የሰንበት ት/ቤቶች የመማሪያ እና ሌሎች አገልግሎት የሚውሉ ለቢሮ ግንባታ የሚውል ቦታ ጉዳይ ወጥ የሆነ የህንጻ ዲዛይን የአዲስአበባ ሀገረ ስብከት አንድነት እንዲያዘጋጅ መመርያ ያስተላለፋ ሲሆን በዛም መሰረት በየቦታው የሚገነቡ የሰንበት ት/ቤቶች ህንጻ አንድ አይነት እስታንዳርድ እንዲሆኑ እንዲሁም እስከ አሁን መማርያ መጽሐፍት ያልገዙ አጥቢያዎችን በሊስት እንዲቀርቡ መመረያ አስተላልፈዋል።
ብጹእ አቡነ ቀለሜንጦስ ለውጥ የሚመጣው እቅድን መሠረት አድርጎ ሲሰራ እና ዛሬ እንዳየነው ጉባኤ አባላት በጠንካራ ሀሳብ ሲሞግቱ መሆኑን ገልጸው ይህ አስራር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል ከዛም በተጨማሪ የበጀት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አለመኖሩ ግርምት የፈጠረባቸው መሆኑ እና ለስንት ሀገረ ስብከት በፈሰስ እያስተዳደረ ያለ ምሳሌ የሆነ ሀገረ ስብከት እንዴት ለራሱ አካል አጠገቡ ላለው በጀት አይኖረውም የሚል ጥያቄ ለክቡር ስራ አስኪያጁ አቅርበዋል። በምላሹም የበጀት ጉዳይ ጅማሮ እንዳለ እና እልባት እንደሚያገኝ የሀገረ ስብከቱ ስራ አስኪያጅ ለብጹእነታቸው ቃል ገብተዋል።
በስተመጨረሻም በተጓደሉ አመራር ምትክ ዲ. በእሱፈቃድ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ዋናስራ አስፈጻሚ ሆነው እንዲያገለግሉ በጉባኤ ጸድቆ ጉባኤው ከምሽቱ 12:30 በጸሎት ተጠናቋል።