስቱ በዓላት በታላቅ ድምቀትና ውበት ተከብረው መዋል እንዲችሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ልዩ ትኩረት በመስጠት የክብር እንግዶች የሚቀመጡበት መድረክ ከነ ሙሉ ግብዓቱ፣የድምጽ ማጉያና መሰል ለበዓል አከባባሩ የሚያስፈልጉትን ሁሉ በከተማ አስተዳደሩ ወጪ በመሸፈን ስላቀረቡልን እንዲሁም ከኮሪደር ልማቱ ጋር በተያያዘ የታቦታት እንቅስቃሴ እንዳይስተጓጎል አስፈላጊውን መመሪያ በመስጠትና አፈጻጸሙን በቅርበት በመከታተል ከልማቱ ጋር የተያያዘ ምንም አይነት መጉላላት እንዳይፈጠር በማድረግ በዓሉ የጋራችን መሆኑን የሚያረጋግጥ ሥራ በመስራት ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ ቤተክርስቲያናችን  ምስጋናዋን ታቀርባለች።
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

21 Jan, 05:10

3,544

📸ልዩ የሚያሸልም የጥምቀት ፎቶግራፍ ውድድር
በሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሚዲያ ክፍል የተዘጋጀ 🏆

እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!

   ┄┄┉┉ ‌  ✽‌  🌺🌺‌  ✽‌   ┉┉┄┄
    
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት በቴሌግራም ቻናሉና ቡድኑ ላይ ለከተራ ፣ ለጥምቀት እንዲሁም ለቃና ዘገሊላ በዓላት ያነሳችዋቸውን ፎቶግራፎች ሰብስቦና አወዳድሮ መልሶ ለእናንተው ሊያደርስ ተዘጋጅቷል።

👉 በውድድሩም ከማንኛውም ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤት ዓባላትና ምዕመናን መሳተፍ ይችላሉ። ለአሸናፊዎችም ልዩ ሽልማት ተዘጋጅቷል።

👉ይመጥናሉ ያሉትን በበዓሉ ላይ የተነሱ  ፎቶግራፎች ለዚሁ ውድድር ባዘጋጀነው የቴሌግራም ቦት 

@t4mesbot

ላይ እስከ ሐሙስ ጥር 14 ድረስ በመላክ መሳተፍ ይችላሉ።

✍️ ከሚያስገቡት ፎቶግራፍ መካከል በዚህ ቻናል ለምርጫ የሚለጠፈው የበዓሉ አከባበር መንፈሳዊ እሴቶቹን  የጠበቀ ከሆነ እና ከኤዲቲንግ የፀዳ ከሆነ ብቻ ነው።

🚫ለመወዳደሪያ የሚልኳቸው ፎቶዎች ቀድመው በማንኛውም የማህበራዊ ሚዲያ የታዩና የተለቀቁ መሆን የለባቸውም።

✍️ በተጨማሪም ተወዳዳሪዎች ለውድድሩ ብቁ የሚያደርጋቸው ወደ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የቴሌግራም ቡድን @eotcgssu21 አንድ አባል መጨመር  ፣ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/@eotc-gssu ሰብስክራይብ ማድረግ አልያም የሰ/ት/ቤት ፌስቡክ ፔጅን https://www.facebook.com/gssu.eotc ላይክ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

መልካም በዓል!
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

18 Jan, 12:58

2,861

እንኳን አደረሳችሁ !
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት በአዲስ አበባ ለሚገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ፤ ለሰንበት ተማሪዎች ፤ አገልጋዮች እንዲሁም ለመላው የኢ/ኦ/ተዋህዶ እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልክት አስተላልፎል።
ምንጭ:- የአ/አ/ሀ/ስ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

16 Jan, 04:11

5,094

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

የ2017ዓ.ም የ1ኛ ወሰነ ትምህርት ማጠቃለያ የ4ኛ፣ 8ኛ እና 10ኛ ክፍል የሙከራ(ሞዴል) ምዘና በሀገረ ስብከት ደረጃ እንደሚሰጥ ይታወቃል። በመሆኑም ምዘናው #የካቲት_22_እና_23 ስለሚሰጥ ከላይ የተጠቀሱትን ክፍሎች እያስተማራችሁ የምትገኙ ሰንበት ትምህርት ቤቶች ከወዲሁ ተማሪዎቻቹን እንድታዘጋጁ እናሳስባለን።

ምዘናው በአ/አ/ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ትምህርት ክፍል ተዘጋጅቶ በፒዲኤፍ በክ/ከተማቹ ትምህርት ክፍል በኩል የሚላክላቹ ሲሆን በየአጥቢያችሁ ፕሪንት በማድረግ በተጠቀሰው ቀን ምዘናውን የምታከናውኑ ይሆናል። ምዘናውን የወሰዱትን ተማሪዎች ውጤትና መረጃም ከምዘናው ጋር በሚላክላቹ ቅጽ መሠረት እንድትልኩልን ከወዲሁ እናሳስባለን።

#ምዘናው_የሚያካትታቸው_ትምህርቶች
~>4ኛ ክፍል/ከ1ኛ-4ኛ ክፍል/:- መሠረተ ሃይማኖት፣ ግእዝ እና ክርስቲያናዊ ሥነምግባር
~>8ኛ ክፍል/7ኛ እና 8ኛ ክፍል/:- መሠረተ ሃይማኖት፣ ግእዝ እና ክርስቲያናዊ ሥነምግባር
~>10ኛ ክፍል/9ኛ እና10ኛ ክፍል/:- ቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት (መጽሐፈ መነኮሳት)፣ ግእዝ፣ ጠቅላላ እውቀት (ጥናትና ምርምር ዘዴ)

#የሙከራ_ምዘናውን_ያልወሰደ_ተማሪ_የማጠቃለያ_ምዘና_መውሰድ_አይችልም!

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን!

በአዲስ አበባ ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ትምህርት ክፍል የምዘናና እውቅና ንዑስ ክፍል
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

13 Jan, 11:48

3,465

#እግዚአብሔር_ይመስገን!!!

"መልካም ማድረግን ለሌሎችም ማካፈልን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መስዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና፡፡"  ዕብ. 13፡17

የ2017 ዓ.ም የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ በክፍለ ከተማችን ምግባረ ሰናይ እና የማኅበረ ቅዱሳን የየካ ክ/ከተማ ወረዳ ማዕከል እንዲሁም የክ/ከተማችን ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት (ልማትና በጎ አድራጎት ክፍል) አስተባባሪነት በየካ አባዶ ጥምቀተ ባህር ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ተረጂዎች በማሰባሰብ፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ በተገኙበት፣ የየካና ለሚ ኩራ ክፍላተ ከተማ ቤተ-ክህነት ሥራ አስኪያጅ ክቡር መልአከ ምህረት ዘካርያስ ሐዲስ በተገኙበት፣ የክ/ከተማው ምግባረ ሰናይ ኃላፊ ክቡር መልአከ ምህረት በተገኙበት፣ የክ/ከተማው የመምሪያ ኃላፊዎች፣ የደብራት አስተዳዳሪዎች፣ የማኅበረ ቅዱሳን የወረዳ ማዕከል ሥራ አመራሮች፣ የክ/ከተማው ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ሥራ አመራሮች እንዲሁም ሥራ አስፈጻሚዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ-ክርስቲያን አባቶች ካህናትመምህራነ ወንጌል፣ ዘማሪያን፣ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት ከምገባ ባሻገር ዘይት፣ ሽሮ፣ ፓስታ፣ መኮሮኒ እንዲሁም ከሕጻናት እስከ አዋቂዎች አልባሳትን ጨምሮ ከ500 በላይ ለሚሆኑ ወገኖቻችን ድጋፍ ተደርጓል፡፡
ምንጭ:-የየካ ክ/ከተማ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ልማትና በጎ አድራጎት ክፍል
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

11 Jan, 05:52

1,176

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ 
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የተላለፈ አባታዊ ጥሪ
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

08 Jan, 05:23

2,040

መድኃኒት ተወልዶላችኋል!

“እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱ ክርስቶስ እግዚእ ቡሩክ በሀገረ ዳዊት-እነሆ፥ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል፡፡ (ሉቃ.2፥11)

ቅዱስ ሉቃስ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቤተልሔም ሲወለድ ስለነበረው የልቱን ነገር ሲተርክ “በዚያን ሌሊት በቤተ ልሔም ይኖሩ የነበሩ እረኞችም ከብቶቻቸውን ሲጠብቁ የእግዚአብሔር መልአክ በእረኞቹ አጠገብ ቆመ፤ የእግዚአብሔርም ብርሃን በዙሪያቸው በራ፤ በጣምም ፈሩ፡፡ መልአኩም እንዲህ አላቸው እነሆ ለእናንተና ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ደስታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ እነሆ፥ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋል፡፡ እናንተም ባገኛችሁት ጊዜ ምልክቱ እንዲህ ነው፡፡ ሕፃን በጨርቅ ተጠቅልሎ በበረት ውስጥ ተኝቶ ታገኙታላችሁ፤ ድንገትም ከዚያ መልአክ ጋር ብዙ የሰማይ መላእክት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መጡ፡፡” በማለት ቤተልሔምን በዓይነ ሕሊናችን እንድናይ አድጎ በሥዕላዊ አገላለጽ ይነግረናል፡፡ (ሉቃ.2፥11-13) ቅዱስ ሉቃስ በዚህ የወንጌሉ ክፍል ከድኅነታችን ጋር በቀጥታ የሚገናኙ መሠረታዊ ነገሮችን ነገሮናል፡፡ ከእነዚህም መካከል፡-

1.የእግዚአብሔርም ብርሃን በዙሪያቸው በራ፤
ይህ ብርሃን ፀሐይ ወይም ጨረቃ አይደለም፡፡ ልዩ የእግዚአብሔር ብርሃን ነው፡፡ ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌሊት ተወልዶ በማብራት የብርሃናት ፈጣሪ እውነተኛ ብርሃን መሆኑን አሳየን፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ በዓለም ላይ ጨለማ እንደነበረ እውነተና ብርሃን በመጣ ጊዜ ጨለማ እንዳለሸነፈው ገልጾልናል፡፡ (ዮሐ.1፡9) አስቀድሞ ኢሳይያስም በጨለማ ይሄድ የነበረ ሕዝብ ብርሃን አየ በጨለማና በሞት ጥላ ለነበሩ ብርሃን ወጣላቸው፡፡ (ኢሳ 9፡2) በማለት በሥጋ ስለሚገለጠው ብርሃን ተናግሮ ነበር፡፡ ክርስቶስ እስኪወለድ ድረስ በአዳም ኃጢአት ምክንያት ዓለም ሁሉ ማለትም የአዳም ልጆች ሁሉ በጨለማ ተውጠው ነበርና ቅዱስ ሉቃስ ጨለማውን የሚያስወግድ ብርሃን እንደተወለደ ነገረን፡፡

2. ለእናንተና ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ደስታ
የእግዚአብሔር መልአክ በለሊት ከብቶቻቸውን ሲጠብቁ ለነበሩና ከተገለጠው ብርሃን የተነሳ እጅግ ፈርተው ለነበሩ እረኞች ለእናንተና ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ደስታ ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ አላቸው፡፡ በዚህም የክርስቶስ መወለድ ለእረኞችና ለዓለም ሁሉ ደስታ መሆኑን ይነግረናል፡፡ ለአምስት ሺ አምስት መቶ ዘመናት ከሰው ልጅ ደስታ ርቆ የአዳም ዘር ሁሉ በኀዘን ተውጦ ነበርና ለእናንተና ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ደስታ ታላቅ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ በማለት የኀዘንና የፍርኃት ዘመን እንደተወገደ የምህረት ዘመን እደመጣ ደስታችንም እንደተመለሰ ደስታው ደግሞ ለሕዝብም ለአሕዛብም በአጠቃላይ ለዓለም ሁሉ መሆኑን ነገረን፡፡

3.መድኃኒት ተወልዶላችኋል
በበደል ምክንያት ቆስለን ፍጹም ፈውስ የሚያመጣ መድኃኒት የሚያስፈልገን ታማሚዎች ነበርንና የምሥራቹን የነገረን የእግዚአብሔር መልአክ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት ተወልዶላችኋል አለን፡፡ በዚህም በቤተልሔም ከድንግል ማርያም ተወልዶ በግርግም ተኝቶ ያያነው ክርስቶስ አዳምንና ልጆቹን ከኃጢአታቸው የሚያድናቸው ከቁስላቸውም የሚፈውሳቸው መድኃኒት መሆኑን ተረዳን፡፡

4.የሰማይ መላእክት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መጡ
ወንጌላዊው ሉቃስ የጌታን ልደት ሲተርክ የነገረን ሌላው ቁም ነገር “የሰማይ መላእክት እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መጡ” የሚል ነው፡፡ ይህም በሰውልጅ መዳን መላእክት እንደሚደሰቱ እና በኃጢአታችን ምክንያት አጥተነው የነበረውን የመላእክትና የሰው ልጆች አንድነት በጌታችን ልደት እንደተመለሰ የሚያሳይ ነው፡፡ በዚህም የጋራ ዝማሬ በምድር ላይ ሰላም እንደሆነ ተገልጧል፡፡ በልደተ ክርስቶስ ሰውና እግዚአብሔር መላእክትና ሰው፣ ነፍስና ሥጋ፣ ሰማይና ምድር፣ ሕዝብና አሕዛብ ታርቀዋልና በምድር ሰላም ኾነ ሰውና መላእክትም በአንድነት ዘመሩ፡፡
በአጠቃላይ የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት፡- የእግዚአብሔር ብርሃን  በጨለማ ለነበርነው ሁሉ የበራበት፣ ፍርኃት የተወገደበት፣  ለእረኞቹና ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ደስታ ደስታ ታላቅ የምሥራች የተነገረበት፣ ሰውና መላእክትም በአንድነት የዘመሩበት ታላቅ የደስታ በዓል ነው፡፡
ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እግዚአብሔር አምላክ የሰውን ዘር በሙሉ ያዳነበትን ድንቅ ሥራ ሲገልጽ “ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረው እርሱ ሕፃን ሆኗልና፡፡ እኔ ፈጽሜ አደንቃለሁ፡፡ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚሆን፣ በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ፡፡ ከሥጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ፡፡ ኀጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት፤ ይህን ወዷልና፤›› (ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈወርቅ፣ ፷፮፥፲፯) በማለት የመወለዱንና የትሕትናውን ነገር እያደነቀ ይናገራል፡፡
ይህ በዓል የአምላክ ትሕትና የታየበት የተዋረደው የሰው ልጅ ደግሞ መክበሩ የተገለጠበት በዓል ነው፡፡ ስለሆነም ልደተ ክርስቶስ ከትዕቢት ይልቅ ትሕትናን እንድንይዝ፣ ከጥላቻ ይልቅ ሰላምን እንድንሰብክ፣ ጌታችን ወደ ተዋረድነው የሰው ልጆች መጥቷልና በኑሮ ከእኛ ዝቅ ወዳሉት በትሕትና እንድንሄድ ደግፈንም እንድናነሳቸው፣ የእውነተኛው ብርሃን ልጆች ነንና በሕይወታችን የብርሃን እንጂ የጨለማ ሥራ እንዳይታይ፣ ለሰው ሁሉ የደስታ እንጂ የኀዘን ምክንያት እንዳንሆን የክርስቶስ ልደት ያስተምራናል፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ ተወልዶ ውሉደ እግዚአብሔር ያደረገን ክርስቲኖች የፍቅርና የሰላም ሰዎች በመሆን፣ ከጨለማ ሥራ በመራቅ ትሕትናንም ገንዘብ በማድረግ የክርስቶስ ልጆች መሆናችንን ልናሳይ ይገባል፡፡

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰለም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል ይሁንልን!

መጋቤ ሐዲስ ጸጋ ወ/ትንሣኤ
በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት
የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሓላፊ

(የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት)
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት

06 Jan, 11:36

2,308

#መልእክተ_ቅዱስ_ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤
ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት በሙሉ፤

በምሉእ ፍቅሩ ሰውን ከባርነት ወደ ነጻነት ለመመለስ በሥጋ ሰብእ የተወለደው ጌታችን  ኣምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ሰባት ዓመተ ምሕረት የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡

“ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ለዘሠምሮ ለሰብእ፤ ክብር በሰማያት ለእግዚአብሔር ይሁን›› በምድርም እጅግ ለወደደው የሰው ልጅ ሰላም ይሁን” (ሉቃ ፪÷፲፬)
ይህ ቃለ ሰላም በጌታችን ዕለተ ልደት የተነገረ ነው፣ ቃሉ የተነገረው እንዲሁ እንደ ተራ ነገር ሳይሆን በቃለ መዝሙር እየተደጋገመ ነው፡፡ የተዘመረውም በምድራውያን ደራሲዎች ሳይሆን በሰማያውያን መላእክተ እግዚአብሔር ነው፣ የያዘው መልእክትም ሰማያውያንና ምድራውያንን ሁሉ ያካለለ ነው፡፡ የመልእክቱ ገዢ ሓሳብም አምላክ ከሰውነታችን ጋር ባለመለያየት፣ ባለመጠፋፋት፣ ባለመቀላቀል፣ ባለመዋዋጥ፣ ባለመለዋወጥና ያለባዕድና አንድ አካል፣ አንድ ክዋኔ፣ አንድ ጠባይ ሆኖ በተዋሕዶ ተገልጾኣልና እግዚአብሔር ይክብር ይመስገን፡፡ የተዋሕዶውም ምስጢር ሰላምን ያሰፍናልና እግዚአብሔር ሰውን በእጅጉ መውደዱ ከዚህ ተዋሕዶ ዓውቀናል የሚል ነው፡፡

በእርግጥም እግዚአብሔር ሰውን ለመውደዱ ከዚህ የበለጠ ማሳያ ወይም ማስረጃ የለም፤ እንከን የለሽ ንጹህ አምላክ የእኛን ኃጢአተኛ ሰውነት አካሉ አድርጎ ተወለደ ሲባል ላስተዋለው ሰው ምንኛ ቢወደን ነው የሚለው ጥልቅ አድናቆትን ያጭራልና ነው፡፡ይህ ብቻም አይደለም በዚህ ነገረ ተዋሕዶ ምክንያት ሰውነታችን አምላክ ሆኖ በመንበረ ጸባኦት እንዲቀመጥ መብቃቱ የድኅነታችንና የክብራችን ከፍታ ምን ያህል አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንደደረሰ መንፈሳችን በአንክሮ ይረዳዋል፡፡ድምር ውጤቱም በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ፍጹምና አስተማማኝ ሰላም መፈጠሩን ያስረዳናል፤ ሰማያውያኑ መላእክተ እግዚአብሔር በመዝሙራቸው ያበሰሩን ይህንን የምስራች ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

እኛ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር በእጅጉ ይወደናል ስንል እንዲሁ ከሜዳ ተነሥተን ኣይደለም፡፡ በበደላችንና በኃጢአታችን ሳይጸየፈን ሰውነታችንን በረድኤት ወይም በኅድረት ያይደለ በኩነት ተዋሕዶ ወደ አምላክነት ደረጃ ከፍ ስላደረገው  ነው እንጂ፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ፍጹምና ምሉእ ፍቅሩ ሰውነታችንን በመበረ ጸባኦት ኣስቀምጦ መላእክት ሳይቀሩ ፍጥረታትን በሙሉ እንድንገዛ አድርጎናል፤ ምክንያቱም መላእክት በዕለተ ልደት የዘመሩለት በተዋሕዶ አምላክም ሰውም ለሆነ ለቤተ ልሔሙ ሕፃን እንጂ ለመለኮት ብቻ ኣይደለምና ነው፡፡ የዕለተ ልደት መዝሙር ዛሬም በሰማያትም ሆነ በምድር በተዋሕዶ ሰውም ኣምላክም የሆነ አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመለክበታል፣ ይመሰገንበታል፡፡የሰማዩና የምድሩ ዕርቅ ወደ ኋላ ላይመለስ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በዚህ ተከናውኖኣል፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ የሰውም አዋጭ ምርጫ ይህ ዕርቅ ተጠብቆ እንዲኖር ነው፣ ያለ ዕርቅ ሰላም ሕይወት የለውምና፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

የእግዚአብሔር ክብርና ሰላም በእጅጉ የተሳሰሩና የተቆራኙ ናቸው፤ እኛ እግዚአብሔርን ካከበርነው፣ ካዳመጥነው፣ ከታዘዝነውና ከተከተልነው ሰላም አለ ማለት ነው፡፡ ለሱ ካልታዘዝንና እሱን ካላከበርን ግን ዘላቂ ሰላምን ማግኘት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው፤ ምክንያቱም ሰላምን ጨምሮ መልካም ነገር ሁሉ ያለው በእግዚአብሔር እጅ ነውና፡፡ ዛሬ በሁሉም የዓለማችን ማዕዘን የሚታየው የሰላም መደፍረስ እግዚአብሔርን ካለማክበራችንና ለሱ ካለመታዘዛችን የተነሣ እንደሆነ መዘንጋት የለብንም፡፡ ዓለም ከእግዚአብሔር ቃል ርቃ ለመሄድ በእጅጉ እየኳተነች ነው፤ በዚህ እኩይ ተግባርዋ ደግሞ እግዚአብሔር ለስጋትና ለጉስቁልና አሳልፎ እየሰጣት ነው፡፡ እግዚአብሔር በምስጢረ ሥጋዌው ቢታረቃትም ዕርቁን ማክበር አቅቶአታል፤ ይህንን የእግዚአብሔር ጸጋ ቸል ብላ የምታደርገው ሩጫ የትም ሊያደርሳት እንደማይችል ብታውቅና በንስሓ ብትመለስ እግጅ ተጠቃሚ ትሆናለች፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

የእግዚአብሔር ቃል “እናንተስ ከማይጠፋ ዘር ተወለዳችሁ” ብሎ ተስፋውን እንደነገረን ምድባችን ከማይጠፋ ዘር እንዲሆን ክርስቲያኖች የሆን ሁላችን በአእምሮ ጐልብተን፣ በሥነ-ምግባር ኣምረን፣ ጤናማ ሕይወትን ልንመራ ይገባናል፡፡

የአምላካችንን በዓለ ልደት ስናከብር ነገረ እግዚአብሔርን፣ ነገረ ፍቅርን፣ ነገረ ዕርቅንና ነገረ ሰላምን በማኅበረሰባችን የማሥረጽ አጀንዳ ይዘን ልናከብር ይገባል፡፡

ጠቡ ፣ ጥላቻው፣ መለያየቱ፣ መጠፋፋቱ፣ ለወንድሜ  ከማለት ይልቅ ለኔ ለኔ ማለቱ ሲጎዳን እንጂ ሲጠቅመን ኣላየንም፡፡ አሁንም ወደ ልባችን እንመለስና በፍቅር፣ በዕርቅና በእኩልነት፣ በስምምነትና በወንድምነት ወደሚገኝ አንድነት እንምጣ፤ የልደቱ መዝሙር ያስተማረን ይህና ይህ ብቻ ነውና፡፡ በሌሎቹ ክፍለ ዓለማት እንደሆነው ሁሉ በሀገራችን የተከሠተው አላስፈላጊ ግጭት ብዙዎችን አሳጥቶናል፤ ብዙዎችንም ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎ ሜዳ ላይ ፈሰው የሰቆቃ ኑሮ እንዲገፉ አድርጎብናል፡፡ የሀገር ሀብት እንዲወድም ሆኖአል፤ ልጆቻችን ምናለ ከእንግዲህ ወዲህ ቢበቃንና ምድሪቱን የሰላም አየር እንድትተነፍስ ብንፈቅድላት፤ ይህ የወቅቱ የቤተክርስቲያናችን ዋነኛ መልእክትና ጥሪ ነው፡፡    

በመጨረሻም፡-

በዓለ ልደት የእግዚአብሔር በዓል ነውና፣ እግዚአብሔር በምድራችን ሰላምን ያወርድ ዘንድ ካለን ከፍለን ለተፈናቃዮች፣ ለነዳያን እና ለአካል ጉዳተኞች በመለገስ በዓሉን በመንፈሳዊ ደስታና በሰላም እንድናከብር አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤

መልካም በዓለ ልደት ያድርግልን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር  አሜን!

      አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ
ተክለሃይማኖት
ታኅሣሥ ፳፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ